#መጥኔ #ለኢትዮጵያ ፖለቲካ። #ተስፋዬ መዳህኒተ ዓለም ብቻ ነው።

 

#መጥኔ #ለኢትዮጵያ ፖለቲካ። #ተስፋዬ መዳህኒተ ዓለም ብቻ ነው። 
 
"የቤትህ ቅናት በላኝ።"
 
 
 
የወጣትነ ዘመን፣ የጎልማሳነት ዘመን #ካቴና? መጨረሻው መራራ ስንብት።
 
ለአንዲት ቀን የነፃነት ብርኃን የተነፈጉ ወገኖቻችን ከውስጣችን ብናስባቸው፣ እዮራዊ ምህረት #አይርቅም ነበር። #ሳቅ #ርቆናል። ለምን? #ጭንቀት #ስንቃችን ስለሆነ። መፍትሄውም #ዝንቅንቅ ስላለ። ስለሆነም #እኔ #ተስፋዬ አምላኬ ብቻ ነው።
 
የሃይማኖት አቨው ጠንክረው ቢፆሙ፤ ቢሰግዱ፤ ሱባኤ፤ ድዋ ቢያደርጉ ጥሩ ይመስለኛል። ርህርህና ርቆናል። ከሳሽም፤ ተደሳሽም የእርግማናችን ስጦታ እንጂ ውስጣችን ሳይድን አገር ማዳን፤ ተስፋን ማዳን፤ ነገን ከጭንቀት መታደግ አይቻልም። ከሰሞኑ በአማራ ክልል ያሉ ህዝባዊ ውይይቶችን እንደ አንድ ኢትዮጵያዊ ባተሌ ዜጋ ሆኜ አዳመጥኩት። የቀሩኝ ስላሉ ስጨርስ እጽፍበታለሁኝ። 
 
በፍጹም በፍጹም ሁኔት ብዙ ክስተታዊ ገጠመኞችን አናውቃቸውም፤ #ብናውቃቸውም አልገባንም። ለነገሩ እንዲገባን መፍቀዳችንም በሚመለከትም ዳታው የለኝም። የተራራቀ ፍላጎት እና ምኞት፤ ነፃነት እና ጎዳናው ሁሉም ክስተት ከእኛ የፖለቲካ ክህሎት አቅም በላይ ሆኖ ነው ያገኜሁት።
 
የሆነ ሆኖ የአውሮፓውያኑን 2025 ልንሸኝ ጥቂት ቀናት ይቀሩናል። ያው እኔ የተስፋ ተስፈኛ ነኝ እና እስር ቤት ላሉ የፖለቲካ እስረኞች መፍትሄ ጠባቂ ነኝ። አቤቱታም አቅራቢ ነኝ። ህልሜ ዕውን ቢሆን ዊዝደሟ ኢትዮጵያ ላይ #የፖለቲካ እስረኛ እንዳይኖር ነው። ይህ ደግሞ የገዢውን የብልጽግና የፖለቲካ ሙሉ አቅም ይጠይቃል። ፕሮፖጋንዳ አገር ሰርቶ አያውቅም። የፖለቲካ አቅም ማለት የጽንሰ ሃሳብ ጥራት እና ብቃት ነው። ይህ #በ60 ዓመታት ሳይቻል ትውልድን ተስፋውን ሲዘርፍ ኖሯል። 
 
የፖለቲካ ውክልናው ቀርቶ እነኝህ የኢህፓ ታጋዮች ቢያንስ በህይወት እያሉ ነፃ የጸሐይ ብርሃን ያገኙ ዘንድ እመኛለሁኝ። በህይወት ያሉ ቤተሰቦቻቸው #ወህ ቢሉ። ለዓይነ ሥጋ ቢበቁ። እነሱም #ለጥሞና ጊዜ ሰጥተው መኖርን ቢጀምሩ ምኞቴ ነው። 
 
ለቤታችሁ፤ ለወገናችሁ ፈጣሪ ያብቃችሁ። አሜን።
 
ቸር አስበን፤ ቸር እንሁን። አሜን።
ቅን አስበን፤ ቀና እንሁን። አሜን።
እግዚአብሄር ይስጥልኝ። አሜን።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
21/12;2025
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

የእኔ እማ ልዕልቴ እንዴት ነሽ?

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።