ከእርቁ ደስታ ይልቅ የበቀሉ ቀጣይ ፋስ ይጠነክራል - ነገ። ፈንጠዝያው ለጨካኝ ሚዲያወች ይሁን።

 

ከእርቁ ደስታ ይልቅ የበቀሉ ቀጣይ ፋስ ይጠነክራል - ነገ። ፈንጠዝያው ለጨካኝ ሚዲያወች ይሁን።
ዬከበደን ነገር ማስተዳደርም አቅም ይጠይቃል - ደመመን ነውና።
ዬከበደን ነገር #አክባጁን #አሞግሶ ማጠናቀቅም ምጥን ምራኝ ማለት ነው፦ህጋዊ ዕውቅና መስጠትም።
የቅድስቷን የማይደፈር አልፋ ኦሜጋ አቅም መተርተር ነውና ዬአሳቻው ጠቅላይ ሚር አላማው። ጥንቃቄ።
ወታደሮቿ ካለምንም ቅድመ ሁኔታ ከፎቶው ቀድመው መፈታት ነበረባቸው። የሁለት ዓመት ዬትግራይ እስራት ሙሉ ካቢኔ ትግራይ ሲገባ አይተናል። ብርኃን ሁን ሲሉ ብርኃን፤ ጨለማ ሁን ሲሉ ጨለማ????
የአባቶቻችን ውሳኔ፤ መግለጫን በጥንቃቄ ማዬት ይገባል። አፈፃፀሙን እምናውቀው ነገር ዬለም። ዬመጀመሪያው አዋጅ እና ዬአፈፃፀሙ መግለጫ በሚመለከት ማጥናት ይጠይቃል። መንፈሱን እኔ ሳዬው ማህበረ ምዕመኑ፤ ከእኛ ዕምነት ውጪ ያሉ ኢትዮጵውያን ወገኖቻችን፤ አህቲ እህት ቤተክርስትያናትን ጨምሮ አንድነታቸው ዬሰማይ ታምራትን እንዳያራርቅ፦ እንዲፈራቀቅ ዬተፈለገ ስለሆነ ያሰጋኛል።
አንድነቱን ለመናድ አስተዋፆ እንዳይኖረው ስጋት አለኝ። ጲላጦስን፤ ሄሮድስን፤ ፈርዖንን፤ ናዚን፤ ሙሶሎኒን ብናስብ ኢትዮጵያ ያለችበትን መከራ ዬቀደምቶቹ ጭካኔ እና ዬአፈፃፀም ስልት ማመጣጠን ይቸግራል። በህይወትም እያሉ፤ ሲያልፋም ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ አሊን ማወቅ አይቻልም። ከሞቱ በኋላ አጥንታቸው ተመርምሮ ዬሚደረስበት ሁነት ካልኖረ። #ቬርሙዳ #ትርያንግል ናቸውና።
ምን ለማለት ነው ይሄ? ተጽዕኖ ፈጣሪውን ሰማያዊ ዕውነት ለመሰንጠቅ ዬሙሉ ጊዜ ሥራቸው ይሆናል ዬኢትዮጵያ ቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ። ስለዚህ ጥንቃቄ እናድርግ። ልቅናዋን እና ልዕልናውን አቅም ማሳጣት ፕሮጀክታቸው መሆኑን አውቀን ሊሆኑ ዬሚገባቸውን ዕይታወች በትህትና መግለጽ። ግን አንድነታችን አጥብቀን ሊሆን ይገባል። ከእርቁ ደስታ ይልቅ ዬመጪው የበቀል ፋስ ስለሚጠነክር ዬአመራሩ አቅም እና እኛ እንዳንለያይ ጥንካሬ ማድረግ ይገባናል።
አባቶቻችን ቅኖና ተጣሰ ብለው ዬማይመለሱበትን ሰማዕታት በወረቀት እፍታ ማዛል አይኖርባቸውም ባይ ነኝ። ለመሆኑ ለእነኛ ህይወታቸውን ላሳጡ ወገኖቻችን ምህረት ሰጪው ማን ነው? እንደገናስ ያ ዬውንብድና ክብር ተሰጥቶት በብልጽግና ሪኮመንዴሽን በቅዱሱ ቦታ ሲመለስ መሬት ትሸከመዋለችን?
ስጋቴ ዬገዘፈ ነው። ስክነት ይጠይቃል። ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ አጀንዳቸው አልነበረም። ንቀውት ነበር። የ6 ወር የሥራ ግምገማ ላይ በማናህሎኝነት እና በእብሪት እንደ ማሟያ አጀንዳ ያዩት ዬገዘፈ ትንግርት እቤቷ ድረስ ሂደዋል። ግን ኦፊሻል ይቅርታ ዬለም።
1) ጨርሷት፤ ፈጥሟት ብለው ዓውጀዋል።
2) አስቸኳይ ጊዜ ታውጇል።
3) መፈንቅል ሊደረግብኝ፤ ሽብርተኛ አደራጅታብኛለች ብለው ከሰዋል።
4) ሚዲያ አልባ እንድትሆን አድርገዋል። ዜግነቷን ጥሰዋል።
5) ጥበቃዋ ተነስቶ ያሻው ያሻውን ያደርግ ዘንድ በይነዋል።
6) ሺወች ታስረዋል። አካላቸው ጎድሏል። ተሰደዋል። ክብራቸው ተረግጧል። በ24 ቀናት ውስጥ ማቅ፤ ዕንባ፤ ደም፤ መስቃ ፈሰውብናል። ይህ በሞገስ ማጠናቀቅ ይከብዳል እጅግ ድቅድቅ ሸክም ነው። በፈጣሪያችን ጉባኤ መመስገን ካለበት ፈጣሪ ብቻ። ነገር ግን ዓላማው አንድነታችን መተርተር ስለሆነ ጥበብ ይጠይቃል።
7) በተከታታይ ዬወጡ መግለጫወች፤ አንድም ዬመንግሥት አካል ያገባኛል ብሎ ደጇ እንዳይደርስ ዕቀባ ጥለዋል።
በዕለተ ሰንበት በመዲናዋ በአዲስ አበባ ሥርዓተ ተክሊል፤ ሥርዓተ ፍትኃት፤፦ሥርዓተ ቅዳሴ፤፥ሥርዓተ ቁርባን፤ ሥርዓተ ሐሴት ታግተዋል። የሰማይ መላዕክታን ጥቁር ተፈርዶባቸዋል። ሥርዓተ ቅዳሴ የቅዱሳን ነውና።
ሌላ ተዳብለው ዬቀረቡ እነሱ ያሰቡበት እኛ ያልታዬን ጉዳይ አለ። ለመሆኑ ዬቤተክርስትያኗ ብሄራዊ የሥራ ቋንቋዋ ምንድን ይሆን? ጥሰት ወይንስ ስብራት? ህግ ይከበር ብላ ግሎባሊ እዬጮኽች በምትጠዬፈው መከራ እንዳትዘፈቅ እሰጋለሁኝ።
የተሳሳጡ ብዙ ነገሮች አሉ። ልብ ላለን ሰወች። በቤተክርስትያን አገልግሎት የቆዳ ስፋት ሳይሆን ዬአገልግሎት ጥራት እና አቅምን ይጠይቃል። ዬአፈፃፀም መመሪያው እራሱ ኢትዮጵያ ሁለመናዋን ለአፈንጋጭ ቡድን #እንድትገብር ያወጀ ነው። ይህን ሚዛን ላይ ቅዱስ ሲኖዶስ ሊያስቀምጠው ይገባል።
ምክንያት አማራ ክልል አገልጋዮች አብዛኞቹ #ተጋሩ ናቸው። በብሄር ተዋፆዖ ልዩ እንክብካቤ ለኦዳወገዳ ከተሰጠ ብዙ ነገር ይናዳል። የሐዋርያት ሥራም በፋስ ይተረተራል። ሐዋርያት ከአንድ አካባቢ ለዛውም ወንድማማቾች ሁሉ እንዳሉበት እምዬ ብፁዑ አቡነ ኤርምያስ አበክረው ሲያስተምሩ ነበር። መጨረስ አልቻልኩም ዬስምምነቱን ሰነድ ሳዳምጥ። መርግ ነው ዬሆነብኝ። ዬተበደለ ተበድለህ ዝለቅ፤ ዘመነኛ ይሞሸር ዓይነት ነው። ጣዕሙ፤ ጠረኑ ይከብዳል።
በአሁኑ ዬከበሩ የኦሮሞ የተዋህዶ ልጆች የዕውነት አርበኝነት ውሎ ይህን ዬአፈፃፀም ዝበትም ይሞግቱታል ብዬ አስባለሁኝ። ቅድስታችን አገልግሎቷን ዬምታበረክተው ለሁሉ በእኩል ዓይን ሊሆን ይገባልና። በጦርነት ለተጎዱ፤ ለተፈናቀሉ ሁሉ እናት ናት እና። እስረኞቻችን በሚመለከት # #ክሱ #ተቋርጦ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ መፈታት ነበረባቸው። ወታደሮቿ ናቸውና። ከፎቶው በፊት። ሰማዕቱን መመለስ ባንችል። ቢያንስ ይሄ።
አንድነታችን ጠብቀን ጎደሎወችን ግን መናገር ግዴታችን ነው።
ጉልሆችን አድኖ በመበከል ማሰናበት አንዱ የጃርት ፖለቲካው የጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ አሊ ዒላማ ስለሆነ ይህ እንዳይሆን ስለ አባቶቻችን ቀጣይ ህይወት ተጋድሎው በሎቢ ሊጠናከር ይገባል። መዛል አይገባም። ሥራቸውም ተፈጥሯቸውም ጽልመት ናቸው እና ዶር አብይ አህመድ አሊ።
"ዬቤትህ ቅናት በላኝ።"
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
16/02/2023
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።