ልጥፎች
“የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሄርን መፍራት ነው” {ከጸሐፊ እና ከተርጓሚ አቶ መስፍን ማሞ}
- አገናኝ አግኝ
- ፌስቡክ
- X
- ኢሜይል
- ሌሎች መተግበሪያዎች
“እንኳን ወደ ቀንበጥ ብሎ በሰላም መጡልኝ።” “የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሄርን መፍራት ነው” ከጸሐፊ እና ከተርጓሚ አቶ መስፍን ማሞ ተሰማ ሠላም ለናንተ ይሁን! ኢትዮጵያ በዘመናት ታሪኳ እስከ 1966 ዓ / ም መጨረሻ ድረስ የመሯትና የህዝቧም እረኛ ሆነው ፥ እንደ ቀስተ ደመና ቀለማት ህብር ውበት ሁሉ፣ የተለያየ ባህል ባለቤትና ቋንቋ ተናጋሪ ህዝቧን በአንድ መሶብ አሰባስበው፣ መተሳሰብ መዋለድ ህብረትና ሀገራዊ ማንነት ተዋህደውና አምረው እንዲሰርፅና እንዲኖር ያስቻሉት እኒያ መሪዎቿ ፈሪሃ እግዚአብሄር ያደረባቸው ነበሩ። የክርስትና እና የእስልምና ሀይማኖት አባቶችም ለእምነቱ ህግጋት ተገዢ ፈጣሪያቸውንና አማንያንን አገልጋይ ነበሩ። ፈጣሪም ከእነርሱ ጋር ነበረ። የቀደሙት የኢትዮጵያ መሪዎች በፈሪሃ እግዚአብሄር እየተመሩ የህዝባቸው መልካም እረኛ ሆነውና በሀይማኖቶችም አከባብረውና አስማምተው ህዝባቸውን አኖሩ። ኢትዮጵያን እንደ ሀገር አቆሙ። ከጠላት ጠበቁ። የኢትዮጵያ ህዝብም ልበ ቅን፣ በራሱ ላይ ሊያደርጉበት የማይፈልገውን በጎረቤቱና በሌሎች ወገኖቹ ላይ የማያደርግ፣ ፈሪሃ እግዚአብሄር ያደረበት ሆኖ ተባብሮና ተሰባስቦ ኖረ። ለዘመናት የተገነባው ይህ ሀገራዊ / ኢትዮጵያዊ እሴት በዘመነ ደርግ ፈተና ገጠመው። ፈተናው ፖለቲካዊና መንፈሳዊ ነበር እንጂ ዘርን ተገን አድርጎ ሀገራዊና ኢትዮጵያዊ ማንነትን የዳጠ፣ የጨፈለቀ፣ ያዋረደና ኢትዮጵያዊነትን ...
አሉታዊው የዴሞግራፊ ፍልስፍና የበቀል ፍልስፍና ነው። {የወግ ገበታ}
- አገናኝ አግኝ
- ፌስቡክ
- X
- ኢሜይል
- ሌሎች መተግበሪያዎች
እንኳን ወደ ቀንበጥ ብሎግ በደህና መጡልኝ የውጥንቅጥወጥ ውጥን። አሉታዊው የዴሞግራፊ ፍልስፍና የበቀል ፍልስፍና ነው። ኢትዮጵያ ውስጥ የተወጠነው፤ ተወጥኖም ተግባር ላይ እዬዋለ የሚገኘው ጸረ ሰው፤ ጸረ -ሥነ -መኖርም ነው ጸረ ሥነ አዕምሮም ነው። ክፍል ሁለት። „ የደከሙት ን እጆች አበርቱ፤ የላሉትን ም ጒልበቶች አጽኑ። “ ትንቢተ ኢሳያስ ምዕራፍ ፴፭ ቁጥር ፫ ዝግጅት ከሥርጉተ © ሥላሴ Sergute©Selassie 06.06.2019 ከእመ ዝምታ ሲዊዘርላንድ። ተስፋ ሂደት፣ ተስፋ ዘመን፣ ተስፋ አድዮ ነው። · እፍታ። የተከበራችሁ የቀንበጥ ብሎግ ታዳሚዎቼ እንዴት ናችሁ? ዛሬ ቪንቲ ፏ ፍንትው ብላለች። በእለቱ አሉታዊውን የኦዴፓን የዴሞግራፊ ፍልስፍና በቀጣይነት እናያለን … እርግጥ በሁለት እርእስ ነው የመጣሁት። አውራው እርሰ ጉዳይ ከማጠናከሪያው እርስ ጋር የተዋደደ ነው። መስተጋብራዊ ውህደቱ በሚስጢር ሳይሆን በይፋዊ ጉባኤ ነው። አሁን ኢትዮጵያ ውስጥ እንደምናዬው አውራው ድርጅት ኦዴፓ እና የዴያስፖራው አውራ ድርጅት የቀሰተደመና ወራሽ ግንቦት 7 አብረው በትብብር እንደሚሰሩት። ትብብር ነው ያለኩት ቅኔዎ ቼ?ተቀናቃኝ/ ተቃዋሚ/ ተፎካካሪ አልወጣኝም። ያ ክስመት ነው ትንት እንበለው ይሆን። ትንት ይሻላል ... ትናት አሰኝቶት መጪ ብሏል ... እቴ እነሱ ግጥግጡን እያስነኩት ነው ስላችሁ ...፧...