ከሳጥናኤል በላይ እኔ ሳጥናኤል ልሁን ያሉት ጠቅላይ ሚኒስተር ሄሮድስ አብይ አህመድ አሊን ሰብዕና በጨረፍታ
ከሳጥናኤል በላይ እኔ ሳጥናኤል ልሁን ያሉት ጠቅላይ ሚኒስተር ሄሮድስ አብይ አህመድ አሊን ሰብዕና በጨረፍታ። "እግዚአብሄር ቤትን ካልሰራ ሠራተኞች በከንቱ ይደክማሉ እግዚአብሄር ከተማን ካልጠበቀ ጠባቂ በከንቱ ይተጋል።" መዝሙር ፻፶፮ (፻፳፯ ) ቁጥር ፩ ዛሬ በውል እንቅልፍ ይወስደኛል ብዬ አስቤ ነበር። ያው #ዕለተ #ሲቃ ነበር። ሌሊቱም መብራቴን ቦግ አድርጌ ስገላበጥ ነጋ። ዬተስፋ ትጉህ ስለሆንኩኝ አንተን ተስፋ ያድርግ ያ ዬዕንባ ዋናተኛ ህዝቤ አልኩኝ። ለአማካሪዬ ስለሆነው ነገር ሁሉ ጽፌላት ስለነበር "ሚዲያወች ስለምን ዝም አሉ" ብላ ጽፋልኝ ስለነበር እኩለ ሌሊት አልፎ ዬአልጀዚራን ሊንክ ላኩላት። ሲነጋ መልስ ጽፋልኝ እንደሆን ብዬ ሳይ "ዬአውሮፓወችን ሚዲያወች ማለቴ ነው ብላ የቱርክ እና የሶርያ ዬመሬት መራድ የዜናውን ጉልበት አነፃጽራ "የተረሳ ህዝብ ነው ብላ ፃፈችልኝ። " አወን ዬኢትዮጵያ ህዝብ ጨለማ ውስጥ ነው።መፍቻው ይከብዳል ብዬ መለስኩላት። ዛሬ ይህን እያወጣሁ እያወረድኩኝ ዘመን ስለሰጣቸው ዘመናይ የኢትዮጵያ መሪ እና መጪው ጊዜን አሰብኩት። ከቀደመው #በከፋ ሁኔታ ከበደኝ። ተቋማትን ውጠዋል። ያልተመቻቸውን በጥፊም በእርግጫም ብለው አምክነዋል። ሌላም ይነሳል ብለው አያስቡም። የቅድስት ተዋህዶ ነገር ለእሳቸው ዱብ ዕዳ ነበር። ሚስጢሩ ለተገለጠለት እትዮጵያን እንደገና ሠርታታለች። መንፈሷን ዬተዘረፈውን በረቂቅ አቅሟ አስመልሳለች። ይህ አደናብሯቸዋል። ፋከራቸው ድንፋታቸው የዓዋጅ፤ ዬመግለጫ፤ የጡንቻ ትርዒት ሲያሳዩን ሰንብተዋል። ዬሆነ ሆኖ ዘመናቸውን ሙሉ እንዴት እንደ ተሰናዱ? ሲፈርሱ እና ሲሰሩ የባጁት የኢትዮጵያ ፖለቲከኞች እንደምን አሳልፈው ህዝባችን ለጭካኔ እንደሰጡት መዘንኩት...