"ቅድሥት ሥላሴ ዩንቨርስቲ በሰጠው የዚህ ዓመት ዕድል 40 ነበር። 10 ለኦሮምኛ ቋንቋ ተናጋሪ ነው ዬተሰጠው።"

"ቅድሥት ሥላሴ ዩንቨርስቲ በሰጠው የዚህ ዓመት ዕድል 40 ነበር። 10 ለኦሮምኛ ቋንቋ ተናጋሪ ነው ዬተሰጠው።"
"ምድሪቱ ኢትዮጵያም አልቅሳለች። ይህ ለቅሶ አድራጊውንም አስደራጊውንም ጠርጎ ይወስዳል።"
ብፁዑ አባታችን አቡነ ፊሊጶስ።
ከልባችሁ ሁናችሁ አዳምጡት። ስንት ነገር እንደማናውቅ። ተኝተህ በለኝ ነው የያዝነው።
ብፁዑ አባታችን አቡነ ናትናኤል በሚያስተዳድሯቸው አገረ ስብከቶች "የመክፈያ ሰነድ ካርኒ በኦሮምኛ ቋንቋ" ሌላውስ?
#በስብከተ ወንጌል ዓራት ዓይናማው ሐዋርያ እና ዲፕሎማቱ ብፁዑ አባታችን ከአቡነ በርናባስ
" ዬአዕዋፍን እናቶች ስናይ ለልጆቻቸው ዬእንሰሳትን እናቶች ስናይ ባጠቃላይ የፍጥረታትን ነገር ስናይ፤ እናት ለልጆቿ ያላትን ስስት፤ ያላት ናፍቆት፤ ያላት ጭንቀት መቼስ ዬታወቀ ነው። መቼም ከፍጥረት እንደመማር ያለ ዬለም። እና በዚህ ሰዓት ልጆቻችን፤ ምዕመናን ምን ያህል እያነቡ በደከሙበት ቤተክርስትያን፤ በገነቡት ህይወታቸውሲታደስበት በሚኖረው እንዳይገቡ እዬተከለከሉ፤ ዬገቡትም በጥይት እዬተደበደቡ፤ በዱላ እንደ አውሬ ራሳቸው እዬተቀጠቀጠ እንዲሞቱ ነው ያለው። ለምሳሌ ሻሸመኔ እኒ በአጠቃላይ በልጆቻችን ላይ እዬደረሰ ያለውን ስንመለከት፤ አባት ሆኖ መገኜት በጣምከባድ ነው። ምክንያቱም አባት ብቻ ሳንሆን ለልጆቻችንእናትም ጭምር ነን ለልጆቻችን። ከእናትም ዬበለጠ ለልጆቹ ዬሚጨነቅ ዬለም። እያዘን ነው ያለነው። ግንአንድ የምንደሰትበት ነገር ቢኖር ቤተክርስትያናችን የጽጌረዳን ተክል ነው የምትመስለው። የጽጌረዳን ተክል ስናይ ግንዱ በጣም #እሾኃማ ነው። ጫፋ ላይ ያለው ግን #ማዕዛው #ከሩቅ ዬሚስብ #አበባ ነው። ተወዳጅ፤ በታላላቅ ሰወች ፊት የሚቀርብ ………"
ብፁዑ አቡነ በርናባስ
#እምዬ ብፁዑ አባታችን አቡነ ኤርምያስ
" አባቶች የምንለካበት የምንመዘንበት ሰዓት ላይ ነን።
ጭምቱ አባት አቡነ ህርያቆስ
" አባትነት በዚህ ዘመን ከመልበስ ይልቅ ማሳዬት ቢቻል። በጣም ጥሩ ነበር። ቀላልም ይሆን ነበር። …… ፈተናወች ሁልጊዜ ደስታንይዘውይመጣሉ። በእኛ ሁሉም አማርኛ ቋንቋ ይሰማል። በዬቋንቋቸውም አገልግሎት ይሰጣል። ችግርም ዬለብን።"
በደቡብ ክልልችግርም አሉ ሲሉ አንድ አዋኪ ጉድ ጠቅላይ ሚር አብይ ሸንቁረው ነበር። ደቡብ እኮ የሥራው ቋንቋ አማርኛ ነው። ያነን ለማወክ ነውሽንሸና ላይ ዬሚገኙትኆ።ደቡብ የሚለውን የውህድ ማንነትንም ደርምሰውታል። እግዚአብሄር ይይላቸው አሜን።
#ርቱዑ ብፁዑ አባታችን አቡነ ናትናኤል
"………ፈተና ያሸልማል። መከራ ያሸልማል። ………ዬገቢ መሰብሰቢያ ደረሰኝ ካርኒ ሳይቀር በኦሮምኛ ቋንቋ ነው የሚታተመው"
#ግልፅና ቀጣትኛ አባታችን ብፁዑ አቡነ ፊሊጶስ ።።
" ችግሩ አቅጣጫውን እና መልኩን ቀይሮ ነው እንጂ ቤተክርስትያን ሁልጊዜም ፈተና ውስጥ ነው የምትራመደው። በፈተና ውስጥእዬተራመደች በማዕበል ዬሚያምታት መርከብ ሆና ነው ሁሌ ዬምናያት። ግን የሚገርመውመርከቡ ውስጥያለው፤ ዬመርከቧ ተቆጣጣሪ እንደማትገለበጥ፤ መፍረስ እንደማይገጥማት አረጋግጦልናል። አሁን ቅድም እንደተባለው ምዕመናን፤ ካህናት፤ መነኮሳት፤ ዲያቆናት ሁሉ ከቅዱስ ፓትርያርኩጀምሮ እስከ ታችኛው ድረስ ያለው በዕውነት አድራጊ እና አስደራጊ በመሆን ቀኖና ቤተክርስትያን፤ ዶግማ ቤተ ክርስትያን በተጣሰ ሰዓት እና በተሰበረ ሰዓት ያልታመመ ዬለም። ያላዘነ ዬለም። ሁሉም አልቅሷል። ሁሉም አንብቷል። #እኔ #ምድሪቱ #ኢትዮጵያም #አልቅሳለች #ብዬ ነው እማዬው። እና ይህ ለቅሶ አድራጊውንም አስደራጊውንም ጠርጎ ይወስዳል። ቤተ ክርስትያን ቀኖናዋም፤ ዶግማዋም እንደተጠበቀ ትቀጥላለች። ……… ውስጣችን በሃዘን ጠቁሯል። …… ሃይማኖታችን ለነገ ይደር ብለን ዬምንደራደርበት ጉዳይ አይደለም። ……… የሥልጠና ዕድልን ብፁዑነታቸው ሲገልፁም በ2012 --- 26 ከዛም 27 ከዛም በዚህ ዓመት ከነበረው አጠቃላይ ድርሻ ለኦሮምኛ ቋንቋተናጋሪወች ከ40 ዕድል 10 ተሰጥቷል።"
ይህ ማለት 1/4ኛው ዕድል ተሰጥቷል። ይህ ፍትኃዊ አይደለም። ከዚህ ጋር አያይዤ እማነሳቸው አበይት ጉዳዮች አሉ።
1) በደቡብ እና በኦሮምያ ማሰልጠኛ ተቋማት አሉ። በአማራ ግን 0 አልቦሽ።
2) ርቱዑ በሆኑት ብፁዑ አባታችን አቡነ ናትናኤል በሚመሯቸው አገረ ስብክቶች አብዛኛው የአማርኛ ቋንቋ ተናጋሪው ፍትህ አጥ እንደ ሆነ ይሰማኛል። ልክ እንደ ፖለቲከኞች ሥራው በኦሮምኛ ብቻ ከሆነ ይከብዳል።
3) በጀት ጥቂት አገልግሎት በኣ።ሚለጥበት እና መጠነ ሰፊ አገልግልግሎት በሚሰጥበት ዬበጀት ምደባው እኩል መሆንም ኢ ፍትኃዊ ነው። ይህንንም ቅዱስ ሲኖዶስ ሊያስተካክለው ይገባል። ዬሃይማኖት መሠረት መሆን፤ በነፃ አገልግሎት መስጠት አልጠቀመም። ህግ እና ሥርዓት ይከበር ሲባል አስተዳደራዊ ፍትህም ለስሜን ኢትዮጵያ ያስፈልጋል።
4) ግዕዝሳናውቅ በግዕዝ ስንማር ቆይተናል። በተለይ አማራ ክልል። ከእንግዲህ ግን ዬቤተክርስትያናችን መደበኛ የአገልግሎት ልሳናት በሙሉ ቅድስታችን በቻለችው ልክ በአማርኛ ቋንቋ እንዲተረጎሙ ሊደረግ ይገባል። መብትን ዬማይጠይቅ ማህበረሰብ ግዴታ ሲጠቀጥቀው ይኖራል። ይህን ስል ሥርዓተ ቅዳሴን እና መሰል መፃህፍት በአማርኛ ቋንቋ አልተተረጉም እያልኩ አይደለም።
ቃለ ምልልሱ ሁለት ክፍል አለው በጥሞና ተከታተሉት።
EOTC TV | "ወቅታዊ ጉዳይ 15 ዓመት ሙሉ ምንም አልሠሩም"
EOTC TV | "ሕግ አስከባሪዎች ሕግን ሰበሩ | ክፍል 2"
ወሥብኃት ለእግዚአብሄር።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
10/02/2023

 

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።