የጨረቃ ቤት {ብልጽግና} የመርኽ ጥሰት እና ልብዱ ስብሰባ።
እንኳን ወደ ቀንበጥ ብሎግ በሰላም መጡልኝ። „ተግሳጽን የሚወድ ዕውቀትን ይወዳል።“ ምሳሌ ምዕራፍ 12 ቁጥር 1 የጨረቃ ቤት የመርኽ ጥሰት እና ልብዱ ስ ብሰ ባ ። ሥርጉተ © ሥላሴ Sergute © Selassie ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ። 04.01.2020 እፍታ። ውዶቼ ይህ የዕለቱ መከወኛ ጹሑፌ ነው። የጨረቃ ቤት {ብልጽግና ፓርቲ?}ተመሰረትኩ ካለበት ጀምሮ ዝንፈቱን እንዲያስተካክል በፌስ ቡኬ ስወተውት ባጀሁኝ። ከዛ ሰሚ ሳይገኝ እንዲያውም ምርጫ ቦርድ ዕውቅና ሰጠው የሚል ዜና መጣ። ይህ ጫን ያለ ችግር ነው ብዬላችሁ እኔ እህታችሁ „የዲሞክራሲ ጽንሰት ውርጃ“ ዘለግ ያለ ሙግት ለምርጫ ቦርድ አቀርብኵኝ። መርኽ መጣሱ ብቻ ሳይሆን የአገር መርኽ የሆነ ዕቅድ ከመሰረታዊ ሰነዶች ከፕሮግራሙ እና ከደንቡ ተነጥሎ ጸደቀ አልሰማነም። እረቂቅም አለ አላዳመጥነም። ያው ሁለቱ መሰረታዊ ሰነዶች ህገ ወጥ በሆነም መንገድ ጸደቁ መባሉ እራሱ ሥርዓት ያልጠበቀ ቢሆንም እቅድ መዘለሉ ደግሞ የሚገርም ዓይነት ግድፈት ነበር። የሚገርማችሁ የአገር ውስጥ እና የውጭ አገር ሚዲያዎችም፤ ጋዜጠኞች፤ ተንታኞች የኢኮኖሚ ሊሂቃን እራሱ ጭራሽ ይህን ግድፈት ባሊህ አላሉትም ነበር። የሚገርም እኮ ነው። ዕቅድ አልባ በምን ስሌት ፓርቲ ተብሎ ዕውቅና እንደተሰጠው ግራ ይገባችኋል። ያው የቤተ ዘመድ ውሎ ስለሆነ ነው እንጂ። የሀነ ሆኖ ዘሃበሻ ይባረክ ስላተመው ጹሑፌን አሁን ሳምንት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ የኢህዴግ ነበር ሥ/አኮሜት ህወሃትን ሳይጨምር ተሰበሰበ ይኸውን ዕቅድ ሊያጸድቅ። ይህም ቢሆን ወደል ግድፈት ነው። ግን መኖሩ ቢያንስ ጥሩ ነገር ነው። ለማረም መሰናዳታቸውም ሌላ...