እኔ የአናርኪዝም ፀር ነኝ።
እኔ የአናርኪዝም ፀር ነኝ። አናርኪዝም በዬትኛውም መስፈርት አቅም ሊዋጣለት የሚገባ ጉዳይ አይደለም። ፈፅሞ። የአማራ ህዝብ በጆኖሳይድ ይከሰስ ዘን ህወሃትም፣ ኦነግም ሰርተውበታል። ኦነግ ስል ኦህዴድ መራሹም ኦነግ ነው። ይህ ዘመን ለአማራ ህዝብ ከተፈጥሮው በላይ ጥንቃቄ ሊያደርግበት የሚገባ ዘመኑ ነው። አናርኪዝም ለአማራ ህዝብ ተፈጥሮው አይደለም። ከሁሉም በላይ ከ50 አመት በላይ በነበረው የተጋድሎ ዘመን ሬሼው ይውጣ ቢባል የአማራ ህዝብ በደም፣ በመንፈስ፣ በስንቅ፣ በትጥቅ፣ መኖሩን በመገበር የከፈለው ላቂያ ነው። ግን ለማን? ግን ለምን ሲባል፣ ምንም ነው። በቃ ምንም። አሁን ያለው ይህን ሁሉ መከራም ተሸክሞ ማገዶነት ከእሱ ይጠባቃል። ሌላም የስልት ለውጥ እንዲያደርግ መርህ ይነደፍለታል። አግባብነት የለውም። አማራ እኮ ብዙ ንቅናቄ አድርጓል። መሪ ነው ያጣው። የሆነ ሆኖ በጥንቃቄ አገር ቤት ያሉት በህግ አግባብ እዬሞገቱ ነው። እዬተፋለሙ ነው። እኛም የምንችለውን እያደረገን ነው። አማራ በውስጡ መኖር መቻል አለበት። ውስጡ መርህ ነው። ውስጡ ሥርዓት ነው። ያን አክብሮ ይታገል። አንድ ነገር ደፍሮ ከተማ ላይ ቢጀምር የባሰ ጣጣ ነው የሚመጣው። ለባልደራስ የተናገርኩት ቁምነገር አድማጭ አጥቶ ይኽው መከራ አመረተ። አናርኪዝም ከመጣ ዓለም አማራን እንዲረዳን የምንደክበት ጉዞ ሁሉ ይደርቃል። እኔ በበኩሌ ዝም ነው የምለው። ብዙ የሚሠሩ ሥራወች አሉ። ቲውተር ላይ ተግቶ መሥራት። ዓለም ስለ አማራ ህዝብ የሚያውቀው የለውም። ሥልጣን ላይ ያለውን ሥርዓት ለመጣል የሰከነ፣ የተደራጀ ፖለቲካዊ ትግል እንጂ አናርኪዝም መፍትሄ አይሆንም። ለዛውም ቀውስ መ...