ከሳጥናኤል በላይ እኔ ሳጥናኤል ልሁን ያሉት ጠቅላይ ሚኒስተር ሄሮድስ አብይ አህመድ አሊን ሰብዕና በጨረፍታ
ከሳጥናኤል በላይ እኔ ሳጥናኤል ልሁን ያሉት ጠቅላይ ሚኒስተር ሄሮድስ አብይ አህመድ አሊን ሰብዕና በጨረፍታ።
ዛሬ በውል እንቅልፍ ይወስደኛል ብዬ አስቤ ነበር። ያው #ዕለተ #ሲቃ ነበር። ሌሊቱም መብራቴን ቦግ አድርጌ ስገላበጥ ነጋ። ዬተስፋ ትጉህ ስለሆንኩኝ አንተን ተስፋ ያድርግ ያ ዬዕንባ ዋናተኛ ህዝቤ አልኩኝ። ለአማካሪዬ ስለሆነው ነገር ሁሉ ጽፌላት ስለነበር "ሚዲያወች ስለምን ዝም አሉ" ብላ ጽፋልኝ ስለነበር እኩለ ሌሊት አልፎ ዬአልጀዚራን ሊንክ ላኩላት። ሲነጋ መልስ ጽፋልኝ እንደሆን ብዬ ሳይ "ዬአውሮፓወችን ሚዲያወች ማለቴ ነው ብላ የቱርክ እና የሶርያ ዬመሬት መራድ የዜናውን ጉልበት አነፃጽራ "የተረሳ ህዝብ ነው ብላ ፃፈችልኝ። " አወን ዬኢትዮጵያ ህዝብ ጨለማ ውስጥ ነው።መፍቻው ይከብዳል ብዬ መለስኩላት።
ዛሬ ይህን እያወጣሁ እያወረድኩኝ ዘመን ስለሰጣቸው ዘመናይ የኢትዮጵያ መሪ እና መጪው ጊዜን አሰብኩት። ከቀደመው #በከፋ ሁኔታ ከበደኝ። ተቋማትን ውጠዋል። ያልተመቻቸውን በጥፊም በእርግጫም ብለው አምክነዋል። ሌላም ይነሳል ብለው አያስቡም። የቅድስት ተዋህዶ ነገር ለእሳቸው ዱብ ዕዳ ነበር። ሚስጢሩ ለተገለጠለት እትዮጵያን እንደገና ሠርታታለች። መንፈሷን ዬተዘረፈውን በረቂቅ አቅሟ አስመልሳለች። ይህ አደናብሯቸዋል። ፋከራቸው ድንፋታቸው የዓዋጅ፤ ዬመግለጫ፤ የጡንቻ ትርዒት ሲያሳዩን ሰንብተዋል።
ዬሆነ ሆኖ ዘመናቸውን ሙሉ እንዴት እንደ ተሰናዱ? ሲፈርሱ እና ሲሰሩ የባጁት የኢትዮጵያ ፖለቲከኞች እንደምን አሳልፈው ህዝባችን ለጭካኔ እንደሰጡት መዘንኩት። ከነዳሁት። እና ነገ ከዛሬው በላይ ከበደኝ።
ህዝባችን ለበላህሰብ ተሰጥቶ ነፍሱ የንብ ያህል ዋጋ ዬላትም። እሳቸው የመረጡት መንገድ ያልተፈቀዱትን እኩይ ምግባራት አሰልጥነው አጋሮቻቸውን አሰልፈው አሁን ሰው፤፥አሁን አፈር፤ አሁን እሳት፤ አሁን በረድ፤ አሁን ሙሽራ፤ አሁን ጥንዙል ሆነው ዘመናት ያለፋባቸውን የግድፈት መንገዶችን ሁሉ በዚህ ዘመን እንደ ጥንቸል የመሞከሪያ ጣቢያ አደረጓት አገራችን እና ህዝቧን። የሦስት ቀናቱ ፆመ ኢትዮጵያ የፈጣሪ ሥራ ነበር። የተከደነው ዬተገለጠበት፤ ዬተበተነው የተሰበሰበበት፤ የራቀው የቀረበበት፤ ዬጠወለገው ያሸተበት፤ አቅም፤ ኃይል፤ ጉልበት የላይኛው ብቻ መሆኑ ዬተረጋገጠበት ነበር። አዲስ ዬተቀደሰ ምዕራፍ ነበር።
እሳቸው ግን ባዬሁት ሙሉ ፭ ዓመት ናዳ ናቸው። መብረቅ ናቸው። አሳቻ ናቸው። ኢትዮጵያን ይቀኑባታል፤ ዬበቀል ሰይፍም መዘውባታል ብዬ አስባለሁ ሳይሆን አምናለሁኝ። ሃሳባቸው ጥቁር። መንገዳቸው ጥቁር። ግባቸውም ጥቁር ነው።
ከዲያቢሎስ በላይ ዲያቢሎስነት … ልሁን ያሉ፦
ከጭካኔ ተፈጥሮ በላይ ጊንጥነትን … ዬተፎካከሩ፥
ከክፋት ተፈጥሮ በላይ ጃርትነት … ያስናቁ፦
ከሰውኛ ሴራ በላይ ሴረኝነት … አልቀው ዬተረጎሙ፥
ከበቀል ተፈጥሯዊ ተበቃይነት በላይ ተበቃይነትን ዬሞሸሩ፦
ከቂም ተፈጥሮ በላይ ቂመኝነት … አፋፍተው ዬዳሩ፤ የኳሉ፥
ከእራስ ወዳድነት በላይ ራስወዳድነት … ተክሊላቸው ያደረጉ፦
ከተንኮል በላይ ተንኮለኝነት … አዘምነው የፈፀሙ፦
ከእሾህ ተፈጥሮ በላይ እሾኃማነት … አብቅለው ያፀደቁ፥
ከጨለማ አስፈሪነት በላይ ድቅድቅነት … ያቀኑ፦
ከውሸት በላይ ዓራት አፍ ያለው ዕብለተኝነት … አለምልመው የሾሙ ዬሸለሙ፥
ከጥላቻ በላይ ጥልማሞት ጥላቻ …ን አዳብረው ያከፋፈሉ፦
ከከፋፋይነት በላይ ስልታዊ በታኝነት … አሰልጥነው ሥራ ላይ ያዋሉ፤
ከትዕቢት በላይ ማንኽሎኝነት … ዘውድ ዬደፋለት፦
ከክህደት በላይ አሪወሳዊነት … ዬተጎናፀፋ፤
ከማስመሰል በላይ እስስትነት … በጲላጦስነት ለማዕረግ ያስበቁ፥
ከንቀት በላይ ናቂና አፍቅሮተ ወዳቂነት …… በድርጊት በዕውን ያሳዩን፦
ከድብቅነት በላይ የመቃብር ሥፍራነት ለምን መረጡ? ብዬ እራሴን ስሞግተው ቁጭ እንዳልኩኝ ነጋ። ከ30 በላይ ንፁኃንን ጨፍጭፈው በሻሸመኔ ደሙን አይቸዋለሁኝ ሙሉ አስፓልቱ ፍሪዳ ተሰልፎ ዬታረደበት ይመስላል። በማግስቱ ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ በ ጣሊያን ነበሩ። እንዲህ ዓይነት ሲኦላዊ ሰብዕና ምድራችን እንዴት ልታፈራ ቻለች? ጣሊያን አገር አቀማመጣቸውን አዬሁት። "ከገነት የወረዱ መላዕክ" መስለው።ግን ከገኃነም የተላኩ #ኃጢያት ናቸው። ቀጥለው ማልታ፤ ፈረንሳይም ተገኙ። እኔ እማልደብቃችሁ በሰላም አገር ቤት ይገባሉ ብዬ አላሰብኩም ነበር። የሰማይ ቁጣ ስላለ።
ያ ሲደንቀኝ ሙሽራ መስለው እንደ አልባሌ ጨርቅ ለንግግር #ማሟያ ያላበቁትን ቅዱስ ሲኖዶስ ልዑክ ደጅ ተገኙ። ምን ለመሆን? ምን ለማግኜ ኘት? #በኢትዮጵያ #ቅድስት #ኦርቶዶክስ #ተዋህዶ #ያወጁትን #የጨለማ ዘመን ይፍታህ እንዲባል አልነበረም። ኃጢያታቸውን፥ ንቀታቸውን፤ ዕውቅና አሰጥቶ ግርማ እና ሞገስ ተጎናጽፎ #የጭካኔ ጉልላታቸውን ለማፀደቅ ማህተም ለማስመታት ነበር። የሚገርመኝ አጃቢ ሚዲያወቻቸውም አብረው ተገኝተዋል። ጉልበት፤ ጡንቻ፤ መታበይ አገር እዬገዛ ስለመሆኑ ለማመሳከር።
ለእኔ በቁማቸው ሙተዋል። ለእኔ ወድቀዋል። የፈለገ ቢወታተፍ ከእንግዲህ እንደ ሰው ዬሚያቸው ማንም አይኖርም። ይሆነኛል፤ መሠረቴ ያሉት አንባም ለማተቡ አደረ። ቁርጣቸውን አወቁ። ካቢኒያቸው ከል ለብሶ በወታደር አቀባበል ሲደረግለት ባጅቶ በባዶ ወና ዬህሊና አቅም እዛው ክብር እና ሞገስ ከሰጠቻቸው መንበር ተገኙ። በራቁትነት። ተመልምለው። ውስጣቸው ደርቆ። በሰው ሰውኛም፤ በመንፈሳዊ አቅምም ነኩቶ እና ደቆ ህልም እና ራዕዩ።
ነገም በዬትኛውም ዬአብይዝም ፕሮጀክት ተሳታፊ መጨረሻው አይሆኑ ሆኖ ክትመት ይሆናል። ይህን አድራጊው ግፋን ዬሚመዝነው አምላካችን ይሆናል። የራሄል ዕንባ ፈሶ አይቀርምና። ፕሮጀክቶቻቸው የዶላር ዝናብ አለባቸው። ግን ለኢትዮጵያ ተፈጥሮ ስለማይገጥም መጥፊያቸው ይሆናል። ያልተገለጡ ብዙ ገመናወች አሉበት። ዬምትዝናኑበት ፓርክ ገንዘቡ ከዬት እንደመጣ መርምሩት። እናም ተጠዬፋት። እሚወገዘውን መቀበል ይሆናል የሳቸውን የድሎት ፕሮጀክት ላይ መታደም። እያሰመጠ ዬሚያጠፋ ነውና። የሰሞናቱ አዋጅ እና ውጤቱ የስውሩ ፕሮጀክት በኽረ ትልም ነው።
እግዚአብሄር ይስጥልኝ።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
16/02/2023
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ