ሰባት ለአንድ ከተረቦች ሁሉ የላቀው የጠ.ሚር ቢሮ ድራማ።

እንኳን ደህና መጡልኝ።
ሰባት ለአንድ ከተረቦች ሁሉ
የላቀው የጠ.ሚር ቢሮ  ድራማ።
 „በፊቱ ካለው ብርሃን የተነሳ
ደመናትና በረዶ የእሳት ፍምም አለፉ።“
መዝሙር ፲፯ ቁጥር ፲፪
ከሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
08.03.2019
ከእመ ዝምታ - ሲዊዘርላንድ።



ጅብ ወለደ። አዎን ኢትዮጵያ በጸሐይ ውስጥ ዝናብ ሲኖር እንደዛ ነው የሚባለው። ዛሬ ሙሉ ቀን ወጀብ ነበር። ማምሻ ላይ ደግሞ ጸሐይ ወጥቶ ነበር። እንደገናም ይዘንባል። እናም ጅብም ቪንቲ ላይ ወለደ ማለት ነው።

ትናንት ማምሻ ላይ አንድ ቧልት አዳምጬ ነበር። ዛሬ ጥዋት ሳተናው ላይ ስገባም አነበብኩት። በቀደመው የደርግ ጊዜ ዘመቻ ዘመቻ የሚባል ነገር ይዋቀር ነበር። አሁን ደግሞ ኮሜቴ፤ ኮሜሽን ሆኗል። ሌላ ሥራም አጣ የጠ/ሚር ጽ/ቤት ... አደናግሬ!

የማንነት የወሰን ኮሚሽን የሚባል በዓዋጅ ተደራጅቷል። በፓርላማ ሹመቱ ከጸደቀ በሆዋላ ደግሞ የፈለጋችሁን ማስገባት ትችላለችሁም ተብሏል። ይህ በራሱ ሳይመረመር እንደተሸፈነ የታለፈ ገማና ነው። እኔ ጥሞና ላይ በነበርኩበት ጊዜ ስለነበር ብዙም አልሄድኩበትም ... ብቻ ዋዛ አና ብሏል ... ሜጫም እንዲሁ ... የሜጫው ሱናሜ እማ ምን ኡጡ ... 

ግብታዊ ነገሮች በቃ እንደወረደ ሆነ ይህም ብቻ አይደለም ተፎካካሪ/ ተቃዋሚ/ ተቀናቃኝ የሚበሉትም እጃቸውን ለኦዴፓ ሰጥተው በዚህ ተግባር ኮሚሽን ላይ ተሰማርተዋል። ቧልቱ እንዲህ ነው የተጀመረው። ተዋህደዋል ማለት ነው በትርጉም ሲቃና።

አሁን ደግሞ ይህ አካል እያለ ለአዲስ አባባ እና  ለኦሮምያ ሌላ ኮሜቴ አደራጅቻለሁ ብሎ ይተርባል የጠ/ሚር አብይ አህመድ ቢሮ። በነገራችን ላይ ዛሬ የፕሬስ ጉባኤ ነበር አሉ እንዲህ ወደ አዲስ እና የሜንጫውን ንጉሥ አቶ ጃዋርን ይዘው አቶ ንጉሡ ጥላሁን ሲቀርቡ ጉድ ስለሚፈላ ባለቅ ሰዓት ለማሟያ በድንገተኛ ጋዜጠኛ ሲሳይ አጌና እንዲገኝ ተደርጓል አሉ።  የሚገርመኝ ተሰብሳቢው ነው አሁን ከሜንጫ ምን አገኛለሁ ብሎ ይሆን የተጎለተው? መላ በሶች ናቸው … ሁልጊዘ በበሮድ ግግር መነከር ... ወይንም መዝለብ። 

ወደ ቀደመው ምልስት ሲደረግ የሚገርመው ያን በስንት ሃላፊነት የታጨቀውን የሰላም የሚር መ/ቤት የሚመሩት ወ/ሮ ሙፍርያት ካሜል ናቸው ሰብሳቢዋ ለዚህ ለመላ ቢሱ ኮሜቴ። ህመም እምም ነው ይህ በራሱ። 

መጀመሪያ ያን የገዘፈ ተግባር ለመውጣት አቅሙ ይኑራቸው የተሰጣቸውን የሚርነት ቦታ፤ ሥንት ሚ/መስሪያ ቤት ነው ደራርበው እዬሠሩ የሚገኙት ከልክም ከአቅምም በላይ የሆነ አካል ነው የተሸከመው ቢሯቸው።

ከዚያ በላይ ጌዲኦ ላይ ያንት ያለህ የሚሉ ወገኖች ሰሚ አጥታው እዬተንከራተቱ ነው። ከሁሉ የሚብሰው ደግሞ ኦዴፓ ያደራጀላቸው ሃይል ስብሰባ እንዳለ አካላቸው ጥሶ ገብቶ ደብድቦ ዓርማዬ የሚሉትን በእሳት አንድዶ ስብሰባውም ተቋርጦ ሰፊ የሆነ ሥነ - ልቦና ድቅት ላይ ነው የሚገኘው ድርጅታቸው። 

በዚህ ምስቅልእል ደግሞ አዲሱን ሹመታቸውን እሺ ብለው ተቀበለዋል። ወንበሩን አልጠግበው አሉ። ኢትዮጵያ የሴት ሊሂቅ ያጣች ይመስል በዬቦታው ያው እንሱ እየተገለበጡ አንብቡልን እዬተባለ ነው። እንዴት እራሱ ሥሙ ግልምት እንዳለኝ … አክብሮቴ ሁሉ እያለቀ ነው … በሌላ በኩል የደህዴን አቋም በአዲስ አባባ ላይ በሳቸው ሰብሳበቢነት ግልጥነቱ ተረጋግጧል። ተልዕኳቸው ኢትዮጵያን መዲና አልባ ለማድረግ ሃሳብ ለማቅረብ ነው። 

ሌላው በድርጅት ተግባራት ኮሜቴ ሲዳራጅ በጎደሎ ቁጥር ነው። ይህ መርህም ነው። 3 ወይንም 5 ወይንም 7 ወይንም 11 ወይንም 13 ወይንም 15 ነው መሆን የሚገባው ምክንያቱም ድምጽ እኩል ለኩል ከመጣ የሰብሳቢው ድምጽ ወሳኝ ስለሆነ። 

ይህን የግብር ይወጣ ኮሜት አንድ ለ7 በሆነ መዋቅር ነው የተደራጀው። አንድ ለሰባት የምልበት ምክንያት የሌሎቹ አቋም የሁለቱ ስለማይታወቅ ነው። የትግራይ እና የደቡብ። የብአዴኑ ተወካይ ይታወቃል። ቀሪዎቹ ባለ ሜንጫዎቹ ወይንም ለሜንጫ የሚያደገድጉ ናቸው።

መቼም እንዲህ ዓይነት ዝርክርክነት፤ እንዲህ ዓይንት ሙርቅርቅነት እኔ ከጠ/ሚር አብይ አህመድ መንፈስ ፈጽሞ አልጠብቅም ነበር። ስንዱ ነበሩ እኮ። ቀድሞ ነገር ያን ያህል የኦዴፓ ድርድር ከሳገቡ ስለምን ኮሜቴ ማደራጀት አስፈለጋቸው? ያው እንደ ታከለ ዓዋጅ አሳውጆ 16ኛውን መቶ ክፍለ ዘመን አህዱ ማለት ነበር። 

የእኛ ነው የሚሉትን አሰባሰብው ነው ፍትህ አለ ቢሉ ምን አልባት ተምሶ የተቀበረ በድን መንፈስ ሊያምናቸው ይችል ካልሆነ በስተቀር ሰው ነኝ የሚል ፍጡር ይህን የባለሜንጫ አብዛኛው ቁጥር ያለበትን ጭነት አይደለም ውሳኔውን ለመጠበቅ ደግሞ ሊስቱን ለማንበብ የሚፈልግ የለም። ለዚህም ነው እኔ ዝርዝሩን ያላቀርብኩት።በውነቱ ኦዴፓ ስልትች ነው ያለኝ።

አልቻሉበትም አልሆነላቸውም። እራሱ ያ የሚሳሳለት የአብይ አቅም እና ክህሎት ድቅቅ ብሎ ነኩቷል። ወደ መቃብርም ልኮታል የዚህ ኮሜቴ አደረጃጀት። አስፈላጊነቱም እኔ አይታዬኝም።

ከሆነም ከፖለቲካ ውሳኔ የወጣ ነፍስ ያለው፤ ከህሊናው ጋር ያለ ውክል አካል እንጂ በደመነፍስ እና በጭካኔ ተክኖ ሜንጫውን ትክሻው ላይ ይዞ እዬተንጎባለለ አገር እያመሰ ባለ መንፈስ አጭቆ ኮሜቴ ማለት ዘበት ነው። እኔ የኮሜቴ አባል ብሆን አልቀበለውም። ቀድሞ ውሳኔው ስለሚታወቅ። ምን መድከም ያስፈልጋል። ለሜንጫ ሱናሜ …

ቀልድ እኮ ነው የተያዘው። ኢትዮጵያን የቅልሞሽ ጨዋታ ነው ያደረጓት። ህዝቧንም ህሊና ቢስ ነው ብለው ንቀውታል። ብአዴን እንዳለም አይቆጥረውም ኦዴፓ። ከነመፈጠሩም ብአዴን ረስቶታል። ኦዴፓ አወዳደቁም እጅግ የከፋ ነው የሚሆነው። እሚይዘውን እሚጨብጠውን አጥቷል። ቀጣዩ እንግዲህ ጠበንጃ ይሆናል ብዬ አስባለሁኝ። ቤት ለቤት እዬሄዱ አስሶ ማሰር፤ ከስራ ማፈናቀል፤ ስብበ ፈልጎ የሚሹትን ማድረግ። ይህ ለጨካኞች ምንም አይደለምና።

መቼም እንዲህ ዓይነት የጅልነት ዝልቦነት ታሪክ አስተናግዶ አያውቅም። ያን የመሰለ የምልዕት ፍቅር እንደዛ እንዳልነበረ አድርጎ ብን ትን አደረገው? የጠ/ሚር አብይ አህመድ ስጦታስ? እንዲህ ሌት እና ቀን የባከኑበት ጉዳይ አፈር ልብሶ ተምሶ ተቀበረ።

የሆነ ሆኖ በኮሜቴው አደረጃጀት ያዬሁት የበዛ መታበይ ነው። ስለዚህ የኦዴፓ ግስጋሴ  በአጭሩ ይቀጫል። መቀጨት ስል ከህዝብ ከግሎባሉም ዓለም ፍቅር ይወጣል። ምክንያቱም ገና በጥዋቱ የተሰጠውን ፍቅር ፈቅዶ እና ወዶ ራሱ ምሶ ስለቀበረው። ይልቅ አሁን ኦዴፓ የወደቀበትን ቀን አስቦ ድንኳን ጥሎ ሀዘን ቢቀመጥ ይሻለዋል ናዝሬት ላይ።

በዛ ግብታዊ መግለጫ ስንገረም አሁን ደግሞ የሜንጫ ባላባቶች የከበሩበት አዲስ መዋቅር ዘረጋሁ ሲል ተረት ተረቱን ይዞ ከች አለ። አልሆነለትም፤ አልተሳካለትም፤ ዕድሉም ከእጁ እያመለጠው ነው። ያን የመሰለ የህዝብ ፍቅር ለሌላ አሳልፎ እየሰጠው ነው … ተዝረከረከ … ተንቦጫረቀም። ሁሉም ቦታ በአንድ ሰው ትክሻ አይሆንም … አቅም ያለው ሰው ጠፋ።

የአሁኑ መዝረክርክ ከዬት መጣ ቢባል- ኦዴፓ ስለተረገመ ምርቃቱ ስለተነሳ ነው። „ቂም ይዞ ጸሎት“ ስለጀመረ ነው። ለነገሩ የኢትዮጵያ አምላክ የከዱት ለታ እንዲህ ነው የሚያደርግ። ሁሉም ደርሶት አይቶታል። አንዱ ከሌላው መማር ተስኖት እንዲህ በክትመት ተሸኝቶ ሌላ ክትመት ደግሞ ይተካበታል።

በህልሜ ካዬሁት ባዶ ወንበር አንድ ሙሉ አካሉ ከሁለት የተሰነጠቀ የተፎካካሪ የሥም ድርጅት ሊቀመንበር አይቼ ነበር እና ቦታውን ቀጥ ብሎ ቁምጥ ብሎም እዬጠበቀ ነው  … ያው እሱም የቂም ማህበርተኛ ብላሽ ስለሆነ አይችለውም። አቅምም የለውም ... 
እና መፍቻውም መካተቻውም ምን ሊሆን እንደሚችል መድህኒተ ዓለም ይወቀው።

 ምክንያቱም ይሻላል የሚባል ስሌለ ሁሉም የቂም ማህበርተኛ ስለሆነ። ሌላው አቅም ያለውም የለም። እንዲያው እሺ ቢሉ ኮ/ ጎሹ ወልዴ ሽግግሩን ቢመሩት ይሻል ይመስለኛል። ቅንም ንጹህም ልቦና ስላላቸው። ለማስቀጠልም አቅሙም ክህሎቱም አላቸውና … ምኞቴ እሳቸው ቢሆኑ ነው … በተረፈ ግን "አሞራው በረረ ቅሉ ተሰበረ እዬተሆነ ነው …" መንፈስ ከሸፈተ ምን ነገር አለነ ... ትዕግስት ሲያልቅ ፍቅር ይሰዳዳልና።

ያሳዝናል ያ ለዛ እና ውበት እውን ሆኖ ቢሆን መልካም ነበር። አሁን ግን ባረገረገ መረብ ላይ ነው ሁሉም ነገር … ኢትዮጵያን ታሸነፍለች የሜንጫን ሱናሜ ቀጥታ ወደ መጣበት ትመለስዋለች … የኢትዮጵያ አምላክ አይተኛም አያንቀላፋም … ፍርዱንም ይሰጣል። 

Ethiopia || ሰበር መረጃ - በአዲስ አበባ ጉዳይ ጠቅላይ ሚኒስትር /ቤት መግለጫ ሰጠ ||news Abel



ኢትዮጵያዊነት የሚስጢር ፏፏቴ!

የኔዎቹ ኑሩልኝ።

መሸቢያ ጊዜ። 

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።