#ለዘዋራ ሰብዕና ዬድፍረት ሐጢያት ያሰምጣል። #ለአሳቸው እና ለዘዋራው ለጠቅላይ ሚር ነው መልዕክቴ።
"ከንቱ ዬከንቱ ከንቱ ሁሉ ነገር ከንቱ።"
ሄሮድስ ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ ንቅንቅ ሳይል በትረ ሥልጣኔ ይቀጥላል ብለው በጨቀጨቅ መጪ እያሉ ነው። አሳቻነታቸው መስታውት ሆኗል። የሰው ልጅ ደም ለዛውም ሙሉ አምስት አመት ወደ እዮር ይላካል። ፈለጉትም አልፈለጉትም። አሁን ባለው ሁኔታ እሳቸው ፈብርከው ከሚፈጥሩት ቀውስ ውጪ አንድም ነፍስ ያለው ተቋም ቀርቶ አሰባሳቢ አጀንዳ ያለው የፖለቲካ ድርጅት ዬለም። ሁሉንም ፈጥፍጠው አፍዘውታል።
የተዋህደው ተዋህዷል፤ ዬተንከረፈፈው ጠርዝ ላይ ተንጠልጥሎ ኮሽ ባለ ቁጥር እዬተጣመረም እዬተሰባሰበም የመግለጫ ሲሳይ ሆኗል። በሳቸው ዘመን እንኳንስ የዓለምኔ ፖለቲካ ዬሚመጥን አቅም ያለው ተፎካካሪ የፖለቲካ ድርጅት ተጽዕኖ ፈጣሪ ግለለብ ማውጣት አይታሰብም። ምክንያት አንደኛው ሰላይ ናቸው።
ሁለተኛው በተፈጥሯቸው ዬተዥጎረጎሩ ሁነው ዬተፈጠሩ ናቸው።
ዬዓለሙን ሎሬት ሽልማት ከመውሰድ በላይ ድል ዬለም። በጨካኝ ሥርዓት ተወልገው አድገው ወስደዋል። እራሳቸው አስመራጭ ኮሜቴ ሆነው ፕሬዚዳንት ዬሚል ሥያሜ ቀርቶ ነበር ጠቅልለዋል። እሳቸው አይታመሙም፤ አካላቸው አይጎድልም፤ ድምፃቸው አይዘጋም፤ ዬምንም ዓይነት አደጋ አይደርስባቸውም። ዘሊለማዊ ናቸው። ዕሳቤያቸው ይህ ነው።
ዬሚያስታግሱን ሰጥ ለጥ ካደረጉ በኋላ በዬቤቱ እዬዞሩ በዶላር የሚያማልሉትን በዶላር፤ በስልክ ዬሚያማልሉትን በስልክ፤ በሽምግልና ዬሚያማልሉትን በሽምግልና፤ በብክል ዬሚሸኙትን በብክል፤ ለካቴና ዬሚሰጡትንም እንዲሁ። ኢትዮጵያ መዳፋቸው ውስጥ ናት።
አባ ቶርቤ መሃንዲስ፤ አስተናጋጅ፤ ሃኪም፤ ነጋዴ፤ ተማሪ፤ ዬቢሮ ሰራተኛ ሁሉ ቦታ አለ። ድምጽ ሳያሰማ ዬልቡን ያደርሳል። ይህ ግን አንድ ቀን ለፍፃሜ ይበቃል። ሰው አይሰራውም። ፈጣሪ ይሰራዋል። ሸቀጥ ለሸቀጥ ዬሆነው ሁሉ ዬዕንቧይ ካብ ይሆናል። በፈጣሪ ኃይል።
እግዚአብሔር ይስጥልኝ።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
09/02/2022
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ