ልጥፎች

ከቶ የአላዛሯ ኢትዮጵያ ባለቤቷ ማን ነበር?

ምስል
ከቶ የአላዛሯ ኢትዮጵያ ባለቤቷ ማን ነበር 27 ዓመት ሙሉ? „እግዚአብሄርም ቃየልን ወንድምህ አቤል ወዴት ነው አለው፤ ቃዬልም እኔ የወንድሜ የ አቤል ጠባቂ እኔ ነኝን አለ።“ መጽሐፈ መቃብያን ቀዳማዊ ፳፰ ቁጥር ፬ ከሥርጉተ©ሥላሴ  13.11.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ።  ·       መነሻ። https://www.youtube.com/watch?v=crQyRhfQXY4 ሰሞኑን በሕግ ቁጥጥር ስር የዋሉ ሰዎችን በተመለከተ የጠቅላይ አቃቤ ሕግ መግለጫ፣የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽንን በተመለከተ የፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ·       መቅደመ ብልሃት። እኔ ሥርጉተ ሥላሴ ዶር . አብይ አህመድን እንዴት ትተረጉሜያቸዋለሽ ብባል   ብሄራዊ ቀናችን ናቸው ብዬ ነው።   ኪንግ ማርቲን ሉተር አሜሪካን የማዳን የመሪነት ብቃታቸው ዛሬ ነው ይበልጥ የታዬ የተገለጠው - በወጉ። አሜሪካ ለራሷ ተርፋ የብዙዎች ተስፋ መሆን መቻሏ   የትናንት የኪንግ ማርቲን ሉተር የተጋድሎ ውጤት ነው ።   ተስፋ ባጣንበት፤ ጥልፍልፉ ችግራችን መፍትሄ አልቦሽ ሆኖ ከጭቃ ወደ ጭቃ በዙር አዳክሮ በደቆስን ሰዓት፤ ጨንቆን ጥግ አልቦሽ በሆንበት ወቅት ብቅ ያለ የመሪነት ልዩ ድንቅ ክህሎት ነው የ ዶር . አብይ አህመድ መንገድ ። እርግጥ ዛሬ ፍሬውን ልናይ አንችል ይሆናል፤ ብንከተለው ግን   ብሄራዊ ቀን የሚያስወስን ቁም ነገር በዚህ ታላቅ ኢትዮጵያዊ ህሊና ውስጥ...

"ለእግዜር አይቀርበት ለሰው አይቀርበት ሰሌ ከሰራው ቤት እኛ ገባንበት"

ምስል
„ለእግዜር አይቀርበት ለሰው አይቀርበት ሰሌ ከሰራው ቤት እኛ ገባንበት።“ „ከእኔ ጋር ማን ነበር? ትንቢተ ኢሳያስ ፵፬ ቁጥር ፳፬ ከሥርጉተ©ሥላሴ  13.11.2018 ከጭምቷ ሲወዘርላንድ። ·       መነ ሻ ከኑሮ በዘዴ ዩቱብ። https://www.youtube.com/watch?v=F3t2z-NL1DM #Eritrea   #Ethiopia Teddy Afro - ቴዲ አፍሮ ታሪካዊውን የኢትዮ - ኤርትራ የፍቅር ሩጫ ሲያስጀምር | The First Ethio - Eritrea Great Run https://www.youtube.com/watch?v=a_yFYkayg0w #Ethiopia   #TeddyAfro   #Eritrea ቴዲ አፍሮ ኢትዮ - ኤርትራ የፍቅር ሩጫን ላሸነፉ ሽልማታቸውን ሲሰጥ ·          እ ንዲህ እስቲ እንበልለት … እንዴት ናችሁ የኔዎቹ ቅኖቹ ደህና ናችሁ ወይ? አንድ ቀን ከአይቲ ጋር ሲለዩ ብዙ አዳዲስ ነገሮች ይኖራሉ። ትናንት የጥሞና ቀኔ ነበር። የሃሳብ ቀኔ። ማሰብ ማሰብ ማሰብ እስከ ህልፈት ድረስ። ስለ ሃሳብ አንድ ጹሑፍ ጽፌ የሥነ -ጹሑፍ ኮርስ ስጨርስ በምርቃታችን ዕለት እንዲቀርብ አልፎልኝ ግን ያን ቀን በጤና ጉደለት ምክንያት ሳይሳካ ቀረ። ሃሳብ የማይለቅ የህይወት ጓደኛ። በእኔ ህይወትም የሃሳብ የተለዬ ቀን አለኝ። ሃሳብ ለማሰብ የምወሰንለት ዕለት ልብሴም ቤቴም የዓውደ ዓመት ያህል ልዩ ክብር አለው።   ውዶቼ፤ እርእሱ የጎንደር ሰው የሚለው ነው። እንግዲህ ጣሊያን በሽንፈት በኢትዮጵውያን አርበኞች ሲሰናበት...

ከግራጫማ ሰብዕና ማናቆር የሚጠበቅ ነው።

ምስል
ከግራጫማ  ሰብዕና ማናቆር የሚጠበቅ ነው። „የሽንገላ ከንፈሮችን ሁሉ  እግዚአብሄር ያጠፋቸዋል“  መዝሙር ፲፩ ቁጥር ፫ ከሥርጉተ©ሥላሴ  11.11.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ። ·        መ ቅድመ ዕለት። የአብይ አቅም፤ ክህሎት፤ መክሊት፤ ሰብዕና ስኬታማ ትልም፤ ነጋዊነት፤ አዲስአዊነት፤ እኛዊነት፤ አቃፊነት፤ ሰብዕዊነት፤ ክህሎታዊነት፤ ሰብሳቢነት፤ አቅራቢነት፤ አደራጅነት፤ ታጋሽነት፤ አያያዥነት፤ ቅኔነት፤ አድማጭነት ከሳበረገጋቸው ሰዎች አንዱ አቶ ጃዋር መሃመድ ነው። ትናንትም ዛሬም የሚያብንነው ይኸው ነው። ይህ ባላስበነው ወቅት እና ሁኔታ ከች ያለው ብልህነት የእሱን ደረጃ ቁልቁል ያስገባም ነው። የአሱን ተደማጭነት ወደ አልነበረ ያሸጋገረም ነው። የጠ/ሚር አብይ አቅም ልክ እንደ ፏፏቴ ነው። ሲሰጥ አይነግር የሚባል መክሊት ነው ያላቸው። ይህን ደፍሬ እምናገረው እኔ ከ2016 ጀምሮ ስላጠናኋዋቸው ነው። የግራ ሴራ ፖለቲካ ነው ለማደናቀፍ እዬተፈታተናቸው ያለው እንጂ ሰላም ቢሆን ስንት ታምር ባዬን ነበር ከዚህም በላይ። ግን እንቅፋቱ በዛ።    በተጨማሪም በሁለቱ ሊሂቃን ማህከል በዶር ለማ መገርሳ እና በዶር አብይ አህመድ ያለው የተከደነ የክህሎት ሲሳይ ጃዋርውያን እና መሰሎቻቸውን ቢያሰበረግጋቸው ይገባል። ማወዳደር የሚቻለው ተቀራራቢ ነገር ሲኖር ብቻ ነው። ማነጻጸርም የማይደፈር ነውና።ለዛውም ከእኛ ተፈጥረው እንጂ ስካንዳንቢያ አገሮች ቢፈጠሩ ኖሮ ስንት መጸሐፍ በታተመላቸው ነበር። አብዝቼ ለሁለቱ እምጸልዬው ንፋስ እንዳያስገቡ እንዲህ በቅናዊ አሃታዊነታቸው እንዲቀጥሉ ነው። ...