#ነገን #ስለማትረፍ። ስለሰው ልጅ ታላቅነት ዕውቀት የሰው ልጆች በጣም #ያንሰናል።

 

#ነገን #ስለማትረፍ። ስለሰው ልጅ ታላቅነት ዕውቀት የሰው ልጆች በጣም #ያንሰናል። 
 
አሳዘኝ ክስተት። ይሰቀጥጣል። ይህን መሰል ጥላቻን ስር ነቀል ለውጥ ለማምጣት
 
1) የፍቅር ተፈጥሮ #ካሪክለም ተነድፎለት እያንዳንዱን ልጅ በትምህርት ቤት ማስተማር ይገባል ብዬ ሙግት ከጀመርኩ 15 ዓመት ተቆጠረ። 
 
2) በሌላ በኩል ህግ የጥቂት ሙያተኞች ብቻ ሳይሆን #የማህበረሰቡ ይሆን ዘንድም ከአጸደ ህፃናት ጀምሮ እያንዳንዱ ልጅ በአገሩ #ህገ መንግሥት እና #በታህሳስ 10/1948 ዓለም ዓቀፋ ድንጋጌ ታንጾ ሊያድግ ይገባል።
 
እኔን መሰል ሙሉ ዕድሜ ላይ ለምንገኝ ደግሞ በፓናል ዲስከሽን፤ በሰሚናር፤ በጉባኤ በየቀበሌው መሠረታዊ የፍቅር ተፈጥሮ እና የህግ ጉዳይ #ልንማር ይገባል። ስለ ሰው ልጅ ታላቅነት እውቀት በጣም ያንሰናል። 
 
አንድ ሰው ግዴታውን ካላወቀ ወንጀል ሊሠራ ይችላል። ህግ ከታወቀ ግን ዓይን ይከፈታል። መብትእና ግዴታን አጥርቶ ማወቅ ይቻላል። ፍጽምነት ባይኖር በአንፃርነት።
 
#መማር#ማወቅ ጥቁር እና ነጩን መለየት ይቻላል። ይህን መሰል አሰቃቂ ወንጀል ምንጩ አንድም #የህግጋትን ድንጋጌወች አለማወቅ፤ በሌላም #ጥላቻን #የሚነቅል ተቋም ዓለማችን ስሌላት ነው፤ እንዲህ ትውልድ #መርዶ ስንቁ እንዲሆን የተደረገው።
 
በውነቱ አውስትራልያ ይህን መሰል አሰቃቂ ሃዘን ብዙ የማይገጥመው አገር ነበር። እጅግ አሳዛኝ ጥቁር ዕለት ነው ለአውስትራልያውያን እና ለመላ የዓለም ህዝብም።
 
የሆነ ሆኖ ለተጎጂ ቤተሰቦች #መጽናናትን እመኛለሁኝ። ሥጋቸው ከነፍሳቸው የተለዩት #ሰማዕታት ናቸው። እረፍታቸውን ፈጣሪ የሰላም ያድርግ። አሜን። ክሪስማስ ሲመጣ ሁልጊዜ ይህን መሰል መከራ ይመጣል። ፈጣሪ ለዓለም ህዝብ #ሰላም ይሰጥ ዘንድ አቅሙ ያላቸው ይፀልዩበት ዘንድ በትህትና አሳስባለሁኝ።
"አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ።" አሜን።
ሥርጉትሻ 2025/12/15

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

የእኔ እማ ልዕልቴ እንዴት ነሽ?

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።