ሽብር እና ጭካኔ እስከ መቼ???! #ንጹሁ ፍጡር ገበሬ በጅምላ ለምን በባዕቱ ይፈጃልን? ለምን? #አብረን #እናምጥ!
ሽብር እና ጭካኔ እስከ መቼ???! #ንጹሁ ፍጡር ገበሬ በጅምላ ለምን በባዕቱ ይፈጃልን? ለምን? #አብረን #እናምጥ ! "የቤትህ ቅናት በላኝ።" ዛሬ ዕለተ ሃሙስ የቀን ቅዱስ ከመሆኑም በላይ እኔም መላ ቤተሰቤም ተወልደን ባደግንበት በዓት በ፵፬ቱ እቴጌ ጎንደር #የአዳም ቀን ይባላል። በስቅለቱ ልጆች ሆሆ ምሻምሾ ብለው ያጠራቀሙት ዱቄት ዘይት እና ድልህ ተሰናድቶ በወል ይመገባሉ። ዛሬ ደግሞ ስለ #ስለአዳም ተብሎ ልጆች ለምነው በሚሰበስቡት ቅቤ፤ ቋንጣ፤ እንጀራ ተሰርቶ ወጡ በጋራ ልጆች ይበላሉ። ሁለቱም ትውፊት ጥልቅ ትርጉም ያለው መከራን እና ደስታን በጋራ ማስተናገድን ዕውቅና የሚሰጥ ክስተት ነው። እኔ ዛሬ ይህን ከባድ ሃዘን ባልዘግብ በወደድኩኝ። ግን ባለመታደል ምዕራፍ ፲፮ ለመጀመር ዳርዳር ስል ያገኜሁት ውስጤን የነካ ሃዘን ማቅረብ የግድ ሆነ በዕለተ አዳም ቅዱስ ቀን። የማከብራችሁ የአገሬ ልጆች እንዴት ናችሁልኝ። ብኖርም ባልኖርም ተግባሬን አክብራችሁ ለምትልኩልኝ ሐዋርያዊ መልዕክቶቻችሁ እጅግ አመሰግናለሁኝ። ኑሩልኝ። አሜን። ባልነበርኩበት ወቅትም ሼር ያደረጋችሁልኝ ውዶቼ ተባረኩልኝ። አሜን። የዓመቱ ፋሲካ፤ የሁዳዴ ፆም መፍቻ ለዛውም በንጹኃን ገበሬ ላይ የተፈፀመው ሰቅጣጭ ጭካኔ #ውረድ እና ፍረድን ያጠይቃል። ገበሬን? ጉሮሮን ለምን ይጨከንበታል??? ከጥቂት ደቂቃወች በፊት የሉዓላዊ ሚዲያ ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ሲሳይ አጌና የሰጠውን ማብራሪያ አዳመጥኩኝ። በተጨማሪም ከሥር የተሰጡ አስተያዬቶችንም በተወሰነ ደረጃ አነበብኩኝ። ወጥ ዕይታ ወጥ አቀራረብ ነበረው። መቅደም የሚገባው #መደንገጥ ፤ እንደሰው #መጨነቅ አብሮ ማዘን ሲገባ፦ ለድርጊቱ አፈፃፀም ፋክቱን በውስጥነት ማፈላለግ ሲገባ፦ ያ...