ለኢትዮጵውያን የልቅ እና በልዕልና የከፍታ ደረጃ ክብርት ሳህለወርቅ ዘውዴ ናቸው - ለእኔ። ክብርቷ ለክብርት ኢትዮጵያ #ልኳ ናቸው። #ተመድን ለመምራትም ልክ ትክክል ናቸው። የአፍሪካ አንድነትን ለመምራትም። ኢትዮጵያ አገር ብቻ አይደለችም ለእኔ - #ትንፋሽም።

 

"የቤትህ ቅናት በላኝ።" 
 
ለኢትዮጵውያን የልቅ እና በልዕልና የከፍታ ደረጃ ክብርት ሳህለወርቅ ዘውዴ ናቸው - ለእኔ።
 
ክብርቷ ለክብርት ኢትዮጵያ #ልኳ ናቸው። #ተመድን ለመምራትም ልክ ትክክል ናቸው። የአፍሪካ አንድነትን ለመምራትም።
 
ኢትዮጵያ አገር ብቻ አይደለችም ለእኔ - #ትንፋሽም
 
 
 May be an image of 1 personMay be an image of 7 people and text
እንዴት አንዴት አደራችሁ? ደህና ናችሁ ወይ? ዓለማችን ብቁ ሴቶችን፤ ሞጋች ሴቶችን በፖለቲካው ዘርፍ፤ በዲፕሎማሲው ዘርፍ፤ በተፈጥሮ እና ማህበራዊው ሳይንስ ዘርፍ አፍርታለች። ኢትዮጵያም ድንቅ የሆኑ ሊቀ - ትጉኃን አንስቶችን አፍርታለች። ቀደም ባለው ዘመን በዓለም ዓቀፍ ደረጃ የሴቶች እኩልነት በማይታሰብበት ዘመን አገርን የመሩ የተከበሩ ብቻ ሳይሆን የተቀደሱም ንግሥታት፤ እቴጌወች ነበሯት። ኢትዮጵያን ለመድፈር ሲታሰብ ጀግኖች እናቶቻችን ጦር መርተው ለድል መንበር አብቅተውናል። መኖርን በማስዋብ በተለያዩ የፈጠራ ሥራወች እና ስልጣኔወች፤ ከተሞችን በመቆርቆር እና በማደራጀትም ድንቆች - #ድንቅነትን #አብርተዋል
 
ዛሬም ቢሆን እራሳቸውን ከደን አድርገው፤ "ሙያ በልብን" ሰንቀው #የልብ #አድረስ ተግባራትን የሚከውኑ አንቱ ሊባሉ የሚገባቸው እህቶች በዬዘርፋ አሉን። ከእነኝህ ሁሉ #ቁጥር #አንድ በብቃት፤ በተመክሮ፤ በትዕግሥት፤ በመቻል አቅም፤ ዘለግ ባለ ሁለገብ ተመክሮ በዕውቀት ባንታደል እንጂ ክብርት ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴን የሚልቅ አይደለም #ሴት #ተባዕት ኢትዮጵያዊ/ #ኢትዮጵያዊት አለን ብዬ እኔ በግሌ አላምንም። ከዘባጣ፤ ጠናና ሥርዓት ጋር በመሥራታቸው ወርቃቸው ጊዜ አጣ። ውስጣቸው በተመክሮ ዕንቁ የከበረ ነው።
 
የመጨረሻው #የብቃት #ደረጃ ለኢትዮጵውያን ክብርት ሳህለወርቅ ዘውዴ ናቸው። በዬትኛው ሴሪሞኒ እንደሆን አላስታውሰውም ኩታቸውን እጥፍ አድርገው ከትክሻቸው ላይ ጣል አድርገው ሳያቸው አንጀቴ ነው የተንሰፈሰፈላቸው። ውስጣቸው ኢትዮጵያ ናት። ክብርቷ ለክብርት ኢትዮጵያም ልክ ናቸው። እርግጥ ነው በሰባዕዊነት ላይ ያለው ጫና ሲበዛ፦ ሲከፋኝ አክብሬ ብሞግታቸውም ግን ኢትዮጵያን ኢትዮጵያን የሚለው #ተናፋቂ ጠረናቸው ሁልጊዜም ልቤን ይገዛዋል። ኢትዮጵያ አገር ብቻ አይደለችም ለእኔ። #ትንፋሼም እንጂ። 
 
እኔ ምስላቸውን መጥኜ ካስቀምጥኳቸው ለእኛ ትውልድ ግሎባል ተጽዕኖ ፈጣሪወች ውስጥም ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ #አቻ ናቸው። ከአውሮፓ አንከር ከቀድሟዋ የጀርመን ካንስለር ደጊቱ ክብርት ዶር አንጌላ ሜርክል፦ ከቀድሞ የአሜሪካ እጩ ፕሬዚዳንት ተወዳዳሪ እና የውጭ ጉዳይ ሚር ክብርት ወሮ ሄነሪ ክሊንተን፤ ከአሁኗ የአውሮፓ ህብረት መሪ ክብርት ዶር ኡርዙላ፥ ወዘተ የሚመጥን ሙሉ አቅም አላቸው።
 
 የማያሳፍር አንገትም የማያስደፋኆ። ክብርቷ በእርግጠኝነት ተመድን ለመምራት ሙሉ ብቃት አላቸው። ኢትዮጵያን ለመምራት ሙሉዑ ብቃት አላቸው። የአፍሪካ አንድነት ድርጅትን ለመምራት ሙሉ ብቃት አላቸው። ግን ዕድሉን አላገኙም። ተኮርኩመው እንዲቀመጡ ነው የተደረጉት። ይህ ደግሞ ለእኔ ሸፍጥ ነው። ጊዜ ማቃጠልም ነው።
በተጨማሪም ክብራቸውን፤ ደረጃቸውን ከማይመጥን ሥርዓት ጋር አብረው በመሥራታቸው እንሆ አደባባይ ላይ እንዲህ ተቃለው ታዩ። 
 
ኢትዮጵያም በስላቅ ተደበደበች። "2000000 ብር ለእኔ ስድብ ነው" ተባሉ። አበስኩ ገበርኩ። 05 ሳንቲም ሳያገኙ ሙሉ ዕድሜያቸውን ስለአገራቸው የሚባትሉ እኔን መሰል ምንዱባወች እኮ አለን። እንደምን ኦህዴድ ለሥልጣን እንደበቃም ፈጣሪ ያውቀዋል። በማን አቅም? እንዴትስ? አዬር ላይ በሚከንፈው መረጃ አልነበረም ለዚህ የተበቃው።
 
የሆነ ሆኖ በአትሌቶች የምስጋና መሰናዶ ላይ አሰልጣኝ ገመዶ ደዶፎ የፈፀሙት ድፍረት የሥርዓቱን፦ ሥርዓት አልበኝነት ቁልጭ አድርጎ ያሳያል። ሸቅጥ አምላኪ ሰብዕና ለብሄራዊነት ኢትዮጵያዊነት ምን እና ምን እንደሆነ ልኩን አሳይቶናል። ኢትዮጵያ ከሸቀጥ በላይ ዊዝደም ናት። ኢትዮጵያ ፍልስፍናም ሳይንስም ናት። 
 
ኢትዮጵያ ህግም ዩንቨርስም ናት። በህውኃት ማኒፌስቶ ወተት ላደገ ይህ ምንም ሊሆን ይችላል። አይደለም ለእኛ ለዓለም ኢትዮጵያ የግሎባሉ መንፈስ ቁምነገር ናት። የህዝቧ ጭምትነት እኮ በቂ ነው። እሚታመሰው ፖለቲካው እንጂ የኢትዮጵያ ጉልህ መንፈስ አይደለም። ኢትዮጵያ በዬትኛው የፖለቲካ ድርጅት፤ የፖለቲካ ሰብዕ ልትለካ፤ ልትመዘን አይገባትም። ፈጽሞ። እነሱ #በክህደት የተደወሩ ናቸው። 
 
የሆነ ሆኖ ፕሬዚዳንት ወሮ ሳህለወርቅ ዘውዴ በብዙ ሁኔታ ከዚህ ጨካኝ ሥርዓት ጋር፤ አይዟችሁን ካሰደደ ሥርዓት ጋር፤ አጽናኝነትን #ደመኛው ካደረገ ሥርዓት ጋር አብረው መሥራታቸው ውስጣችን በመከፋቱ አክብረን ብንሞግታቸውም ክብርት ሳህለወርቅ ዘውዴ ኢትዮጵያ ደግማ የማታገኛቸው ዕንቁዬ ናቸው ለእኔ። የተፈለጉትም ላቂያ ስለሆኑ፤ ላቂያነታቸውን አረም ለማልበስ እንደሆነ ነው እኔ እማስበው። የአሳቸው ጠሚር አብይ አህመድ ዋና ተልዕኮ ሲነሪቲ ያላቸውን መሪወች በአንድም በሌላ ማራቆት ነውና።
 
ይህ ፕሮጀክታቸው የተሳካለትም ነው። ብዙወች ከዓይን ያውጣህ ዓይኔ አይይህ ተብለዋል። እሳቸውም ተጠቅመው እንደ አሮዬ አካፋ እና ዶማ የትም ወርውረዋቸዋል። ሌሎችም ፖለቲከኞች ዕድሉን ሲያገኙ ግብግባቸው ከአቅም ጋር ስለመሆኑ እናውቃለን። ብቅ ያለን መንቀል ወይም ሙጃ ማልበስ የኢትዮጵያ ፖለቲከኞች ራዕያቸው ነው። በዶር አብይ ብቻ አይደለም እንደማለት።
 
ኢትዮጵያ በእኛ ትውልድ ክብርቷን ያህል ልቅና በልዕልና ያላት ዲስፕሊንድ ሙሉዑ አንስት ከሳቸው ሌላ የላትም። ይህ ሃቅ ነው። ይህ ዕውነት ነው። ነገር ግን በአሳቻው ሥርዓት ተጠልፈው የሳቸው ክብር አይደለም የኢትዮጵያ ክብር እንዲጠቀጠቅ ሆኗል።
ክብርቷን ያህል ብቃት ያላት ሴት ኢትዮጵያ ለማግኘት ቢያንስ 100 ዓመት ኢትዮጵያ መጠበቅ አለባት። 
 
መሪነት ለሳቸው አቅቷቸው አይደለም። ማስተዳደር ለሳቸው ጋዳ ሆኖባቸው አይደለም። እናትነቱን አጥተውት አይደለም። ያሉበት ቦታ እና ኦነጋዊው አመራር የኢትዮጵያ የልቅና የአመራር ዘይቤ ሊገናኝ፦ ሊዋህዳቸው ስላልቻለ ብቻ ነው። አብዛኞቹ ፕሮፊሽናል ዲፕሎማቶች ቋንቋቸውም፤ ሥነ - ምግባራቸውም ለእኛ በቀጥታ ሊገባን አይችልም። በበዛ አደብ፤ በበዛ ቁጥብነት፦ በበዛ ትዕግሥት መኖራቸውን የኳሉት ስለሆነ።
 
ክብርት ወሮ ሳህለወርቅ ዘውዴ #በተረገመችው ዕለት ከዛ ዓለምዓቀፍ የዕውቅና ማማ አውርዶ ተሸሽገው፤ ተሸጉጠው እንዲኖሩ ከተገደዱበት ዕለት ጀምሮ ዓለማችን ከክብርቷ ልታገኝ የሚገባትን በሳል ተመክሮ፤ #እናታዊ ፀጋ አጥታለች። የእኛም ግሎባል የዕውቅና ደረጃችን ተነጥቀናል። የእኛን አንደበት በዓለምዓቀፍ ማድረክ መዘረፍ ብዙ እንድናጣ አድርጎናል። 
 
በማይሰራ ቦታ፤ እንግዳ በመቀበል እና በመሸኘት የሴሪሞኒ ቦታ ብቻ ማስቀመጥ ለእኔ ሳይለንት ዲስክርምኔሽን ነው። ዱላም ነው። የሆነ ሆኖ አሁን #የሚገፋበት ጊዜ ዋዜማ ስለመሆኑ ምስክሩ የአሰልጣኝ ገመዶ ደደፎ ምስክር ነው። ማን ግፋ በለው እንዳላቸው የሚውቁት አሰልጣኙ ናቸው። መከፋትን ለመግለጽ ጊዜን፤ ሁኔታን፤ ቦታን ይጠይቅ ነበር። 
 
እኔ እንደማስበው ግን ምን ያህል የክብርት ፕሬዚዳንቷ ተቀባይነት እንደወደቀ #ቴስትም ነው። ግብረ መልሱን መዝኖ ስንብቱን ማጧጧፍ። አዋን አድርጎት ነው። ምነው ባላቀቃቸው። በዲፕሎማሲያዊ ሥርዓት ተኮትኩተው አድገው በስክነታቸው ቀንዲል የሆኑ ሊቀ - ሊቃውንት ከተኮረኮሙበት ማዕቀብ ቢገላገሉ እኛም እፎይ ባልን ነበር። በሕይወት እንዲኖሩ ከተፈቀደላቸው መልካም ዕድልም ነው። ሙግታችንም ይኽው ነው።
 
 እንጂ ለእኔ በግሌ ክብርቷ ክብርም፦ ዘውድ እንደሆኑ ነው እማምነው። ለዚህም ነው ንግግራቸውን ጠብቄ እማደምጠው።ከውስጤ ስላሉ። እምሞግተውም ከውስጤ ሰው ሲኖርም ነው። እንደ እኔም ሚዛናቸውን የጠበቁ ሚሊዮኖች ይኖራሉ ብዬ አስባለሁ። በተለይ ሳይለንት ማጆሪቲው ላይ። 
 
እኔም ሆንኩ ሌሎቹ ከሥርዓቱ ጋር መሥራታቸው ብቻውን ለኢትዮጵያ እንዳገለግሉ ሳይቆጥሩት፦ ይልቁንም በሚመጥናቸው ዓለምዓቀፍ መድረካቸው #ፒላርነታቸው ቢቀጥል ዬኢትዮጵያ አንደበቷ ነፃነቱ ይጠበቃል። 
 
እርግጠኛ ነኝ አንድ አገር ሰላይ መሪ ካላት በዙሪያው የሚሠሩ ቁልፍ ሰወች ሁሉ ሁለመናቸው በደህንነት ሥር እንደሚወድቅ ይታወቃል። የፍርኃት ጫናም እንዲኖር ይደረጋል። ከዚህ መሰናክል ክብርቷ ወጥተዋል ብዬ አላምንም። መኖሪያቸው በሙሉ በስለላ መረብ የታጠረ ይሆናል የሚል ዕምነት አለኝ። ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ #አሳቻ መሪ ናቸውና። 
 
በምንም መሥፈርት፤ ማንም ፖለቲከኛ ወይንም ተጽዕኖ ፈጣሪ ቢሆን ከክብርት ሳህለወርቅ ዘውዴ ጋር #ሊመጣጠን አይችልም። ፈጽሞ። ከብቃት በላይ #ላቂያ ናቸው እና። ዝምታቸው፤ ጭምትነታቸው በራሱ የዊዝደም አቅማቸውን ጥልቀት ያሳያል። የመርህ፤ የፋክት፤ የተመክሮ #መጸሐፍ ናቸው። አናባቢ ናቸው። 
 
ክብርት ወሮ ሳህለወርቅ ዘውዴ በዬት ባገኜነሽ የሚባሉ እንጂ እንዲህ ከፍ እና ዝቅ ሊደረጉ አይገባም። "ባለቤቱን ካልናቁ አጥሩን አይነቀንቁ" "ጌታዋን የተማመነች በግ ላቷን ውጪ ታሳድራለች።"
 
 
ትልቅ ስህተት ፈጽመናል። ያሳሳተን "ኢትዮጵያ ሱሴ ናት" መፈክር ነበር። #ፈሰናል። ተቀደናል። ተቦዳድሰናል። ዕድላችን ለማህበረ ኦነግ አሳልፈን መስጠታችን ብሄራዊነት መቃብር ውስጥ መኖሩን እንዲያደርግ ፈርደንበታል። ከማህበረ ኦነግ ኢትዮጵያዊነትን ማለም ዕብደት ነበር። 
 
አሁንም የአሜሪካን መንግሥት፤ አውሮፓ ህብረትን ጨምሮ የተርገበገበ ውሳኔ ላይ እንዳይደርሱ በአጽህኖት አሳስባለሁ። ፀረ ኢትዮጵያ ኃይሎች በአንድም በሌላ አሰፍስፈው እንደሚገኙ አስተውላለሁ። ለዳግም ቅርጫ። አደብ ያስፈልጋል። ጥሞና ያስፈልጋል። ስክነት ያስፈልጋል።
 
ኢትዮጵያ ከአንድ ዩቲውበር፤ ከአንድ የሚዲያ ሰብዕ፤ ከአንድ ጠቅላይ ሚኒስተር፤ ከተወሰነ ስብስብ፤ ከአንድ አጋጣሚ ከሰጠው ተጽዕኖ ፈጣሪ በላይ ናት። ብርቱ ጥንቃቄ ይጠይቃል በኢትዮጵያ ህልውና ቀጣይነት ላይ አስተዋፆ የሚያደርጉ የውጭ ኃይሎች። ከብሄራዊ ስሜት ጋር አንቧጓሮ የሚገጥሙ ሰብዕናወች ዕድሉን አግኝተው ያለንን አቅም ሁሉ ዬበረዶ ግግር አድርገውታል። 
 
የኢትዮጵያ ፕሬዚዳንት ክብርት ወ/ሮ ሳህለወርቅ ዘውዴ አይደለም ለኢትዮጵያ ለዓለምም ልዩ አቅም ናቸው። በአገራቸው በአደባባይ የደረሰባቸው ዱላ ግን ታይቷል። ምንም እንኳን ለማህበረ ኦነግ ፕሮቶኮል፤ ሥርዓት ባይታዋሩ ቢሆንም።
 
በቦታ ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ ቢኖሩ ይህ ድፍረት አይሞከርም ነበር። ወይንም የወያኔ ሥርዓት ቢሆን ጭራሽ አይታሰብም ነበር። የልብ ልብ የሰጠው፤ ጣሪያ የነካው እብጠት የተከሰተው ፕሬዚዳንቷን እንደ ባዕድ በመቁጠር ብቻ ሳይሆን በፆታቸውም ይመስለኛል። ነው አላልኩም ይመስለኛል። ዬ2000000 ሽልማት ቼክ ከመለሱ በኋላ የአሰልጣኙ አረማመዳቸው ጉሮወሸባዬ እራሱ ምስክር ነበር። ዘመኑ የእኔ ነው። ማንም፦ ምንም አያመጣም ዓይነት ነው።
 
አሁንም አበክሬ እማስገነዝበው ቀጣዩ የትግል መስመር ልዩ ጥንቃቄ የሚሻ ስለመሆኑ ነው። የተስፋችን መቀመጫ ከመታበይ፤ ከሥርዓት ጥሰት፤ ከስድብ፤ ህግ ከመተላለፍ፤ ከመታበይ፦ከመንጠራራት ጋር ንክኪ ያለው ሰብዕና ለነገም ጠንቅ ነውና በቅጡ ሊታሰብበት ይገባል። የኢትዮጵያ ሕዝብ በተፈጥሮው ደግ መሆኑ ብቻ ሳይሆን ሥርዓት አክባሪ እና ለህግ ተገዢ ነው። እሱን የሚመጥን መሪ ለማፍለቅ አደብ፤ ጥሞና፤ ድዋ፤ ፆም ፀሎት ያስፈልጋል።
 
 https://www.youtube.com/watch?v=giNKkgRZj20
“ክቡር ፕሬዚዳንታችን እርሶን ካላስከፋዎት …ሽልማቴን መመለስ እፈልጋለሁ” - አሰልጣኝ ገመዶ ደደፎ
 
 
እግዚአብሄር ይስጥልኝ።
 
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
15/08/024
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።