ልጥፎች

ትንሽ ቆይታ ከጃዋሪዝም የአብይዝምን አቅላይነት ጎዳና ጋር ………

ምስል
  ትንሽ ቆይታ ከጃዋሪዝም የአብይዝምን አቅላይነት ጎዳና ጋር ………   "የቤትህ ቅናት በላኝ።"     #ጠብታ ።   ወርኃ የካቲት የታቦቴ የብላቴ ሎሬት ጸጋዬ ገ/ መድህን በስጋ የተለዬን ስለሆነ እያዘከርነው ቢሆን። ለ17 ዓመታት በዘለቀው በእምዬ ሲዊዘርላንድ በራዲዮ #ሎራ 97.5 መካከለኛ ሞገድ በወር ሁለት ጊዜ በዕለተ ሃሙስ በቀን ቅዱስ ከ15.00 -16.00 ጸጋዬ ራዲዮ በድንቁ አማርኛ ቋንቋ በሚተላለፈው መሰናዶ በአግባቡ በዬአመቱ ተከብሮ ይዘከራል። የራዲዮ ፕሮግራሙ የተመሰረተበት ዓላማም ግብም ይኽው ነውና። ለታላቅ ባለውለታ የቅኔ አባት መታሰቢያው ክብሩን፤ ልዕልናውን፤ የአማርኛ ቋንቋን የሥልጣኔ ትውፊቱን ማስቀጠል ነውና የትውልዱ ድርሻ።    #ውሽክታ ። አቶ ጃዋር መሃመድ ስለ አዲስ አበባ ሰሞኑን ያለው ቁምነገር አለ። ከዛ ያጎረፈ ሃሳቡ በፍፁም የተለዬ አዲስ አበባን የገነባትን #ጉራጌን አትዝለሉ ሲል ለኦሮሞ እና ለአማራ የአዲስ አበባ አቀንቃኞች መልዕክቱን ሳደምጥ #ቁጥር አንድ ውሽክ አልኩ። በነገራችን ላይ የጨመቱ ጉራጌ፤ ጋሞ፤ ወላይታ፤ አማሮ፤ አፋር ወዘተ ማህበረሰቦች ኢትዮጵያ ስለሰጣት ፈጣሪን አላህን ልታመሰግን ይገባታል።    ቁጥር ሁለቱ ውሽክታ ደግሞ በአገረ ጀርመን ላይ "እኛ መንግሥት መገልበጥ ሰልችቶናል" ሲል ውሽክ ብዬ ነበር። ኧረ በሞቴ አይሰልችህና ሞክረው በማለት መልሱንም ጥፌያለሁ። ሊንኩም ተቀምጧል።   ሰሞኑን ደግሞ በኦነግ ዓርማ በተንቆጠቆጠው አዳራሽ በአሜሪካ ኦሪንገን ላይ ተሰብሳቢወች በጀርባ በሚታዩበት የጃዋሪዝም ጉባኤ ላይ በኦሮምኛ ተናግሮ የተተረጎመውን " ማለዳ " በሚባል ዩቱብ ቻናል፤ "መንግሥት መገልበጥ ከሰለቸን ተሃድሶ ይባል፤ ተጠግኖ ተጠግ...

ከዬት ልጀምረው? #ዕውነት #ጋራጅ #አያስፈልገውም።

ምስል
  ከዬት ልጀምረው? #ዕውነት #ጋራጅ #አያስፈልገውም ።   "የቤትህ ቅናት በላኝ።"     ክፍል አንዱን ያዳመጡ "ልብ ወለድ ያሉት" አሉ። ልበወለድ ነው ብንል ጸሐፊው #የፋክት ልበወለድ ጸሐፊነቱን መካድ የሚገባ አይመስለኝም። እን በወርኃ ታህሳስ በ2019 የፃፍኩት እኮ አለሁኝ - በህይወት። ሂደቱን ብቻ ተመልክቼ። እንኳንስ ድርጊቱ በቁሙ በሚነበብበት፤ በሚተረጎምበት ወቅት ዛሬ ላይ። ሂደቱ ለሁሉም አይጠቅምም። #ክህደትም ነው። መታመንን የሰለቀጠ።    የሆነ ሆኖ ከሦስተኛ ወገን የሚመጡ ጉዳዮች ቅመማ ቅመም ሊጨማመርበት ቢችልም ጭብጡ ግን ፋክት ተኮር ነው። ጠንክረው የወጡ ተደጋጋሚ #ዝንባሌወች እንዳሉ ተመልክቻለሁኝ። አትኩረተ ኤርትራ፥ ነገረ ጎጃም እና ጎንደር። ጥቅሙ ግን አቅም መግቦት ላይ የባጁትም እራሳቸውን ይመዝኑበት። አባ ጎልጉል አቶ ሽመልስ አብዲሳ እኮ #እንቅጩን ተናግረዋል። "ኮንቢንስና ኮንፊይዝድ" በማለት። #ለ7 ወራት የማህበረ ኦነግ ጉዞ እንዳይደናቀፍ ታሽጎ ተቀምጦ በኋላ ወጣ። ከወጣ በኋላ ጥድፊያ ነበር የኮፒ ራይት። በዛ ውስጥ እምሽክ ስላለው የኢትዮጵያ ተስፋ ይሁን የአማራ ሰቆቃ ባለቤት አልባ ነበር።   ማህበረ ቅንነት ይመስላችኋልን አዲስ አበባ በፌድራሉ ሥር እንዳለች? #እእ ። እኔ ለአምስት ዓመታት ጽፌበታለሁኝ። ከመስከረም 5/2011 ጀምሮ አዲስ አበባ በኦሮምያ ሥር ናት። ለኦነግ የተገባው ቃል የኤርትራው ስምምነትም ይሄው ነው። ዶር ለማ መገርሳ እና ዶር ወርቅነህ ገበዬሁ ወደ ኤርትራ ሲጓዙ ዜና ነበር። ሲመለሱ #ፀጥታ ።    በወቅቱ ብሎጌ ላይ ጽፌበት ነበር። 5 የአዲስ አበባ ልጆች ተረሽነው፦ 1300 ወደ ጦላይ የተላኩትም ለኦነግ #ርችት ነበር። እስከ ...

#የጃዋሪዝም #ሞገድ #ዳጥ።

  #የጃዋሪዝም #ሞገድ #ዳጥ ።   "የቤትህ ቅናት በላኝ።"   ማህበረ አወንታውያውያን እንዴት አደራችሁልን? አወንታውያን የትውልድ #አንበል ናችሁና ደህንነታችሁ በእጅጉ ያስፈልገናል።   #ጠብታ ።   ትናንት ከአዲስ ኮንፓስ ጋር ውይይት ያደረገ ወጣት ጋዜጠኛ ነበር። ብዙ ጊዜ ሳዳምጠው ለእናት አገራችን ለኢትዮጵያ ያለውን ንጹህ ቅንነት አይበታለሁኝ። ለዚህም ነው ጊዜ ሰጥቼ የማዳምጠው። በጋዜጠኝነትም ህይወት ውስጥ ዝልቅ ተመክሮ ያለው ወጣት ነው። በዬትኛም ሁኔታ፤ በማናቸውም ጊዜ #ቅንነት ካዬሁ ወይንም ካዳመጥኩ እሳባለሁኝ። መዳኛችም ቅንነት ነው። ውድቀታችንም የቅንነት ፍልሰት ነው። • https://www.youtube.com/watch?v=AC2qgGIlmbI «የትራምፕ መንገድ፣ ለውጡና ምክክሩ፣ "ጊዜያዊ የተኩስ አቁም"   ወጣቱ ጋዜጠኛ አንተነህ የብልጽግና ጉዞውን የሚደግፍ ይመስለኛል። በጠሚር አብይ አህመድ የአመራር አቅምም ላይ ተመስጦ እንዳአለው አስተውያለሁኝ። ይህ ሙሉ መብቱም ነው። እኛ እንቃወም የለምን? ጋዜጠኛ አንተነህ ሙግት ሲኖርም በቀጥታ ይሞግታል። በተለይ ፕሬስ ህግጋት ላይ።   ስለ አዲስ አበባ ትናንት ሲገልጥም የመከፋት ግን ጊዜን የመጠበቅ አስፈላጊነት ፍንጭ የሚሰጡ ዝንባሌወችን አዳምጫለሁኝ። ዕውነት ለዴሞክራሲ የምንታገል ከሆነ የሚመቸንም፤ የማይመቸንንም ሃሳብ እኩል አዳምጡ ሳያጋንኑ፤ ወይንም ሳያይሸበሽቡ በሃሳብ መሞገት የተገባ ይሆናል። ያ ሃሳብ በብዙኃኑ ድምጽ ከፀደቀ በዛ መገዛት ግድ ይላል። እኔ እንዲያውም እኔ የማራምደውን ሃሳብ ከሚያነሱት ይልቅ ከእኔ ለዬት ያለ ሃሳብ ያላቸውን ባደምጥ እመርጣለሁኝ።   በአዲስ አበባ የቤቶች ፍርሰት ሁኔታ ዴሞግራፊ አለ ...