#አገር #ነሽ። እቴጌ ጎንደር የልጆችሽን ትጋት የምታዘክሪበት ዕለት #ናፈቀኝ።
ከጫጫታው ከሁካታው፤ ከግርግሩ ከጩኽቱ #ረብ ብለሽ ስለ ልጆችሽ በምልሰት ቅኝትሽ ተጠሙነሽ ዘመኑን የምታስደምሚበት ቀንሽ ይናፍቀኛል። በውነት ሽው ይለኛል። እናትነትሽ ለኢትዮጵያዊነት መሆኑን ብጽናናበትም፤ ይህን በታላቅ ገቢር ያነበቡልን፤ የተረጉሙልን፤ ያመሳጠሩልንን ሊቀ ትጉኃንን መቼ ይሆን የጨመተ ቀን ኖሮሽ የምታዘክሪያቸው።
#እነዋ እናንዬ እናት ዓለም አውቃለሁኝ ፈተናሽን። በየዘመኑ የምትታጭበት ስሌቱም ይገባኛል። ሁልጊዜ #ለማገዶነት። ይህም ሆኖ ውስጥሽን እምታይበት ዘመን #ውል ይለኛል። አንቺው እራስሽ ውልም ቃልኪዳንም ነሽና። የማልደብቅሽ ሁልጊዜም ትናፍቂኛለሽ። ምንጊዜም ከውስጤ ነሽ። መከራን በመቻልሽ፤ ግማዱን በተሸከምሽ በየዘመኑ ይከተክቱሻል። ግን አንቺ ምንጊዜም አንቺው ነሽ። ወድቀሽ የማትወድቂ፤ ተረስተሽ የማትረሺ #ደርባቤ።
ዛሬ እንዴት ያለ ውብ ዘንካታ ጥሩ ቀን ነው። #አገር ማለትን የሆኑበት፤ አገር ማለትን #የኖሩበት፤ አገር ማለትን #ያስተማሩትን ክቡር አቶ አለማየሁ ስመኝን አየሁኝ። እግዚአብሄርን አመሰገንኩኝ። እኒህ የአገርን አገርነት በዓለም ዓቀፍ የንግድ ሥርዓት ውስጥ #ያሰለጠኑ፤ የመሩም #ጭምት ከድንቅ በላይ የተስፋ #ሐሴት የሆኑ ታላቅ ሰው ዜና ሰማሁኝ። #ታቦት ሊቀረጽላቸው የሚገባ። ህይወታቸው #መጸሐፍ የሆነ የመሆን ጉልላትን ዛና ሰማሁኝ።
የተከበሩ አቶ አለማዬሁ ስመኝ የአባት #ቀኜ #ቅኔም #ትውፊትምናቸው፤ የትጋት ተምሳሌት፤ #የታታሪነት አብነት፤ የሞራል #ልዕልና፤ የመዋዕለ ህይወት #ኢኒስቲቲዩት፤ የምግባር ጉልላት፤ የቤተሰብ የለመለመ አለማየሁ ማዕዶት፤ የአገር #ዋርካ፤ የመኖር #ትርጉም፤ የሥልጣኔ #ቀንዲል። የሥራ ባህል #ዊዝደም ናቸው። ደግነታቸው መጠነ ሰፊ ነው። እርህርህናቸው በተደሞ ነው። ለእርዳታ ያላቸው ፈጣንነት ትንግርት ነው። እኔ በስማ በለው አይደለም እማጫውታችሁ ያዬሁትን ዕውነት ነው እምመሰክረው። ሁሉን የሰጣቸው የመልካምነት የፊደል ገበታ ናቸው።
የትህትና #ተክሊል። የመሆን መቻል #ካስማ። የሥነ ምግባር #አናባቢ። የአክብሮት #ሁነኛ። ሁሉ የተሰጣቸው ምሩቅ! የምዕት ሽልማት! በህይወት ሂደቱን ሳይ ዕንባዬ ፈቃዴን አልጠየቀም። ስለምፈራ እንዴት ናቸው ብዬ ጠይቄ አላውቅም።
ስለ ልጆቿ እንቅልፍ ላይ ላለችው ጎንደር የማንቂያ ምልክት ነው። አቶ አለማየሁ ስመኝ፤ ፕሮፌሰር ዶር ማለደ ማሩ፤ አርቲስት ኃይሌ ገሪማ፤ የቀደሙት እነ አቶ በላይ ለዋጥህ፤ አቶ ጌጡ ልዋጥህ ከሊቃውንታት እነ መምህር በላይ፤ እነ አለቃ መንክር፤ እነ አለቃ አራጋው፤ እነ አለቃ ሲራክ፤ እነ መላዕከ ብርኃናት ገብረ አጋይስት፤ እነ አለቃ አስካለ፥ እነ ጄኒራል ፈንታ በላይ፤ እነ ጄኒራል ነጋ ተገኝ በየዘመናቸው ላደረጉት አገራዊ ትጋት ለመቼ ሆነ የምስጋና ቀጠሮሽ እመዋ??? ጎንደር ሆይ ልጆችሽን በህይወት ያሉትን የምታመሰግኚበት፤ በሥጋ የተለዩትን የምታዘክሪበት ቀንሽ መቼ ይሆን?
ቸር አስበን፤ ቸር እንሁን። አሜን።
ቅን አስበን፤ ቀና እንሁን። አሜን።
እግዚአብሄር ይስጥልኝ። አሜን።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
16/12/2025
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ