UEFA Champions League 2018.
አሳዛኙ ስውር የራሞስ ሴራ አሸነፈ። ከሥርጉተ ሥላሴ 27.05.2018 (ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ።) „ልጄ ሆይ በክፉ ሰዎች አትቅና፣ ከእነሱ ጋር መሆንን አትውደድ፣ ልባቸው ግፍን ታስባለች እና፣ ከንፈራቸውም ሽንግላን ትናገራላችና።“ (መጽሐፈ ምሳሌ ምዕራፍ ፳፬ ቁጥር ከ፩ እስከ ፪ ።) የ2018 የአውሮፓ ሻንፒዮን ሊግ የዋንጫ ውድድር ፍጻሜ ቀን ነበር - 26.05.2018። እኔ ለሁለቱም ቡድኖች በተመጠነ ስሜት ለመከታታል ነበር ዕለቱን የታደምኩት። ምክንያቱም እኔ ወይ ከገዳመ አገር ከሲዊዝዬ አንድ ክለብ ወይ ከጀርመን ባዬር ሙንሽን / ዶርትሙንድ ቢኖሩልኝ ነበር ምኞቴ። የሆነ ሆኖ ያው ዘረ ዶርትሙንድ ስለነበር የተሻለ የስሜት ዝንባሌ ነበረኝ። የአስልጣኝ ዩርግን ክሎፕ አብነታዊ የውሳኔ ሰብዕና እጅግ ስለምመሰጠበት ዝንባሌዬ ለሊቨርፑል ነበር ማለትን በእርግጠኝነት መናገር እችላለሁኝ። ያው የጠይም ዕንቁ ቤተመንግሥታዊ የሰርግ...