ልጥፎች

ነፍስ ይማር። አሜን!

ምስል
ነፍስ ይማር። አሜን! „ከምድር ስተገኘህ ወደ መጣህበት መሬት እስከትመለስ ድረስ  … እንጀራህን በፊትህ ትበላለህ፤ አፈር ነህና ወደ ዐፈር ትመለሳለህ“ ዘፍጥረት ፫ ቁጥር ፱ ከሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 19.12.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ።                                                                     ዛሬ ኢትዮጵያ ብሄራዊ የሃዘን ቀን ነው። ይህ ብሄራዊ የሀዘን ቀን የታወጀበት ምክንያት ደግሞ የቀድሞው የኢትዮጵያ ፕሬዚዳንት ግርማ ወ/ጊዮርጊስ በስጋ ከእናት ምድራቸው በመለየታቸው ምክንያት ነው። ሟቹ ፕሬዚዳንት ግርማ ወ/ጊዮርጊስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህድ ቤተክርስትያን ወደ አንድ መምጣቷ ከስደሰታቸው የኢትዮጵውያ የፖለቲካ ሊሂቃን አንዱ ናቸው። እርቁን በንጹህ ህሊናቸው፤ በንዑድ መንፈስ ተቀብለውታል። ብጹዕን ቅዱስ ሊቀና ጳጳሳትን ጨምሮ 4ኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ፓትርያርክን ብጹዑ ወቅዱስ አባታችን አቡነ መርቀሪዮስንም ከቦታው ድርስ ተገኝተው ጠይቀዋል። እንኳን ደህና መጣችሁም በለዋል። የብፁዕ ወቅዱስ አባታችን የአቡነ መርቀሪዮስ ባዕለ ስመትም በብሄራዊ ደረጃ መከበር እንዳለበት ቃለ ምህዳን ሰጥተዋል። በባዕሉ ላይም በአካል ተገኝተዋል።     ብጹዐኑ ሊቀ ቤተክርስትያናት ከስደት ወደ አገራቸው መመለሳቸውን በሚመለከ...

ጥማት።

ምስል
ጥማት!! „እግዚአብሄርም እንዲህ ይላል፤ --- በተወደደ ጊዜ ሰምቼሃለሁ፤ በመድሃኒቴም ቀን ረድቼህ አለሁ፤ እጠብቅሃ አለሁም፤ ምድርንም ታቀና ዘንድ፣ ውድማ የሆኑትንም ርስቶች ታወርስ ዘንድ፤ የተጋዙትንም ውጪ በጨለማም የተቀመጡትን ተገለጡ  ትል ዘንድ ቃል ኪዳን አድርጌ ለህዝቡ  ሰጥቼአለሁ።“ ትንቢተ ኢሳያስ ፵፰ ከቁጥር ፰ እስከ ፱ ከሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 18.12.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ                       የለማ የዴሞክራሲ ጀግንነት እንዲህ ነው በአፍሪካ ፊደል ያሰቆጠረው ጤና ይስጥልኝ የኔዎቹ እንዴት ናችሁ? ደህና ናችሁ ወይ? አጀንዳችን ባለቀው የወያኔ ሃርነት ትግራይ ማንፌስቶ አብሮ ደመር በመቀመጥ ሳይሆን በ27 ዓመት ውስጥ በጠፉን፤ በሾሎኩን ወደፊትም መጥፋቱም ሆነ መሽሎኩን ለመገደብ ወሳኙን ግንዱ ላይ ማተኮር የተገባ ነው ብዬ አስባለሁኝ። ግንዱ ደግሞ አዲሱ ትውልድ ነው።  ከ7 እስከ 18 ዓመት ያለው። ያን ነው አንጸን ነፍስ ባለው የዜግነት ትሩፋት አንጸን መገንባት ያለብን። ያ ነው የዛሬው የቤት ሥራችን ሊሆን የሚገባው እንደ ሥርጉተ ሥላሴ።  እንደ ሥርጉተ ሥላሴ እኛም ማስቲካ የሆን ይመስለኛል።  ያለቀ አሮጌ ቆርቆሮ ለምን አፈሰስክ፤ ስለምን የወዬበው ግድግዳህ ወረዛ፤ ስለምንስ መቆም የተሰነው ምርጊትህ ፍርክርክ ብሎ ህልምህ እንዲህ እና እንዲያ ሆነ እያለን የምናባክነው ጊዜ የተገባ አይመስለኝም። ይልቁኑ በቆሰለው፤ በተጎዳው፤ በደማው የማግስት ድልድይ ላይ እያንዳንዳችን ልናደርግ ስለሚገባው ብናተኮር እና ብንሥራ መልካም ...

ክርስትና እና እስልምና ዓይናችሁን አደራ ጠብቁ!

ምስል
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ሃይማኖት +  የኢትዮጵያ እስልምና ሃይማኖት  ዓይናቸውን የመጠበቅ አምላካዊ  ግዴታ አለባቸው። ክርስትና ማለት  ሆነ እስልምና መታመን ነው። „የሰው ልብ መንገድን ያዘጋጃል፤ እግዚአብሄር ግን አካሄዱን ያቃናለታል“ መጽሐፈ ምሳሌ ፲፮ ቁጥር ፱ ከሥርጉተ©ሥላሴ Sergute ©Selassie 17.12.2081 ከጭምቷ ሲወዘርላንድ ምሩቁ ይስህቅ! ·        ጠብታ ጤና ይስጥልኝ ውዶቼ የማካብራችሁ እና የምናፍቃችሁ የአገሬ ልጆች እንዴት አላችሁልኝ። አውሮፓ ስሜን አሜሪካ ያላችሁ እንዴት ይዟችኋዋል ብርዱ? ዘንድሮ በጋውም እረጅም ነበር፤ ክረምቱም ቀለል ያለ ነው እዚህ እንደ ሲዊዝ ከሆነ። ለነገሩ ገዳማዊቷ አገር ሲዊዘርላንድ በጋውም ሆነ ክረምቱ በልክ ነው፤ እጁን ታጥቦ የፈጠራት ብጽዕት ናት እና። በረድ የሚጥለው ተራራ ላይ ነው።  ሙቀትም በበጋ ምን አልባት ቢበዛ እስከ 5 ቀን ነው ከፍ ያለ የሙቀት ደረጃ የአዬር ንብረት ያለው እንጂ ቀሪው ለጤና ተመጣጥኖ እንደሚሠራ ምቹ ምጥን ነው። የገዳማዊት አገር ነገር እንዲህ ነው እንደ ህዝቧ ሁሉም በደንበር ነው፤ በልክ  …. የታደለች! ·        ዓይን። ብሩካን! ዓይን ፖስተኛ ነው። ዓይንም ብርሃን ነው። ዓይንም የምርምር ተቋም ነው ለአካላት ሁሉ። ዓይን በጥበብ ውስጥ የተቀመረ ተፈጥሮ ነው ያለው። ይህን ስል ግን ልበ ብርሃን የሆኑ ሉላዊ ዜጎችም እንዳሉን ነው እማስበው። የእነሱ አፈጣጠር ደግሞ ከማስተዋል ጋር ብልህነቱምን አርቅቆ ነው የፈጠራቸው። ል...