ደስታን ማኔጅ ስለማድረግ። ትጥቅ መፍታት ??? ዘመኑ ቴርሞሜትር ገዝቷል። ስክነት።

 

ደስታን ማኔጅ ስለማድረግ። ትጥቅ መፍታት ??? ዘመኑ ቴርሞሜትር ገዝቷል። ስክነት።
"የቤትህ ቅናት በላኝ።"
መቀሌ ተያዘ ሲባል ፈንጠዝያውን በሚመለከት በምልሰት ልመልሰው ያንጊዜ ይህንኑ ጭብጥ ጽፌያለሁ። ጦርነት እንደማያስፈልግም ጽፌያለሁኝ። ብዙ የማኔጅመንት ችግር አለብን። ደስታ ምድራዊ ነው። ሐሴት ግን ምድራዊውም ሰማያዊም ነው። አሁን ደስታ በሁለቱም ወገን አያለሁኝ። ድህረ ገፆችንም ዞር ዞር ብዬ አይቻለሁኝ።
እርግጥ ነው ትንፋሽ ተገኝቷል። 100/200 ዓመት የማናገኛቸው ብፁዓኑ ለሰከንድ በሲኦል መሪወች ውስጥ አለመሆናቸው። በተረፈ ከሰይጣኒዝም ምህረት፤ ከመቃብር ስፍራ ሰናይ ዬለም። አብይዝም ሰይጣኒዝም፤ አብይዝም ዬመቃብር ሥፍራ ነው። ስፅፈው ባጅቻለሁኝ። ደስተኞች በልክ ያዙት። ለምን? በሦስት ምክንያት።
1) ተጨማሪ ደስታ ስታገኙ መደርደሪያችሁ እንዳይሞላ።
2) ደስታው ሲሟሽሽ ተስፋ ቆራጭ እንዳትሆኑ እና እንዳትታመሙ።
3) ፈጣሪ ፈንጠዝያው ሲያል ምርቃቱን አንስቶ እርግማን እንዳያዘንብ።
በመንፈሳዊው ሳይሆን በገኃዳዊ አስተምህሮ ዬዘመኑ የፖለቲካ ባህሪ አሉታዊ ዴሞግራፊ ላይ ነን። ይህ ማለት ዘመነ ወረራ፤ ዘመነ፤ መስፋፋት፤ ዘመነ ገዳ፤ ዘመነ አስምሌሽን፤ ዘመነ ዲስክርምኔሽን። ከዚህ በተጨማሪ ዘመን መጣሽ ገመናወች ደግሞ አሉ። አልዘረዝራቸውም። ግን ሄሮድስ ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ ሁሉንም ዓይነት የከንቱነት መሞከሪያ #ሰሌዳቸው ኢትዮጵያ መሆኗን አትዘናጉ። አፍሪካንም ከቻሉ። ለዚህ ነው ፓን አፍሪካ ሙቭመንት ይጀመር ዬምለው።
መንፈሳዊውን በሚመለከት ለተዋህዶ ልጆች ሙሴ አለን። ቃላቸውን እንጠብቅ። የበዛ ፈንጠዝያ ቤተ መቅደሳችንም አትፈቅድም። ዘመኑ ዬሰጠን ፀጋ ቴርሞሜትር ነው።
ለአቶ ወንድም አቤ ቱኩቻው ግን መልዕክት አለኝ ርዕሱን ስላዬሁ ምቀኞች ምንትሶ ቅብጥርሶ ይላልና። እሱን ደልቶታል እና። ዬመጀመሪያው ዕለት ሥራህን ሪባይዝ አድርገው ልለው እሻለሁኝ። አልነበርክም አብረህን። ሰሞነ ጥቁርን አግልለህዋል። እንዲፀና ለምትማፀነው ዬገዳወዖዳ ሥውር እጅ ተፈጥሯዊ፤ ሰዋዊ እንዲሆን ምከረው። ድህነቱን ሳይሆን እንጦርጦሱን እያፋጠናችሁት ስለሆነ። ይህ የደም ዘመን ምኑ አደብ ይሰጠው ይሆን? ኢትዮጵያን ቀንቶባት፤ ተመቅኝቶ መፈንቅል ላይ ስላለ። ልብስ አይደለም ኢትዮጵያዊነት ውስጥ እንጂ።
ዬሚያንቀላፋ ይኖራል። እፎይ ተገላገልኩ ብሎ ትጥቁን ዬሚፈታም። ሆድ እና ቀን ዬማያርድን የቆረጥን አለንበት። ዕንባ እስኪቆም እንተጋለን። አንድ ድህረ ገፅ ሥሙን አልጠቅስም ከጉድጓዱ ስርዓት በከፋ መልኩ #ጥምልምል አድርጎ ጽፎት መንፈሳዊ ተጋድሎውን አንብቤያለሁኝ። #ጥጋበኛው መንግሥታችሁ #ዝልግልጉ ተግባሩ ላመጣው ጦስ ተጠያቂው እሱው ልሙጡ አስተዳደራችሁ ነው። እሱን ግሩት። ኢትዮጵያ በዘመኗ ሁሉ እንዲህ ልቅ በሆነ አናርኪዝም ተመርታ አታውቅም። ጨካኝ አይዟችሁ ባዕቱን የተዘረፈበትም ዘመን። ከቤቴ ሁላችሁም ስላላችሁ ታዩት አላችሁ።
እኔ እንደ ሥርጉተ ሥላሴ ግን ትጥቄ የሚላላው ነፍሴ ከሥጋዬ ሲለይ። ዕውነት፤ መርህ፤ ፋክት፤ ክብር እስኪመለስ ትጋቱ ይቀጥላል። ለሙሉ የሥርዓት ለውጥ ነው የምታገለው። አሁን አመጣሽ ጥገናዊ ለውጥም እንደሚኖር አውቃለሁኝ። ለእኔ በዴሞግራፊ ውስጥ የሚገኝ ፈውስ ዬለም።
ፖለቲከኞች ወጀብ በመጣ ቁጥር መጠለያ እንደ ፓራሳይት መጠለያ ዛኒጋባ ከመፈለግ ሥራ ሥሩ። አቨውንም ተጨማሪ ጫና አትፍጠሩባቸው፤ ነፃነታቸውን አትጫኑት። ዲስክርምኔሽን ስለማይ ነው። ማኒፌስቶ ለማዘጋጀትም ዬሚያስቡ አይቻለሁኝ። 50 ዓመት ሙሉ ዬተወገዘች በፀና ጽናቷ ህልው የሆነችው መሪዋ መንፈስ ቅዱስ ነው። ለመንፈስ ቅዱስ ደግሞ ፕሮፖጋንዲስት አያስፈልገውም።
ዲያቢሎስ እሷን አያሸንፋትም። ይህ ሊታወቅ ይገባል። ተጋድሎዋም ይህው ነው። መንፈሳዊ ጎዳናዋ። ከጋህዱ ዓለም ጋር አንዘበራርቀው።
እግዚአብሄር ይስጥልኝ።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
11/02/2023
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።
ስክነት!

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።