የዩኔስኮ የሰላም ሽልማት የእሾኽ አክሊል ነው።


እንኳን በደህና መጡልኝ
የዩኔስኮ የሰላም ሽልማት
 የእሾኽ አክሊል ነው።

„ትእግስት ታላቁን ሃጢያት ጸጥ ያደርጋልና
 የገዢ ቁጣ የተነሣብህን እንደ ሆን ስፍራህን አትልቀቅ።“
 መጽሐፈ መክብብ ፲ ቁጥር ፬

ከሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
05.05.2019
ከእመ ሲወዘርላንድ

·       ፍታ።

„ጠ// የተባበሩት መንግሥታት የሳይንስና የባሕል ድርጅት (ዩኔስኮ) ጉሌርሞ ካኖ የዓለም የፕሬስ ነፃነት የሽልማት ስነ - ሥርዓት ላይ ለሚያደርጉት የእራት ግብዣ ለመታደምና ሃሳብን በመግለጽ ነፃነት ዙርያ ለመነጋገር ነበር። መርሐ ግብሩም በመልካም ሁኔታ ተጠናቋል።“ ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ እንደ ዘገበው።

ከጠ// እና የውጭ ጉዳይ / ጋር! (ጋዜጠኛ ውብሸት ታየ )
May 4, 2019

ዛሬ ለስላሳው ጋዜጠኛ አቶ ውብሸት ታዬ ለሰልፊ መፈለጉ ራሱ መልካም ነው። በእሱ ስቃይ ሽልማቱ እንደተሰጠ ግን ልብ ያለው አይመስልም ጭብጡን እንደተረዳሁት። ፍንሽንሽም፤ ፍንክንክም ብሏል። ከእስር እንደ ተፈታ ያን ጊዜ በቤተ መንግሥት ተጠርቶ ለቡና ቁርስ በቅቶ ቢሆን ኖሮ ነበር ለእኔ ገድል ልለው እችል የነበረው ልክ እንደ ኡሳታዞች።

አሁን ግን ያው ለኦነጋዊ መንፈስ ማገራዊ ጥበቃ ማጣበቂያ ማስትሽነት ነው። የሽንገላ መግል። እዬበረደኝ ነው ያነበብኩት መንፈሱን እራሱን። ምክንያቱም በራሱ ዕይታ ልክ የተሠራው በሙያው ማሰተርሱን የያዘው ሟቹ ጋዜጠኛ አቶ ደምስ በለጠ አገር ሲገባም፤ ነፍሱ ከሥጋው ሲያልፍም መንግሥት ሆዱ በሚያውቀው መልክ የከወነውን መከወኑን አስተውላለሁኝ። ዜጋ ለአገር እኩል ነው ኢትዮጵያ መሬት ላይ አይሰራም። 

በህይወት እያለ ጋዜጠኛ አቶ ደምስ በለጠ እውነት የእኔ በምለው አዋድ፤ እሱም አውነት አለኝ ብሎ በሚያምንበት በጋራ ቤታችን በዘሃበሻ ብሞገtውም፤ አገር ሲገባ የነበረው ሁኔታ እንዲሁም አሟሟቱ ግን ስለሰው ተፈጥሮ፤ ስለ እኩልነት፤ ስለነጻነት፤ ስለ እውነት ስለዜግነት ለሚተጋ ብዕርና ብራና እንደዜጋ ላልታዬ ነፍስ እሱን ለፈጠረች ድምጽ አልባዋ እህት፤ ድምጽ አልባዋ እናት፤ ድምጽ አልባዋ ሚስትና ልጆች ጥብቅና መቆም ካልቻለ የሥርጉተ መንፈስ እኔ ከሰው ተራ የወጣሁ ዱዳ ነኝ ማለት ነው። 

በሃሳብ መለያዬት ደመኝነት አይደለም። በሃሳብ መለያዬት ጠላትነት አይደለም። በሃሳብ መለያዬት የህሊና ሥልጣኔ ልኬታ የውሃ ልክ ነው። ይህ አቅም የጠ/ሚር አብይ ፕሬስ ሰክሬታርያት ቢሮ አለውን ሲባል በድፍኑ መተው ይሻላል። ይልቅ አሁን አቻውን ድንብልብል አጎሽቶጎልሏል። 

ብሰል ከቀሊል፤ የክት እና የዘውትር፤ ቅልብተኛ እና ለሙያው ያደረ፤ የተደመረ እና ያልተደመረ፤ ነጉሥ ጋዜጠኛ እና ሎሌ ጋዜጠኛ፤  የቤት እና የእዳሪ ሚዲያ  ከዛ ዘለግ ባለው ደግሞ የዘመንኛ ብሄር አባልነትም አለበት። ይህ ለኢትዮጵያዊው እውነት ሆነ አምክንዮ አይመጥንም።

ስለሆነም እኔ ይህ ሽልማት የእሾኽ አክሊል ነው ብዬ ነው እማስበው። ልኩንም አላገኘም። ምክንያቱም ኢትዮጵያን ውስጧን ሰላም ለማድረግ በአንድ መሪ ቃል ውስጧን አስክኖ መርህ ጠገብ ክንውን ለማድረግ ስላልቻለ የጠ/ሚር አብይ አህመድ መንፈስ። ንጠት፤ ስጋት፤ ፍርሃት፤ ሽብር፤ ቀውስ ትርጉማቸው ሰላም ከሆነ ይህን የሚያውቀው አለምአቀፉ ድርጅት ዩኔስኮ ብቻ ይሆናል መስፈሪያውን የሰላምን ማለቴ ነው።

አለመመጠናቸውንም እሳቸው አሳምረው ስለሚያውቁት ሽልማቱ የተለበጠ ቅብ ወይንም የተሸነገለ  ስለመሆኑ ይገባቸዋል፤ ልባም ስለሆኑ ጠ/ሚር አብይ አህመድ። ማለት ሽልማቱን ወደ እሳቸው ለማስጠጋት፤ የራሳቸው የጥረት ውጤት አድርገው ለማዬትም፤ ከደማቸው ጋር አዋህዱ ንዑድ ሐሤት ለማግኘትም ሽንግላን በጤና አዳም ካላሰኛቸው አይቻላቸውም። በፍጹም! ፌዝ ነው። ሰላም ታቅዶ እዬታመሰ፤ ታቅዶ በቀወስ ተደራጅቶ እዬተቃጠለ ለሰላም ተሻላሚነት ዱላ ነው ለዛውም በርግጫ።

"ሽብር በአዋሳ እና የመንግሥት ዝምታ" በጸሐፊ አቶ ዳሞ ጎታሞ ( አቶ መስፍን ማሞ ተሰማ እንደ ተረጎሙት።)


አንድ የጎርምሳ ጉሩፕ ዓለምአቀፉን ጋዜጠኛ አቶ እስክንድር ነጋን ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳይሰጥ የውስጥ አግዳ ሲጥል፤ የ4ኪሎ መንግሥት ስለሰላሙ እርግጠኛ አይደለሁም እና ሰላም ያለችው ቤተ መንግሥት አዳራሽ ብቻ ነውና እዛ መጥቶ ይስጥ ጋዜጣዊ መግለጫ ነበር ያለው። መሳቂያ!

ይህም ብቻ አይደለም በቀጣይም ህዝባዊ ስብሰባውንም በጎረምሳ ሲታገድ ከአዲስ አበባ ውጪ በመጡ የጎረምሳ ቲም መንግሥት ስለ ሰላም ተጋድሎ ፈጽሜ ተሸልምኩ ማለት ለእኔ ልግጫ ነው። 

ዩኔስኮንም ከደረጃው በእጅጉ ዝቅ ያደርገዋል። ይህ ሁሉ የርዕሰ መዲናዋ ህግ አልባነት የሰላም ሽልማት ካሰጠ ዩኔስኮ ለፕ/ ሳዳምም ሁሴንም ቢሰጠቸው የተገባ ይመስለኛል። ግሎባሉ ዓለም ደግሞ „ሰላም“  ስለሚለው ግዙፍ ሁልአቀፍ ጽንሰ ሃሳብ የፊደል ገበታ እንደገና መቀረጽ ያለበት ይመስለኛል። ሰላም ማበጫያ ወይንም የግድግዳ ኖራ ስላልሆነ። ዓለም አቀፉ ተቋም ኢትዮጵያን እንደ ጥንቸል የመሞከሪያ ጣቢያም ያደረጋት ይመስለኛል፤ ደስ ብሎታል ማለት ይሆን በዚህ ምስቅልቅል?

የርዕሰ መዲናን ደህንነት ከአቅሙ በላይ ከሆነ የፌድራሉ መንግሥት ጠቅልሎ ገዳም ይግባ።


ስለሆነም እንደ ቀድሞዋ ደጋፊያቸው እንደ ሞጋቿ ሥርጉተ ሥላሴ ዕይታ የሽልማቱ ዕድምታ የትውስት ይሆንባቸዋል። ለእኔ ዕዳ ነው። በወለድ አገድ የተያዘ የአራጣ ጣሪያ በድርብ ንብርብር ካቴና።

ይህ ሽልማት ከመጋቢት 24 ቀን 2010 ዓ.ም ቃለምህዳን ብቻ ለሆነው ተግባር ላይ ባመዛኙ ትነት ለዘፈነበት ንግግር ከሆነ ግን ይስማማኛል።

ባሉት ልክ ሳይሆን ቃሉ፣ ስንኙ፣ ከአንደበታቸው ስለመውጣቱ ከምቱ ዜማዊነት፤ ቅኔያዊነት፤ ጅግንነት ጀምሮ ዛሬ ላይ ምን ሆኜ ሳለ ነበር የተናገርኩት እንደሚሉ ዶር አብይ አህመድ እርግጠኛ ነኝ። እኛም ሐሤት አይበርክትላችሁ ተብለን የተረገምን መሆናችን አሳምርን ጥጥት እዬያደረግን ለሽ ብለናል፤ እንጂ ለዚህ የሚያበቃ አመክንዮ የነቁጥ ያህል የለም። ኢትዮጵያዊነት የተሴረበት ስለመሆኑ ለሚያውቅ ምራቁን ለዋጠ ህሊና።    

በሌላ በኩል ዩኔስኮም ደህና ሞጋች ቢገጥመው ሽልማቱን እንደገና ሊያዬው የሚደድበት ጉዳይ ይመጣል ብዬ አስባለሁኝ። ይህን ዘርዘር አድርገን እንዬው። ግን ጀግና ቢገኝ ማለት ነው። ኢትዮጵያ ልጅ ቢኖራት? ? 

1)               ለምሳሌ የኢትዮ አፍሪካን ርዕሰ ከተማ የአንድ መንደር ሥም ሰጥቶ „ፊንፊኔ“ ማለት በራሱ ከቅርስ፤ ከትውፊት ውጪ ያደረጋል ለአንድ የአፍሪካ ቀንድ ለሰላም ታታሪ ጠ/ሚር። ለዛውም ለተመድ ተልዕኮ በተግባር ለተገኘ ወታደር።

ይህን በተደጋጋሚ አዲስ አባባን ጠ/ሚር አብይ አህመድ ሳይቀፋቸው፤ ቅጭጭም ሳይላቸው፤ ሳያፍሩበት የኢትዮጵያ መሪ ሆነው „ፊንፊኔ“ ሲሉ እሳቸው ለቅርስና ለውርስ ያላቸው ክብር፤ ከድርጅታቸው ከኦዴፓ ፍላጎት በላይ አድርገው ለማዬት አገርን እንዴት የተሳናቸው አቅመ ቢስ ስለመሆናቸው ያመለክታል።

2)               የዘንድሮ የአድዋ ድል አከባበር እና ተመስጥዎ ከንጉሶች ንጉሥ ከዳግማዊ አጤ ሚኒሊክም፤ ከዘብርሃን ኢትዮጵያ ከእቴጌ ጣይቱም መንፈሱን አርቆ ለመወሰድ የሄዱበት መንገድ በራሱ ሌላው ውርዴ ነው። መጀመሪያ ኢትዮጵያዊነት ይዋጡት - በትህትና። ለዚህ ሽልማት ያበቃቸው ኢትዮጵያዊነታቸው እንጂ ኦሮማዊነታቸው አይደለም። አልነበረም። ሥልጣኑ የኢትዮጵያ የክብር ኒሻን እንጂ ኢትዮጵያዊነትን በበዛ ሁኔታ ለመጫን አይደለም። የህዝብ ድጋፉም መሰረቱም ያ ነው ሚስጢሩ። ስለሆነም አዲስ አባባ እና አማራ ክልል ላይ ያላቸውን ጫና ይመርምሩት። ማንን እና ምን እንደሚያስፈራቸው፤ እንደሚመራቸውም፤ እንደሚያርዳቸውም በዚህ ውስጥ ሽልማት? ? ? ? ?  አሰንጋላ ነው።

ለእሳቸው ለዶር አብይ አህመድ ከመጋቢት 24 ቀን 2010 ጀምሮ የኢትዮጵያ መሪ፤ ጠቅላይ ሚ/ር መሆናቸውን ደወል ወይንም አለርም በዬጊዜው መሞላት የሚያስፈልጋቸው ይመስለኛል። መሪነታቸው የኢትዮጵያ ስለመሆኑ ልብ ያሉት አይመሰለኝም። የጌዴኦ እናት „እኛም ኢትዪጵያዊ ከሆን“ ስትል ነው የጠዬቀችው። ይህ ክብር ሆኖ ካሸለመ፤ እንቅልፍ ካስወሰደ ማዬት ነው።

ጠ/ሚር አብይ አህመድ ትምክህታቸው በኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊነት ሳይሆን በቡራዩ፤ በለገጣፎ፤ በለገዳዲ፤ በሰበታ በሚኖረው ህዝብ ሳይሆን በምርጥ ዘራቸው ሀረጋቸው ብቻ የተሰኩ፤ በዛም ጥበቃ እንደሚደረግላቸው በአደባባይ ነግረውናል። ደጀናቸው፤ ክብራቸው ኩሩታቸው ያ ህዝብ ብቻ ስለመሆኑ በወታደራዊ ኩዴታ ወቅት በሰጡት መግለጫ እሰረግጠው ግልጸዋል። ሲያሻቸውም ይኸው አዲስዬን ያስምሱበታል ጎረምሶቻቸውን በፈለጉ ጊዜ እያሰለፉ።

3)               „አኖሌና“ ቅርስ እና ሰላም?

ያው እኔ አኖሌ አጀንዳዬ ሆና አታውቅም። የህሊና ጣወቱ መርዙ ብክሉ ልኬታው በምን ያህል መጠን የውስጤ ስለመባሉ ስለምረዳ። የሆነ ሆኖ በንጉሦች ንጉሥ ዳግማዊ አጤ ሚኒሊክ ቤተ መንግሥት  የቅርስ እና የውርስ እድሳትም ላይ „አኖሌን“ ሰርተህ፤ አሰርተህ አንድን አገርን እውቀት ቀርጾ፤ ደንብ ሰርቶ ህግ አርቅቆ፤ ሥልጣኔ ከምኽዋር ጋር አስማምቶ፤ ገሃዳዊ ዓለምን ከመንፈሳዊ ህይወት በቅኔ ዘጉባኤ አዋዶ የሰራን ህዝብ „መጤ፤ የሚኒሊክ ሰፋሪ፤ ስደተኛ“ የሚል ቡድን ህጋዊ እውቅና እዬሰጠህ፤ በራስህ ፈቃድ የህዝብን ይሁንታ ሳታገኝ አገር በቀል ጥበበኛ ኢትዮጵያዊ ሰው ጠፍቶ ከቻይና በመጡ ማህንዲሶች ቅርስን፤ ውርስን፤ ፓተንትን ማስወረር በራሱ ምን ያህል ለቅርስ እና ለውርስ ጥንቁቅ ስለመሆናቸው፤ ምን ያህልም ህዝብ አሳታፊ የሆነ ሰላማዊ ሁኔታ እንደሰጡት ጠቅላይ ሚ/ር አብይ አህመድን ያሳጣቸዋል።  

ህዝብን የሚወክሉ ሞራላዊ ባለሙያ፤ የታሪክ ሰው፤ የጥበብ ሰው፤ የፖለቲካ ሊሂቃን፤ ራሱ ሃላፊነት የተሰጠው የባልሥልጣኑ መ/ቤት ያልመከረበት እድሳት ነው እያደረጉ የሚገኙት። ለዛውም ለምን ብላቸሁ አትጠይቁም አለበት። ይህ የሰላም ኒሻን ካሰጠ ዓለም እራሷ እስፈሪ መሆኗን ያመለክታል።  

የሰላም ሰው … ለምን? ለማን? እንዴት? የት? መቼ? ወደዬት? የማን? ለማን? ስለማን? እነዚህን ተፈጥሯዊ ሰዋዊ መጠይቆች አይፈራም። የሰላም ሰው እርግቤ ነው። ለተጎዱ እርዳታ ለሚያደርግ ሰብ ክብር እንጂ ባሩድ፤ ካቴና፤ አፈና አያዝም። ይህን  በአዲስ አባባ፤ በጌዲኦ ግፍ አይተናል።

4 እንደ ፈረንጆቹ አቆጣጠር  በሸኘነው ሚዚያ ወር የዚህ የትውፊት ጥበቃ ባለስልጣን ዳይሬክተርን አቶ ዮናስ ደስታ የተነሱበት ምክንያት ጠ/ሚር አብይ አህመድ ድርጅቱን ሳያማክሩ የጀመሩት የንጉሦች ንጉስ የዳግማዊ አጤ ሚኒሊክ ቤተ መንግሥት እደሳት ላይ ባቀረቡት ጥያቄ ከሥልጣን ማንሳታቸው በቅርስና በውርስ ጥንቃቄ የመንፈስ ውርርስ ላይ ያላቸውን አቃላይ ምልከታ እና አንባገነናዊ መንፈስ ያሳዩቡት መሆኑ ይህም ለቅርስና ለውርስ ሉላዊ ሰላማዊ ሽልማት አሰጣጥ ላይ ዕዳ ነው። አቶ ዮናስ ደስታ ቤተሰብም አድናቂም አላቸው፤ ተመክሯቸው ደግሞ ሉላዊ ዕውቅና ያገኘ ነው። በዚህ ውስጥ የአንድ ነፍስም ሰላም መታወክ ካለ እንኳንስ የሚሊዮኖች ሰላም እጦት አገር ምድሩን እዬነጠው ሽልማቱ ሚዛን ላይ ሲቀመጥ ለዛውም ጫን ያለ ዕዳ አለበት።

5.    በዩኔስኮ በተመዘገበው በዓለም የማይገኛው የድንቅ የዋሊያ መናህሪያ ባዕት ስሜን ባርክ ቃጠሎ ላይ ጠ/ሚር አብይ አህመድ የወሰዱት አዝጋሚ እርምጃም ሌላው እሳቸውን በዚህ በውርስ እና በቅርስ ሰላማዊ መንፈስ ላይ ያላቸውን አትኩሮት ስስነት፤ ደብዛዘነት፤ ያመለከታል ወይንም የበታችነት ስሜትን ያመለክታል። በዚህ ላይ የተሳማቸውን ሃዘን ራሱ መግለጥ ነበረባቸው ኦፌሻሊ።

እንሰሳትም፤ ጋራ ሸንተረሩም፤ ዜጋ ናቸው ኢትዮጵያዊው በዞጋዊ ካላሰሉት በስተቀር … እራሱ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው መልክምድራዊ አቀማመጥ በጠላትን የተጠለፈ ነው። ይህን መንፈስ መቅርፍ ደግሞ ደፍሮ መጀመር የሚገባው መሪ ሙሴው እሳቸው መሆን ይገባቸው ነበር። ግን አላዬሁም። እንዲያውም እስራኤላውያን  ለእርዳታ በፈጠኑበት ልክ እንኳን እክል አጋጥሞ አንደነበር አዳምጫለሁኝ። የደም ነገር ሆኖ ግን  የእስራኤል ቡድን ታሪካዊው ተልዕኮውን በድል አጣናቋል። ይልቅ በዚህ አጋጣሚ መግለጽ እና ማስታወስ እምሻው ይህን ቀን እና ሌት ድግስ እና ግብር የሚያንበሸብሹትን አቁመው ለዚህ መሰል እሳት አደጋ ሁለት ኤሊኮፍተር ቢገዙበት የተሻለ ነው። ባለሙያም ቢሰለጥንበት። ያው ዕድሉ ከኖረ ለማን እንደሚሰጥ ይታወቃል። ድግሱን ስታሰቡት ኢትዮጵያ የጠላት አገር ሆና ነው የታየዬቸው፤ ሌት እና ቀን ድግስ ... 

6      በሌላ በኩል በአፍሪካ የጥቁሮች ታሪክ ውስጥ ዘመን የማይሽረው ቅርስና ውርስ ደረጃውን የጠበቀው ቤተ መንግሥት የሚገኘው ጎንደር ፋሲል ግንብ ነው። የጥምቁቱ ፋሲለደስም እንዲሁ። ባለፉት ወራት ጠ/ሚር አብይ አህመድ ከአቻቸው ከሱማሌ እና ከኤርትራ መሪ ጋር እዛው ጎንደር ነበሩ። ቅርሱን ለማስጎብኘት ምንም ፍላጎትም ድፈርትም አላሳዩም ነበር። ከዛ የግድብ ሁኔታ ይልቅ ይህ የልቅና ልቅና፤ የጥበብ አብነት ደማቅ ነገር ነበር። መይሳው ሐውልትም ላይ የአበባ ጉንጉን ሊቀመጥ ይገባ ነበር በክብር።  

ሦስት የአፍሪካ መሪዎች እንደዛ ሲገኙ ከዚህ ቀን ውጪ አጋጣሚውን ደግሞ እንደገና ለማግኘት አይቻል ይሆናል፤ ጎንደር ድረስ ሄደው የአፍሪካ የኩራት ምንጭ የሆነው በዩኔስኮ የተመዘገበውን በኢትዮጵያ የቱሪስት ኢንደስትሪም ላይ ከፍተኛ እሰተዋፆ በማድረግ ላይ የሚገኘውን የፋሲል ግንብን ማዬትን፤ ማስጎብኘትን ጠ/ሚር አብይ አህመድ አለፈቀዱም። ለነገሩ አሁንም ስጋት አለኝ በታቀደ ቀውስ አንድ ነገር ይሆናል እያልኩኝ።  

በተጨማሪም እሳቸው ጎንደር ወደ ሦስት ጊዜ ተገኘተዋል በክብር። በተለወጠው ማንነታቸው እያሉ የፋሲል ግንብን አክበረው ለማስከበር ያደረጉት ጥረት ምንም ነው። በዚህም ሲለካ ጠ/ሚር አብይ አህመድ ለቅርስ እና ለውርስ ያላቸውን የመንፈስ አቅም በሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ሚ/ር ከነበረው ጋር ሳነፃፅረው እድገት ማሳዬት ሲገባ ቁልቁል መወረዱን አስተውያለሁኝ። 

7.    በሌላ በኩል የአንድ አገር የሃብት ሃብት ህዝብ ነው። እሳቸው ከመጡ በኋዋላ በህዝብ ተሳትፎ የተገነቡ፤ የቅርስ እና የእምነት ቋቶች 10 አብያተ ክርስትያናት ነደዋል። ዘጠኙ በሱማሌ ክልል፤ አንዱ ደግሞ በስሜን ሸዋ። በእነዚህ ጥንታዊ አብያተ ክርስትያናት መንፈሳዊ ሁነቶች ሁሉ አብረው ነደዋል፤ አብረው ወድመዋል። ሰማዕታት በግፍ ተገድለዋል። መንፈስም አብሮ ከስሏል። መንፈስ ስል በዬትም ቦታ የሚገኝ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ነፍስ አብሮ ነዷል። እሳቸው „ኦርቶዶክስ አገር ማለት ነው“ ብለውን አልነበረምን? ሁላችንም በመንፈስ ነደናል። ቀጣዩም ምን እንደሚሆን አናውቅም ዘመነ ጉዲት፤ ዘመነ ግራኝ ዓመት ድገሙ እያለን ነው ... በሌላ በኩል አንድ መስኪድም እስቴ መንደዱን አዳምጫለሁኝ። ቅርስና ውርስ ሃብትነታቸው የእምነት ብቻ ሳይሆን የህዝብም  የአገርም ናቸው። ሰላም ቢሰከን እኒዚህ ቅርሶች አምልኳዊ ቅዱስ ስፍራዎች በግፍ አይነዱም ነበር። 

እነዚህ ነፍሶች በሰላም አምክንዮ ውስጠት ሲሰፈሩ የአብይ ካቢኔ ሲለካ አሁንም የተሰጠው ሽልማት አቅሙ አይመጥንም ማለት ይቻለኛል። ተጽዕኖ ፈጣሪ ለ100 ቀናት በሚል ሊያስኬድ ይችል ካለሆነ በስተቀር በቅርስ እና በውርስ ክብር፤ በሰላም ጉዳይ፤ ልዕልና ትውፊትን በማስቀጠል አትኩሮት ያላቸውን ዜጎች አክብሮ በመያዝ እረገድ አቅማቸው ቀዝቃዛ ነው። በ አገር ውስጥ መፈናቀል እኮ ኢትዮጵያ የመጀመሪያ ረድፈኛ ናት እኮ? ይህ ክብር ነውን? ይህ ማእረግ ነውን? ይህ ሰላምን ያጬጌዋልን? እእ። 

ሌሎች የፖለቲካ ሊሂቃንም እንዲሁ ናቸው። ከቀደሙት አያት ቅደመ አያቶቻችን የወረሱት እንጥፍጣፊ ጥበባዊ ነገር የላቸውም። እንዲያውም ያ ብርቅ እና ድንቅ የሆነ ትውፊት እንደጠላት ነው የሚያዩት። እነሱ የማድረግ ጥበቡም አቅሙም ስለሌላቸው። ይሻላሉ ብዬ ያስብኳቸው ጠ/ሚር አብይ አህመድም ያው ተዛው ላይ ቸክለው ቀርተዋል። 

ከዚህ ላይ የማይዘለለው የአማራ ተጋድሎ በ10 ከተሞች ባደረገው ህዝባዊ ሰላማዊ ሰልፍ የላሊበላ ውቅር አብያተ ቤተክርስትያናት ጉዳት ያን በሚመለከት በህዝብ ጫና ከፈረንሳይ መንግሥት ጋር የተደረሰበት ስምምነት እና በቀጣይ የተከናወነው መልካም ነገር በውጥን ደረጃ በአውንታዊነት የሚነሳ ነው። ተደሞው የተቀመመበትም ግን የራሱ ዕድምታ አለበት። አትኩሮታቸው የትና በምን ሁኔታ እንደሆነ ከእኔ ጋር ልብ በልብ ተገናኝተናል። ቀረቤታቸው ባለሦስት ፈርጅ ነው። ልብ ያለን ሰወች ይህን እናስተውላለን።   

8.    ሌላው የጣና እንቦጭ አረም ጉዳይም ጣና ካለው ዓለም አቀፍ አስተዋጾ ጋር፤ ብቻ ሳይሆን የቅርስ እና የውርስ ዲካው፤ የገዳማት፤ የብርቅዬ አእውፋት ዝርያ  ሲለካ የነቁጥ ያህል በጠ/ሚር አብይ መንፈስ ውስጥ በቂ ቦታ ያላገኘ ነው። ቀደም ብዬ የገለጽኩት በ10 ከተሞች የአማራ ታገድሎ ህዝባዊ ስልፍን አቅጣጫ ለማስቀዬር የርብን ግድብ ለመመረቅ በሄዱ ጊዜ በቦታው ተገኝተው እንደ ነበር አይቻለሁኝ። ንግግሩ ራሱ መርዘን ያውጃል። ያን ጊዜ ለዛውም ሙሉ ተስፋዬ ባልተሟጠጠበት ሁኔታ ግን ማስመሰልን ማስጠጋት ስለማይችል መንፈሴ ሊያስጠጋው ስላልቻለ ሪፖርቱን አለዘገብኩትም ነበር።አትኩሮቱ የውሃ ልክ ስንተዋወቅ ነው … መከራው ግን እሳቸው ከመጡ የሆነ አይደለም። ያው በተስፋ ለሚኖር አገር እና ህዝብ ግን ከሰፈርም ከዞግም የዘለለ ትኩሮት እንደመሪ እኔ አላዬሁም።  

9.    የሚገርመው ሽልማቱ የተሰጠው በዓለም የፕሬስ ቀን ነው። ይህ ጉራማይሌ ነገር ነው። ይህ ቀን ለምን እንደተፈለገም ይታወቃል። „አንድም የታሰረ ጋዜጠኛ የለም“ የሚለው ትርክት እኔ ነገን ያላዬ ብቻ ሳይሆን፤ ለኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊነት አንከር የሆነው ጋዜጠኛ አቶ እስክንደር ነጋ ነው። ትውልድ በዚህ ዘመን ይተካዋል የማይባል ለእውነት ያደረ አመክንዮ ነው ጋዜጠኛው። የአሱ መንፈስ እግር ከወርች በታሰረበት ሁኔታ በዚህ ቀን ጠ/ሚር አብይ አህመድ ሽልማቱ ሲሰጣቸው ለኢትዮጵያዊ አመክንዮ፤ ለኢትዮጵያዊ ዕውነት ውርደትም ዱላም ነው። በለገጣፎ ለጋዲድ የመታበይ የህዝብ ፍልሰትም ጋዜጠኛ ተደብድቦ አይተናል፤ የጌዶኦ መከራ፤ የሻሸመኔ አሳር ሁሉ በምን ሁኔታ ላይ ተቀብሮ እንዲቀር ሁሉ እንደተደረገ አስተውለናል። ይህ ለግሎባል ሽልማት ካበቃ መቼም ዓለምም እብደቱ እዬጎበኛት ነው ያሰኛል።  

በሌላ በኩል ሊታሰሩ የማይገባቸው „የብዕር አንጋቾች“ በምን ሁኔታ መረጃው ተቀነባብሮ ይታሰሩ እንደነበር ይታወቃል። አፈታታቸው ደግሞ በአማራ እና በኦሮሞ የጸና ተጋድሎ ነው። ይህ ተጋድሎ አብይወለማ ሠራሽም በዛ ምህንድስናም የተከናወነ አልነበረም። አብረው ከመርከቧ ጋር ላለመስመጥ አፈንግጠው ከህወሃት ወጥተው የተሻልን ነን በማለት በጣና ኬኛ ኩዴታ አደናግሬ የነፃነት ትግሉ ተጠልፎ ድሉ ተወረሰ። አሁን የብቻችን ነው ቀደምን ስንታገል ቆይተና እያሉ እዬተረኩልን ነው እነ ኦዴፓ።

የሆነ ሆኖ በዚህ ሂደት ኢህአዴግ እሰረኞችን የፈታው እንዲያውም ጋዜጠኞች የተፈቱት በቀድሞው ጠ/ሚር ሃይለማርያም ደሳለኝ ሥልጣን ላይ በነበሩበት ወቅት ነው። አንድም ቀን ከጋዜጠኞች ጋር ጠ/ሚር አብይ አህመድ ስብሰባ ተቀምጠው አያውቁም። መንፈሳቸው ለማስጠጋት ራሱ ፈቃደኛ አይደለም። ስለምን አመክንዮ ስለሚፈሩ ብቻ።

የአሁኑ የፎቶ ሾፕ ከለስላሳው ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ ጋር ለዩኔስኮ ሽልማት ህትመት ማህተምነት ነው። እውነት የሚፈራ መንፈስ እውነትን መፈለግን ከጥዋቱ አልፈለገም። ቢሆንማ ኑሮ የመጀመሪያ ተግባሩ ከሰብአዊ መብት ተሟጋቾች እና ከጋዜጠኞች አገር ውስጥ መከራን ፍዳን ስቃዬን ካሸነፉ ጀግኖች ጋር የመጀመሪያውን ውይይት ማድረግ የነበረበት ያን ጊዜ ግንቦት 3 ቀን 2010 በሆነ ነበር።

በዚህ ላይ አሁንም አንደበትን ለመዝጋት የፌስ ቡክ ቲምን አገር ውስጥ ድረስ ጠርቶ ሶፍት ዌር የገጠመ ጉዳኛ መንፈስ ነው አሁን የሉላዊው ሰላም ተሸላሚ የሆነው።

የፌስቡክ ተቀናቃኙ /ሚር ሌጋሲ ዶከክብኝ።


10. ሌላው ስለቅርስ እና ውርስ ከተነሳ የአዲስ አበባን ዴሞግራፊ የመለወጥ ሁኔታስ ዩኒስኮ እንዴት ሊያው ይሆን? 


አቶ ለማ መገርሳ አንድ ሚሊዮን ኦሮሞዎችን አዲስ አበባ ለማስፈር ሲባል ሆን ብለው ከሶማሌ ክልል ራሳቸው እንዳፈናቀሏቸው ተናገሩ
February 26, 2019

የጠ/ሚር አብይ ካቢኔ ግማሽ ሚሊዮን ኦሮሞዎችን ከሱማሌ ክልል አምጥቶ አዲስ አባባ እና ዙሪያዋ አስፍሯል። ይህ የትውፊት ዘረፋ፤ ብወዛ እና ስብጥር ዩኔስኮ እንደ ድርጅት እንዴት ይመለከተዋል፤ በምንስ መስፈርት ያዬዋል? ይህ አኮ ንጹህ ዲስክርምኔሽን ነው።

11.         ሌላው የኢትዮ አፍሪካ ዋና መዲና፤ የኢትዮ አፍሪካ መለያ መናህሪያ የሆነችው አዲስ አባባን ከመላ የኢትዮጵያ ህዝብ ባለቤትነት አውጥቶ ለራሳቸው ድርጀት ቅርስና ውርስ ለማድረግ የ29 ዓመት ዕድሜ ላለው ድርጅት ለማውረስ ቀን እና ሌት እዬተጉ ስለመሆናቸው ጠ/ሚር አብይ አህመድ ተገልፆልናል። ይህን አፍሪካን ኢትዮጵያን ቅርስ ውርስ አልባ ለማድረግ የሚሰራን መንፈስ፤ እንዴት ከጉዳይ ሳይጥፍ ዩኒስኮ ሽልማቱን ሊሰጥ አሰበው?የመንፈስ ዝርፊያን ማበረታት ነው ለእኔ።

Ethiopia: ታከለ ኡማ በአዲስ አበባ የኦሮሚያን ልዩ ጥቅም ለማሳካት ቀን ከሌት እየሰሩ መሆኑን አቶ አዲሱ አረጋ ቂጤሳ በአንደበታቸው አረጋግጠዋል፡

12.         ሌላም ላንሳ ሉሲ ድንቅነሽ የዓለም ናት። ሉሲ ድንቅነሽ  የአለም እናት ናት። የሉሲ የድንቅነሽ መናገሻ መዲና ደግሞ አዲስ አባባ ነው። ይህን የ3.5 ሚሊዮን ዓመት ቅርስ ታሪክ መናህሪያ አልባ ለማድረግ የሚሰራ መንፈስ ድርጅቱ ዩኔስኮ ከተቋቋመበት ዓላማ መርህ ጋር አንዴት ታርቆ ነው ይህን ሽልማት ሊሰጥ የቻለው ዩኔስኮ?

አዲስ አበባዬ የልዕልት ሉሲዬ ዬድንቅነሽም ናት!


13.         አዲስ አበባን ለማበልጸግ አንድ ፕሮጀክት የጠ/ሚር አብይ መንፈስ አቅዷል። ለዛ የራት ግብዣ ዝግጅት እንዳለው አዳምጠናል። የራት ግብዣው ጥሪ በሥሟ አዲስ አበባ ማለት ተሰኖት „እንዳያማም ጥራው እንዳይበላም ግፋው“ በሆነ ሁኔታ „ሸገር“ በሚል ነው ጥሪውን ያስተላለፈው፤ ለሉላዊ ዲታዎችን ሳይቀር።
ሉላዊ ዲታዎች ከኒዎርክ ከጄኔባ ቀጥሎ የሉላዊ መንፈስ መቀመጫን የሚያውቋት አዲስ አባባን ሥሟን በፈቃድ ሽሮ „ሸገር“ የሚል የቤት የቅጥል ሥሟን አዲስ ሥያሜ ለሰጠ የቅርስ እና የውርስ አዲስ የፍልሰት ዝንባሌ ያለውን መንፈስ እንዴት አይቶት ነው ይህን ሸልማት ሊሰጥ የደፈረው ድርጅቱ ዩኔስኮ? ሥምም እኮ ቅርስ ውርስ ነው።

14.            አሁን ሳስበው „የሰላም ሚኒስተር“ የታሰበው ይህን ሽልማት አቅዶ ስለመሆኑ ሂደቱን ሳስተውለው እንደዛ ዓይነት መንፈስ አይቸበታለሁኝ። „የሰላም ሚ/ር“ ዕንባ ከማዋጣት በስተቀር ለአንዲትም ቀን ከተመሰረተበት ዕለት ጀምሮ ከሞት፤ ከዋይታ፤ ከሮሮ፤ ከትካዜ፤ ከሃዘን፤ ከጥቁር ልብስ፤ ከቀውስ አልታደገነም። ሥሙን ብቻ ተሸክሞ የጥንቷን ተወዳጇን አዋሳን እንኳን ሰላም ውላ እንድታደር ማድረግ ሳይቻለው እንዴትስ መላ ኢትዮጵያን የሰላም አንባ ማድረግ ይቀለለው? ለዛውም ለግሎባል ሽልማት መብቃት?

"ሽብር በአዋሳ እና የመንግሥት ዝምታ" በጸሐፊ አቶ ዳሞ ጎታሞ ( አቶ መስፍን ማሞ ተሰማ እንደ ተረጎሙት።)


15.         በሁሉሙ አቅጣጫ ሲመዘን ውርስ እና ቅርስ ሰላም ሲኖር ነው። ከ2.5 ሚሊዮን ያለነሰ ህዝብ በጠ/ሚር አብይ አህመድ ዘመን ከቀዬው ሲፈናቀል ውርሱን፤ ቅርሱ፤ የአናኗር ዘይቤውን፤ ሥነ  ልቦናዊ ጽናቱን ትስስሩን፤ ሥልጣኔው ሁሉ ሰላሙን አጥቷል ማለት ነው። ይህ ሰላም ማጣት የሚያሸልም ከሆነ ሸጋ ነው … እንደዛም ከሆነ ከላይ እንደገልጽኩት ፕ/ ሳዳትንም በቀጣይነት መሸለም ነው ዩኔስኮ ያለበት።

16.         የጠ/ሚር አብይ አህመድ በሚመሩት ዘመን በታሪክ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ 5  የኦሮሞ ድርጅቶች በወልና በጋራ ስንት ዓለም አቀፍ የዲፕሎማቲክ ጽ/ቤቶች በሚገኙበት፤ በሚኖሩበት አዲስ አባባ በኪራይ ነው የምትኖሩት ብለው መግለጫ ሲያወጡ፤ ዘግይቶም ድርጅታቸው ኦዴፓ ሲያትምበት፤ የአዲስ አባባ ነዋሪዎች በጽንስ ያሉ ዕንቡጦችን ጨምሮ ከዛችን ዕለት ጀምሮ ስጋትን ጠጥተው፤ ፍርሃትን ጎርሰው መኖርን እዬሸሹት እንዲኖሩ ሲገደዱ ይህ ሰብዕዊነት ከሆነ፤ ይህ ሰላማዊነት ከሆነ፤ ይህ ተፈጥሯዊነት ከሆነ ጥሩ ነው ሽልማቱ …? ? ? ለነገሩ ድሮም ፍላጎታችን ሳናውቀው ወጀብን አምነን ነበር ስንታገል የነበረው፤ ወጀቡም እንዳሻው ወጅቦ ወጀብ አድርጎን ብን ትንን ብለን ቀርተናል።  

17.                 ያው ጠ/ሚር አብይ አህመድ ከሚታወቁበት ዋናው ጉዳይ ዓውዳመትን ተንተርሰው ቃለምህዳን መላክ ነው። የቡራዩ ንጹሃን ደም በከንቱ ሲፈስ ዓውደ ዓመትን ተከትሎ ነበር። ጠ/ሚር አብይ አህመድ ወደ ስልጣን ከመጡ ጀምሮ በደቡብ የጨንበላላን ባዕል አስታኮም ዘግናኝ ሰቆቃን ኢትዮጵያ አስተናግዳለች፤  አብሶ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖትን ተክትሎ ከዋዜማ ሳምንታት ጀምሮ ነው በተደጋጋሚ ሰቆቃ ጠንክሮ እና ከሮ የሚከተለው፤ ስጋትም በገፍ የሚላከው እንዲዚኽው ነው። ቅዱስ ዮሖንስ የጋሞ ኢትዮጵያ ዜጎች ያን ያህል ሲታረዱ የጠ/ሚር አብይ አህመድ ካቢኔ ነበር።

ለነዛ ለተጎዱት እንኳን እርዳታ ያደረጉ የአዲስ አባባ ወጣቶች 5 ሰማዕታት በበቀል ደማቸው ባደባባይ አፍሷል፤ ከአንድ ሺህ በላይ በጦላይ አሳራቸውን አይተዋል?ግንቦት 7 አሸባሪ እንዳይል ማጣፊያው ሲያጥረው ፍልስጤም ምንትሶ ብሎ መቼም ውሸት አያልቅበትም እና።

ሰሞኑንም በአማራ እና በጉምዝ ግጭቱም ያው ዜጎችን ነፍስ አሳጥቷል፤ የጠ/ሚር አብይ አህመድ መንፈስ ለቅርስ እና ለውርስ አሳቢ ከሆነ፤ ለሰላም ተቆርቋሪ ከሆነ ቅዱስ ዮሖንስ፤ መስቀል፤ ልደትን፤ ትንሳኤም፤ እኮ ለቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አማንያ ብቻ ሳይሆን የአለም ውርስና ቅርስ የሰላም መሰረት ናቸው። ግን ያዬነው እነዚህ ዓውዳመቶች ሁሉ ጠ/ሚር አብይ አህመድ ሥልጣን ከያዙ ጀምሮ የደም ሰሞናት ሁነው ነው … እና ይህ ለዩኔስኮ የሰላም ሽልማት ተመችቶታል ማለት ነው በትርጉም ሲቃና?  

እኔ እውነት ብናገር ለ100 ቀናቱ የመሪነት፤ የተጽዕኖ ፈጣሪነት፤ ያታታሪነት፤ የንግግር አዋቂነት ብለን ሸለምነው ቢባል እስማማለሁኝ። ከዚህ ባለፈ ግን ጉለሌ ላይ ተቀምጦ የንጹሓን ነፍስን በእንባ ጎርፍ ለሚያጥበው መንፈስ ጠበቃ፤ አጋር፤ አጋዢ፤ የሎጅስተክስ አቅራቢ ለሆነ ልዑላዊነት ለተዳፈረ መንፈስ በአለም አደባባይ በህግ ቢያስጠይቀው እንጂ ለሽልማት የሚያበቃ ሆኖ አለገኘሁትም። ዴሞግራፊው ራሱ በቂ ነው።

በዬመስሪያ ቤቱ ያለው የስጋት ድባብ ራሱ ሌላ ብራና ነው። አዬር መንገድ፤ ገቢዎች ሚ/ር፤ ጠ/ሚር ቢሮ፤ ከንቲባ ቢሮ፤ አቃቢ ህግ፤ መከላከያ፤ አዬር ሃይል፤ ብሮድ ካስት … ምን ዴሞግራፊ ያልዞረበት ቢቆጠር ይሻላል … ሥነ ጥበብ ተካታይ ነው።

አሁን የመንግሥት ሚዲያ ነጻ ነው ተብሎ ይሆን ሽልማቱ? ምነው ሰው ተገድሎ ተዝቅዝቆ ሲሰቀል ሻሸመኔ ላይ አልዘገበ የብሮድ ካስት ቲም? ምነው ከህግ በላይ ስለሆኑ ግለሰቦች እውነቱን አይነገረንም በካቴና ተጥርንፎ ቅልብ እዬተባለ እያቃሰት፤ እያቀተተ የሚገኘው የመንግሥት ሚዲያ በኦዴፓ የሚሾረው … የሚኮረኮመው የመንግሥት ሚዲያ … >?

እኔ የእሾኽ አክሊል አድርጌ ነው የወሰድኩት። ኦሮሞ አገር መምራት አይችልም ለሚለው ሥነ - ልቦናዊ የውስጥ ህመማዊ ጥቃት አጥሚት፤ ሜድቴሽን ሊሆን ይችላል፤ በሉላዊ በመንፈስ አቅሙ፤ በባልዩ አቅሙ፤ በትሩፋት አቅሙ፤ የሁላችን ኩራት አድርገን በመቀበል አቅሙ ግን የማይመጥን ሽልማት ነው። ለሳቸውም ይጎረብጣቸዋል። ለታሰሩት ጋዜጠኞች፤ የሰብዕዊ መብት ተሟጋቾች፤ ለጠፋው ነፍስ ሁሉ ተጠያቂነት ሲታሰብ ደግሞ ቋቅ ነው። ብቻ ለዩኔስኮ „አለባብሰው ቢያርሱት ባረም ይመለሱ“ ነው የሆነው …  አይዘልቅም አይቆይም። ጎርፍ፤ ጤዛ፤ ሳሙና አረፋ ነው …

·       የቁርጥ።

የዘፍጥረትን የጣሰ ማንፌስቶ በህዝብ አደባባይ እዬተሰበከ፤ ግን በህግ ተጠያቂ አይደለም። ስለምን ዘመን ሰጥ የንጉሶች ዘር ስለሆነ።

ነጋዴ በኦሮምኛ ካልሸጠ አትግዙ – አቶ በቀለ ገርባ
March 23, 2019

ህዝብ እርስ በእርሱ እንዲተላለቅ ሚዲያ ተከፍቶ እየታወጀ ነው፤ ይህም አይጠዬቅም፤ ከምርጥ ዘር መፈጠር እንዲህ ያንደላቃል ...

ህዝባችን ከተቆርቃሪ መሳይ ቤንዚን አርከፍካፊዎች ፌክ ዜና እራሱን ይጠብቅ- ከንጹሃን እልቂት ለማትረፍ መፍጨርጨር እጅግ ያሳፍራል ያስጠይቃልም
May 3, 2019
አቶ ወንድወሰን ተክሉ ( ጋዜጠኛ እና ፖለቲከኛ)
ዴሞግራፊ ፍልስፍና በይፋ እና በአደባባይ እዬተከወነ፤ ለአንድ ብሄር የበላይነት እና አንድነት ተትግቶ እዬተሰራ „ሰላም“ የሚለውን ቃል የያዘ ሉላዊ ሽልማት ኢትዮጵያ ስለፍትህ፤ ስለ እውነት፤ ስለ አምክንዮ የሚታገል ልጅ ነጥፎባታል ዓይነት ነው ለእኔ። ንቀትም ነው። ይህን ሳስብ እርግብ ደሟም፤ ጸጉሯም፤ ልቧም ክስል ብሎ ከስሎ፤ አሮ የተፈጠረ ያህል ይሰማኛል።

እውነት ለመናገር ለሳቸውም ለጠ/ሚር አብይ አህመድም አዲስ ማጭድ ነው። ለማይመጥነው እውነት ሽልማት እርግማን እንጂ ምርቃን ስላልሆነ። አልመጥንም እኮ ይባላል ህሊናው ቢኖር … ያን ቢያደርጉ ጠ/ሚር አብይ አህመድ ነበር እኔ እውነትን የደፈሩ ጀግና እላቸው የነበረው። ሽልማቱም ይገባቸዋል ብዬ እሞግትም ነበር። 

እንደሳቸው ግን እውነትን ፈሪ የለም። ጀግኖች ሲይዟቸው እኮ ቀጥ ነው ያሉት እንደባንዴራ … የባልደራስ ንቅናቄ እና የአማራ ህዝብ የማንነት ተጋድሎን ለማፈን የተነሱበት መንገድ እውነት ጋር እርቀ ሰላም ለማወረድ ያላቸውን አቅም አሳይቶኛል። 

በዚህ ውስጥ ኢትዮጵያዊነት አቅማቸውም በራሱ ውስጥ አለመኖሩን አስተውዬበታለሁኝ። ወላዋይነት እና ለውሳኔ ቁርጠኝነትንም አንሷቸው በብዙ ሁኔታ ተለምክቻለሁኝ። ኢትዮጵያዊነት እሳቸው ይሸሹታል እሱ ደግሞ ይከተላቸዋል፤ ሽልማቱ እኮ የኢትዮጵያ ጠ/ሚር ተብለው አይደል? 

የአማራን ህዝብ ያነጣጠሩበት፤ ሰላሙን የነሱበት መሰረታዊ ምክንያት ኢትዮጵያዊነትን ሸሽት ነው። እሱን ሸሽቶ ከብሮ መኖር ደግሞ ባያሰቡት ነው የሚሻላቸው።  

ባለው ውስጥ ለመዝለቅ የተሳነው መንፈስ እውነትን መድፈር በተሳናው ቁጥር በሽልማት መንበሽበሽ እርግማን ያስውጣል እሰገድዶ፤ የለበጣው ምርቃት ደግሞ ክብርን ያሳጣል፤ ያሰጣል፤ ያነጣል ፍቀት ስለሆነ። የተከበሩት እሳቸው ዛሬ ሳይሆን፤ ሲሸለሙ ሳይሆን መጋቢት 24 ቀን ያደረጉት ንግግር ዕለት ነው። ቀድመን ያከብርናቸው ልንኖርም እንችላለን። ከዛ በመለስ እሳቸው እና እኛ፤ እሳቸው እና እውነት፤ እሳቸውና ለሰባዕዊ መብት ተሟጋችነት አራባ እና ቆቦ ነው። ደፍረው ስለ ጀግኖች አይመሰክሩም። 

ደፍረው ስለሚሞግቷቸው ነፍሶች አይመሰክሩም። ደፍረው ስለ ኢትዮ አፍሪካ ተቆርቋሪ ኢትዮጵውያን ሊሂቃን አይተነፈሱም። የት ሊያድሩ? ያው ዘንቦ ተባርቆ ጠብታ ከተገኜ በዛ ላይ ሲስሉ ሲኮሉ አዳምጠናል። ሥልጣኑም ሹመቱም በዚኽው ልክ ነው። ቀረቤት መጎራረሱም ያው በዛው እሱ በእሱ። 

·       አንድ ደፋር ጹሑፍ ዘሃበሻ ላይ አግኝቻለሁኝ፤
የጠቅላይ ሚንስትሩየሰላምሽልማት እና የምዕራባውያን ሴራበተመስገን  አስጨነቅ  ዘለቀ

ውድ ጸሐፊ አቶ ተመስገን አስጨነቅ ምዕራባውያን ብቻ ሳይሆኑ እኛም ብዙ ሰርተንበታል ጠ/ሚር አብይ አህመድ ሳይንስ እና ቴክኖጂ ሚ/ር በነበሩ ጊዜ የነበራቸው ራዕይ ጤናም ስለነበር። በማይንድ ሴትም ተሳትፏቸው ኢ - ሰብዕዊ ህፃጽ ይኖርባቸዋል የሚል ግምት አልነበረኝም እኔ በግሌ። አገራዊ፤ አህጉራዊ ራዕያቸው ብቻ ሳይሆን ሰዋዊ ምልከታቸውም አጓጊ ነበር። አብሶ በሌብነት ላይ የነበራቸው አቋም ይናፍቅ ነበር? ይህ ሽልማትስ ከታሪክ ሌብነት ጋር? ሆኖ ከመገኘት ጋር ምን እና ምን ሆነ ይሆን? ያው ሙስና በሁሉም ዘርፍ ... ይለካ እንደማለት ... 

ብቻ እሳቸው እንደሉት አዋሳ የህዝብ ለህዝብ ስብሰባ ላይ ወንበር ሥልጣን የሚረጋቸውን ካለማወቅ ወይንም የቆዬ የቋሳ ድፍድፍ እያገረሸባቸው ብቻ ባልተወቀ ሁኔታ እሳቸው ሰብዕናቸውን በተቀበልንበት ልክ እሳቸውም ነኝ አይሉም እኛም ናቸው ብለን ለመቀበል አንደፍርም አብሶ እኔ።

አሁን ላይ ገፃቸውን ደፍሬ ማዬትም፤ ድምጻቸውን ፈቅጄ ለመስማትም ድርቅ የመታው ሆኗል። ሙግት ራሱ ብናግረው ያዳምጠኛል፤ የጎበጠ ያቃናል፤ ይሻላል የሚባል መንፈስ ሲኖር ነው የእኔ የምትሉትን በድፍረት መተቸትም፤ መውቀስም የሚጥመው። ለአንድ ኦሮሞ ለሚታገል፤ ትምህክቱም በዛ ላይ ለሚንሳፋፍ ጠ/ሚር ሙግትም፤ አቤቱታም፤  የአቅምቲን የመንፈስ ሃሳብም ማቅረብ ከጅልነት በታች ነው። ራሳቸውን ብቻም ነው ማድመጥን የሚወዱት። 

ለዛውም እኮ እነሱ አይደለም ያን ያህል የወርቅ አክሊል የደፋላቸው። ሰብዕናቸውን የማበሻ ጨርቅ ያህል እንኳን ክብር ያልሰጡ ነፍሶች ናቸው አሁን የሳቸው ቅርበኛ ፍቅረኛ። ሌላው ደግሞ ተሳዳጅ፤ ያልተደመረ ምንትሶ እዬተባለ ፍዳውን ያያል፤ የአማራ ክልል እና የአዲስ አባባ ህዝብ ፍዳው „ባጎረስኩ እጄን ተነከስኩ ነው“ የሆነው ለይሉንታ ቢሱ ቲም ለማ …  
ጠ/ሚር አብይ አህመድ ብዙ ሰው ግድፈት እንዲፊጽም ሁሉ ምክንያት ሆነዋል። ሃሳዊ መሲህነት ሚናን ነው የተጫወቱት። ስንት ዓይነት አብይ እንደለን ግራ እስኪገባን ድረስ ዥንጉርጉር አደርገውናል። ስንት ታላላቅ የአገር ጉልላቶች የሰጡት ምስክርነት ሁሉ ውሃ የበላው ቅል ነው ያደረጉት። 

ከምን ዓይነት ንጥረ ነገር ነፍሳቸው እንደተሰራ ራሱ መመርመር አለበት። ስልበኛውን፤ ምርኮኛውን ሁሉ ለሽ አድርጎ እንዲህ ውስጡን ጎርጉሮ ያስነጠፈ … ነፍስ ከምን ተሰራህ ያሰኛል። ወትሮ ወትሮ ተጠራጣሪነተቻን ብዙ ነበር በሳቸው ግን አብዛኛው ህዝብ ተስፋ አድራጊ ነበር እኔን ጨምሮ … ግን አመዱን።

እኔ የፌስ ቡክን ቲም ኢትዮጵያ ድረስ ጋብዘው፤ ያንም እንደ ጀግንነት ሲነግሩን አዲስ ሶፍት ዌር ገጥመው ለመላክ ካደረጉት ምስጥነት በላይ ሌላ ምንም ማስተባበያ ለህሊናዬ አቅርቤ ተስፋ ለማድረግ አልሻም። ጸረ አብስኒያ ፍልስፍናቸው እና ዴሞግራፊውንም ሳስበው፤ ሰላምን በማሳጣት የትኛው ማህበረሰብ ላይ አቅደው እዬተጉ ስለመሆኑ በግራ ቀኝ ወጥረው መያዛቸውንም ከልብ እያስተዋልኩት ነው። ይህንን የዛሬ ዓመት ግንቦት 5 ቀን አብይ ሆይ እኔም ዜጋ ከሆንኩ ብዬ ሞግቻቸዋለሁኝ።

የሆነ ሆኑ  … የዓለምን የመናገር ሥልጣኔ ለማገታት ለተጋ የሰላም ሽልማት በሉላዊው የፕሬስ ቀን? ቅብጥርሶ ምንትርሶ እንቶ ፈንቶ ስለሆነ ነገር … 

የፌስቡክ ተቀናቃኙ /ሚር ሌጋሲ ዶከክብኝ።

·       በእንቦቀቅላው የነቀዘው ምህንድስና ...

አንድ የሰላም ልዑል መንፈስ ምን ያህል ውስጥ ለውስጥ ነቀዝ ስለማብቀሉ ደግሞ ለዛውም ሴት ሚ/ር በሆነበት አንባ የሆነው ይህን አዳምጡ ውዶቼ … ለዚህ ነው ጠ/ሚር አብይ አህመድ እዬተጉ ያሉት በመስከረሙ የኦዴፓ ጉባኤያቸው ለኦሮሞ አንድነት እታገላለሁ ቃለ ምህዳን ስለመሆኑ ዝርግ ሆኖ እያዬነው ነው። እና እኛ ምን ባዮች ነን? ስጋጃ አንጣፊዎች? ቀለም ቀቢዎች? ወጥ ሰሪዎች? ሥራ ቤቶች? እኮ ምን ባዮች ነን?

Ethiopia -የገቢዎች ሚኒስተር በአንድ ወገን ተይዟል- ክፍል 2

Published on Apr 5, 2019

·       ክወና።

ውዶቼ በአክብሮት ከመሰናበቴ በፊት ቀንበጥ ብሎግ አንዳንድ ነገሮችን በድምጽ እዬሠራች ማስቀመጥ ስለሚኖርባት ይህንም ጎብኝት አድርጉ የቻላችሁ ሳብስክራይብ አድርጉት … ትንሽ መድከም አሻኝ እና በድምጽም አልፎ አልፎ መስራትን ወደድኩት።


ታሪክን በትውስት ሳይሆን በእውነት ማዕቀፍ ማስቀመጥ ያስፈልጋል ሌላው ሰው እንደ ዋዛ አይቶት ሊሆን ይችላል እኔ ግን የዘፍጥረትን ተፈጥሮ በድፍረት የደረመሰው የአቶ በቀለ ገርባ ማንፌስቶ እና የቲም ለማ የዴሞግራፊ ፍልስፍና ሚዛኑን ለማስጠበቅ የግድ ጠንክረን መስራት እንዳለብን አምናለሁኝ።

ቢያንስ የህዝብ አስተሳሰብ ሚዛኑን እንዲጠብቅ ማድረግ። ለዛሬ ሳይሆን ዕድል ሳይሰጣቸው ያላፋቸውን ታሪክን እንዳሻቸው በፎቶ ሾፕ ለሚሰሩ ምስኪኖች ሚዛን ለማስጠበቅ መትጋት ይኖርበናል። በግንባሩ እንጂ በጀርባው የአንቦን ቀልሃ የማያስተናግድ መሪ እስክናገኝ ድረስ።  

ግርባው ብአዴን ራሱን በጥላሁን ግዛው ፍልስፍና ሲንድ እንደኖረው አሁንም በዴሞግራፊ ፍልስፍን እያፈረሰው ነው ያለው ራሱን በራሱ። ቅርስ እና ውርስ ከቤተ መንግሥት እድሳት ጋር ቡርቦራው፤ ሽርሸራው ባለቤት አልባ ሆኖ እዬተከወነ ነው። በተረፈ የቅኖች አቅማችን አምላካችን ነውና መጸለይም ጥሩ ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ሰላምን ለማምጣት፣ ለማስጠበቅና ለማቆየት ላደረጉት አስተዋፅኦ የዩኔስኮ ፌሊኒክስ ሃፌፍ- ቦኒይ የሰላም ሽልማት
May 2, 2019 | Filed under: የዕለቱ ዜናዎች | Posted by: -ሐበሻ



ዕዳ ለባለዳው እውነት ለፈጣሪው!
ትእግስት ሲያልቅ ፍቅር ይሰደዳል
ፍቅር ሲያልቅም ትእግስት ይሰደዳል።

ኑሩልኝ የኔዎቹ። ማለፊያ ሰንበት።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።