#ትውልድን በልቅና የመቅረጽ #የጎጆ ተጋድሎ። #የ40 ልጆች ህሊና ባለውለታ ሦስት ጉልቻ።

#ትውልድን በልቅና የመቅረጽ #የጎጆ ተጋድሎ። #የ40 ልጆች ህሊና ባለውለታ ሦስት ጉልቻ። 
 
ለእኔ ይህ ፕሮጀክት አልበርት አንስታይን በኢትዮጵያ ደግሞ የመፍጠር ትጋት ነው።
 
«ከጎዳና ተነስቶ እዚህ መድረስ የሚያስደንቅ ነው ፥አዲሱን ቤታቸውን ጎበኘሁ #love #lovestory #ethiopianpodacst #ethiopia»
 
 
"አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ።" አሜን።
 
 ዳኒ የፀሎቴ መልስ ነው ፥ሰው ስጠኝ ብዬ ፀልዬ ነበር #love #lovestory #ethiopianpodacst #ethiopia
 
የፈጣሪ ጥበብ የታዬበት ጎዳና። የአቶ ፍጹም ፍሰሃ፤ የመምህር ዳኒ እና የቅድስት ማርታ ዕውነተኛ ታሪክ ከድንቅ በላይ ነው። የትውልዱን ፈተናን የማሸነፍ ልዩ አቅም የሚያሳይ ታምራታዊ ሂደት ነው።
 
የፍፄን ታሪክ በስሱ ሰከላ አባይ ሚዲያ ላይ ይገኛል። የመምህር ዳኒ እና የቅድስት ማርታ ደግሞ ንቁ አንደበቶች ንቁ ፖድካስት ላይ ይገኛል። ሆሊውድ ቢያገኜው ይህን ታሪክ ሁሉ እላለሁኝ።
 
የትውልድ ጉዳይ በዝንቅንቅ ገጠመኝ የሚሞከር አይደለም። ከስሜታዊነት በፍጹም ሁኔታ የጸዳ፤ ኃላፊነት እና ተጠያቂነት የሚሰማው አጽናኝ ውስጣዊነትን ይጠይቃል።
 
ሴት ወጣት በዚህን ያህል ጥንካሬ ማየት ለእኔ ፈውሴ ነው። ምህረቴም። የዘለው ተስፋዬ የሚረጋጋው ይህን የመሰለ ትንግርት በድርጊት ስመለከት ነው። ወጣቶቹ ጥሪያቸውን አላስተጓጎሉም።
 
ድፍረታቸው ይገርመኛል። ጥንካሬያቸው ይደንቀኛል። በዚህ ውስጥ ፈላስፊት ኢትዮጵያ ሳያት ተስፋዬ ያቆጠቁጣል። ተስፋዬ ተስፋን ያማትራል። 
 
እነኝህ ጥንዶች ለ2018 የ12 መልቀቂያ ፈተና 40 ታዳጊወችን በሥነ ምግባር፤ በሞራል፤ በህሊና ብቃት፤ በለማ የዕውቀት ክህሎት አብቅተን እንገኛለን ብለው ሌት ተቀን እየተጉ ነው።
 
የገረመኝ ወላጆች እነሱን አምነው ልጆቻቸውን መስጠታቸው ነው። ሌላው የደነቀኝ የቅድስት ማርታ የእናትነት ቅንነት፤ የመምህር ዳኒ የአባትነት ቆፍጣናነት ነው። 
 
የጨነቀኝ ደግሞ ልጆቹ የሚተኙበት #አልጋ #የላቸውም። ፍራሻቸው የውሻ ምላስ ዓይነት ናት። ከ40ወቹ ውስጥ 16 ተማሪወች #እስፖንሰር የላቸውም። ግን ጀግኖቹ ኃላፊነት እና ተጠያቂነቱን በፈቃዳቸው ተቀብለው ተያይዘውታል። ለእነኝህ ስፖንሰር ለሌላቸው ተማሪወች 50 ሎሚ ለአንድ ሰው ሸክሙ፤ ለ50 ሰው ጌጡ ስለሆነ ብዙ ቅን ኢትዮጵውያን ስላሉ ይህንን ተስፋ ሰጪ ፕሮጀክት ቢያግዙ ለመኖራቸው ታላቅ ስጦታ ነው። #መታደልም ነው። 
 
በባህሬየ ተጨናቂ ነኝ። #ጭንቀቴ የአዲስ አበባ የአየር ሁኔታ #ተለዋዋጭ ስለሆነ መሬት ላይ ሲተኙ ቅዝቃዜው በጤናቸው ላይ ምን ያስከትል ይሆን ነው??? ፋታ የማይሰጥ ጉዳይ ይህ ነው። 
 
እኔ "ላምረኛ ቢያኮርፍ ምሳው እራቱ ይሆናል" የሚለውን ፈሊጥ አልከተልም። አስፈላጊ ሆኖ ከተገኜ እንዲህም እጠይቃለሁኝ። በማኩረፍ፤ በፋክክክር፤ በማጣጣል የሚገኝ ትሩፋት የለም። ጊዜም እየጣለ ነው የሚሄደው። ጊዜውን መሻማት ብልጠት ሳይሆን ብልህነትም ነው። የፈንግጪው ጉዞ ቋት አይገፋም። ሰክኖ ማሰብ። ረግቶ መትጋት ይገባል። 
 
1) በትምህርት ዙሪያ ትምህርት ሚር በቀጥታ ጉዳዩ ስለሚመለከተው ይህን ጉዳይ ባሊህ ቢለው ብዬ አሰብኩኝ። ለፕሮፌሰር ዶር #ብርኃኑ ነጋ 20 ተደራራቢ አልጋ ብቻቸውን ሊያደርጉት የሚችሉት ጉዳይ ይመስለኛል። በአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ በነፃ ማስተማራቸው የታሪካቸው ክፍል ስለሆነ ዘመኑ ለጠየቀው ታላቅ የትውልድ ለትውልድ ተጋድሎ ጥሪ ወዬ ቢሉ፤ ይህ ካልሆነ ትምህርት ሚር በራሱ የሚሸፍንበት ሁኔታ ቢመቻች?
 
2) #ፍራሽ አምራች ድርጅቶችም ይህን ጉዳይ ባሊህ ቢሉት ጥሩ ነው።
 
3) #የቀዳማዊ እመቤት ቢሮም በትምህርት ጉዳይ ስለሚሳተፍ ይህን በኽረ ጉዳይ አለሁልህ ቢለው ክብር ለራስም ነው።
 
4) በህይወት ይኑር አይኑር አላውቅም የሴቶች የህፃናት የወጣቶች የሚባል #የሚኒስተር መስሪያ ቤት ነበር፤ እነሱም ህልውናቸው ካለ አለንላችሁ ቢሉ፤ ይህን ይህን መሥራት እኮ ነው ተግባራቸው። ቢያንስ ቅኖች የጀመሩትን ተግባር #ማሳለጥም አንድ ነገር ነው።
5) የአዲስ አበባ ከንቲባ ጽ/ ቤትም ይህን ጉዳይም የኛ ቢለው፤ መልካም ነው። 
 
6) ከክልሎች የተረጋጋ ተግባር በመከወን ላይ የሚገኜው #ሱማሌ ክልል ስለሆነ እነሱም በዚህ መሰል የትውልድ ተግባር ቢሳተፋ ያተርፋሉ።
 
7) በአገር ውስጥም በውጭም የሚገኙ #ባለሃብቶችም ይህን የመሰለ // #ለትውልድ // #ስለትውልድ /// #በትውልድ የተጀመረ ቀና ጉዞ ለማገዝ ቢያስቡበት ጥሩ ይመስለኛል።
 
በተረፈ ጠንካሮቹን ቤተዳኒወማርቲ፤ ፍፄን እና ቲሙን አመሰግናለሁኝ። 
 
• ተስፋና የተስፈኞችን ህይወት ለማወቅ የሚሻ ታጋሽ ወገን።
 
«ንብረቱን ሸጦ ቻይና ለላከኝ አባቴ እንዴት እውነቱን ልንገረው#teacherdani#teacher #ethiopianpodcast #podcast»
«ምርጫ አልነበረኝም የሁሉንም ተማሪዎች ስልክ ቀማሁ#teacherdani #ethiopianpodcast #podcast «
«እነ ማርታን ለማግኘት በቴሌግራም እና whatsapp በዚህ ቁጥር ይደውሉ 0932502010#ethiopianpodcast #teacherdani»
ክብረቶቼ እንዴት አደራችሁልኝ። ኑሩልኝ።
 
ቸር አስበን፤ ቸር እንሁን። አሜን።
ቅን አስበን፤ ቀና እንሁን። አሜን።
እግዚአብሄር ይስጥልኝ። አሜን።
 
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
23/12/2025
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።



አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

የእኔ እማ ልዕልቴ እንዴት ነሽ?

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።