ዓለም እና #ዛሬወነገ። የዓለማችን ፖለቲካ #ኢንፍሌሽን (ግሽፈት) እንደገጠመው ይሰማኛል።

 

ዓለም እና #ዛሬወነገ። የዓለማችን ፖለቲካ #ኢንፍሌሽን (ግሽፈት) እንደገጠመው ይሰማኛል።
 
ስለሆነም ዓለማችን በጠና ታማለች። አይዞሽ ባይ #አጽናኝ መንፈስ ትሻለች። #አናርኪዝምም ያስፈራኛል።
 
"አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ።" አሜን።
 
 May be an image of map
 
#ምዕራፍ ፲፰ በርከት ያሉ ዕርዕሰ ጉዳዮች በአንድ የወግ ገበታ።
 
ዓለም የመረጠችው ጎዳና በሁሉም ዘርፍ ጭንቅ ሆኗል። ጫናም በዝቶባታል። በሌላ በኩል የዓለማችን ፖለቲካ ኢንፍሌንሽን የገጠመው ይመስለኛል። በዘመኑ የፖለቲካ ባህሪ አንፃር ሳስተውለው ካፒታሊዝም እድገቱን ጨርሶ ወደ #ኢንፕሪያሊዝም እያማተረ ይመስለኛል። ስለሆነም የፖለቲካ ሊቃናት ሰራሽ ችግሮች የተሻለ ዕድል ያገኙ ይመስለኛል። የህዝብ የመወሰን አቅም ደግሞ ፈተና ላይ የወደቀ ይመስለኛል። ይመስለኛል እምለው ጥናታዊ መረጃዊ ሁነትን ስለአላካሄድኩ ነው። 
 
በዚህ ዙሪያ የሁሉም የሃይማኖት ተቋማት አቨው የዓለማችን የመኖር ቀጣይነት በሚመለከት አጀንዳቸው አድርገው ስለ ዓለማችን የጸሎት ቀናትን ወስነው ሊተጉ የሚገባ ይመስለኛል። ዓለም ሃዘን ላይ ናት። አጽናኝ መንፈስ ትሻለች - ና።
 
በሁሉም ቦታ #ስጋት አለ። በሁሉም ቦታ የሰው ልጅን የሰው ልጅ ይገድለዋል። #ጭካኔ መለያ #ማልያ የመሆን ዝንባሌም አለ። በሁሉም ቦታ #የታመቀ ጭንቀት አለ። በሁሉም ቦታ አስፈሪው የጦርነት ሁነት አድማጭ አግኝቶ ገኖ ይታያል። ጦርነት ተፈጥሮ ሰራሽ አይደለም። ጦርነት ፖለቲካ ሰራሽ ቀመር ነው። ፖለቲካ ደግሞ የሰው ልጅ የሚፈላሰፍበት አንኳር የዕውቀት ዘርፍ ነው።
 
ስለሆነም ጦርነትን የሚያነሳሱ፤ የሚገፋፉ፤ የሚያበረታቱ ሁነቶችን መግታት ፖለቲከኞች ይችላሉ። ግን ፈቃዳቸው እንብዛም ነው። ባለፋት አራት ዓመታት ውስጥ እንኳን ……
 
1) የዩክሬን እና የራሺያ ጦርነት፤ የአውሮፓ ህብረት ኔቶን ያካተተ ነው ፍጥጫው። የዘለንስኪዝም ፑቲናዊነትን አክሎ ገዝፎ ለመውጣት የሚያደርጉት ውጥረት።
 
2) የእስራኤል፤ የጋዛ ጦርነት ከቅርብ ከሩቅም ሁለቱን በሚደግፋ አገሮችም ፍጥጫው አይሎ ታይቷል። የመጀመሪያዋ የሃማስ የጥቃት ዒላማ እና መራራ መዘዙ ………
3) የሱዳኑ የእርስበርስ ጦርነት፤ የስደተኛ ፍልሰት እና የጎረቤት አገሮች ሁነት።
4) በብልጽግና እና በህወሃት፤ በኦላ እና በብልጽግና፤ ዘግየት ብሎም በብልጽግና እና በፋኖ ያለው የእርስ በርስ ጦርነትና ግጭት፤
5) ኢራን ውስጥ ያለው አሁናዊ የንጹሃን እልቂት እና ከአሜሪካ ጋር ያለው የፋመ ፍጥጫዊ ሁነት፤ ቀደም ሲል ከእስራኤል ጋር የነበረው ጦርነት፤
6) የትራንፒዝም የዴንማርኳን ራስገዝ ግሪንላንድን #የመናፈቅ ክስተት፤ የአሜሪካ እና የአውሮፓ ህብረት የታሪፍ ፖለቲካ፤
7) የግብጽ ሊቃናት ለጋዛ እና ለእስራኤል ጦርነት ትግታ እኔ በፈጸምኩት ሮል ልክ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ ለውለታዬ #የናይል አራጊ ፈጣሪነት፤ ሱፐር ፓወርነት፤ ማስተር ማይንድነት ይረጋገጥልኝ ቲወሪ በትራንፒዝም ፖለቲካ ይካተት ዘንድ መቋመጥ፤ በቀጥታ ትርጉሙ ባለፈውም ጊዜ ጽፌበታለሁኝ ቅኝ ተገዝታ የኖረችው ግብጽ፤ ቅኝ ተግዛታ የማታውቀውን ፈላስፊት ኢትዮጵያን ቅኝ ግዛቷ ለማድረክ የእርሰወም ይሞክሩ የኪወስክ ትዕይንት። ኢትዮጵያ ዘመኗን ሁሉ በነፃ ላበረከተችው ውሃ፤ ለም አፈር እና ቅዱስ መንፈስ ካሳ ልትጠይቅ ሲገባ ለሽ ስላለች በግብጽ በኩል መቀናጣቱ #አና ማለቱ። 
 
8) እየገፋ፤ እየተጋፋም የመጣው የኢትዮኤርትራ የዳግም የጦርነት ሽውታ በግራቀኙ መሪወች ዘለፋ ታጅቦ ከባህር በር፤ ከወደብ፤ ከአሰብ ናፍቆት ጋር ተያይዞ ሲብላላ የቆዬው ሁነት አፋፍ ለአፋፍ ያሰኜው ስለመሆኑ ……
 
9) የነገረ ቤኑዙላ የሰዓታት የአሜሪካ የድል ኦፕሬሽን፤ የኪውባ ኢኮኖሚ ዕጣ ፈንታ 
 
10) የቻይና እና የአሜሪካ ያልተገለጠው ፋክክር …… ወዘተ ……
 
እውነት ለመናገር የትራንፒዝም የሰላም ጥረት ከዘለቀ የጋዛ እና የእስራኤል ጦርነት ተግታ የብዙ ነፍሳትን ሩህ እንደታደገ ይሰማኛል። በሌላ በኩል በዚህ መስመር በተሻለም ሁነት ዓለማችን ድምፆዋን ከፍ አድርጋ #ጦርነት በቃኝ! በቃ ጦርነት! የምትልበት ግሎባል ትዕይንተ ህዝብ ሁነት አለመኖር እጅግ አሳሳቢው ጉዳይ ነው።
 
ጦርነት በቃ የሚል ህብራዊ ዘመቻ በግሎባል ደረጃ አይሰማም። ቢያንስ #ሴት የዓለማችን ሊቃናት በዚህ ዙሪያ ስለምን እንደማይተጉ አይገባኝም። እርግጥ ነው የዚህ የሰላም ሁነት መሪ ሊሆን የሚገባ ተመድ ነበር። አቅሙ በአንድም በሌላም #እየበረደው ይገኛል። ትራጀዲም ነው።
 
ይህ ድርጅት ኃላፊነቱን ለመወጣት ካልቻለ አያያዥ #መረቦች ሁሉ እየላሉ ከሄዱ፦ እስከዛሬ ድረስ ዓለምን በአንድ ማዕከላዊ ሰላማዊ እና ህጋዊ ሁነት ይዞ የቆየው #ማስትሽ ከለቀቀ #አናርኪዝም ይከሰታል። ይህ አደገኛው መስመር ነው። ኃይል ያላቸው አቅመ ደካሞችን ሊውጡ ይችላሉ። ይህ ሲሆን ነው እኮ #ኢንፐርያሊዝም ክሱት ሆነ የሚባለው።
 
ይህንን ውጥንቅጥ፤ ይህን ውስብስብ፤ ይህን ድንበር አልቦሽ ችግር ለማስታገስ ከፈጣሪ ጋር መምከር፤ ጥሞና መውሰድ፤ ለሰው ልጅ መኖር እና ለተፈጥሮ ውበት መጨነቅ ይገባ ነበር።
 
ዓለማችን ቆንጅዬ ናት። ስልጣኔዋ ያጓጓል። የትውልዱ ፈጣን የፈጠራ ችሎታ እና ትጋት ያሳሳል። ግን አክሳዩ ጦርነት ሁሉን መልካም ዕድሎች ሁሉ እየፈተነው ነው። የሰላም ዳኛ፤ አጽናኝ ሰብዕና፤ ታጋሽ ፖለቲካ፤ ሰውኛ አትኩሮት፤ ሩህሩህ ህሊና፤ አርቆ አሳቢ ጭንቅላት፤ ጥላቻን የተጸየፈ አብሮነት፤ እራስን ያወቀ አቅም እና ክህሎትን ትፈልጋለች ዓለማችን። ሳቅን የሚያበረታታ ብቻ ለሳቅ የሚሆን ብቁ አቅምም። በአንድም በሌላም የነገ የዓለም ትውልድ ሁነት ያሳስባል።
 
በተለይ ሦስተኛው የዓለም ጦርነት እኔን በእጅጉ ያሰጋኛል። ለዓለማችን የሚበጀው የጠራ ጎዳና #ሰላም ብቻ ነው። 
 
ቸር አስበን፤ ቸር እንሁን። አሜን።
ቅን አስበን፤ ቀና እንሁን። አሜን።
ኑሩልኝ። አሜን።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
27/01/2026
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

የእኔ እማ ልዕልቴ እንዴት ነሽ?

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።