ዬማተቤ ድምፅ ብቻ መሪዬ ነው።

ዬማተቤ ድምፅ ብቻ መሪዬ ነው።
"ኢትዮጵያ ነነዌ ናት። ዕውነት ማብራሪያ አይሻም። ዕውነት እራሱ በቂ ነው። ያለ ደም መስዋዕትነት አለ። ሥራ አታብዙብን። ያለብን መከራ ይበቃናል። "በኢትዮጵያ ውስጥ ዬጥቁር ቀን ታሪክ ተጽፏል።"
(ብፁዑ አባታችን አቡነ ጴጥሮስ።)
EOTC TV | "ወቅታዊ ጉዳይ | የሴራ ፖለቲካ አያዋጣም"
ከጽናት ጉልላት ዬኢትዮጵያ ቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ድምጽ በስተቀረ ሌላ ለማድመጥ አንፍቀድ። መሪ አለን። ሙሴ አለን። እረኛ አለን። መሪ፤ ሙሴ፤ እረኛ ያለው የሃይማኖት ሰው ድምፁን የሚያገኜው ከማተቡ ብቻ ነው።
አዳምጡት። በዛ መስመር እንጓዝ።
መረጃውን ማሰባሰብ ጥሩ ነው። ጉዟችን ቀያሽ ግን ዬኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ብቻ ልትሆን ይገባል። ጋዜጠኛ፤ ፀሐፍት፤ ዬፖለቲካ ተንታኝ ለገኃዱ አለምነው። ለመንፈሳዊ ሕይወት ሚስጢረ ጥምቀት ነው ብርኃናችን። ቅድስታችን ፕሮፖጋንዲስት፤ ማኒፌስቶ፤ ካቢኔ አይደለችም። የሐዋርያት መሠረት እንጂ። ድምፀ ተዋህዶ ከኢትዮጵያዊው ቅዱስ ሲኖዶስ ብቻ።
እግዚአብሄር ይስጥልኝ።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
09/02/2023
የብፁዓን ቅዱሳን አቨው ፀሎት እና በረከት ይደርብን። አሜን።

 

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።