ነፃነቱን #ለነፃነት ቅድሚያ በመስጠት የነፃነት ህይወትን የኖረበት #የመሰጠት አባወራ - የጥበብወርቅ #ብራ።
ነፃነቱን #ለነፃነት ቅድሚያ በመስጠት የነፃነት ህይወትን የኖረበት #የመሰጠት አባወራ - የጥበብወርቅ #ብራ ። "አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ።" አሜን። አርቲስት፤ ሞደሬተር የሳቅ #አጤ አቶ ነፃነት ወርቅነህ ጥበብን አክብሮ - ተቀብሎ፤ በህይወቱም - ኑሮበት በሥጋ የተለዬ የዘመናችን የሳቅ #ጉልላት ነበር። እኔ ወንድሜ ሃይልዬ ቁርጥ እሱን ይመስልም ስለነበር በበዛ #ስስት የምመለከተው አርቲስት ነበር። ሃይልዬም ዘመኑ ባይፈቅድለትም ኮመዲ ዓይነት ነበር። ሃይልዬን ስናጣው የ፳ወቹ መግቢያ ላይ ስለነበር አርቲስት ነፃነትን ሳይ ዕድሜ ኑሮህ ቢሆን እሱን ትሆንም ነበር እያልኩ ከራሴ ጋር እወያይ ነበር። በጥበብ ቤተኞች ዘንድ " #ድንገቴ " የአዘቦት ጉዳይ ሆነ። ዜና ከመደበኛ ወጥቶ በቀን ሦስት አራት ጊዜ "ሰበር፤ የሰበር ሰበር፤ ልዩ ሰበር" የሚሉ ድምፆች ከአብይዝም ጋር አብረው የመጡ ሲቆዩ ወደ ባህል ሊሻገሩ የሚችሉም ይመስላሉ፤ አያያዛቸው። "ሰበርን" ማዘውተር አዘቦትኛ የመሆን ያህል ሆኗል። "ሰበር" ስለምን ተወዳጅ ሆነ? መደንገጥም ስላለበት ቀስ በቀስ እየተዋህደ የመጣም ይመስላል። የሆነ ሆኖ ድንገቴ ሁነቶችን እኔ #ደራሽ በሚል እተካዋለሁኝ። አማርኛ ቋንቋ ዲታ ስለሆነ ለህዝባችን ሥነ - ልቦናዊ ጸጥታ፤ የማረጋጋት ዓውዶችን ቢፈጥሩ ሚዲያወች መሻቴ ነው። ህዝባችን ስንቱን ይቻል? ቢያንስ በእጃችን በሚገኜው እራሳችን አርቀን ወይንም ገርተን ጭምቱን ህዝባችን ለድንጋጤ በማያጋልጡ ሁነቶች ብንተጋ ሰውኛ ይሆናል። ጥረታችን። እንተዛዘን እንደማለት። እያንዳንዱ ልጅ ሲወለድ #መክሊት ይዞ ይወለዳል፤ እያንዳንዱ ልጅ ሲወለድ #መልዕክት ይዞ ይወለዳል፤...