የአዲስ አበባ ዬመንበሩ መዲናነት እንደገና ዬመወለድ ማህተም ነበር። አቡዬ። ግን #ተስተጓጎለ፤ #ጓጎለም
ሀምሌ ፭ = ዬካቲት ፭
አቅምን፤ ዕድልን ማኔጅ የማድረግ አመክንዮ።
ማህበረ ኦነግ በስልት ገብተው አጓጉለውታል። ለምን የኦሮምያ ክልላዊ መንግሥት #ስላልፈቀደ። ስለማይፈቅድም። ባለፈውም አይፈቀድም ብዬ ጽፌ ነበር። አዲስ አበባ የኦሮምያ ክልል ዬሆነችው ከመስከረም 5/02/2011 ዓም ጀምሮ ነው።
እኔ የመንፈስ ቅዱስ ባሪያ ነኝ። አሻቅቤ ማዘዝ አልችልም። ግን ሰማያዊ ዕድል እንዳመለጠን ይሰማኛል። ቢያንስ በታሪካችን ሐዋርያት የመሩት ሰላማዊ ሰልፍን ትዕይንት የማዬት አዲስ ርግብ በር ነበር። ይኽው መግለጫ እዛው ላይ መነበብ ይችል ነበር። ሱባዬውን፤ ተጋድሎውን፤ ምርቃቱን ለማመስገን መስቀል አደባባይ ትክክለኛው እዮር የመረጠው፤ ያፀደቀው ቦታ ነበር። ልክ እንደ ታቦር ተራራ።
ዕርዕሰ መዲናችን የሚለው መንፈስ ማህተሙ ነገ ነበር ዬካቲት ፭ ቀን። ላልተወሰነም ጊዜ ይሁን ለተወሰነ ጊዜ ፈቃደ እግዚአብሄር ትልልፍ ተፈፅሞበታል ብዬ አምናለሁኝ። መንበረ እጬጌው በኦሮምያ ክልል ሥር ስለመሆኑ አልገባውም። ርዕሰ መዲናም እንደሌለው አልተረዳም። ዬአሸማጋዮች ድርሻ ይህ አናርኪ ሥርዓት እያረገረገ ስለሆነ መሰረት ማሳያዝ ነበር። ተሳክቷል።
ቤተክርስትያኗ አደባባዮዋ፤ ርዕሰ መንበሯ ላይ መብት እንዳላት ሰነዷ ነገ ዬካቲት5/ 2015 ነበር። ሌላው ስምምነቱ፤ ቃል ዬተገባው ነገር ሰነድ አለውን? በዬትኛው ህግ ይሆን ዬሚገዛው??? ዬራሺያው መሪ ጎርባቾብ እና አቻቸው በአሜሪካ ያደረጉት ስምምነት ሰነድ ስላልያዘው እኮ ነው ዬአሁኑ የኔቶ እና የራሽያ ፍጥጫ። ለዛውም ቤርሙዳ ትርያንግል፤ አሳቻ እና ዘዋራ ከሆነ መሪ ጋር የሚደረግ ድርድር። የመጀመሪያ ፕሮጀክቱ አዲስ አበባ ከተማችሁ አይደለችምን ማረጋገጥ ነበር። አሳክተዋል።
በቀጣይ በጉዞ፤ በምግብ ብክለት፤ በህክምና ግድፈት፤ በሙስና በማለት ከሊቅ እስከ ደቂቅ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት ልጆች ላይ ሁሉ ዓይነት መከራ ከፍቶ ይፈፀማል። አዲስ አበባ ላይ አፋኝ፤ ገዳይ ቡድን አለ። ስውር እስር ቤቶችም አሉ። በአደባባይ በዓላት ጉልህ ዬኢትዮጵያ ልጆች ዬሚታፈሱበት፤ ዬሚታፈኑበት።
ሰልፋ ለምስጋና ለልጆቿ አስቀጥላው ቢሆን ግን ቅድስቷ አቅሟን ሴብ ማድረግ ትችል ነበር። ድካሙም መቋጫው ያማረ ዬሰመረ ይሆንነበር። ግን። ላላ።
ለወራሪው ኃይል ደግሞ ክፍተቶችን አጥንቶ አዲስ አቅም ፈጥሮ ዬሚያገግምበት ሙሉ ቡራኬ ተሰጠው።
#እኛ ምን እናድርግ?
ዬተላላዋን እናታችን ድምጽ አክብረን በፊት በፖለቲካ ብቻ እንተጋ ዬነበረውን ቢያንስ ስለ ብፁዓን አበው ህልውና ጥበቃ እንዲደረግ ዬሎቢ ሥራችን አጠናክረን እንሠራለን። አጅሬው ጃርት ዬሆነውን ተግባራቸውን ይቀጥላሉና። ሄሮድስ ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ አሊን በህይወት እያሉም፤ ሲያልፋም መሬት ልትተረጉማቸው ፈጽሞ አትችልም። ለአፍሪካም ጣር ናቸው።
ዬሆንብንን፤ እዬሆነብን ያለውን በአኃቲ መንፈስ ሐዋርያት በመሩት አደባባይ ተፈጽሞ ቢሆን ኖሮ እርግብ ከሰማይ ይወርድም ነበር። በሳማይ ላይ ምልክትም ይታይ ነበር። ዶር አብይ ወደ ሥልጣን ሲመጡ ተከታታይ የሰማይ ቁጣ ነበር። የዕድምታ ባለሙያ አላገኝም እንጂ። እኔም ጽፌዋለሁኝ።
በቁስለት ተቀበሉት። በሃዘን አዳመጥኩት። ምን ተይዞ ነው ሰልፋ ዬተራዘመው? እዬገደሉ ስምምነት? እዬዘረፋ ውይይት እነሱ ሲያካሂዱ ቢያንስ ሰላማዊ ሰልፋን አስቀጥሎ በፍሬ ነገሮች ላይ ብቻ ማተኩር ይጠይቅ ነበር። እነሱ እዬተወያዩ መግለጫወች ሲንጋጉ ነበር። "ቁሞ ቀር???" ስላቁ፤ መስቃው፤ ልግጫው ………
ገዢ መሬቷን ቅድስታችን አስረክባለች ብዬ አስባለሁኝ። በሙት መሬት ላይ ድል በቀጣይ? ዲታ አቅሟንስ መልሳ ልታገኜው ትችላለችን? እግዚአብሄር ይወቀው። በፆም ግድፈት። በሱባኤ እክልን መጫን። ያ ሁሉ ገድለ ዊዝደም በአንድ ዲስኩረኛ ተረታ። ያሸነፈው ቲም ማህበረ ኦነግ ነው።
ወረራው መሠረትን ከመንቀል ጋር ተስማምቶ ስለመሄዱ ዬዘመን ተርጓሚ ያስፈልጋል። በመንፈሳዊ። በገሃዱ ዓለም ምልሰት ወደ 500 ዓመት ማድረግ ነው። ዬሚፈሩት ነገር ሁሉ ይሆናል። ብዙ ግራጫማ አመክንዮ ታጭቆ ዬተያዘበት #ዕምል ዘመን ላይ ነን።
ብፁዓንን ፈጣሪ ይጠብቅልን። አሜን። ዬማቱሳላን ዕድሜ ይስጥልን። አሜን።
እግዚአብሄር ይስጥልኝ።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
11/02/2023
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ