ልጥፎች

ሚስጢረ - ባቲካን። • ዕርዕሱ የእኔ ዘገባው የBBC አማርኛው ክፍል።

ምስል
  ሚስጢረ - ባቲካን። • ዕርዕሱ የእኔ ዘገባው የBBC አማርኛው ክፍል። https://www.bbc.com/amharic/articles/cq80g5ene7jo «ቀጣዩ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ ከአፍሪካ ሊመረጡ ይችላሉ?» 24 ሚያዚያ 2025, 07:00 EAT   «ቀጣዩን የሮማ ሊቀ ጳጳስ ለመምረጥ መስፈርቱ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን በፍጥነት እየተስፋፋች ያለችበት አካባቢ ከሆነ በእርግጠኝነት ከአፍሪካ ሊሆን እንደሚችል መተንበይ ይችላል።   ከየትኛውም የዓለም ክፍል በተለየ በአፍሪካ የካቶሊክ እምነቱ ተከታዮች ቁጥር በከፍተኛ መጠን እያደገ ነው። እየጨመረ ያለው የእምነቱ ተከታዮች ቁጥር በመላው ዓለም ካሉ አህጉራት አንጻር ሲወዳደር ከግማሽ በላይ የሚሆነው እድገት የተመዘገበው በአፍሪካ ነው።   ከዚህ ቀደም ከ1500 ዓመት በፊት አፍሪካዊ መሆናቸው የሚታመነው የቤተ ክርስቲያኒቱ ጳጳስ ገላሲያስ ቀዳማዊ ቤተ ክርስቲያኒቱን በርዕሳነ ሊቀ ጳጳስነት አገልግለዋል።    የሮማ ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያንን በቀጣይነት የሚመራውን አባት የሚመርጡት ካርዲናሎች ሲገናኙ ውሳኔያቸውን ይህ እውነታ ተጽዕኖ ያሳድርበት ይሆን?    ናይጄሪያዊው ካህን አባ ስታን ቹ ኢሎ አመራሩ ዓለም አቀፍ ምዕመኑን የሚያንፀባርቅ መሆን እንዳለበት በመግለጽ "አፍሪካዊ ጳጳስ ቢኖር በጣም ትልቅ ነገር ነው" ይላሉ።   አባ ስታን ቺ ኢሎ ካርዲናሎቹ ከፍተኛ ተቀባይነት እንዲሁም "ተሰሚነት ያለውን ጳጳስ" ሊመርጡ እንደሚችሉ ተናግረዋል። "ተግዳሮቱ በቫቲካን በአሁኑ ወቅት ከፍተኛ ሹመት ላይ ያለ አፍሪካዊ ካርዲናል የለም፤ ያ እንቅፋት መሆኑ አይቀርም" ይላሉ። "ጳጳስ ሆነው ለመሾም ብቃት ያላቸው፣ በዓለም የካቶሊክ ማኅበረሰብ ዘንድ ተሰሚነት ያ...

ሽብር እና ጭካኔ እስከ መቼ???! #ንጹሁ ፍጡር ገበሬ በጅምላ ለምን በባዕቱ ይፈጃልን? ለምን? #አብረን #እናምጥ!

ምስል
  ሽብር እና ጭካኔ እስከ መቼ???! #ንጹሁ ፍጡር ገበሬ በጅምላ ለምን በባዕቱ ይፈጃልን? ለምን? #አብረን #እናምጥ !   "የቤትህ ቅናት በላኝ።"   ዛሬ ዕለተ ሃሙስ የቀን ቅዱስ ከመሆኑም በላይ እኔም መላ ቤተሰቤም ተወልደን ባደግንበት በዓት በ፵፬ቱ እቴጌ ጎንደር #የአዳም ቀን ይባላል። በስቅለቱ ልጆች ሆሆ ምሻምሾ ብለው ያጠራቀሙት ዱቄት ዘይት እና ድልህ ተሰናድቶ በወል ይመገባሉ። ዛሬ ደግሞ ስለ #ስለአዳም ተብሎ ልጆች ለምነው በሚሰበስቡት ቅቤ፤ ቋንጣ፤ እንጀራ ተሰርቶ ወጡ በጋራ ልጆች ይበላሉ። ሁለቱም ትውፊት ጥልቅ ትርጉም ያለው መከራን እና ደስታን በጋራ ማስተናገድን ዕውቅና የሚሰጥ ክስተት ነው።   እኔ ዛሬ ይህን ከባድ ሃዘን ባልዘግብ በወደድኩኝ። ግን ባለመታደል ምዕራፍ ፲፮ ለመጀመር ዳርዳር ስል ያገኜሁት ውስጤን የነካ ሃዘን ማቅረብ የግድ ሆነ በዕለተ አዳም ቅዱስ ቀን።   የማከብራችሁ የአገሬ ልጆች እንዴት ናችሁልኝ። ብኖርም ባልኖርም ተግባሬን አክብራችሁ ለምትልኩልኝ ሐዋርያዊ መልዕክቶቻችሁ እጅግ አመሰግናለሁኝ። ኑሩልኝ። አሜን። ባልነበርኩበት ወቅትም ሼር ያደረጋችሁልኝ ውዶቼ ተባረኩልኝ። አሜን። የዓመቱ ፋሲካ፤ የሁዳዴ ፆም መፍቻ ለዛውም በንጹኃን ገበሬ ላይ የተፈፀመው ሰቅጣጭ ጭካኔ #ውረድ እና ፍረድን ያጠይቃል። ገበሬን? ጉሮሮን ለምን ይጨከንበታል???   ከጥቂት ደቂቃወች በፊት የሉዓላዊ ሚዲያ ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ሲሳይ አጌና የሰጠውን ማብራሪያ አዳመጥኩኝ። በተጨማሪም ከሥር የተሰጡ አስተያዬቶችንም በተወሰነ ደረጃ አነበብኩኝ። ወጥ ዕይታ ወጥ አቀራረብ ነበረው። መቅደም የሚገባው #መደንገጥ ፤ እንደሰው #መጨነቅ አብሮ ማዘን ሲገባ፦ ለድርጊቱ አፈፃፀም ፋክቱን በውስጥነት ማፈላለግ ሲገባ፦ ያ...

ፕላኔታችን አጽናኝ አባቷን አጣች።

  ፕላኔታችን አጽናኝ አባቷን አጣች።   • ትንሳዔን ዓውጆ በትንሳዔ ወደ አባት ጥሪ፤ መታደል።   “አፈር ነህና፣ ወደ አፈርም ትመለሳለህ።” (ዘፍጥረት ፫ ቁጥር ፲፱- ፳)     የተመረጡት ንጹህ አባት ሰው ሆኖ መፈጠር የከበረ የመዳህኒዓለም ስጦታ መሆኑን በድርጊት ያመሳጠሩ ሩሁሩህ አባት፤ ትንሳዔን ዓውጀው ወደ ናፈቃቸው አባት በብርሃን ዕለት መጠራት ሚስጢር ነው።    የካቶሊክ ሃይማኖት የዓለም ሃይማኖት እስኪመስል ድረስ ደግነታቸው ሐዋርያ ነበር። ለመላ የዓለም ህዝብ መጽናናትን እመኛለሁኝ። ለአባ ዘላለማዊ እረፍት እመኛለሁኝ። ቅብዓ እንዲህ ነው። ሲፈጠሩም፤ ሲኖሩም፤ በሥጋ ሲለዩም ተመስጥሮ። መታደል።    አስታውሳለሁኝ አንድ ጠሎተ ሃሙስ እስር ቤት ተገኝተው ቀለም፤ ዞግ፤ ሃይማኖት ሳይገድባቸው እስረኞችን ሁሉ ተጎንብሰው እግር አጠቡ። እኔም በመደነቅ አንድ ጹሁፍ ጽፌ ነበር።    ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 22.04.2025   "ወደ እግዚአብሄር ቤት እንሂድ ባሉኝ ጊዜ ደስ አለኝ።"