ብቃት እንደ ወንዝ አሽዋ ከሜዳ አይታፈስ። ከሥልጠናም መሰጠትን ይጠይቃል።
ብቃት እንደ ወንዝ አሽዋ ከሜዳ አይታፈስ። ከሥልጠናም መሰጠትን ይጠይቃል።
"የቤትህ ቅናት በላኝ።"


ዶር ለገሰ ቱሉ በተማሩበት ሙያ ለደረጃቸው በብቃታቸው ልክ ቢመደቡ ጥሩ ነው። የግድ እንደ ጋዜጠኛ፤ እንደ ሞጋች ማድመጥ ያለብኝን ጉዳይ #ችዬ ማድመጥ ግድ ይላል። የኮሜንኬሽን አገልግሎት ሙያ ብቻ ሳይሆን #መሰጠትን ይጠይቃል። አቅም፦ ችሎታ በሁለተኛ እና ሦስተኛ ደረጃ የሚመጣ ነው። አንባሳደር ፍጹም አረጋ ቀዳሚው ነበሩ። የጨመቱም - ብቁም ነበሩ።
ያው ቦታው ለኦሮሞ ሊቃናት #የተመደበ ነው። ከዬትኛውም ክልል ይወከል፦ ለዚህ የአብይዝም ሥርዓት የኦሮሞ ልጅነት መስፈርት ሆኖ ለስድስት ተከታታይ ዓመታት ቀጥሏል። እሺ ይሁንላችሁ ብንል፦ ግን ቢያንስ የሚደመጥ #ለዛ ያለው ሰብዕና፤ ለኢትዮጵያም የአቅም ልክ የሚደመጥ ሰው - ይመደብ። ትዕዛዝ አይደለም እንደ አንድ ኢትዮጵያዊ ዜጋ የግል ዕይታ ነው። የአቶ ለገሰ ቱሉ አንደበትም፤ የንግግር ጥበብ አቅምም ውሱን ነው። በቀላል አገላለጽ ለኢትዮጵያ ተፈጥሮ #ሸክም ነው። አብዝቶ በውስጡ የታጨቀ ቂም እና በቀል፤ #ጥላቻ እና #ማንአህሎኝነት የተከዘነበት ነው። ይህ ደግሞ ተፈጥሯዊ ለሆነችው ለልዕልት ኢትዮጵያ #የገጀሞ ያህል ነው።
አንድአንድ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ሊቃናት ጠሚር አብይን አላዳምጣቸውም ሲሉ አደምጣለሁ። እርግጥ ነው 365 ቀን ሙሉ የሳቸው ዲስኩር አለ። አንደበቶቻቸው ሚዲዮቻቸው፤ የጸጥታ አካሉ በሙሉ በአንድ መንፈስ ይናገራሉ። ሁሉን ለማዳመጥ የበዛ ታጋሽነትን እንደሚጠይቅ አውቂለሁኝ። ለታማሚው የኢትዮጵያ የፖለቲካ ተስፋ ግን ማድመጥ የግድ ነው። ካልተደመጠ በያትኛው አመክንዮ የትግል ታክቲክ እና ስትራቴጅ ሊነደፍ ይችላል? በብዕር እንደ እኔ በሰላማዊ ሁኔታ ለመሞገትም ጭብጡ በማድመጥ፤ በማንበብ፤ ሳይሰለቹ በመከታተል ነው የሚገኜው። ታግሼ #አደምጣለሁ። አስፈላጊ ሲሆን ደግሞ እንዲህ እሞግታለሁም።
እኔ በተለያዬ ሁኔታ እንደ ተከታተልኳቸው አቶ #አድማሱ #ዳምጠው ለቦታው ብቁ ናቸው። ይመጥናሉም። ከሚዲያ ጋር በቤተሰብነት መቆዬታቸው ብቻ ሳይሆን #ኮንፊደንሳቸው፤ የሚናገሩትን #ማስተር አድርገው የመግለጽ ክህሎታቸው ለዚህ ቦታ ትክክለኛው ሰው ይመስሉኛል። የእኔ የማደራጀት ሙያ እና ለኃላፊነት እጩወችን የማዘጋጀት ተመክሮዬን #ስፈትነው የሰጠኝ ፊድባክ ይህን ነው። እርግጥ ነው በፋና ብሮድ ካስት ያላቸውን የአስተዳደር አቅም በቅርበት የማዬት ዕድሉ የለኝም። በመድረክ ፕረዘንቴሽናቸው ግን በጣም በአትኩሮት የሚደመጥ ሰብዕና እንዳላቸው እረዳለሁኝ።
ንግግር መክሊት ነው። ከፈጣሪ ከአላህ /// የሚሰጥ። ይህን ስጦታ በስልጠና #መኳል ይቻላል። ንግግር #ጥበብ ነው። ጥበብነቱ ነው እንደ ታለንት እንዲታይ ያደረገው። አንድ ብቁ ተናጋሪ የአድማጭን ህሊና #መዳፋ ውስጥ ማድረግ ይችላል። #ቃር ካልሆነ - ተናጋሪው። ተናጋሪ እና አድማጭ ጋብቻቸው #ቃር ከሆነ የንግግሩ ተልዕኮ ይከሽፋል። ለዚህ አገላለጼ ትክክለኛው #መልኩ ደግሞ ዶር ለገሰ ቱሉ ናቸው። አንደበታቸው #የታረመ አይደለም። በውስጣቸው የሚንተከተክ የጥላቻ #ቁሊት ወይንም #ድፍድፍ አለ። በድፍረት የሚናገሩትም፤ የሚጽፋትም ብዙ የሞራል፤ የተፈጥሮ፤ የዕምነት፤ የይትብኃል #መተላለፎች ይበዙበታል። ለቦታው ዲስፕሊንድ አይደሉም።
በአለባበሳቸውም ከረባታቸው ጥምም ብሎ ነው። ይህ ማለት ለቤተ-መንግሥቱ ፕሮቶኮልም እርቀታቸውን ያሳያል።
ለዚህ ኃላፊነት …… ጨዋ፤ ፍፁም ታጋሽ። ደግ እና እሩህሩህ ህዝብ ሊያከበር የሚችል ሰብዕናን ይጠይቃል። ንቀት፤ መታበይ ለህዝብ መሪነት ፈተና የሚጥሉ አጓጉል ባህሪያት ናቸው። በሱ ሥም ተምሮ፤ ለደረጃ መብቃት ለድፍረት ንግግር ሊሆን አይገባም።
ብጣቂ ትህትና ከዶር ለገሰ ቱሉ አይቼ አላውቅም። በሥራቸው የሚገኙ ሠራተኞች ቀራኒዮ ላይ እንዳሉ ይሰማኛል። በፍጹም ለትውልዱ ሮልሞዴል ሊሆኑ የሚችሉ አይደሉም። በፍጹም። ስስ አቅም ቢኖር እንኳ በባህሬ ምራቁን የዋጠ ሰብዕና ከኖረ ያካክሰዋል። ሁሉ ከሌለ ግን መከራው ዳጥም አለበት።
የሚገርመኝ ጉዳዩን ማስተር እንዳደረገ ሰው የተፃፈላቸውን ማንበብ ትተው በቃላቸው #ባልታረመ አንደበት ሲያፋልሱት ነው። ብቁ ተናጋሪ ስላልሆኑ የተፃፈላቸውን፦ ንዴታቸውን ዋጥ በማድረግ ማንበብ እንኳን አይችሉም። ይህ ቀልድ ይቁም ነው የጹሁፌ ዓላማ። ቦታው ቋያ መሆኑን አውቃለሁኝ። ከዛ የሚመደብ ሰብዕና በግራ በቀኝ በቋያ ነበልባል መገረፋ አይቀሬ ነው። ግን የሚደመጥ ሰው ይመደብበት። #ቃር #ተሸከሙ አንባል።
ይህን ወሳኝ አመክንዮ ካሰብኩበት ቆይቻለሁ። አንድ ዓመት ይሆነኛል። ግን ቀኑን መወሰን አቃተኝ እና በጣም አዘገዬሁት። በዘገየሁ ቁጥር ቁልፋ ቦታ #ቆሳሰለ። አንዳንድ ጊዜ መጨረስ እያቃተኝ፦ እያቆራረጥኩ ነው እማዳምጠው። ያ ደግሞ የጭብጡ ተከታታይነትን ያጓጉለዋል፤ ወይንም ያጎፈረዋል። ማድመጥ ይኖርብኛል - ግድ ነው።
ካደመጥኩ በተከታታይ ሊሆን ሲገባ ከድምፃቸው ቃና ጀምሮ፦ የትህትና የአክብሮት ልሙጥነት፤ የአቀራረቡ ዝርግነት እና ተባደግነት፦ ፈጽሞ ለዚህ ዘርፍ ትውር ሊሉ የማይገባ ሰው ነው የተመደቡበት። ዶር ለገሰ ቱሉ አልተፈጠሩበትም። ቅብዓም የላቸውም። ጥሩ ተናጋሪም፤ ብቁ #አድማጭም አይደሉም ዶር ለገሰ ቱሉ። ይህ ቦታ ለኮታ ብቻ ተብሎ ረግረግ ላይ ሊተው አይገባም።
የኢትዮጵያ አንደበት ለመሆን ጥንቃቄ፤ እርጋታ፤ ብቃት፤ ክህሎት፤ አክብሮት፤ ትህትና፤ ሚዛናዊነት፤ ቁጥብነት፤ የበዛ ትህትና፤ ጭምትነት፤ #ዲፕሎማሲያዊነትን፤ ቁጥብነትን፤ ከጥላቻ ጽዕዱነት፤ የሚዲያ ሊቅነት ዲስፕሊን አብዝቶ ይሻል። ዶር ለገሰ ቱሉ ደግሞ በዘርፋ #ወና የሆነ ነገር ነው እማይባቸው። ጠንቃቃ አይደሉም። ብዙ በጣም ብዙ የፖለቲካ #ኤለመንቶች ነው ዳሜጅ እያደረጉ የሚገኙት።
መሪው ጠሚር አብይ ቢፈልጉ እንኳን እሳቸውን አሳምኖ ወደ ትክክለኛው አቅጣጫ ሊመራ የሚችል ሊቀ - መኮስ ኢትዮጵያ ያስፈልጋታል። ተያይዞ እንዲህ ገደል - ለገደል፤ ተያይዞ እንዲህ አፋፍ - ለአፋፍ፤ ተያይዞ እንዲህ ረግረግ - ለእረግረግ ከመንከራተት።
ቸር አስበን፦ ቸር እንሁን። አሜን።
ቅን አስበን፤ ቀና እንሁን። አሜን።
ማህበረ ቅንነት መሸቢያ ጊዜ። አሜን።
እግዚአብሄር ይስጥልኝ። አሜን።
ሥራጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
16/02/2025
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።
ዕውነት ጋራጅ አያስፈልገውም።
ትዕግሥት ሲያልቅ፦ ፍቅር ይሰደዳል።
ፍቅርም ሲያልቅ፤ ትዕግሥት ይሰደዳል።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ