#የበረዶ #ወጀብ በአሜሪካ እና በካናዳ። ዘገባው የቢቢሲ BBC ነው።

 

#የበረዶ #ወጀብ በአሜሪካ እና በካናዳ። ዘገባው የቢቢሲ BBC ነው። 
 
" አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ።" አሜን።
 
ለሰው ልጅ ሊቆጣጠረው የማይችል የተፈጥሮ አደጋ በቂ ነው። ይህን መሰል ችግር አሳሳቢ ነው። አሜሪካ እና ካናዳ ለሚኖሩ የዓለም ዜጎች ሁሉ ፈጣሪ አምላክ #ምህረቱን ይላክላቸው። አሜን። በየሰዓቱ የሚሰማው ዜና እጅግ አሳሳቢ ነው። በሁለቱም አገሮች ሰፊ ቁጥር ያላቸው ወገኖቻችን አሉን። የእኔ ድንግል ጥላ ከለላ ትሁናቸው። አሜን።
 
በበረዶው ምክንያት ህይወታቸውን ላጡ ሁሉ ነፍሳቸውን በገነት ያስቀምጥልን አምላካችን፤ አላሃችን። በሌላ በኩል መኖራቸው ለተጎሳቆለ፤ የዕለት መብራት ላጣ፤ ከቀያቸው ለተፈናቀሉ፤ ቤተሰቦቻቸውን ላጡ ሁሉ አምላካችን አብዝቶ መጽናናትን ይስጥ አሜን። ለዚህ መሰል ተፈጥሯዊ ያልተለመደ ክስተት ፈጣሪ ምህረት ይልክ ዘንድ ብሄራዊ የጸሎት ቀን አውጆ ጥሞና ማድረግ ይገባል።
 
ሥርጉትሻ 27/02/2026
 
አምላካችን ሆይ! ምህረትህና ቸረንተህ አይለዬን። አሜን።
 
"በአሜሪካ በተከሰተው ከባድ የአየር ሁኔታ ቢያንስ 21 ሰዎች ሞቱ"
«በአየር ሁኔታ ምክንያት በአሜሪካ ከ10 ሺህ በላይ በረራዎች ተሰረዙ»
«ካለፈው ሳምንት ማብቂያ ጀምሮ በአብዛኛው የአሜሪካ ግዛቶች ውስጥ በተከሰተው ከባድ ቅዝቃዜ እና የበረዶ ወጀብ የተነሳ እስካሁን ድረስ ቢያንስ 21 ሰዎች መሞታቸው ተዘገበ።
 
የተለያዩ ግዛቶች ባለሥልጣናት እንዳስታወቁት ከተከሰተው ከባድ የክረምት ቅዝቃዜ ጋር በተያያዘ በበርካታ ግዛቶች ውስጥ እስከ ሰኞ ሌሊት ድረስ የ21 ሰዎች ሕይወት ያለፈ ሲሆን፣ ቁጥሩ ሊጨምር እንደሚችል ተሰግቷል።
 
ከባዱ የበረዶ ወጀብ ባለፉት ቀናት ከነበረባቸው አካባቢዎች እየተስፋፋ በርካታ ግዛቶችን እያካተተ ነው። በዚህም ሳቢያ ከ200 ሚሊዮን በላይ አሜሪካውያን በከባዱ የአየር ሁኔታ ስጋት ውስጥ ናቸው።
 
እየጣለ ባለው በረዶ ምክንያት በጎዳናዎች፣ በአየር ማረፊያዎች እና በሌሎችም መሠረተ ልማቶች ላይ ከፍተኛ ክምር በመፍጠሩ፣ እንቅስቃሴዎች ከመስተጓጎላቸው ባሻገር የኤሌክትሪክ አቅርቦት በበርካታ ቦታዎች ተቋርጧል።
 
ባለፉት ቀናት በሺዎች የሚቆጠሩ የአገር ውስጥ እና ዓለም አቀፍ የአውሮፕላን በረራዎች የተሰረዙ ሲሆን፣ በቀጣይ ቀናትም የሚኖሩ በረራዎች የመሰረዝ ወይም የመዘግየት ዕጣ ይገጥማቸዋል ተብሏል።
 
በበርካታ ግዛቶች ሰዎች ከቤታቸው መውጣት ስለማይችሉ ትምህርት ቤቶች እና ሌሎች ተቋማት ተዘግተዋል። ግዛቶች አስቸኳይ የአደጋ ጊዜ ቡድኖችን በማሰማራት ወሳኝ መሠረተ ልማቶችን ከበረዶ ክምሮች ለማጽዳት እየሞከሩ ቢሆንም የአየር ሁኔታው በመቀጠሉ ያሰቡትን ያህል ስኬታማ አልሆኑም።»
 
«በአየር ሁኔታ ምክንያት በአሜሪካ ከ10 ሺህ በላይ በረራዎች ተሰረዙ»
"በአሜሪካ በተከሰተ ከባድ የበረዶ አውሎ ነፋስ ቢያንስ ሰባት ሰዎች ሲሞቱ 800 ሺህ ነዋሪዎች ኤሌክትሪክ ተቋረጠባቸው"

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

የእኔ እማ ልዕልቴ እንዴት ነሽ?

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።