«#ማቆም።» #የመንፈስ #ቅዱስ #ስጦታ። የመወሰን አቅም #በ፭ አመቷ ህፃን። #እኛንም #ታዘብኩት። #እኛንም #ፈራሁት።
"እግዚአብሄር በአንድም በሌላም ይናገራል። ሰው ግን አያስተውለውም።"


የእኔ በኽረ አጀንዳ ትውልድ እና እናትነት ነው። እመኑኝ ብዬ አላስቸግርም። ማታ ሸምቼ የማድረው ይህን የምክር አገልግሎት ነው። በዚህ ዓውድ የሰማዕት እናት ቅድስት እየሉጣ እና የህፃኑ ቅዱስ ቂርቆስ ታሪክ ጋር ጭብጡ ተዋህደብኝ። ስለሆነም እኔ የተሰማኝን ውስጥ ላጋራችሁ ፈለግሁኝ። አደብ። አቅል። ተመስጦ። ተደማዊነት ይጠይቃል።
ግልቢያ፤ ግልብልብ የሆነ ነገር፤ ጥድፊያ እና ችኮላ ግጥሜ አይደሉም። የሆነ ሆኖ እናትነትም፤ ነገን ለማን የሚያስጨንቃችሁ ቅን ወገኖቼ ህሊናን የሚጠይቅ፤ የሚፈትሽ የቅድስት ኤልዳና ባዬን ቆይታ በዶንኪ ቲውም ትከታተሉት ዘንድ በታላቅ ትህትና እጠይቃለሁኝ። ቤተመንግሥትም የኢትዮጵያው እንዲያዳምጠው እመኛለሁኝ።
ሥጦታ የመንፈስ ቅዱስ ነውና። ግን ውስጥን አጥርቶ ሊሆን ይገባል። ከአንደበት ውጪ ያሉ የአካላችን ክፍሎች ቋንቋ አላቸው። ወደ ጦርነቱ ቀጠና ቃለ ምልልሱ ሲገባ እንደ እናት ኮስተር ስትል፤ እንደ ምክር አገልግሎት ሰጪም ውሽክ ብላ ስትገልጽ የምህረት ዓዋጅ ኪኖ ነው። ማስተዋሉን ለሰጠው።
እራሱ ዶንኪ ቲዩብ መንፈስ ቅዱስ እንዳልራቀው ምልክት ነው። በእኔ በኩል ገንፎ ነገር፤ ተጨማሪ ማስታወቂወችን ደርቶበታል። ቢቆርጠው ኤዲት ቢያደርገው ምኞቴ ነው። ለነገሩ እኛን እንደ ሰው የሚቆጥር የለም። ፌስቡኩን ተከትዬው ነበር። ባን ያድርጉኝ፤ ሚዊት አይታወቅም። ከዲያስፖራም የክት እና የዘወትር አለ። በተጽዕኖ ፈጣሪወች ዘንድ። አርቲስት አማኑኤል ብቻ የቤታችን አባል ነው። እንደ ሰው አይቶናል እና አመሰግነዋለሁኝ። ለመልዕክትም ብቸኛው ኢትዮጵያዊ ነው መልስ የሰጠኝ።
#የላይኛው የእዮር መልዕክት። ስክሪፕት ነው በዕውነተኛ ታሪክ የተመሰረተ አዳኝ ማኒፌስቶም። የትም የማይገኝ። አልማዝ።
"ሀ) አሁን እኔ ገጠር ልገባ ነው።
ለ) ገጠር ከዛ ለመሞት ፈልገኃል እንዴ? ከዛ እኮ ተኩስ ነው፤
ሀ) እና ይቅርብኝ በትህትና ደንግጦ ይጠይቃታል።
ለ) አወ #ይቅርብህ። የዓይኗ ምልከታ ከአባት በላይ ነበር። ድገሚው ብትባል ያን ስሜት አትችልም።በወቅቱ ከእሷ ጋር የነበረው ቅዱስ መንፈስ በድምጽም በአካላት እንቅስቃሴ፤ በስሜትም ትዕይንት ነበር። ተሼም አንገቱን #ደፋ። ደነገጠም።
ሀ) ቀጠለ ትምህርት ትማሪያለሽ?
ለ) አልማርም።
ሀ) ለምን?
ለ) ተኩስ ሲሆን እኔ እናቴ ትፈራለች።
ሀ) ጸጉርሽን ስትተኮሺ ብሎ ፈገግ ብሎ ከድንጋጤው ተመልሶ ይጠይቃታል።
ለ) አይ… አይደለም።
ሀ) እህ? ይላታል።
ለ) ትምህርት ቤት ስማር ተኩስ ሲነሳ ትፈራለች።
ሀ) የምን ተኩስ ብሎ ደግሞ ይጠይቃታል።
ለ) ሰው ለመምት።
ሀ) ጥይት ነው እንዴ ይተኮሳል?
ለ) አወን።
ሀ) እናንተ ቦታ ለምን?
ለ)) ግጥሚያ አንዳንድ ጊዜ ይገጥማሉ።
ሀ) እግር ኳስ ነው ይላታል?
ለ) ጥልቅ በሆነ በተመስጦ ውስጥ ሁና #ጦርነት ነው ትለዋለች።
ሀ) አንቺ በምን አወቅሽ ይላታል።
ለ) እለቅሶ ሲለቀስ ነዋ ትለዋለች።
ሀ)……… አዬዬ ለቅሶ ይለቀሳል? ምን ይባላል? ትንሽ ተዚህ ላይ ውስጠ ስሜቱ??? የማይለመድ ሞት ተለመደና እኛን አጣነው።
ለ) ደግሞ ምን ይባላል? አሃ! ወንድማለም ወንድሜ ነው እንጂ ሌላ ምን ሊባል ነው?
ለ) ተመቶ ነው። ተኩስ ሲተኮስ እስማው የለ።
ሀ) አንቺ አሁን የጥይት ድምጽ ሰምተሽ ትለያለሽ?
ሀ) ወዴት?
ለ) #ትፈራለች።
ሀ) አሃ ……… ሲተኮስ?
ለ) አወን!
ሀ) የመጀመሪያ ቀን ጥይት ሲተኮስ ምን ተሰማሽ አንቺ?
ለ) ምን ይሰማኛል እነ መቅደስ #ሊሞቱ ነው እንጂ አልኩኝ።
ሀ) ማለት እነ መቅደስ እነማን ናቸው?
ለ) እህቶቼ።
ሀ) ታላላቆችሽ?
ለ) አወን።
ሀ) ሲተኮስ እናትሽ የምትሰጋው የሆነ ነገር ይሆናሉ ብላ ነው?
ለ) አወን ሲገድሉ የሰው #ደብ ብሎ የሚሞት፤ ………
ሀ) አሃ እሱን ስትሰማ አካላቷ አብሮ ነው የሚሄደው። ጥይቱ ሰው ሲመታ ደብ ነው የሚለው፤ ካልመታ ጥይቱ ምንድን ነው የሚለው?
ለ) አ ……… #ጢው ጢው ነው።
ሀ) እንዴት አወቅሽ አንቺ?
ለ) አውቃለኋ! መደበኛ ትምህርቷ እኮ ሆኗል ተሼ። በጣም በእርግጠኝነት ነው የምትመልሰው።
ሀ) ቆይ! ጥይቱ ሲተኮስ ነው ማለት ነው እህ። ዝም ብሎ ሂዶ ምንም ያላጠፋ ሰው ቢሆን ይገድላል እንዴ?
ለ) አወን።
ሀ) እኔ እማውቀው ጦርነት ህፃናት ሰፈር ውስጥ የኮባ ሽጉጥ ሰርተው ሲጫወቱ ነው።
ለ) እሱ ነው እንዴ የምታውቀው? #በትዝብት ነው ይህን ጥያቄ ያነሳችው? ቀደም …… እንደዛ ነበር የምንጫወተው።
ሀ) ግን አንቺ ጦርነት እንዲቆም ወይንስ እንዲቀጥል ነው የምትፈልጊው?
ለ) #እንዲቆም።
ሀ) ጦርነቱ እንዲቆም ምንድን ነው ሁላችንም ማድረግ ያለብን ብሎ ተሼ ምክር ይጠይቃታል። ጥልቀቷ - ገርሞታል። አቅሟ - ደንቆታል። ሲያት ከመጀመሪያው ይልቅ በተለዬ ሁኔታ ነበር። መለሰች - አጭር - ግልጽ - ፋክት አመክንዮዊ መልስ ሰጠች። መልሷ የሁላችን ህሊና ለዛሬ፤ ለነገም፤ ለነገ ተወዲያም ሰነዳችን፤ ድንጋጊያችን ማኒፌስቷችን ሊሆን ይገባል።
ለ) "#ማቆም!"
ሀ) አንቺ ትጸልያለሽ?
ለ) አወን።
ሀ) ምን እያልሽ።
ለ) ጌታ ሆይ! ምህረት እና ጸጋን በእኛ ላይ አሳድር ነው እንጂ ሌላ ምን እላለሁኝ? ይህ አገላለፆዋ እራሱ ከውስጥ ጋር ይዋሃዳል።
«አረቄ እጠላለሁ !! ከእናትሽ ጋር እነጋገራለሁ!! አስደናቂዋ ህጻን ኤልዳና ያቀረበቸው የሰላም ጥሪ!!#dinklijoch #donkeyyoutube #ድንቅልጆች «
"እግዚአብሄር በአንድም፤ በሌላም ይናገራል፤ ሰው ግን አያስተውለውም።"
* ምዕራፍ ፲፯።
* መቅድመ ዕይታ።
እንዴት አደራችሁ ውዶቹ፤ ውቦቹ ክብረቶቼ። እኔ አምላኬ ክብሩ ይስፋ ደህና ነኝ። ደህንነታችሁ እጅግ ያስፈልገኛል። እኔ ካለ እናንተ ምንም መሆኔን አውቀዋለሁ እና። ትህትናችሁ ከምትጠብቁት በላይ ቆሞ ያስተምረኛል። የትህትና ልዕልት፤ የዝምታ ክብር አቨይ ቢያሳድጉኝም ዕለታዊ ህይወቴ ሲቀጥል የታነጸው በማህበረሰባችን ልዩ ክትትል እና ጥንቃቄ ነው።
ይህን ቃለ ምልልስ ሼር ሳደርግ ከዚህ ከእኔ ፌስቡክ ይልቅ ከቦታው ዶንኪ ቲውብ ላይ ብታደምጡት ፲፯ ቀናት ውስጥ አንድ ሚሊዮን ካገኜ የ፶ ሺብር ታገኛለች ታምረኛዋ፤ ብልኋ፤ የመወሰን አቅም የተሰጣት ህፃን።
ከቲክቶከር ወጣቶች እሰጣ ገባ በተያያዘ ልጅ ሞገስ ዘውዱ የሃሳብ ገበታ አዘጋጅ ጨረፍ አድርጎ አንስቶት ነበር። አልኮል መጠጣትን ለልጆች ዕውቅና መስጠት ይሆናል በሚል ስጋት ይመስለኛል። አማራ ክልል ልጅ ሞገስ ስላላደገ እንጂ የአረቂውን ባላውቅም ወላጆች ለልጆቻቸው የቀመሱትን ሁሉ የማቅመስ ባህል አላቸው። የታዘለ ከሆነ በጣታቸው ከሚጠጣው ንክር አድርገው ያቀምሱታል።
በእነሱ እሳቤ ማህበር ቢሆን፤ ጸበለ ፃዲቅ ቢሆን በረከቱ ለልጃቸው እንዳይቀር በሚል ዕሳቤ ነው። የኢትዮጵያ ፖለቲካ እጅግ እግራችን ተብትቦ ስለያዘን እንጂ የኢትዮጵያ ህዝብ አኗኗሩ፤ ወጉ፤ ልማዱ ብዙ በጣም ብዙ ነው። ለህትም አልበቃም እንጂ በ፯ኛው መጸሐፌ ላይ ይህን መሰል ጉዳዮችንም አክዬ ነው የፃፍኩት። የወግ ገበታ። የወግ ገበታ የምለው ዛሬ እሱ የሃሳብ ገበታ ስላለም አይደለም። አልቀዳሁም እንደማለት።
* ለዘመናችን ከመንፈስ ቅዱስ የተላከ መልዕክት።
እኔ ለህትምት በበቁ መፃህፍቶቼ፤ እዚህም ስጽፍ፤ ዩቱብ ላይም የሌሎችን አዳምጬ አስተያዬት ስሰጥ በቋሚነት የምጽፈው፤ የምናገረው ………እያንዳንዱ ልጅ ሲወለድ ………
1) መክሊት ይዞ ይወለዳል።
2) ጥሪ ይዞ ይወለዳል።
3) መልዕክት ይዞ ይወለዳል ፖስተኛ ነው። እላለሁኝ። የዚህች ቅድስት ህፃን ኤልዳነ ባዬ መልዕክት ለእኛ ብቻ አይደለም በጦርነት እሳት በምትንገረገብ ምድራችንም ጭምር ነው። የገዘፋ ጦርነቶች ዓለማችን እያቃጠላት ነው። ሥልጣኔን ሥልጣኔ እያወደመው ነው። ቅድስና ክልል - አህጉር - ዞግ - ፆታ - የቆዳ ቀለም - አድራሻ - የትምህርት ደረጃ - ፆታዊ ሁኔታ - ሃይማኖታዊ አቋም - ፖለቲካዊ ሁነት አይገድበውም። አይከልለውም።
ጦርነቱን ለማቆም ምን ይደረግ ብሎ ኮመዲያን እሸቱ ቅድስቷን ይጠይቃታል። "#ማቆም" አለችው። ይህ መልዕክት ለዩክሬን፤ ለራሺያ፤ ለጋዛ፤ ለእስራኤል፤ ለሱዳን፤ ለኢትዮጵያ፤ ለፓኪስታን ለህንድ፤ ለቻይና ለታይላንድ፤ ለስሜን ኮርያ፤ ለደቡብ ኮርያ፤ ለኢራን፤ ለሶርያ፤ ለናይጀርያ፤ ለአፍሪካ ቀንድ የጦርነት አታሞ ለሚደለቅበት የዓለም አካል ሁሉ ይመለከታል። ለአይሲሲ፤ ለአልሸባብ፤ ለሃማስ፤ ለሂዝቦላ ወዘተ ነውም።
ይህ መልዕክት አጀንዳው አይደለም ሚዲያው ሁሉ። ባለፈም ጭፍጫፊ ጉዳዮችን አይቶ የሚፈረጅ፤ የሚቃለል፤ የሚጣጣል አይደለም። ታላቅ በኽረ ዕንቁ መልዕክት ነው። እኔ ትራንፒዝምን እምደግፈው በፖለቲካ አቅሙ ወይንም አቋሙ አይደለም። ጦርነትን ለማቆም ባለው ትጋቱ እና አትኩሮቱ ነው። ጦርነት ሊታስብ አይገባም ባይ ነኝ። ጥፋት እና ጭካኔ ሊታቀድ ስለማይገባ። ጦርነት ከተነሳ ተጠቂው ክፍል መከላከል ግን የግድ ይሆናል። ይህም ሆኖ ጦርነቱን በአጭር ጊዜ ለማቆም ማናቸውም አማራጮች ሥራ ላይ ሊውሉ ይገባል ብዬ አምናለሁኝ። ሰው ማዳን፤ ሰው ማትረፍ ካልቻለ ፖለቲካ ለሰው አይደለም ለባሩድ ነው የተፈጠረው ማለት ይሆናል።
ትውልድ በዚህ ያህል ፍርሃት እና ራድ፤ ህፃናት ለራሳቸው ትተው ለእናታቸው እና ለቤተሰቦቻቸው በዚህን ያክል መጠን እንዲያስቡ ሲፈረድባቸው መኖራቸውን እየገደልን እንደሆነ ሊታወቅ ይገባል። ሙሉ 60 ዓመት ሐረር፤ ኤርትራ፤ ትግራይ፤ ጎንደር፤፦ወሎ፤ አርሲ በከፊል በአርባጉጉ አቅጣጫ ህዝባችን ህፃናት አሳራቸውን አይተዋል። ጦርነት በቃን!
ይህን በግሎባል ደረጃ ተርጉሙት። ከእኛ የቀደመው ትውልድ ጦርነት ተረከበ። እኛም ጦርነት ተሰጠን። የነገውም ትውልድ ጦርነት ይረከብን? ጦርነት እኮ የጭካኔ፤ የአረመኔነት መግቢያ በር ነው። የሰው ልጅ የተፈጠረበትን የመኖር መብት የሚጥስ፤ የህይወት ዘራፊ ባላንጣ፤ የፍቅር ተፈጥሮ ጠላት፤ የፍርኃት፤ የጭንቀት ፋፍሪካ ነው። ይህን ጠቀራማ ክስተት ማቆብ ነው ለእኔ የፖለቲካ ብቃት። ለእኔ የህሊና ልዕልና።
የሚገርመው ጦርነትን የጠነሰሱ፤ ጦርነትን የመሩ ሰብዕናወችን "አትናገሩ" የሚሉ የታበዩ መንፈሶች አሉ። ጦርነትን የጠነሰሱ፥ የመሩ፤ ጦርነትን የሚያቀጣጥሉ ሁሉ መነሳት አይደለም ህግ ሊጠይቃቸው ይገባል። ይጠየቃሉም። ምድራዊው ህግ ባይጠይቃቸው ሰማያዊው አምላካችን /// አላኃችን ይጠይቃቸዋል። ምን አልባትም በቁም እያሉም የላይኛው ቅጣት ሊቀድም ይችላል። ተሰበሰበ ሲባል ብትን፤ ብን የሚለው ነገረ ጦርነት የእግዚአብሄር ፈቃድ ባለመሆኑ፤ አንድዬ ስለሚከፋም ነው።
* ታምርን የመቀበል አቅም እንደምን?
ታምራት የሰው ዳንቴል አይደለም። ታምራት አምላካዊ፤ ፈጣሪያዊ ቅድስና ነው። አትኩሮታችን ካልሸበሸብነው በስተቀር መንፈስ ቅዱስ ለኢትዮጵያ መልዕክት ልኳል። እዮር ፖስተኛ ልኳል። እሷም ቅድስት ኤልዳና ባዬ ናት።
ልጅ ተሼ መለሰ ለእሷ 50 ሺህ ብር ለመሸለም ቅድመ ሁኔታ አያስፈልግህም። የመንፈስ ቅዱስ ቅዱስ ስጦታ በገብያ ህግ አይተዳደርም። የአደባባይ አይደለም። በጦርነት ጉዳይ ላይ ስትነጋገሩ የነበረውን ገፆዋን ልብ ብለህ እየው። ሌላ ነበረች። አተያዮዋ፤ የድምፆዋ ቃና፤ የመልዕክቷ ምት ልዩ ነበር።
የእኔ ክብሮች መንፈስ ቅዱስ ኢትዮጵያን አልተዋትም። መንፈስ ቅዱስ ዓለምን አልተወም። እነሆ ቅድስት ህፃን ኤልዳና ባየን ሰጠን። ይህችን የጽድቅ ቡቃያ፤ የመፍትሄ ጎዳና እናዳምጣት። እንከባከባት። ህይወቱን ለመኖር እንወስን ዘንድ በትህትና እጠይቃለሁኝ።
© መከወኛ።
…… "አንድ ጣሳ ጠላ እናምጣ?" "ሰው ማስቸገር ካልሆነብኝስ? የህፃንነት ጣዕሟ ማዛው ልዩ ወዝ አለው። ጨጓራም፤ አንጀትም፤ ኩላሊት የለኝም። ሳንባስ ስትባል። አለኝ። ማር ናት።
ቸር አስበን፤ ቸር እንሁን። አሜን።
ቅን አስበን፤ ቀና እንሁን። አሜን።
እግዚአብሄር ይስጥልኝ። አሜን።
ኑሩልኝ። አሜን።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
22/12/2025
በቃን! ጦርነት።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ