#የኤርትራ የፖለቲካ ሊቃናት መሻት የኢትዮጵያ ፖለቲካ #ማስተር ማይንድ መሆን ነው። የጹሁፌ መነሻ የBBC ዘገባ ነው። አያዠዋለሁም።

 

#የኤርትራ የፖለቲካ ሊቃናት መሻት የኢትዮጵያ ፖለቲካ #ማስተር ማይንድ መሆን ነው። 
 
ዘገባው የBBC ነው። እንዳይቆራረጥ ተያያዥ ጉዳዮችን በዬሰዓቱ የወጡ መረጃውን ያካተተ ዘገባ ስለሆነ ይመለከተናል። ስለዚህ ሙሉውን አያይዤዋለሁኝ።
 
• የአሜሪካ መንግስት እስራኤል ለሱማሌ ላንድ የሰጠችውን እውቅና ካጸደቀ አሁን ያለው የዓለም ፖለቲካ መጨናነቅ ረብ ይላል። ይህ ደግሞ አይቀሬ ነው። አንድ ዴሞክራሲን ዕውን ያደረገ ራስ ገዝ አስተዳደር፤ ወሳኝ ለጂኦ ፖለቲክሱ ወሳኝ ሚና ያለው ቦታ የምኞቱ ስኬት ቅርብ ነው። ቢቢሲ ዛሬን አህዱ ያለበትን ተጨማሪ ማብራሪያ አክያለሁኝ። የሰሞናቱ መስማማት ግርም ብሎኛል።
 
"የተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት እስራኤል ለሶማሊላንድ እውቅና መስጠቷን ተከትሎ አስቸኳይ ስብሰባ ጠራ"
"የሶማሊላንድ የዕውቅና ጉዞ እና የእስራኤል ውሳኔ ቀጠናዊ አንድምታዎች
#ቆራጣ ዕይታዬን አክላለሁኝ። 
 
"አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ።" አሜን።
 
 
 የሶማሊላንድ የዕውቅና ጉዞ እና የእስራኤል ውሳኔ ቀጠናዊ አንድምታዎች - BBC News አማርኛ
ለሱማሌላንድ እስራኤል ከሰጠችው የዕውቅና ደፋር መግለጫ ባላነሰ ኢትዮጵያ ሰፊውን የዴፕሎማሲ ተግባር ሰርታላቸዋለች። ምርጫቸውን ዓለም በትጋት የተከታተለላቸው በኢትዮጵያ ምክንያት ነበር ብዬ አምናለሁኝ። ለአሁኑ የእስራኤል ውሳኔ አደፋፋሪው የኢትዮጵያ እና የሱማሌ ላንድ ለጋ ያልጠና ስምምነት ነበር ብዬ አስባለሁኝ።
 
የኢጋድ አቋም አልገባኝም። ባይቸኩል፤ ገለልተኛ ሆኖ ቢቆይ ጥሩ ነበር ብዬ አስባለሁኝ። በሌላ በኩል እስራኤል ለወሰደችው ደፋር ጥንቅቅ ያለ እርምጃ አገረ አሜሪካን ሳታማክር በግብታዊነት ይሆናል የሚል ዕምነት የለኝም።
 
ግብጽ እማ ኦርጋኗን ሁሉ ይንጣል ይህ ጉዳይ። ኢትዮጵያ ከደረጃዋ ወርዳ፤ እሷ የኢትዮጵያን የክብር ልዕልና መውረስ ህልም ስለሆነ አይደንቅም። በቀጣይም አገሯ ላይ ስብሰባ ልትጠራ፤ ሎቢ ቀጥራም ልትሰራ ትችላለች። ኢትዮጵያ ሲባል ለግብጽ የፖለቲካ ሊቃናት የሚያባንናቸው አንዳች ነገር ያለ ይመስለኛል። ለምን ይመስለኛል እላለሁ። ነው እንጂ።
 
#ቱርክ የኢትዮጵያ እና የሱማሌን #የአንካራውን ዲክላሬሽን ክብር፤ ሞገስ፤ ታሪካዊ ስጦታም የሚንድ ስለሆነ በሁሉም መስክ ጠንካራ ብትታገለው አይደንቀኝም።
 
#የአውሮፓ ህብረት፤ የአፍሪካ #ህብረት በዚህ ዙሪያ በተሎ መልስ መስጠታቸው ከተደራጁበት ዓላማ እና ግብ፤ ተቋሞቻቸው ከሚመሩባቸው አህጉራዊ ይሁን ዓለም ዓቀፍ ድንጋጌወች ጋር አስተውለው ሊሆን ይችላል። 
 
ለኢትዮጵያ ዶፋ እየወረደ ያለው ለእስራኤል ነው። ይህንን የመቋቋም አቅሙን ሳይለካ የእስራኤል መንግሥት ቀዳሚ የመሆን ውሳኔ ሊወስን ይችላል ብዬ አላስብም። ከኢትዮጵያ መንግሥት በተሻለ በስክነት ድልዳል ተበጅቶለት፤ በመጪ ችግሮችም በበቂ ተሰናድተው ስለሚሆን እስራኤሎች ይህን የወሰኑት ብዙም ይበረግጋሉ ብዬ አላስብም። በተለይ በዚህ የውሳኔ ዕድምታ ውስጥ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲወች አሳትፈው ከሆነ።
 
እስራኤልን በሚመለከት ስጋቴ ሱማሌ ውስጥ ያሉ የእስራኤል ዜጎች ጥበቃ ላይ፤ ሊደርስ የሚችል ችግርን ለመቋቋም ቀድመው ካልሠሩ ሌላ ይህን ፖለቲካዊ ውሳኔ ሚዛን የሚያሳጣ ጥቃት ሊኖር እንደሚችል ማሰቡ መልካም ይሆናል። ማን ይሁን ማን? የሰውን ልጅ ማትረፍ የዓለም ፖለቲካ መርሆ ሊሆን ይገባል ብዬ አምናለሁኝ። በዓለማችን የፖለቲካ አለመረጋጋት ትውልድ ፈተና ላይ ስለሆነ።
በሌላ በኩል የሱማሌ ላንድ ነዋሪወችም ጥንቃቄ በየአሉበት አገር ቢያደርጉ ምኞቴ ነው። ምክንያቱም የእስራኤል ውሳኔ ቀላል እና በዝም ብሎ ግጥግጥ የሚታይ ስለማይሆን።
 
#የኢትዮጵያ #ማስተር #ማይንድ የመሆን ራዕይ ያለው የኤርትራ መንግሥትን በሚመለከት።
 
የኤርትራ መንግሥት ሚዲያ ላይ ጭምት ነበር። አሁን ግን በትጋት የውሳኔ ሃሳቦች ፍሰትን አያለሁኝ። በብዙ ረጅም ጊዜ ኤርትራን በሚመለከት ዝምተኛ ነው። ፖለቲካውን አውቀዋለሁኝ። ግን በጭምትነት ነው እምከታተለው የሆነ ሆኖ ኤርትራ ዕድሏን ጣምላም ይኑረው አይኑረው ልዑላዊ አገር ሆና ቀጥላለች። ይህም ሆኖ ኢትዮጵያ ከውስጧ አውጥታት አታውቅም። በአወንታዊውም ይሁን በአሉታዊ። ለምን? በአቀደችው የሲንጋፖር ህልም ልክ ለመሆን ፈቃደ እግዚአብሄር ስላረዳት። 
 
"ሰው ያስባል፤ እግዚአብሄር ግን ይፈጽማል"
 
የሆነ ሆኖ ኤርትራ የእሷ የአገርነት ጉዳይ ዕድልን #ቸል ብላየሱማሌላንድን አዲስ ውሃ ያልነካው ዕድል ውሳኔውን በፍጥነት #መቃወሟ የኢትዮጵያ ተስፋ በር #ቢከፈት ያላትን ፖለቲካዊ አቋም አይቸበታለሁኝ። የኤርትራ መንግሥት ስለ ኢትዮጵያ የሚያስበውን #ራዲዮሎጂ ሆኗል። የቀደመውን የሻብያ፤ የጀብኃ የፖለቲካ መሻትን አውቃለሁ። ተምሬውማለሁኝ። ብቻ……… አወን ብቻ፤ ጊዜ፤ ሂደት የሚሰጠው ዕውቀት ስላለ ያንን አምኜ በዝምታ ነው ስከታተል የቆየሁት። የሚያቃልሉ፤ የሚያጣጥሉ ወገኖቼን አዳምጣለሁኝ። 
 
ያ ተገቢ ነው ብዬም አላምንም። የአንድ አገር ጉዳይ የአገሩ ልጆች እና መንግሥት ጉዳይ ነው። ስለሆነም እኔ #የሞፈር #ዘመት ፖለቲካ አራማጅ አይደለሁም። በሌላ በኩል ሁለቱ ህዝቦች የፖለቲካ ኢሊቱ በሠሩት ደባ ነው ተለያይተው የሚኖሩት። ለዚህም ነበር ያን የመሰለ ግኑኝነት ሲፈጠር ደስተኛ የነበርኩት። 
 
በጣም በተቆጠበ ጊዜ የኤርትራ መንግሥት ቃለ ምልልስ ሲሰጥ #ሙሉ ጊዜውን፤ ሰፊውን #እጅ ማለት ይቻላል፤ በኢትዮጵያ ፖለቲካ እንደሚያተኩር አውቃለሁኝ። ለምን? ጊዜ የማይሽረው የኤርትራ የፖለቲካ ሊቃናት ህልም የኢትዮጵያ #ማስተር #ማይንድ መሆን ይናፍቃቸዋል። እንደናፈቃቸውም የሚቀር ይመስለኛል። በምንም ታምር የኤርትራ ፖለቲካ የኢትዮጵያን #ኦርጋኒክ ተፈጥሮ፤ የአፍሪካ ካስማነት፤ የኢትዮጵያን የቀደምትነት ዕሴት እና ልቅና የመሸከም አቅም የለውምና። 
 
ትንሿን አገር ኤርትራን ከሰለጠኑ፤ በኢኮኖሚ ካደጉ አገሮች ተርታ ማሰለፍ አመራሩ አልቻለም። አንድ አይሉ ሁለት የባህር በር ሆነ ወደብ ይዞ። ከሁሉ በላይ ጂኦፖለቲካል የኤርትራ አቀማመጥ ራሱን የቻለ የመሰጠት #ጉግል ነው። ግን ከአለ እዮር ፈቃድ የሚሆን አልሆነም።
በሌላ በኩል በእኔ ዕድሜ የወሎ ክፍለ አገር የውስጥ አካል የሆነው ነገረ #አሰብን በሚመለከት የኤርትራ ሆኖ መቀጠሉ ኤርትራ ከኢትዮጵያ ተቃዋሚወች ጋር ለምታደርገው ድርድር #መያዦ ነው። ፻ አለቃ ማስረሻ ሰጤ በቃ - ለምልልሱ ላይ አጉልቶ የገለጸው "ለህወሃት ወልቃይት ጠገዴን የውጭ" የደንበር አቅም ለማጎናጸፍ ትልሙ የኤርትራ መንግሥት ሲሰራው ጽድቅ፤ እስራኤል ስታደርገው ኩነኔ ሆኖ መታየቱ አይገባኝም። በዘመነ ህወሃት መንበሩን ለማስለቀ ደክሞ ነበር የቀረው የኤርትራ ሊቃውንት። 
 
ፈጣሪ በአሰበው መንገድ ከኤርትራ የፖለቲካ #ችሮታ #ውጪ ነበር ያን የመሰለ ሰላማዊ የሽግግር ክስተት የተከወነው። ለኤርትራ መንግሥት ይሁን ለሚረዳቸው ተቃዋሚወች ስኬቱ #ዱብ ዕዳ ልዩ ፍጹም ልዩ #ክስተት ነበር። ወደፊትም አይቻልም። ኢትዮጵያ የውስጣቸውን ደም የምትዘውረው ሳይለንት ማጆሪቲ የሚባል የጨመተ አቅም አላት። የማይክለፈለፍ፤ ጥልቆ ያልሆነ። ጥብቆነትም የማያሰኜው። 
 
የኤርትራ መንግሥት ከጽኑ ባለአንጣው ከህወሃት ጋር በቅርበት እንደሚሠራ ከጭምጭምታ ያለፈ "#ዕውነት" ሆኗል ካፒቴኑ እንደነገረን። ቀድሞ ነገር የሱማሌላንድ ጉዳይ እና የህወሃት ፍላጎት በታሪክም በፖለቲካ አቅሙ፤ ተክለ ሰውነቱ ማወዳደር የሚያስችል ሆኖ አይደለም ሃሳቡን ያነሳሁት። ብቻ የኤርትራ የፖለቲካ ሊቃናት ነገረ ኢትዮጵያ መደበኛ ሥራቸው ስለሆነም ነው። 
 
ስለሆነም የኢትዮጵያ የባህር በር ይሁን የወደብ ጥያቄ መልስ ማግኜት የኤርትራን የውስጥ የመሻት ፖለቲካዊ ቀጠና #ያንሳፍፈዋል። አትኩሮቱንም ያሳሳዋል። ለዚህም ነው በትጋት የኤርትራ መንግሥት የእኔ ብሎ እየሠራበት የሚገኝ።
 
ስለዚህም ለኢትዮጵያ የወደብ፤ የባህር በር ጉዳይ በዚህ ዙሪያ የሚከፈቱ በሮችን እየተከታተሉ መደፋፈን መደበኛ የኤርትራ ተግባር መሆኑ ፖለቲካዊ ዓላማና ግብ ስለሆነ የሚደንቅ ነገር አይሆንም። ፋክክር ላይ ላለ አንድ አገር ጉዳዩ ነው። መብቱም ነው። መጥኖ መገኜት ደግሞ የኢትዮጵያ መንግስትን ጥንቃቄ፤ አቅም እና ብርታት ይጠይቃል። በሩትን ነገር ከማተኮር ይልቅ በድርጁው የኢትዮጵያ አህጉራዊ አቅም ላይ አተኩሮ ሊሠራ ይገባዋል። 
 
የመገንጠሉ ይሁን ሌሎች ጉዳዮች መሠረቱ ኢትዮጵያን ልቆ የመወጣት፤ ማስተር ፖለቲካዊ ምኞት መሆኑ ይህን ካልሰራ የኤርትራ መንግሥት ምን ሊሠራ ይችላል። ሁልጊዜ የኤርትራ መንግሥት ከግብጽ ጋር ሲገናኝ የሚርዱ ፖለቲከኞችን አዳምጣለሁኝ። ፈጣሪ እና ተፈጣሪ አብሮ መሥራታቸው ሎጅካል ነው። የሚያርበተብትም ሊሆን አይገባም።
 
በሌላ በኩል ሌላ ተፎካካሪ አገር ከኤርትራ ፈቃድ ያላገኜ፤ በኤርትራ መንግሥት ሥር መተዳደርን የማይፈቅድ የአፍሪካ ቀንድ ተፈላጊ አገር ሆኖ መምጣት ውድድሩን ያመጣጥነዋል። ስለዚህ ኤርትራ አቋሟ በጥገኛ የጥበቃ ኃይል ላለችው ሱማሌ መወገን ከራስ ጥቅም እና የአትኩሮት መሳሳት ጋር ስለሆነ ይመስለኛል። በኤርትራ ፖለቲካ ጉዳይ ተከታታይ ክስተቶችን ባውቃቸውም ብዙ ጊዜ ዝምታ ነው ምርጫዬ። ስለሆነም በዚኽው ልከውነው።
 
አንድ ነገር ግን የእስራኤል በትክከለኛ የዴሞክራሲ ምርጫ፤ ሰላማዊ የፖለቲካ ሽግግር በምታደርገው የሱማሌላንድ ፖለቲካዊ አገራዊ ዕውቅና መሰጠቱ ለኢትዮጵያ አሸወይና ነው። ኢትዮጵያ ምኞቷ ባይሳካ እንኳን የሃሳብ ጽንሰቷን ያስፈጸመ ሌላ ጠንካራ አገር ወደፊት መምጣት ተስፋ ሰጪ ክስተት ነው።
 
የጁቢቲው አቋም አይደንቅም። ጉሮሯዋ ለጁቡቲ ኢትዮጵያ ናት። ኢትዮጵያ ሌላ የአማራጭ በር ሰላማዊ ሆኖ ቢሳካላት የጁቡቲ ብቸኛ ዕድል ተፎካካሪ ሲመጣበት ማኩረፍም፣ መበሳጨት ሊሆን የሚችል ነው። የጁቡቲ መሠረትም ኢትዮጵያ ናት። እንዲህ አሁን ጥገኛ ልትሆን። እሰቡት የአፍሪካ ቀንድነት፣ የጁቡቲው ሲታከል ይህ የማይመቹ አገሮች ምቾት የሚሰጣቸው አልነበረም። የሆነ ሆኖ በነጮቹ የአዲስ ዓመት ዋዜማ አፍሪካ ቀንድ በአዲስ የፖለቲካ ሙቀት ከቸች ብሏል። 
 
ቸር አስበን፤ ቸር እንሁን። አሜን።
ቅን አስበን፤ ቀና እንሁን። አሜን።
ነሩልኝ ማህበረ ቅንነት። አሜን።
 
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
28/12/2025
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።
እግዚአብሄር ይስጥልኝ። አሜን።
 
())))))))(((((())))))))))()))))))))))))))))()((((((((()
• «እስራኤል ለሶማሊላንድ የነጻ እና ሉዓላዊ አገርነት ዕውቅና በይፋ ሰጠች»
26 ታህሳስ 2025
 
«እስራኤል ከሶማሊያ ተነጥላ ነጻ አገርነቷን ላወጀችው ሶማሊላንድ "የነጻ እና ሉዓላዊ አገርነት" ዕውቅና መስጠቷን ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታኒያሁ ይፋ አደረጉ።
 
ይህ የእስራኤል ውሳኔ ከሦስት አስርት ዓመታት በላይ ከሶማሊያ ማዕከላዊ መንግሥት በመነጠል የነጻ አገርነት ዕውቅናን ስትጠብቅ ለቆየችው ሶማሊላንድ የመጀመሪያው የአገርነት እውቅና ነው።
 
ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ እስራኤል የሶማሊላንድ ሪፐብሊክን እንደ ነጻ እና ሉዓላዊ አገርነት በይፋ እውቅና መስጠቷ ለአፍሪካ ቀንድ አካባቢ ትልቅ ዲፕሎማሲያዊ እርምጃ ነው ብለዋል።
 
ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ እና የሶማሊላንድ ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት የጋራ ስምምነት ተፈራርመዋል።
ሶማሊላንድን የግዛቷ አካል አድርጋ የምትቆጥረው ሶማሊያ የትኛውም አገር ዕውቅና እንዳይሰጥ ስትከላከል ቆይታለች።
የአሁኑን የእስራኤልን ውሳኔ በተመለከተ የሶማሊያ መንግሥት ምላሽ እየተጠበቀ ነው።
 
ይህንን ይፋዊ ዕውቅናን በተመለከተ ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ሳአር እንዲሁም የሶማሊላንድ ፕሬዚዳንት የጋራ ስምምነት ተፈራርመዋል።
 
ስምምነቱ የተፈረመው በፕሬዚዳንት ትራምፕ አነሳሽነት በተረቀቀው የአብርሃም ስምምነት አማካኝነት መሆኑ ተገልጿል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ሳር አርብ ዕለት እንዳስታወቁት እስራኤል እና ሶማሌላንድ ሙሉ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት መጀመር የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራርመዋል።
 
ይህ ስምምነት የአምባሳደሮች ሹመትን ጨምሮ በሁለቱም አገራት ኤምባሲዎችን ለመክፈት የሚያስችል ነው ተብሏል።
ኔታንያሁ የሶማሌላንድ ፕሬዚዳንትን አብድርሃማን ሞሐመድ አብደላህን እንኳን ደስ አለዎት ያሉ ሲሆን፣ ሰላም እና መረጋጋት ለማምጣት ያላቸውን ቁርጠኝነት እና የሚሰጡትን አመራር አድንቀዋል።
 
የሶማሊላንድ ፕሬዚዳንት ጽሕፈት ቤት እስራኤል የሰጠችውን የሉዓላዊ አገርነት ዕውቅናን ተከትሎ ባወጣው መግለጫ "ታሪካዊ እና በመርኅ ላይ የተመሠረተ ውሳኔ" ሲል አድናቆት ገልጿል።
 
አክሎም እውቅናው ሶማሊላንድ በዓለም አቀፉ መድረክ ለዓመታት እውቅና ለማግኘት ስታደርግ ለነበረው ጥረት መሠረት ነው ብሎታል።
"ይህ ዕውቅና ሶማሊላንድ ለረዥም ጊዜ ዓለም አቀፍ ተቀባይነት ለማግኘት ስታደርግ የነበረው ረዥም ጉዞን የሚያመለክት ሲሆን ይህም ታሪካዊ፣ ሕጋዊ እና የሞራል አገርነት ይገባኛል ጥያቄን ያረጋግጣል" ብሏል።
 
የፕሬዚዳንቱ ጽህፈት ቤት መግለጫ ሶማሊላንድ ከእስአራል ያገኘችው የአገርነት ዕወቅና በአፍሪካ ቀንድ የተረጋጋች፣ ዲሞክራሲያዊ እና ኃላፊነት የሚሰማት አገር መሆኗን ያሳያል ብሏል።
 
ሶማሊላንድ ከ30 ዓመታት ነጻ መንግሥት መሥርታ ከቀሪው የሶማሊያ ግዛት በተለየ የተረጋጋ ሥርዓት ለመገንባት ከመቻሏም በላይ በበርካቶች የተወደሱ ዴሞክራሲያዊ ምርጫዎችን በመካሄድ የመሪዎች ለውጥ አድርጋለች።
 
ነገር ግን ከየትኛውም የዓለም አገር፣ ቀጠናዊ፣ አህጉራዊ እና ዓለም አቀፋዊ ተቋም የአገርነት ዕውቅናን ሳታገኝ ቆይታለች። እስራኤል ለሶማሌላንድ የሰጠችው ሌሎችም ተመሳሳይ እርምጃ እንዲወስዱ በር ሊከፍት ይችላል። ፕሬዝዳንት ትራምፕ ወደ ሥልጣን ከመጡ በኋላ በአሜሪካ ባለሥልጣናት በኩል ለሶማሊላንድ ዕውቅና የመስጠት ጉዳይ በተደጋጋሚ ሲነሳ ቆይቷል።
 
5.7 ሚሊዮን ሕዝብ ያላት ሶማሊላንድ ታኅሣሥ 22/2016 ዓ.ም. ለኢትዮጵያ የባሕር ጠረፍ ያስገኛል የተባለ የመግባቢያ ሠነድ ፈርማ በምትኩ ኢትዮጵያ የአገርነት እውቅና እንደምትሰጣት ተገልጾ ነበር። 
 
ነገር ግን ስምምነቱን ተከትሎ የሶማሊያ መንግሥት ኢትዮጵያ "የግዛት አካሌ ጋር ስምምነት በመፈራረም ሉዓላዊነቴን ጥሳለች" በማለት ተቃውሞ በማሰማቷ እና ውጥረቶች በመከሰታቸው ፍጻሜ ሳያገኝ ቀርቷል።
 
ይህንንም ተከትሎ የሶማሊያው ፕሬዝደንት ሐሰን ሼክ ሞሐሙድ ኢትዮጵያ ከሶማሊላንድ ጋር የገባችውን ስምምነት "ውድቅ የሚያደርግ" ያሉትን ሕግ አውጥተዋል።
 
ፕሬዝደንቱ ሕጉ "አንድነታችንን እና ሉዓላዊነታችንን እንዲሁም የግዛት አንድነታችንን ለመጠበቅ" ወሳኝ ነው ብለው ነበር። በሁለቱ አገራት መካከል ያለው ውጥረት መባባሱን ተከትሎ ቱርክ ጣልቃ በመግባት ከስምምነት ላይ እንዲደርሱ አድርጋለች።
 
ከዚህ ስምምነት በኋላ በተከታታይ የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ጋር ተነጋግረዋል።
በአንድ ዓመት ውስጥ ተግባራዊ ይደረጋል ተብሎ የነበረው የኢትዮጵያ እና የሶማሊላንድ የመግባቢያ ስምምነት መቋጫ ሳያገኝ ቀርቷል።
የሶማሊያ አካል የነበረችው ሶማሊላንድ የሶማሊያ ወታደራዊ መሪ የነበሩት ሲያድ ባሬ በአውሮፓውያኑ በ1991 ከሥልጣን ከተወገዱ በኋላ ነጻ አገር መሆኗን አውጃለች።
 
ሶማሊላንድ የራሷን መንግሥት ያቋቋመችው በሲያድ ባሬ አገዛዝ ዘመን ነጻነታቸውን ለማግኘት ሽምቅ ውጊያ ሲያካሄዱ የነበሩ ታጣቂዎች ረዥም የትጥቅ ትግል ካደረጉ በኋላ ነው።
 
በዚህ የሶማሊያ የእርስ በእርስ ጦርነት በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ሲገደሉ ከተሞች ደግሞ በከፍተኛ ሁኔታ ውድመት ገጥሟቸው ነበር።
ሶማሊላንድ የራሷ የፖለቲካ ሥርዓት፣ የመንግሥት ተቋማት፣ ወታደራዊ እና የፖሊስ ኃይል እንዲሁም የራሷ መገበያያ ገንዘብ አላት።
ከነጻነት በፊት በነበረው በታሪኳ ዘለግ ላለ ጊዜ በብሪታኒያ የሞግዚት አስተዳደር ሥር ከቆየች በኋላ በጣሊያን ቅኝ ግዛት ሥር ከነበረው የሶማሊያ ክፍል ጋር ተዋህዳ ነበር።»
 
• «ለሶማሊላንድ እውቅና የምትሰጥ ሁለተኛዋ ሀገር ማን ልትሆን ትችላለች?
 
እስራኤል ለሶማሊላንድ ሀገርነት ይፋ እውቅና መስጠቷን ተከትሎ የሶማሊላንድ እና የሶማሊያ እንዲሁም የቀጣናው ዕጣ ፈንታ ምን ሊሆን ይችላል የሚለው ጥያቄ መነሳት ጀምሯል።
 
ሶማሊያ፣ ቱርክ፣ ግብፅ፣ ጂቡቲ፣ የአፍሪካ ኅብረት እና ሌሎች የአረብ እንዲሁም የአፍሪካ ሀገራት ውሳኔውን በፅኑ ተቃውመውታል።
በሌላ በኩል ሶማሊላንድ ሌሎችም ሀገራትም እስራኤልን ተከትለው እውቅና እንዲሰጡ የአቅሟን እያደረገች ትገኛለች።
 
የሶማሊላንዱ ፕሬዝደንት አብዲራህማን ኢሮ እስራኤል እውቅና መስጠትን ተከትሎ ባደረጉት ንግግር "ሌሎች ሀገራትም ለሶማሊላንድ እውቅና እንደሚሰጡ" ጠቁመዋል።
 
መገናኛ ብዙኃን እና የፖለቲካ ተንታኞች የእስራኤል እውቅና በቀጣናው ላይ ስለሚኖረው ተፅዕኖ እና ሌሎች ሀገራትስ ይቀላቀሉ ይሆን? የሚለውን ጥያቄ እያብላሉ ነው።
 
#በቀጣይ ምን ይሆናል?
 
በፖለቲካው መድረክ ኃያላን ከሚባሉ ሀገራት መካከል አንዷ እና የአሜሪካ የቅርብ አጋር የሆነችው እስራኤል ከሶማሊላንድ ጋር ያላትን ግንኙነት ማጠናከር እንደምትቀጥል ይጠበቃል።
 
የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታኒያሁ ከሶማሊላንድ ፕሬዝደንት ጋር በነበራቸው የስልክ ውይይት ለትራምፕ መልዕክት እንደሚያስተላልፉ እና ሶማሊላንድ የአብራሃም ስምምነትን እንድትቀላቀል እንደሚጥሩ አስታውቀዋል።
 
ኔታኒያሁ እሑድ ወደ አሜሪካ አቅንተው በፍሎሪዳ ከፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ጋር ውይይት እንደሚያደርጉ ነባር የእስራኤል ባለሥልጣናት ለኤኤፍፒ የዜና ወኪል ተናግረዋል።
 
በያዝነው የአውሮፓውያኑ ዓመት ኔታኒያሁ ወደ ዩናይትድ ስቴትስ ሲያቀኑ ይህ ለአምስተኛ ጊዜ ነው። የፈረንጆቹን ገና እያከበሩ የሚገኙት ዶናልድ ትራምፕ ከኔታኒያሁ ጋር ተገናኝተው በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ እንደሚያወሩ ይጠበቃል።
 
የወዳጃቸው ኔታኒያሁን ውሳኔ ተከትለው ለሶማሊላንድ እውቅና ይሰጡ አንደሆነ በመገናኛ ብዙኃን የተጠየቁት ትራምፕ "ሁኔታውን እያጤንን" የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።
 
አንዳንድ ዘገባዎች እንደሚጠቁሙት የተወሰኑ የአፍሪካ እና ምዕራባዊያን እንዲሁም የአረብ ሀገራት ለሶማሊላንድ እውቅና ሊሰጡ ይችላሉ። ዩናይትድ ኪንግደም፣ ዩናይትድ አረብ ኤሜሬትስ፣ ኢትዮጵያና ደቡብ ሱዳን ከእነዚህ ሀገራት መካከል ይጠቀሳሉ። ቢቢሲ ይህንን ጉዳይ በግሉ ማረጋገጥ አልቻለም።»
 
• «#የኢትዮጵያ ጉዳይ»
 
«ኢትዮጵያ ከሶማሊላንድ ጋር ለረዥም ዓመታት የዘለቀ የንግድ እና የፀጥታ ግንኙነት አላት። ምንም እንኳ ኢትዮጵያ ለሶማሊላንድ እውቅና ባትሰጥም ሀገራቱ በሀርጌሳ እና በአዲስ አበባ ቆንስላዎች አሏቸው።
 
በአውሮፓውያኑ 2024 መባቻ የቀድሞው የሶማሊላንድ ፕሬዝደንት ሙሴ ቢሂ እና የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የተፈራረሙት ስምምነት በሶማሊያ ቁጣን ቀስቅሶ ነበር። ነገር ግን ይህ ስምምነት ፍሬ አላፈራም።
 
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ኢትዮጵያ "የትኛውንም ዋጋ ከፍላ" የባሕር በር ለማግኘት ቁርጠኛ መሆኗን በተደጋጋሚ ሲናገሩ ይስተዋላል።
"ኢትዮጵያ እና ሶማሊላንድ የጋራ ጥቅምና ግንኙነት አላቸው። ምንአልባትም ሶማሊላንድ እውቅና ለማግኘት ይህንን ግንኙነት ትጠቀምበት ይሆናል። ሶማሊላንድ ከሌሎችም ሀገራት እውቅና ማግኘት ስትጀምር ይህን ጉዳይ ያጤኑት ይሆናል ብየ እጠብቃለሁ" ይላሉ የሶማሊላንዱ የሕግ ባለሙያና የፖለቲካ ተንታኝ ጉሌድ ዳፋቅ።
 
በአውሮፓውያኑ 2004 የቀድሞው የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ የብሪታኒያው የፓርላማ አባል ሎርድ ዴቪድ ትሪስማን ጋር ሲወያዩ መለስ "ኢትዮጵያ ለሶማሊላንድ እውቅና ለመስጠት የመጀመሪያዋ ሀገር አትሆንም። ነገር ግን ሶስተኛዋም አትሆንም" ሲሉ ተናግረው ነበር።
 
መለስ ይህን ማለታቸውን ትሪስማን በ2010 በቻታም ሀውስ ባደረጉት ንግግር ነው ይፋ ያደረጉት። ሟቹ ጠቅላይ ሚኒስትር ለሶማሊላንድ እውቅና በመስጠት ኢትዮጵያ ሁለተኛዋ ሀገር እንደምትሆን እቅድ እንደነበራቸው ይነገራል።
 
ጉሌድ እንደሚሉት ከሶማሊላንድ ጎረቤት ሀገራት "በጣም አስፈላጊዋና እውቅና ልትሰጥ የምትችለው" ኢትዮጵያ ናት። በሌላ በኩል የቀድሞው የሶማሊያ ባለሥልጣን እና የፖለቲካ ተንታኝ የሆኑት ሞሀመድ ሙክታር ሁኔታው ለሶማሊያ አደገኛ እንደሚሆን ይናገራሉ። "ኢትዮጵያም ሆነች ሌላ ሀገር እውቅና መስጠቱ ለሶማሊያ ትልቅ ስጋት ነው" ይላሉ።
 
• «#የሶማሊላንድ እውቅና በቀጣናው ምን ሊያመጣ ይችላል?»
 
«የአፍሪካ ቀንድ እና የምስራቅ አፍሪካ የወደፊት ዕጣ ፈንታ በሶማሊላንድ እውቅና ላይ የተመሠረተ ሊሆን እንደሚችል ጉሌድ ይናገራሉ።
ተንታኙ እንደሚሉት ለሶማሊላንድ እውቅና ተሰጠ ማለት በቀጣናው ፖለቲካ አዲስ ጫና ሊፈጥር የሚችል ተዋናይ ተቀላቀለ ማለት ነው።
"እውቅናው ሶማሊላንድን ከፍ የሚያደርግ ነው። ለረዥም ዓመታት ተረስታ የነበረችው ሶማሊላንድ ድምፅ ከግምት ውስጥ መግባት ይጀምራል" ሲሉ ለቢቢሲ ይናገራሉ።
 
ሞሀመድ ሙክታር በበኩላቸው በመንግሥታት መካከል ያለው ፉክክር እና ሌሎች የፖለቲካ ኃይሎች በቀጣናው የሚያደርጉት እንቅስቃሴ ትልቅ ተፅዕኖ አለው።
 
"ቀጣናው ፉክክር እየበዛበት መጥቷል። በጣም ወሳኝ የሚባል ለዓለም አቀፍ ንግድ ትልቅ ቦታ ያለው ስፍራ ነው። የሶማሊያ አንድነትም ሆነ መከፋፈል በቀጣናው ትልቅ ለውጥ ሊያመጣ ይችላል" ይላሉ።»
 
• #የተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት እስራኤል ለሶማሊላንድ እውቅና መስጠቷን ተከትሎ አስቸኳይ ስብሰባ ጠራ
 
«ሶማሊላንድ የመጀመርያውን የሉዓላዊ አገርነት ዕውቅና ከእስራኤል አግኝታለች ከሶማሊያ በስተ ሰሜን የምትገኘው ሶማሊላንድ በኤደን ባሕረ ሰላጤ ላይ የምትገኝ ከፊል በረሃማ የሆነች አካባቢ ናት የሶማሊያ ወታደራዊ መሪ የነበሩት ሲያድ ባሬ በአውሮፓውያኑ 1991 ከሥልጣን ከተወገዱ በኋላ ነጻ አገር መሆኗን አውጃለች»
 
• «ከ 1 ሰአት በፊትኤርትራ የሶማሊላንድ እውቅናን በተለመከተ የፀጥታው ምክር ቤት የማያሻማ ምላሽ ሊሰጥ ይገባል አለች»
«ቤንያሚን ኔታኒያሁ ሀገራቸው እስራኤል ለሶማሊላንድ እውቅና መስጠታቸውን ተከትሎ የኤርትራ መንግሥት ባወጣው መግለጫ የተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት የማያሻማ ምላሽ እንዲሰጠ ጠይቋል።
 
የኤርትራ ማስታወቂ ሚኒስቴር በለቀቀው አጭር መግለጫ “ተውኔቱ ምስጢራዊ አይደለም ሲብላላ የቆየ እንጂ” ብሎ “አደገኛ ቀጣናዊ እና ዓለም አቀፋዊ ቀውስ እና መረበሽ” ይዞ ይመጣል ሲል አስጠንቅቋል።
 
የማስታወቂያ ሚኒስትሩ የማነ ገብረ መስቀል የመንግሥታቸውን መግለጫ በኤክስ ገፃቸው አጋርተው የፀጥታው ምክር ቤት አባላት የማያሻማ ምላሽ ሊሰጡት እንደሚገባ አስምረዋል።
 
መግለጫው “በተለይ ‘ከታይዋን’ ጉዳይ ጋር በተያያዘ ያለውን ጉዳይ ከግምት በማስገባት ቻይና ትልቅ ኃላፊነት ልትወጣ እንደሚገባ” ገልጿል። ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር መቃቃር ውስጥ የገባው የፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ አገዛዝ ከሶማሊያ እና ግብፅ ጋር ልዩ የትብብር ማዕቀፍ ስምምነት እንደደረሰ ይታወሳል።
 
አርብ ዕለት የተሰማውን የሶማሊላንድ እውቅና ዜና ተከትሎ በርካታ የአረብ እና የአፍሪካ ሀገራት የእስራኤልን ውሳኔ እንደሚቃወሙ የሚገልፁ መግለጫዎች አውጥተዋል።» 
 
• «ለሶማሊላንድ እውቅና የምትሰጥ ሁለተኛዋ ሀገር ማን ልትሆን ትችላለች?»
 
«እስራኤል ለሶማሊላንድ ሀገርነት ይፋ እውቅና መስጠቷን ተከትሎ የሶማሊላንድ እና የሶማሊያ እንዲሁም የቀጣናው ዕጣ ፈንታ ምን ሊሆን ይችላል የሚለው ጥያቄ መነሳት ጀምሯል።
 
ሶማሊያ፣ ቱርክ፣ ግብፅ፣ ጂቡቲ፣ የአፍሪካ ኅብረት እና ሌሎች የአረብ እንዲሁም የአፍሪካ ሀገራት ውሳኔውን በፅኑ ተቃውመውታል።
በሌላ በኩል ሶማሊላንድ ሌሎችም ሀገራትም እስራኤልን ተከትለው እውቅና እንዲሰጡ የአቅሟን እያደረገች ትገኛለች።
 
አንዳንድ ዘገባዎች እንደሚጠቁሙት የተወሰኑ የአፍሪካ እና ምዕራባዊያን እንዲሁም የአረብ ሀገራት ለሶማሊላንድ እውቅና ሊሰጡ ይችላሉ። ዩናይትድ ኪንግደም፣ ዩናይትድ አረብ ኤሜሬትስ፣ ኢትዮጵያና ደቡብ ሱዳን ከእነዚህ ሀገራት መካከል ይጠቀሳሉ።
 
እስራኤል ለሶማሊላንድ ሀገርነት ይፋ እውቅና መስጠቷን ተከትሎ የሶማሊላንድ እና የሶማሊያ እንዲሁም የቀጣናው ዕጣ ፈንታ ምን ሊሆን ይችላል የሚለው ጥያቄ መነሳት ጀምሯል።
 
ሶማሊያ፣ ቱርክ፣ ግብፅ፣ ጂቡቲ፣ የአፍሪካ ኅብረት እና ሌሎች የአረብ እንዲሁም የአፍሪካ ሀገራት ውሳኔውን በፅኑ ተቃውመውታል።
በሌላ በኩል ሶማሊላንድ ሌሎችም ሀገራትም እስራኤልን ተከትለው እውቅና እንዲሰጡ የአቅሟን እያደረገች ትገኛለች።
 
አንዳንድ ዘገባዎች እንደሚጠቁሙት የተወሰኑ የአፍሪካ እና ምዕራባዊያን እንዲሁም የአረብ ሀገራት ለሶማሊላንድ እውቅና ሊሰጡ ይችላሉ። ዩናይትድ ኪንግደም፣ ዩናይትድ አረብ ኤሜሬትስ፣ ኢትዮጵያና ደቡብ ሱዳን ከእነዚህ ሀገራት መካከል ይጠቀሳሉ።
 
• «ግብፅ፣ ኢራን፣ ቱርክና ጆርዳንን ጨምሮ በርካታ ሀገራት የእስራኤልን እርምጃ ተቃውመው መግለጫ አወጡ»
 
«ጆርዳን፣ ሳዑዲ አራቢያ፣ ኳታር፣ ጂቡቲ፣ ኩዌት፣ ኢራን እና ኢራቅ እንዲሁም ናይጄሪያ እና ፓኪስታንን ጨምሮ በርካታ ሀገራት በጋራ ባወጡት መግለጫ እስራኤል ለሶማሊላንድ እውቅና መስጠቷን በፅኑ ተቃውመዋል።
 
የጆርዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በማኅበራዊ ሚድያ ገፁ ባጋራው መግለጫ ሀገራቱ እስራኤል የሶማሊያ ክልል ለሆነችው ሶማሊላንድ የሰጠችውን እውቅና በሙሉ ድምፅ “እናወግዛለን” ብሏል።
 
መግለጫው ሀገራቱ የእስራኤልን ውሳኔ ያወገዙት በአፍሪካ ቀንድ፣ በቀይ ባሕር እና በጠቅላላው በመላው ዓለም ሰላምና ፀጥታ ላይ ሊኖረው የሚችለውን አሉታዊ ተፅዕኖ ከግምት ውስጥ በማስገባት እንደሆነ አስታውቀዋል። መግለጫው ይህ “እስራኤል ለዓለም አቀፍ ሕግ ያላትን ንቀት የሚሳይ ነው” ይላል።
 
ጥምር መግለጫው የተባበሩት መንግሥታትን ቻርተር እንዲሁም ዓለም አቀፍ ሕግን አጣቅሶ የሀገራት ሉዓላዊነት እና የግዛት አንድነት መጠበቅ አለበት በማለት ውሳኔው “የእስራኤልን ተስፋፊነት የሚያሳይ ነው” ሲል ወቅሷል። ሀገራቱ ለሶማሊያ ሉዓላዊነት ያላቸውን ድጋፍ አንፀባርቀው የአፍሪካ ቀንዷን ሀገር አንድነት የሚፈታተን ማንኛውንም ውሳኔ እንደሚቃወሙ ገልፀዋል።
 
አልፎም የእስራኤል ድርጊት ይዞት ሊመጣው የሚችለው መዘዝ ከፍተኛ ነው ብለዋል። ባለአምስት ነጥብ መግለጫ ያወጡት ሀገራት አክለው “የፍልስጤምን ሕዝግ በግድ ከመሬቱ ለማንሳት የሚደረግን ሙከራ በፅኑ እንቃወማለን” ይላል።
 
እስራኤል ለሶማሊላንድ የሰጠችውን እውቅና ተከትሎ በርካታ ሀገራት ጥምር መግለጫ ሲያወጡ ይህ የመጀመሪያው አይደለም። 

• «የተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት እስራኤል ለሶማሊላንድ የሰጠችውን እውቅና ተከትሎ አስቸኳይ ስብሰባ ሊያደርግ ነው»
 
«የተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት በሚመጣው ሰኞ እስራኤል ለሶማሊላንድ የሰጠችውን እውቅና በተለመከተ አስቸኳይ ስብሰባ ሊያደርግ መሆኑ ተሰምቷል።
 
ይህንን የገለፁት በተባበሩት መንግሥታት የእስራል አምባሳደር የሆኑት ዳኒ ዳኖን እስራኤል “ከፖለቲካዊ ውይይቶች አታፈገፍግም” ብለዋል። 
 
በኤክስ ገፃቸው ሐሳባቸውን ያሰፈሩት አምባሳደሩ ሀገራቸው “ከአጋር ሀገራት ጋር ትብብርን ለማጠናከር እና ቀጣናዊ መረጋጋትን ለማምጣት በሚል ኃላፊነት በተሞላበት እና ግልፅ በሆነ ሁኔታ” እንደምትንቀሳቀስ አሳውቀዋል።
 
ባለፈው አርብ እስራኤል ለሶማሊላንድ እውቅና መስጠቷን ተከትሎ በርካታ የአረብ ሀገራት ተቃውሞዋቸውን አሰምተዋል። እስራኤል ለሶማሊላንድ ይፋ እውቅና የሰጠች የመጀመሪያዋ ሀገር ናት።» 
 
• 27 ታህሳስ 2025ትራምፕ እስራኤልን ተከትለው ለሶማሊላንድ ዕውቅና እንደማይሰጡ ተናገሩ «የአሜሪካው ፕሬዝዳንት እስራኤልን ተከትለው “በፍጥነት” ለሶማሊላንድ ሉዓላዊ አገርነት ዕውቅና እንደማይሰጡ ተናገሩ።
 
“ሁሉም ነገር ላይ ጥናት እየተደረገ ነው. . . እናጠናዋለን። ብዙ ነገር አጥንቼ ድንቅ ውሳኔ አስተላልፋለሁ። ውሳኔዎቼም ትክክል ናቸው” ሲሉ ከኒው ዮርክ ፖስት ጋር በስልክ ባደረጉት ቃለ ምልልስ ገልጸዋል።
 
“ሶማሊላንድ ምን እንደሆነች በትክክል የሚያውቅ ሰው ግን አለ?” ሲሉም ትራምት ጠይቀዋል። ሶማሊላንድ፤ አሜሪካ ስትራቴጂክ በሆነው የኤደን ባሕረ ሰላጤ ላይ ይዞታ እንዲኖራት ሐሳብ ማቅረቧን በተመለከተ የተጠየቁት ትራምፕ “ትልቅ ነገር አይደለም” ሲሉ አጣጥለዋል።
የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ለሶማሊላንድ ዕውቅና መስጠታቸውን ይፋ ካደረጉ በኋላ፤ ሶማሊላንድ የአብርሃም ስምምነትን ለመቀላቀል እንደምትፈልግ ለትራምፕ እንደሚገልጹ ተናግረዋል። 
 
ትራምፕ ግን ሐሳቡ ብዙም እንዳልተዋጠላቸው ጠቁመዋል። ከኔታንያሁ ጋር በቀጣይ የሚኖራቸው ውይይት የሚያተኩረተው የጋዛ ሰርጥ ላይ እንደሆነም ገልጸዋል። 
 
• «27 ታህሳስ 2025“ግዛት የምታስፋፋው እስራኤል ለፍልስጤም አገርነት ዕውቅና ብትሰጥ ይሻላል”- ኳታር
«ኳታር፤ እስራኤል ለሶማሊላንድ የሰጠችውን ዕውቅና “በጽኑ እንደምታወግዝ” ገለጸች።»
 
“ግዛት የምታስፋፋው” ያለቻት እስራኤል እና ሶማሊላንድ “አንዳቸው ለሌላው የሰጡትን ዕውቅና” እንደማትቀበል አስታውቃለች።
የኳታር የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በማኅበራዊ ሚዲያ ገጹ ባወጣው መግለጫ “ይህ የተናጠል እርምጃ አደገኛ ነው፤ ዓለም አቀፍ ሕግን ይጥሳል፤ የሶማሊያን ሉዓላዊነት፣ አንድነት እና የግዛት ወሰን ይጣረሳል” ብሏል።
 
የሶማሊያን “አንድነት” በሚጥስ መልኩ የሚፈጠር “ትይዩ አስተዳደርን” ኳታር እንደማትቀበል ገልጻለች። የሶማሊያን ደኅንነት እና መረጋጋት ለማስጠበቅ ቁርጠኛ እንደሆነችም አጽንኦት ሰጥታለች። 
 
ኳታር፤ “ከወንድሞቻችን ጎን እንቆማለን” በማለትም አቋሟን ይፋ አድርጋለች። የአገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መግለጫ “ግዛት የምታስፋፋው እስራኤል ለፍልስጤም አገርነት ዕውቅና ብትሰጥ ይሻላል” ይላል።
 
“ፍልስጤማውያን በብሔራዊ ግዛታቸው አገር የመመሥረት መብታቸው ዓለም አቀፍ ድጋፍ ያለው ነው” ሲልም አክሏል።
እስራኤል “ዓለም አቀፉን ማኅበረሰብ መናቋን እንድታቆም” እንዲሁም “ቀጣናዊ አለመረጋጋት የሚያስከትል ደንታ የለሽ ፖሊሲ ከመተግበር እንድትቆጠብ” ኳታር ጥሪ አቅርባለች።»
 
• «27 ታህሳስ 2025“በተናጠል የሚሰጥ ዕውቅና የተመድን ስምምነት ይጥሳል”- ኢጋድ» የምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት ባለሥልጣን (ኢጋድ) እስራኤል ለሶማሊላንድ የሰጠችው “የተናጠል” የሉዓላዊ አገርነት ዕውቅና የመንግሥታቱን ድርጅት እና የአፍሪካ ኅብረትን መርሕ እንደሚጥስ ገለጸ። 
 
በተጨማሪም ከኢጋድ ስምምነት ጋር እንደሚጣረስ አስታውቋል። በማኅበራዊ ሚዲያ ገጹ ባወጣው መግለጫ፤ “ሶማሊያ ሉዓላዊት የኢጋድ አባል አገር ናት” ያለ ሲሆን፤ “በተናጠል የሚሰጥ ዕውቅና” የዓለም አቀፍ ተቋማትን አሠራር ይጥሳል ብሏል። 
 
ለሶማሊያ መንግሥት ያለውን ድጋፍ ገልጾ፤ በቀጣናው ሰላም፣ መረጋጋት እና ትብብር እንዲሰፍን ለማድረግ ሲባል ዓለም አቀፍ ስምምነት እንዲከበር ጠይቋል። ለቀጣናዊ አካታች ፖለቲካዊ ሒደት እና ቀጣናዊ ትብብር ያለውን ቁርጠኛነትም ኢጋድ ገልጿል።»
 
• «27 ታህሳስ 2025እስራኤል ለሶማሊላንድ የሰጠችው ዕውቅና እና የፍልስጤም ስጋት»
 
«እስራኤል በጋዛ ውስጥ ለሁለት ዓመታት መጠነ ሰፊ ወደታራዊ ዘመቻ ባካሄደችበት ጊዜ ጋዛን ሙሉ ለሙሉ በመቆጣጠር ፍልስጤማውያንን ከግዛቲቱ የማስወጣት ፍላጎት እንዳላት በስፋት ሲነገር ነበር።
 
ኋላ ላይም ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የጋዛ ነዋሪዎችን ወደ ሌሎች አገራት በማስፈር ጋዛን የባሕር ዳርቻ የመዝናኛ ስፍራ የማድረግ ዕቅድ እንዳቸላው ይፋ ሲያደርጉ ጉዳዩ መነጋገሪያ ሆኖ ነበር።
 
ከዚሁ ሃሳብ ጋር ተያይዞ ከጋዛ የሚወጡት ፍልስጤማውያን ወደ ተለያዩ አገራት እንደሚሰፍሩ መነገሩን ተከትሎ የተለያዩ አገራት ስም ሲነሳ ነበር። ከእነዚህም መከካል ሶማሊላንድ አንዷ ነበረች።
 
ይህ ፍልስጤማውያንን ከጋዛ አስወጥቶ ወደ ሌሎች አገራት የመውሰዱ ዕቅድ በይፋ ባይነገርም ከተለያዩ አገራት ከፍተኛ ተቃውሞ ገጥሞት ነበር። የሶማሊያ መንግሥት እና ራሷ የሶማሊላንድ አስተዳደር ጭምር ይህንን ሃሳብ እንደማያውቁት እንዲሁም በፍጹም እንደማይቀበሉት በወቅቱ ባወጧቸው በመግለጫዎች አሳውቀዋል።
 
አሁን እስራኤል ለሶማሊላንድ የሉዓላዊ አገርነት ዕውቅና መስጠቷን ተከትሎ ይህ ሃሳብ በስጋት መልክ እየተንጸባረቀ ነው። እውቅናውን ተቃውመው መግለጫ ያወጡት የፍልስጤም አስተዳደር እና ቱርክ ይህነን ጉዳይ ጠቅሰውታል።
 
ፍልስጤም ለሶማሊላንድ የተሰጠውን ዕውቅና እንደማትደግፍ ባስታወቀችበት መግለጫዋ “በተለይም ከጋዛ ሰርጥ ፍልስጤማውያንን በሌላ አገር ከማስፈር ጋር በተያያዘ የሶማሊላንድን ስም እስራኤል ስታነሳ ነበር” በማለት ስጋቷን አመልክታለች።
 
የተሰተውን ዕውቅና ተከትሎ እስራኤል “በማንኛውም ሽፋን ተጠቅማ በግድ ሕዝባችንን እንድታፈናቅል አንፈቅድም” በማለት ከሶማሊላንድ ጋር ተያይዞ ከዚህ በፊት ሲነሳ የነበረውን ሃሳብ በድጋሚ ተቃውማለች።
 
በተጨማሪም የቱርክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የእስራኤልን የዕውቅና ውሳኔ በተቃወመበት መግለጫው ላይ እርምጃው ሕገወጥ እማ በቀጣናው ብሎም በዓለም ዙሪያ አለመረጋጋትን ሊያስከትል የሚችል ነው ብሏል።
 
"ቱርክ ጨምራም እስአኤል በፍልስጤም ግዛቶች ውስጥ የመስፋፋት ፖሊሲዋን በቀጠለችበት እና ፍልስጤም እንደ አገር ዕውቅና እንዳታገኝ ሁሉን ነገር እያደረግቸበት ባለቤእ ጊዜ ለሶማሊላንድ ዕውቅና መስጠቷ ግልጽ ጣልቃ ገብነት ነው ብላለች።»
 
• «27 ታህሳስ 2025ቻይና፣ ሳዑዲ አረቢያ እና ፍልስጤም ለሶማሊላንድ የተሰጠውን ዕውቅና ተቃወሙ»
 
«ፍልስጤም፣ ቻይና እና ሳዑዲ አረቢያ እስራኤል ለሶማሊላንድ ዕውቅና መሰጠቷን በጽኑ አወገዙ። አገራቱ በተናጠል ባወጡት መግለጫ ለሶማሊያ ሉዓላዊነት ያላቸውን ድጋፍም ገልጸዋል። የሳዑዲ አረቢያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ “ለሶማሊያ አንድነት እና የግዛት ሉዓላዊነት ያለንን ድጋፍ እንገልጻለን” ብሏል።
 
እስራኤል ለሶማሊላንድ ዕውቅና መስጠቷ “የተናጠል እና አስገንጣይ እርምጃ” መሆኑን ጠቅሶ “ዓለም አቀፍ ሕግን” ይጻረራል ሲል ኮንኗል። ፍልስጤምም ለሶማሊላንድ የተሰጠውን ዕውቅና እንደማትደግፍ አስታውቃለች። 
 
“በተለይም ከጋዛ ሰርጥ ፍልስጤማውያንን በሌላ አገር ከማስፈር ጋር በተያያዘ የሶማሊላንድን ስም እስራኤል ስታነሳ ነበር” ስትል ፍልስጤም መግለጫ አውጥታለች። እስራኤል “በማንኛውም ሽፋን ተጠቅማ በግድ ሕዝባችንን እንድታፈናቅል አንፈቅድም” ብላለች። በሶማሊያ የቻይና ኤምባሲ በማኅበራዊ ሚዲያው ባወጣው መግለጫ የሁለቱ አገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በስልክ ውይይት እንዳደረጉ ጠቅሶ፤ ለሶማሊያ ያለውን ድጋፍ ገልጿል።
 
“ቻይና የሶማሊያን ሉዓላዊነት፣ ብሔራዊ አንድነት እና የግዛት ወሰን ትደግፋለች” ሲልም የኤምባሲው መግለጫ ያትታል። «
• «27 ታህሳስ 2025"የእስራኤል ውሳኔ አለመረጋጋትን ያስከትላል" ቱርክ «የሶማሊያ መንግሥት ወዳጅ የሆነችው ቱርክ እስራኤል ለሶማሊላንድ የሰጠችውን የአገርነት ዕውቅና በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ በኩል ባወጣችው መግለጫ ተቃወመች።
 
የእስራኤል ውሳኔ “የኔታኒያሁ መንግሥት ሕገወጥ እርምጃ በቀጣናው እና በዓለም አቀፍ ደረጃ አለመረጋጋትን ለመፍጠር ያለመ ሌላ ምሳሌ ነው” በማለት ለሶማሊላንድ የተሰጠውን ዕውቅና ቱርክ ተቃውማለች።
 
የፍልስጤም ጉዳይን በማንሳትም “ይህ እርምጃ የቀጠለውን የመስፋፋት ፖሊሲ እና ፍልስጤም እንደ አገር እንዳትታወቅ ሁሉንም ጥረት የምትዳረገው እስራኤል በሶማሊያ ውስጣዊ ጉዳይ በግልጽ ጣልቃ መግባትን የሚያመለክት ነው” ሲል መግለጫው ወቅሷል።
ጨምሮም የሶማሊያ እና ሶማሊላንድ ክልል መጻኢ ዕጣ ፈንታን በተመለከተ የሚሰጥ ውሳኔ የሶማሊያውያንን ፍላጎት ሚያንጸባርቅ መሆን አለበት ብሏል።
 
በአፍሪካ ቀንድ ሰላም እና ደኅንነት አስፈላጊ መሆኑን የገለጸው የቱርክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መግለጫ ቱርክ የሶማሊያን የግዛት አንድነት በጽኑ እንደምትደግፍ እና ከሶማሊያ ሕዝብ ጎን እንደምትቆም ገልጻለች።
 
የሶማሊያ ወዳጅ የሆነችው ቱርክ በኢትዮጵያ እና በሶማሊያ መካከል በሶማሊላንድ ምክንያት የተፈጠረውን አለመግባባት ያሸማገለች ሲሆን፣ ባለፉት ሁለት ዓመታት ውስጥ ከፍተኛ ምጣኔ ሀብታዊ እና ወታደራዊ ስምምነትን ከሶማሊያ መንግሥት ጋር ማድረጓ ይታወቃል።
• «27 ታህሳስ 2025የአፍሪካ ኅብረት ለሶማሊላንድ ዕውቅና መሰጠቱን ነቀፈ»
 
«የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ማሕሙድ አሊ ዩሱፍ እስአኤል ለሶማሊላንድ ዕውቅና መሰጠቷን ነቀፉ። አርብ ማምሻውን በወጣው መግለጫ ኅብረቱ ለሶማሊያ አንድነት እና ሉዓላዊነት ቁርጠኛ መሆኑን በመጥቀስ እስራኤል ለሶማሊላንድ ዕውቅና መስጠቷ “እጅጉን እንደሚያሰጋ” ተገልጿል።
 
የአፍሪካ ኅብረት እአአ በ1964 ባስተላለፈው ውሳኔ እንዲሁም ባለው የጋራ ስምምነት መሠረት ነጻነትን ማዕከል ያደረገ የአገራትን ድንበር ማክበር ዋጋ የሚሰጠው ጉዳይ እንደሆነ ተጠቅሷል።
 
ኅብረቱ “ሶማሊላንድን እንደ ነጻ አገር ዕውቅና መስጠትን” እንደሚቃወም ገልጾ፤ ሶማሊላንድ የሶማሊያ “ቁልፍ አካል” መሆኗን አስታውቋል። “የሶማሊያን አንድነት፣ ሉዓላዊነት እና የግዛት ወሰን የሚያንኳስስ ውሳኔ ከአፍሪካ ኅብረት መርኅ ጋር ይጣረሳል” ይላል መግለጫው።
 
ውሳኔው “ለመላው አህጉሪቱ ሰላም እና መረጋጋት አደጋ ይደቅናል” ሲልም ኅብረቱ አቋሙን ገልጿል። የሶማሊያ ባለሥልጣናት ሰላም ለማስከበር፣ የመንግሥት ተቋማትን ለማጠናከር እና አካታች አስተዳደርን ለማስቀጠል ለሚያደርጉት ጥረት የአፍሪካ ኅብረት ድጋፍ እንደሚሰጥም አክሏል።»
 
• «27 ታህሳስ 2025የግብፅ፣ የሶማሊያ፣ የቱርክ እና የጂቡቲ ተቃውሞ»
 
«እስራኤል ለሶማሊላንድ ዕውቅና በሰጠች በሰዓታት ውስጥ የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ከሶማሊያ፣ ከቱርክ እና ከጂቡቲ አቻዎቻቸው ጋር የስልክ ውይይት አድርገዋል።
 
በውይይቱ የእስራኤል ውሳኔ በአፍሪካ ቀንድ አካባቢ ያለውን ውጥረት ያባብሰዋል በማለት ስጋታቸውን መግለጻቸው ተዘግቧል።
የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ እስራኤል ሶማሊላንድን እንደ ሉዓላዊ አገር ዕውቅና መስጠቷን የአራቱ አገራት ባለሥልጣናት “ሙሉ ለሙሉ ውድቅ” በማድረግ አውግዘውታል ብሏል።
 
በተጨማሪም አገራቱ ለሶማሊያ ሉዓላዊነት እና የግዛት አንድነት ያላቸውን ድጋፍ በማጠናከር በተናጠል የሚወሰዱ እርምጃዎች የሶማሊያን መረጋጋት በማናጋት “ትይዩ አካላትን” የሚፈጥር ነው ሲሉ አስጠንቅቀዋል።
 
ይህ ለአንድ ሉዓላዊ አገር ግዛት ዕውቅና መስጠት ከዓለም አቀፍ ሕግ እና ከተበባሩት መንግሥታት ቻርተር አንጻር ያልነበረ ሁኔታን የሚፈጥር ነው ማለታቸውን መግለጫው ጠቅሷል።»
 
• «27 ታህሳስ 2025ኔታኒያሁ ለሶማሊላንድ የተሰጠውን ዕውቅና ይፋ ሲያደርጉ ምን አሉ?»
 
«የሶማሊላንድ ሪፐብሊክ ነጻ እና ሉዓላዊ አገር መሆኗን በይፋ ዕውቅና የሚሰጠውን ውሳኔ ዛሬ [አርብ] ይፋ አድርጌያለሁ።
ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰአር፣ ከሶማሊላንድ ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት ጋር በመሆን የተስማማንበትን የጋራ ውሳኔ ተፈራርመናል።
ይህ ውሳኔ በአብረሃም ስምምነት መሠረት በፕሬዝዳንት ትራምፕ አነሳሽነት የተፈረመ ነው።
 
የሶማሊላንድ ፕሬዝዳንት፣ ዶ/ር አብዲራህማን ሞሐመድ አብደላ እንኳን ደስ አለዎ እያልኩ፤ በአመራራቸው መረጋጋት እና ሰላም ለማምጣት ያላቸውን ቁርጠኝነት አድናቆቴን እገልጻለሁ። ፕሬዝዳንቱ በእስራኤል ይፋዊ ጉብኝት እንዲያደርጉ ግብዣ አቅርቤያለሁ።
 
ፕሬዝዳንቱም ለዚህ ታሪካዊ ውሳኔ ምስጋናቸውን አቅርበው፤ ሽብርተኝነትን በመዋጋት እና ለቀጣናዊ ሰላም ላስገኘሁት ውጤት አድናቆታቸውን ገልጸዋል።
 
ለውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሳአር፣ ለሞሳድ ኃላፊ ዴቪድ ባርኒ እና ለሞሳድ ለዛሬው ውሳኔ ላበረከቱት አስተዋጽኦ ምስጋናዬን አቀርባለሁ። ለሶማሊላንድ ሕዝብም ስኬት፣ ብልጽግና እና ነጻነትን እመኛለሁ።
 
የእስራኤል መንግሥት ከሶማሊላንድ ሪፐብሊክ ጋር በእርሻ፣ በጤና፣ በቴክኖሎጂ እና በምጣኔ ሀብት በኩል ያለውን ግንኙነት በአስቸኳይ ለማስፋት አቅዷል።»
 
"የተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት እስራኤል ለሶማሊላንድ እውቅና መስጠቷን ተከትሎ አስቸኳይ ስብሰባ ጠራ"
"የሶማሊላንድ የዕውቅና ጉዞ እና የእስራኤል ውሳኔ ቀጠናዊ አንድምታዎች"
 
ከ 4 ሰአት በፊት
«ከሶማሊያ በተናጥል ውሳኔ የተገነጠለችው ሶማሊላንድ ከ30 ዓመታት ዲፕሎማሲያዊ ጥረት በኋላ የመጀመሪያውን የአገርነት ዕውቅና ታኅሣሥ 17/2018 ዓ.ም. እስራኤል ሰጥታለች። ሶማሊላንድ እውቅናውን ያገኘችው፣ እስራኤል እና ሶማሊላንድ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የአረብ አገራት ከእስራኤል ጋር ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት እንዲፈጥሩ በነደፉት "የአብርሃም ስምምነት" ማዕቀፍ አንዳቸው ለሌላኛቸው እውቅና ለመስጠት እና ሙሉ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ለመጀመር መስማማታቸውን ተከትሎ ነው። ዕውቅናው የሶማሊላንድን ሕዝብ በደስታ ሲያስፈነድቅ፣ ከአፍሪካ እስከ መካከለኛው ምሥራቅ የዘለቀ ብርቱ ተቃውሞም ቀስቅሷል።
 
የሶማሊላንድ የዕውቅና ጥያቄ አነሳስና ጉዞ የሶማሊላንድ የሉዓላዊ አገርነት የዕውቅና ጥያቄ በአውሮፓውኑ 1960 ከብሪታንያ እንዲሁም ደቡባዊቷ ሶማሊያ ከጣሊያን ቅኝ አገዛዝ ነጻ በወጡ ማግስት የሚጀምር ነው። ሶማሊላንድ ከብሪታንያ ነጻ በወጣች በአጭር ጊዜ ውስጥ በፍቃዷ ከሶማሊያ ጋር ተዋሃዳ ነበር። በእነዚያ አጭር ቀናት ውስጥ እንደ ሉዓላዊ አገር ካወቋት ከ30 በላይ አገራት መካከል አንዷ እስራኤል ነበረች።
 
ሆኖም በአውሮፓውያኑ 1980ዎቹ በግዛቲቷ አብላጫ ቁጥር ያለው የኢሳቅ ጎሳ አማጺ ቡድን የማዕከላዊውን የፕሬዝዳንት ዚያድ ባሬ ወታደራዊ መንግሥት አፈና እና መድልዖ በመቃወም የትጥቅ ትግል ማካሄድ ጀመረ። ሶማሊያም በእርስ በርስ ጦርነት ውስጥ ገባች። ቡድኑ ከሌሎች ታጣቂ ቡድኖች ጋር በመተባበር የዚያድ ባሬን መንግሥት በአውሮፓውያኑ 1991 ከጣለ በኋላ፣ ብዙም ሳይቆይ ነበር ሶማሊላንድ ነጻ አገር መኾኗን ያወጀችው።
 
ከዚያም ሶማሊላንድ በ2001 (እአአ በመጀመሪያው ፕሬዝዳንቷ መሐመድ ኢጋል አመራር በ97 በመቶ ድምጽ የግዛቲቱን ነጻነት የሚያውጀውን ሕገመንግሥት በሕዝበ ውሳኔ አጽድቃለች። በዓለም አቀፍ ሕግ ይፋዊ የነጻ አገርነት ጥያቄዋ የሚጀምረው ያኔ ነው።
ግዛቲቱ በዚሁ ሕገመንግሥቷ የመድበለ ፓርቲ ሥርዓት ዘርግታ በርካታ ምርጫዎችን አካሂዳለች። ሶማሊያ በጦር አበጋዞች እና ከዚያም በእስላማዊ አክራሪ ቡድኖች አማካኝነት የእርስ በርስ ጦርነት ውስጥ በገባችባቸው ዓመታት ሁሉ፣ ሶማሊላንድ ባንጻሩ ባሰፈነችው መረጋጋት፣ በተከታታይ ዲሞክራሲያዊ ምርጫዎቿ እና በሰላማዊ የሥልጣን ሽግግር ለአፍሪካ ቀንድ ምሳሌ ተደርጋ ስትቆጠር ነው የኖረችው።
 
ግዛቲቱ ለዓለም አቀፍ ዕውቅና መስፈርቶች የሆኑት ማዕከላዊ መንግሥት፣ የፀጥታ ኃይል፣ የታወቀ ድንበር እና በግዛቷ ውስጥ የሚኖር 5 ሚሊዮን ያህል ሕዝብ ቢኖራትም፣ እውቅና ለማግኘት ያደረገችው ብርቱ ጥረት ግን ሳይሳካ ዓመታት ነጉደዋል። ለዚህም የሶማሊያ ብርቱ ተቃውሞ፣ የቀጣናዊ እና የዓለም ኃያላን አገራት ተቃራኒ ፍላጎቶች እና የቅኝ ግዛት ድንበሮች ጸንተው እንዲቀጥሉ የሚጠይቁት የአፍሪካ ኅብረት እና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ቻርተሮች በምክንያትነት ይጠቀሳሉ።
 
ሆኖም የሶማሊላንድ መሪዎች የዚያድ ባሬ አገዛዝ በሕዝባችን ላይ ከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ጥሰት አድርሷል የሚለውን ትርክት፣ የአገርነት እውቅናውን አስፈላጊነት ሕዝባቸውን እና ዓለም አቀፉን ማኅበረሰብን ለማሳመን እንዲሁም ከሶማሊያ የተለየ ሥነ ልቦና እና ማንነት ለመገንባት ተጠቅመውበታል።
 
ሶማሊላንድ ለዓመታት ዕውቅና ባታገኝም፣ በተለይ ከኢትዮጵያ፣ ከተባበሩት አረብ ኤምሬቶች፣ ከብሪታኒያ እና ከታይዋን ጋር ጠበቅ ያለ የንግድ፣ የኢንቨስትመንት እና ፀጥታ ግንኙነት መመሥረት ችላለች። ሶማሊያም ግዛቲቱን በሰላማዊ መንገድም ይሁን በኃይል ለመጠቅለልም ሆነ ነጻ መንግሥትነቷን ለመሸርሸር በተለያዩ ጊዜያት ያወጣቻቸውን ሕግጋት ተፈጻሚ ማድረግ አልቻለችም። ሶማሊላንድ እና ሶማሊያ ውዝግቡን ለመፍታት ያደረጓቸው የድርድር ሙከራዎችም ፍሬ አላፈሩም።
 
የሶማሊላንድ ዕውቅና ጉዳይ ይበልጥ መነጋገሪያ የሆነው፣ ግዛቲቱ ለኢትዮጵያ የባሕር በር ለመስጠት እና በምላሹ የኢትዮጵያን እውቅና ለማግኘት በ2024 የመግባቢያ ስምምነት የተፈራረመች ጊዜ ነበር። ሆኖም ሶማሊያ እና የሶማሊያ አጋሮች በፈጠሩት ዲፕሎማሲያዊ ተጽዕኖ ስምምነቱ ተግባራዊ ሳይሆን ቀርቶ፣ በቱርክ አሸማጋይነት ኢትዮጵያ የሶማሊያን የግዛት አንድነት እና ሉዓላዊነት መቀበሏን በይፋ ማረጋገጧ አይዘነጋም።
 
ከዚያ ቀጥሎ የፕሬዝዳንት ትራምፕ አስተዳደር ለሶማሊላንድ ዕውቅና ሊሠጥ ስለማቀዱ በሠፊው ሲዘግብ የቆየ ሲሆን፣ ፕሬዝዳንት ትራምፕም ባለፈው ዓመት ነሐሴ ላይ የሶማሊላንድ ዕውቅና ጉዳይ መፍትሄ እንደሚያገኝ መጠቆማቸው የሚታወስ ነው። የትራምፕ አስተዳደር ሶማሊያ ለዓመታት መረጋጋት ባለመቻሏ ድጋፉን መቀነስ የጀመረ ሲሆን፣ "የአንዲት ሶማሊያ" ፖሊሲውን ግን እስካሁን በይፋ አልቀየረም።»

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

የእኔ እማ ልዕልቴ እንዴት ነሽ?

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።