ከዶር አብይ አህመድ የውስጥ ዕንባ "እኔ ብታፈርሱኝ ምን ጥቅም አለው?“
„ውዝፍ እና ክምር አምጥታችሁ ጭናችሁብኝ እኔ ብታፈርሱኝ ምን ጥቅም አለው?“ „ባልቅላችሁ ፍጻሜዬ ቢሆን ምን ትጠቀማላችሁ።“ " ጥበብ በቀደሙ ሰዎች ዘንድ ተመረመረች።" (መጽሐፈ ሲራክ ምእራፍ ቁ ፴፱ ጥር ፩) መነሻ። https://www.youtube.com/watch?v=S3wMGiT74SI ጠ / ሚንስትር አብይ ዛሬ በሀዋሳ ያደረጉት አስገራሚ ንግግር Dr. Abiy Ahmed „ ለማጥናት ጊዜ ያስፈልገኛል ገና እኮ ከተመረጥኩ እኮ ሁለት ወሬ ነው። !! ለእኔስ ጊዜ አያስፈልገኝም ?! ውዝፍ እና ክምር አምጥታችሁ ጭናችሁብኝ እኔ ብታፈርሱኝ ምን ጥቅም አለው ?“ ማልቀስ አይገልጸውም። ባለፈውም ኦቦ ለማ መገርሳ መሰሉን ተናግረው ነበር። እነሱ ታግለው ነፃነቱን ያስከበሩለት ሁሉ ሜዳ አልበቃው ብሎ ሲያብጠለጥላቸው ... ህም! https://www.youtube.com/watch?v=M6Ca9fvJ8oQ heger Werewoch - “ ለ 40 ሺ ነፍሶች ይቅርታ ማድረግ በሰው ልጆችም ሆነ በፈጣሪ ፊት ጥሩ ስራ ነው ” - የሸገር ወሬዎች „ ውዝፍ እና ክምር አምጥታችሁ ጭናችሁብኝ እኔ ብታፈርሱኝ ምን ጥቅም አለው ?“ ልብ ይሰነጥቃል። ህሊናን ከሁለት ይገምሳል። እኔ እሰከ ዛሬ የኖርኩት ይበቃኛ ል። ትግሌም የኢትዮጵያ እናቶች የ43 ዓመት ዕንባ እንዲደርቅ ነበር። አሁን ኢትዮጵያ ብቁ ሙሴ አግኝታለች። እናም ዕድሜዬ የቀረኝ ካለ ፈጣሪዬ ለዶር አብ...