ሰባት ለአንድ ከተረቦች ሁሉ የላቀው የጠ.ሚር ቢሮ ድራማ።
እንኳን ደህና መጡልኝ። ሰባት ለአንድ ከተረቦች ሁሉ የላቀው የጠ.ሚር ቢሮ ድራማ። „በፊቱ ካለው ብርሃን የተነሳ ደመናትና በረዶ የእሳት ፍምም አለፉ።“ መዝሙር ፲፯ ቁጥር ፲፪ ከሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 08.03.2019 ከእመ ዝምታ - ሲዊዘርላንድ። ጅብ ወለደ። አዎን ኢትዮጵያ በጸሐይ ውስጥ ዝናብ ሲኖር እንደዛ ነው የሚባለው። ዛሬ ሙሉ ቀን ወጀብ ነበር። ማምሻ ላይ ደግሞ ጸሐይ ወጥቶ ነበር። እንደገናም ይዘንባል። እናም ጅብም ቪንቲ ላይ ወለደ ማለት ነው። ትናንት ማምሻ ላይ አንድ ቧልት አዳምጬ ነበር። ዛሬ ጥዋት ሳተናው ላይ ስገባም አነበብኩት። በቀደመው የደርግ ጊዜ ዘመቻ ዘመቻ የሚባል ነገር ይዋቀር ነበር። አሁን ደግሞ ኮሜቴ፤ ኮሜሽን ሆኗል። ሌላ ሥራም አጣ የጠ/ሚር ጽ/ቤት ... አደናግሬ! የማንነት የወሰን ኮሚሽን የሚባል በዓዋጅ ተደራጅቷል። በፓርላማ ሹመቱ ከጸደቀ በሆዋላ ደግሞ የፈለጋችሁን ማስገባት ትችላለችሁም ተብሏል። ይህ በራሱ ሳይመረመር እንደተሸፈነ የታለፈ ገማና ነው። እኔ ጥሞና ላይ በነበርኩበት ጊዜ ስለነበር ብዙም አልሄድኩበትም ... ብቻ ዋዛ አና ብሏል ... ሜጫም እንዲሁ ... የሜጫው ሱናሜ እማ ምን ኡጡ ... ግብታዊ ነገሮች በቃ እንደወረደ ሆነ ይህም ብቻ አይደለም ተፎካካሪ/ ተቃዋሚ/ ተቀናቃኝ የሚበሉትም እጃቸውን ለኦዴፓ ሰጥተው በዚህ ተግባር ኮሚሽን ላይ ተሰማርተዋል። ቧልቱ እንዲህ ነው የተጀመረው። ተዋህደዋል ማለት ነው በትርጉም ሲቃና። አሁን ደግሞ ይህ አካል እያለ ለአዲስ አባባ እና ለኦሮምያ ሌላ ኮሜቴ አደራጅቻለሁ ብሎ ይተርባል የጠ/ሚር አብይ አህመድ ቢሮ። በነገራችን ላይ ዛሬ የ...