ልጥፎች

"የድምጻችን ይሰማ" ስኬት ተመክሮ ዕድምታ በሥርጉተ ሥላሴ ዕይታ።

ምስል
 እንኳን ወደ ቀንበጥ ብሎግ በሰላም መጡልኝ  "የድምጻችን ይሰማ" ስኬት ተመክሮ            ዕድምታ በሥርጉተ ሥላሴ           ዕይታ።   „የሰው ልብ መንገድን ያዘጋጃል እግዚአብሄር ግን አካሄዱን ያቃናለታል።“   ምዕራፍ ፲፮ ቁጥር ፱ 07.05.2019 ከእመ ዝምታ ሲዊዚሻ። ·        መግቢያ። እንዴት ናችሁ የኔዎቹ? ደህና ናችሁ ወይ፧ የቀድሞው ፕ/ ዶር ነጋሶ ጊዳዳን ነፍስ ይማር አላልሽም። ለምን የሚል ጥያቄ ቀርቦብኛል። ከቶ እንደ እኔ ስለ ግለሰቦች መልካም ነገር የሚመሰክር ጸሐፊ አለን? ማንም እኮ ስሌለው አድንቆ፤ አክብሮ፤ ተበራታልኝ ብሎ አይጽፍም። እኔ ግን ሲሞላ እና ሲጎድል የተፈጠርኩኝ አይደለሁም። እውነት ነው በምልበት ሁሉ እተጋለሁኝ። ለዛውም የማይደፈረውን ሁሉ ነው የምደፍረው። ሰተት ብዬም ነው ፈተና ውስጥ ራሴን እምማግደው። መጠለያ ጥግ ሳይኖረኝ። ስለሆነም እሳቸውን በሚመለከት ብዙ ጊዜ ጽፌያለሁኝ። ቅሬታዬንም አክብሮቴንም። ኦዴፓ እንኳን ስላደረገላቸው መልካም ነገር አድንቄ ሁሉ ጽፌያለሁኝ። ህልፈታቸውን ሳዳምጥም በድንጋጤ ተውጬ እንዲያውም አንድ ቀን ካደርኩኝ፤ ከተረጋጋሁኝ በኋዋላ ጽፌለሁኝ። አንጀቴ ስስ ስለሆነ አገር ቤት ስለ አንድም ሰው በህይወት አለመኖር ተነግሮኝ አያውቅም። እንደ ጹሁፎቼ እና እንደ ሙግቶቼ ጠንካራ አይደለሁም። ከምትጥብቁት በላይ አዛኝ እና ሩህሩህ ነኝ። ሌላው ደግሞ የማልችላቸው ጊዜያትም ሊኖሩ ይችላሉ። የጤናም ጉዳይ አለ፤ ድካም አለ። እንዲሁም በአመዛኙ ደግሞ እኔ ብዙ አትኩ...

ድምፄ ከውስጤ!

ምስል
 እንኳን ደህና መጡልኝ  ድምፄ ከውስጤ! „ጉድጓዱን የሚምስ ይወድቅበታል፣ ቅጥርንም የሚያፈርስ እባብ ትነድፈዋለች።“ መጽሐፈ መክብብ ምዕራፍ ፲ ቊጥር ፰ ከሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 06.05.2019 ከጭምቷ ሲዊዝርላንድ። እንዴት ናችሁ ቅኖቹ? ድምፄ በሚል ርዕስ ለኮ/ደመቀ ዘወዱ በአንድ ወቅት የጻፍኩት ግጥም ነበር። ከደጉ ሳተናው ድህረ ገፅ ላይ ይገኛል። የዛሬው ድምፄ ከውስጤ ግን ቀንበጥ ብሎግ በድምጽም ሥራ ሥለጀመረች በጹሁፍ የሚወጡት በድምጽ እንደ አግባብነታቸው አልፎ አልፎ ሲቀርቡ እንዲህ ማስተወስ ስለሚገባ ነው።  ስለዚህ ትናንት የጻፍኩት የዩኒስኮ "የሰላም ሽልማት  የእሾህ አክሊል ነው" የወግ ገበታ በድምጽ ተሰርቶ ቀርቧል። ሌሎችም ከሰሞናት በድምጽ የተሰሩ ስላሉ እነሱንም ታደምጡ ዘንድ በትህትና እገባዛለሁኝ። አክባሪያችሁ! ·      የዩኒስኮ የሰላም ሽልማት ተሸላሚ ጠቅላይ ሚኒስተር ዶር አብይ አህመድ እና ዕድምታው በሥርጉተ ሥላሴ ዕይታ (06.05.2019 ) https://www.youtube.com/watch?v=ESbS_aHXoEM&feature=youtu.be ·        "“ ሽብር በአዋሳ እና የመንግሥት ዝምታ " በጸሐፊ አቶ ዳሞ ጎታሞ   ( አቶ መስፍን ማሞ ተሰማ እንደ ተረጎሙት።“ )   https://www.youtube.com/watch?v=jLfvuYjuzVY&t=22s ·        እንዴት ይታራቅ ? (04 05 2019) h...

የዩኔስኮ የሰላም ሽልማት የእሾኽ አክሊል ነው።

ምስል
 እንኳን በደህና መጡልኝ  የዩኔስኮ የሰላም ሽልማት   የእሾኽ አክሊል ነው። „ትእግስት ታላቁን ሃጢያት ጸጥ ያደርጋልና   የገዢ ቁጣ የተነሣብህን እንደ ሆን ስፍራህን አትልቀቅ።“   መጽሐፈ መክብብ ፲ ቁጥር ፬ ከሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 05.05.2019 ከእመ ሲወዘርላንድ ·        እ ፍታ። „ጠ / ሚ / ሩ የተባበሩት መንግሥታት የሳይንስና የባሕል ድርጅት ( ዩኔስኮ ) ጉሌርሞ ካኖ የዓለም የፕሬስ ነፃነት የሽልማት ስነ - ሥርዓት ላይ ለሚያደርጉት የእራት ግብዣ ለመታደምና ሃሳብን በመግለጽ ነፃነት ዙርያ ለመነጋገር ነበር። መርሐ ግብሩም በመልካም ሁኔታ ተጠናቋል።“ ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ እንደ ዘገበው። https://www.satenaw.com/amharic/archives/67322 ከጠ / ሚ / ሩ እና የውጭ ጉዳይ ሚ / ሩ ጋር ! ( ጋዜጠኛ ውብሸት ታየ ) May 4, 2019 ዛሬ ለስላሳው ጋዜጠኛ አቶ ውብሸት ታዬ  ለሰልፊ መፈለጉ ራሱ መልካም ነው። በእሱ ስቃይ ሽልማቱ እንደተሰጠ ግን ልብ ያለው አይመስልም ጭብጡን እንደተረዳሁት። ፍንሽንሽም፤ ፍንክንክም ብሏል። ከእስር እንደ ተፈታ ያን ጊዜ በቤተ መንግሥት ተጠርቶ ለቡና ቁርስ በቅቶ ቢሆን ኖሮ ነበር ለእኔ ገድል ልለው እችል የነበረው ልክ እንደ ኡሳታዞች። አሁን ግን ያው ለኦነጋዊ መንፈስ ማገራዊ ጥበቃ ማጣበቂያ ማስትሽነት ነው። የሽንገላ መግል። እዬበረደኝ ነው ያነበብኩት መንፈሱን እራሱን። ምክንያቱም በራሱ ዕይታ ልክ የተሠራው በሙያው ማሰተ...