መንፈሳዊ የሐዘን ቀን በብሄራዊ ደረጃ አዲስ አበባ ሰላማዊ ሰልፋ ይቻላንል? ኦሮምያ ክልል ከፈቀደ ብቻ። ይህ ለብዙወቻችሁ መርዶ ሊሆን ይችላል።

 

መንፈሳዊ የሐዘን ቀን በብሄራዊ ደረጃ አዲስ አበባ ሰላማዊ ሰልፋ ይቻላንል?
ኦሮምያ ክልል ከፈቀደ ብቻ። ይህ ለብዙወቻችሁ መርዶ ሊሆን ይችላል።
"ዬቤትህቅናት በላኝ።"
በጣም ለረጅም ጊዜ ጽፌበታለሁኝ። አዲስ አበባ ላይ ምንም ዓይነት ህዝባዊ ንቅናቄ በአደባባይ አይፈቀድም። ምክንያቱ ከፔጄ ላልቆያችሁ ለአዲሶቹ መርዶ ሊሆን ይችላል። እንደ ሥርጉተ ዕይታ ከመስከረም 05/2011 ጀምሮ አዲስ አበባ ዬኦሮምያ ክልል ሆናለች። ኦህዴድም፤ ኦፌኮም መግለጫ ሰጥተውበታል። ዬፌድራሉ መንግሥት ማስተባበያ አልሰጠም። አልገሰፁም። ለምንኢትዮጵያ ስለተጠለፈች።
አዲስ አበባ ውስጥ ያሉ የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ፤ ፌድራላዊ ተቋማትም ተጠሪነቱ ለኦሮምያክልል ነው። መርዶ ነው ይሄ ዬማይታዬው እኮ ጠቅላይ ሚሩ ከኦሮምያ ዬመጡ ስለሆነ አይታያችሁም ዕውነቱ። አባይ በጣና ላይ፤ ጣና በአባይ ላይ ተዋህደው ሲኖሩ አይታይም። ልክ እንደዛ ነው። ማንኛውም ብሄራዊ ክንውን በዋዜማው የኦሮምያ ፕሬዚዳንት ወጥተው ይናገራሉ። ለምን? ጠቅላይ ሚሩ አንድ ነገር ቢሆኑ ዬሚተኩ እሳቸው ስለሆኑ ነው። ደቡብ ሲሄዱም ይዘዋቸው ነው ዬሚሄዱት።
በ2011 ዬፃፍኩት ነበር አዲስ አበባ ከውጪ ሲገባ በቢዛ ይሆናል ብዬ። ለምን የያዙት አቅጣጫ ያ ስለሆነ። ለአፍሪካም አስጊ ነው። አንድ ሆቴል የምስራቅ አፍሪካ ባህል ማዕከል በኦሮምያ ዬሚል አዳምጫለሁኝ። ለነገሩ በ2019 ታህሳስ ላይ ለአፍሪካም አስጊ መሆኑን በድፍረት ጽፌበታለሁኝ።
ከሁሉ በላይሄ ሮድስ ጠሚአብይ አህመድ ዘዋራም፤ አሳቻም ናቸው። ብዙ ግሎባል ፍላጎቶችን አከማችተው ለመፈፀም ሁሉ ዲታ ሆነዋል። ይህን ያልተረዱ ሰብዕናወች ምርኩዛቸው ናቸው። አሁንም አቅጣጫእዬሰጡበብፁዓን ቅዱሳን አባቶቻችን ላይ እስር እንዲኖር ዬአቅጣጫ በር ሲከፍቱ ተመልክቻለሁኝ። በእግዚአብሄር ቤት ስለሆነ ፍርዱን እሱን ይሰጣል።
ቢያንስ ስንጽፍ ……
ዬኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት፤ ዬኢትዮጵያኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት ሲኖዶስ በማለት መግለጽን መሳት ዬለባቸውም። ያለንበት ዘመን የወረራ ዘመን ነው። ዘመኑን ለመመከት እራስን ቀጥቶ መነሳት ይጠይቃል። ሌላው መንፈስ ቅዱስን አሻቅበን ለማዘዝ ባይሞከር። ብዙ አያለሁ እንዲህ። ያልተፈቀደልን፤ ያልተሰጠንንባንዘፈቅበት።
በተጨማሪም ዬሚዲያ ሰወች ጥንቃቄ ቢያደርጉ። በተለይ ዬሚከበሩት። በምድር የመላዕክት መንፈስ ቅዱስ ሲኖዶስ ነው። ይከበር። ሲፃፍም ዕርዕስ ሲሰጥም ዝቅ ብሎ በትህትና ይሁን። "አፈረጡት፤ አፈነዱት፤ ቤተ መንግሥቱን ነቀነቁን፤ ፬ ኪሎን ጉድ አፈሉበት" እጅግ ብዙ ያልተገቡ ዕርዕሶችን አያለሁ። በተለይ ወጌሻው አንድ አፍታ። ወጌሻነቱ ጨካኙን ዘመን በማቆላመጥ ነው። ነውር ነው። ሌላ የዕርዕስ ቀለማት የቤተ እግዚአብሄር ቀለም ሰማያዊ ነጭ ነው። በዚህምጥንቃቄ ያስፈልጋል።
ብፁዓን አቨው ያለብን ግማድ ይበቃል። ሥራ አታብዙብን ብለው በትህትና ገልፀዋል። ጆሮ ያስፈልጋል። ጤናማ ጆሮ። ብፁዓኑን አቨውን በ100 ዓመት አናገኛቸውም። ከንግግር፤ ከስምሪት፤ ከአፃፃፍ ብርቱ ጥንቃቄ ልናደርግይገባል። መሻታችን ሃይማኖታችን በሚያድን መልኩ ይሁን። ምኞታችን ቅዱስ ቤተ መቅደሳችን በሚከበክብ ይሁን። አደራ።
ብዙውን ጊዜ መዝሙረ ዳዊት፤ ምሳሌን ማንበብ ይጠቅመናል።
እግዚአብሄር የሰጠን ጊዜ እንዲህ ዓይነት ጽናት፤ ብቃት፤ ልዕልና፤ ዊዝደም እናይ ዘንድ ፈቀደልን። ስለ ብፁዓን አበው ሰላም ዬእኔ፤ ያገባኛል የምንል ከሆነ ህግ መተላለፍን እንጠዬፍ። መንፈሳዊ ማትረፍን ስልት ማድረግ ይገባል።
እግዚአብሄር ይስጥልኝ።
ደህና ዋሉ። አሜን።
ደህና አምሹ። አሜን።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
09/02/2022
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።