ዐይንም ጠንካራ መልዕክት ይልካል።
ዐይን ቋንቋ አለው። ዐይንም ጠንካራ መልዕክት ይልካል። ከሥርጉተ - ሥላሴ ( Sergute © Sselassie ) 02.04.2018 (ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ።) „እግዚአብሄርን አንዲት ነገር ለመንሁት፤ እርስዋንም እሻለሁኝ፤ በሕይወቴ ዘመን ሁሉ በእግዚአብሄር ቤት እኖር ዘንድ፤ እግዚአብሄርን ደስ የሚያሰኘውን አይ ዘንድ፤ መቅደሱንም እምለከት ዘንድ“ (ከልብ አምላክ መዝሙር ፳፮ ቁጥር ፬) · እ ፍታ። ትንሽ ነገር ማለት ፈለግሁኝ። ቋንቋ የፍቅራዊነት (LoveIsm) ረቂቅ ሚስጢር ነው። ቋንቋ የራሱ ሥርዓተ - ህግጋት አሉት። ቃል በሥርዓቱ ውስጥ ሲተገበር ሥርዓቱን ተከትሎ ቤተሰብ ይመሰርታል። የመጀመሪያ የቋንቋ ቤተሰቡ አረፍት ነገር ነው። አረፍተ ነገር ደግሞ ከፍ ያለውን ዞጉን ሲፈጥር ሐረግን ይመሠርታል። ሐረግ ሙሉ ገጽ ሲኖረው ልክ እንደ ፍጡራን ሐገር ይሆናል ቋንቋ - ለእኔ። እንሰሳት ቋንቋቸውን የሚገልጹት ወጥ በሆነ ድምጽ ነው፤ በነገራችን ላይ የእንሰሳት ድምጽ በስዋሰው የተቀመረ አይሁን እንጂ ከሰብም በላይ ግሎባል ነው። ደንበጫ ያለው ዶሮ ኒዮርክ አካባቢ ካለው ገጠር ከሚኖረው ዶሮ ጩኽቱ ጋር ተመሳሳይ እና ወጥ ነው። ጋና ያለው ውሻ ሲዊዘርላንድ ካለው ጋር ተመሳሳይ ድምጽ ነው ያለው። አውስትራልያ ላይ ያለው በግ ይሁን ፈረስ፤ ፈረስ ይሁን ወይፈን ብራዚል ውስጥ ካለው ጋር ተመሳሳይ የድምጽ አገላለጥ አለው። እንሰሳትም እንደ ሰው አካላዊ ቋንቋ አላቸው ብዬ አምናለሁ። ፍቅርን ሲፈልጉ፤ ቁልምጫ ሲፈልጉ፤ አትኩሮት ሲፈልጉ፤ ታማኝነታቸውን ሲገልጹ፤ ሲበሳጩ፤ ጸጥታን ...