ልጥፎች

የኢትዮጵያን ህዝብ ከልብ አመሰግናለሁ! የሄቨን እናት አሁን ያለችበት ሁኔታ! Eyoha Media |Ethiopia ...

ምስል

የኢትዮጵያ እናቶች ይፍረዱኝ! እጅግ ዘግ’ናኝ እና አ’ሰ’ቃ’ቂ እውነት! ‘ፍትህ’ ፍለጋ የተደረገ ከባድ ተጋድሎ! ...

ምስል

ምነው ህጋችን ላላ ልጄን አልቀበርኳትም ብዙ የምናገረው አለኝ የሄቨን አባት | Yegna tv | EBS Mezna...

ምስል

የቀድሞዋ የኢሕአፓ ዋና ጸሐፊ ደስታ ጥላሁን አነጋጋሪ ሃሳብ ሰነዘሩ! | አርትስ ወቅታዊ @ArtsTvWorld

ምስል

#እኛን ማጣታችን #ማለቃችነን ያመላክታል።

ምስል
  #እኛን ማጣታችን #ማለቃችነን ያመላክታል።   "አቤቱ እንደበደላችን ሳይሆን  እንደ ቸርነትህ ይቅር በለን። አሜን።"     እንዴት አደርን? መንጋት አይቀርም ነግቷል። አሰቃቂነት፤ ፀያፍነትም ስንቃችን መሆኑ እንደምን እያደረገን ይሆን? በዚህ 6 ዓመት በይፋዊ፤ በአደባባይ የሚታዩ አረማዊነት ከዬትኛው ዘመን፦ ከዬትኛው አገር ሥርዓተ - መንግሥት ጋር አኽቲ እንደሚያደርገን አላውቀውም። በዘመነ ህወሃት፤ እዛ በቀደሙት ሥርዓቶችም መሰል ጭካኔወች በሃፍረት ካሊም ተጎናጽፈው ተከውነው ሊሆኑ ይችላሉ። የዚህ ዘመን የሚገርመው አስደንጋጭ እና ሰቅጣጭ ሁነቶች #የኦክስጅን ያህል ለሰውነታችን ተዋህጂ መሆኑ ነው።   መደበኛ ዜና ዘጋቢወች ወይንም ተንታኞች " #ሰበርን " መለያቸው #ሎጓቸው ሲያደርጉት ስንት የሰውነት ኦርጋን፤ ስንት ነርብ እንደሚበጣጥስ አይረዱት ሆነው ነው ለማለት አልችልም። ምክንያቱም በሰለጠነ ዘመን ተቀምጦ፤ በሰለጠነ አገር እዬኖሩ #ስጋትን ሎጎ ማድረግ እርስ በእርሱ የሚቃረን ስለመሆኑ ያጡታል ብዬ ስለማላስብ። #የደስታ #ሰበር እንኳን አደጋ አለው እንኳንስ የሃዘን።    ስንቃቸው ይህ የሆኑ ሰብዕናወች ስንቶችን ለሥነ ልቦና ህመም፤ ለልብ ምት መጨመር ወይንም ማቆልቆል፤ ወይንም ለደም ግፊት መጨመር እንደዳረጉ ቢያውቁት። ሰው ሆኖ ለሰው ልጅ ጤንነት አለማሰብ ጨካኝነትም ነው ለእኔ። እኔ በሕይወቴ የመልካም ነገር ሰርፕራይዝ የሚባል ነገር አልወድም፦ እንኳንስ የክፋ ነገር ሰርፕራይዝ። ዕንባዬ ፈቃዴን ሳይጠይቅ ነው የሚወርደው።    ውህድ እዬሆነ የመጣው የስጋት ነጋሪት፤ ጭካኔውንንም እኛኑ እያደረገ አቅርቦልናል። መገለጫችን፤ መለያችን ጭካኔ??? ተከድነው፤ ተንተክትከው፤ በ...

ፍረዱት።

ምስል
 

ብዙ የማትታወቀው የክርስቲያኖች ሀገር ገባሁ

ምስል

MK TV || ዕለታዊ መረጃዎች || በደብረ ታቦር የቡሔ እና የሰማዕቱ መርቆሬዎስን በዓላት በድምቀት ለማክበር ቅ...

ምስል

ለኢትዮጵውያን የልቅ እና በልዕልና የከፍታ ደረጃ ክብርት ሳህለወርቅ ዘውዴ ናቸው - ለእኔ። ክብርቷ ለክብርት ኢትዮጵያ #ልኳ ናቸው። #ተመድን ለመምራትም ልክ ትክክል ናቸው። የአፍሪካ አንድነትን ለመምራትም። ኢትዮጵያ አገር ብቻ አይደለችም ለእኔ - #ትንፋሽም።

ምስል
  "የቤትህ ቅናት በላኝ።"    ለኢትዮጵውያን የልቅ እና በልዕልና የከፍታ ደረጃ ክብርት ሳህለወርቅ ዘውዴ ናቸው - ለእኔ።   ክብርቷ ለክብርት ኢትዮጵያ #ልኳ ናቸው። #ተመድን ለመምራትም ልክ ትክክል ናቸው። የአፍሪካ አንድነትን ለመምራትም።   ኢትዮጵያ አገር ብቻ አይደለችም ለእኔ - #ትንፋሽም ።       እንዴት አንዴት አደራችሁ? ደህና ናችሁ ወይ? ዓለማችን ብቁ ሴቶችን፤ ሞጋች ሴቶችን በፖለቲካው ዘርፍ፤ በዲፕሎማሲው ዘርፍ፤ በተፈጥሮ እና ማህበራዊው ሳይንስ ዘርፍ አፍርታለች። ኢትዮጵያም ድንቅ የሆኑ ሊቀ - ትጉኃን አንስቶችን አፍርታለች። ቀደም ባለው ዘመን በዓለም ዓቀፍ ደረጃ የሴቶች እኩልነት በማይታሰብበት ዘመን አገርን የመሩ የተከበሩ ብቻ ሳይሆን የተቀደሱም ንግሥታት፤ እቴጌወች ነበሯት። ኢትዮጵያን ለመድፈር ሲታሰብ ጀግኖች እናቶቻችን ጦር መርተው ለድል መንበር አብቅተውናል። መኖርን በማስዋብ በተለያዩ የፈጠራ ሥራወች እና ስልጣኔወች፤ ከተሞችን በመቆርቆር እና በማደራጀትም ድንቆች - #ድንቅነትን #አብርተዋል ።   ዛሬም ቢሆን እራሳቸውን ከደን አድርገው፤ "ሙያ በልብን" ሰንቀው #የልብ #አድረስ ተግባራትን የሚከውኑ አንቱ ሊባሉ የሚገባቸው እህቶች በዬዘርፋ አሉን። ከእነኝህ ሁሉ #ቁጥር #አንድ በብቃት፤ በተመክሮ፤ በትዕግሥት፤ በመቻል አቅም፤ ዘለግ ባለ ሁለገብ ተመክሮ በዕውቀት ባንታደል እንጂ ክብርት ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴን የሚልቅ አይደለም #ሴት #ተባዕት ኢትዮጵያዊ/ #ኢትዮጵያዊት አለን ብዬ እኔ በግሌ አላምንም። ከዘባጣ፤ ጠናና ሥርዓት ጋር በመሥራታቸው ወርቃቸው ጊዜ አጣ። ውስጣቸው በተመክሮ ዕንቁ የከበረ ነው።   የመጨረሻው #የብቃት #ደረጃ ...

የአትሌት ሲሳይ ለማ #አብነትነት ትውልዱ፤ የፖለቲካ ድርጅት መሪወች ምን ይማሩበታል?

ምስል
  የአትሌት ሲሳይ ለማ #አብነትነት ትውልዱ፤ የፖለቲካ ድርጅት መሪወች ምን ይማሩበታል?   "የቤትህ ቅናት በላኝ።"     ግን እንዴት ሰነበታችሁልኝ ማህበረ ቅንነት? ደህና ናችሁን? ሰሞኑን ተጠፋፋን። የዘንድሮን ኦሎንፒክ ብዙም አልተከታተልኩትም። ምክንያቴ ውዝግቡ አውሎማ ስለነበር ብቻ ሳይሆን መክፈቻው ላይ የነበረው ሁነትም ብዙ በትጋት እንድከታተለው አልገፋፋኝም። የሆነ ሆኖ የሴቶቼ 10 ሺን፤ የወንዶች ማራቶን እና የሴቶች ማራቶን ተከታትያለሁኝ።   በውድድር ማሸነፍ እና መሸነፍ እኩል ዕውቅና ሊሰጣቸው ይገባል ብዬ አምናለሁ። ድካሙ #እኩል ስለሆነ። በልፋት፤ በጥረት የሚገኝ መሸነፍም ቢመጣ ከባለ መዳሊያው ጋር እኩል ዕውቅና ሊሰጠው ይገባል ባይ ነኝ። አሰልጣኞችም ቲሙም እንደሚያስገኙት ውጤት ሊመዘኑ ይገባል ባይም ነኝ።    አራቱ ኮከብ አትሌቶች መዳሊያ ያስገኙት በዛ ውዝግብ ላይ ሆነው ነው። ይገርማል። እንደምን ተረጋግተው ለድል እንደበቁ ሚራክል ነው - ለእኔ። የውስጥ ሰላም ከሌለ የጎረስከውን እህል እንኳን በቅጡ አጣጥሞ መዋጥ ያቅታል። በአፍህ ውስጥ ከርታታ ስደተኛ ይሆናል። ይተናነቅኃልም። አትሌቶች ተሰናድተው ሄደው ግን የውድድር ዕድል ተነፍጓቸው ሲመለሱ፤ የተፈቀደላቸውም አሰልጣኛቸውም ግዳጃቸውን ሳያጠናቅቁ #ተመላሽ ሲሆን፤ በቀጥታም ይሁን በተጠባባቂነት የተመረጡትም ተመላሽ ሲሆኑ በራሱ በቀሪ ተወዳዳሪወች ላይ ሊያመጣ የሚችለው #ተጽዕኖ ከባድ ነው። ተስፋቸው ይኮማተራል።    አትሌቲክ ብቻ ሳይሆን ስፖርት የአንድ አገር #የውጭ #ጉዳይ ሚር ማለት ነው። ኢኮኖሚካሊም የሚክስ፤ ለተሳታፊወች የመኖር ዕድላቸውን ቧ አድርጎ የሚከፍት፦ ታሪክን በዓለም አደባባይ የሚያበጅ ልዩ አርት ነ...