አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ዕንቁ ሴኒጋል 2 ለ 1 አሸፈ።
የአርንጓዴ ቢጫ ቀይ ዕንቁ ሲኒጋል አውሮፓዊውን የፖላንድ ቡድን
ሁለት ለአንድ አሸነፈ። ከሥርጉተ ሥላሴ 19.06.2018 ከሲዊዘርላንድ።
"በጎ ነገር ከጥንት ጀምሮ ለበጎ ሰዎች ተፈጠረች፤ እንደዚሁ ክፉ ነገርም ለሃጢያተኞች ተፈጠረ" (መጽሐፈ ሲራክ ምዕራፍ ፴፱ ቁጥር ፳፬)
እቴ ድንቡልቡሊት ሉላዊ አቅመኛ ሁሉ ያገኘ ባሰኘው መንገድ ይደልቀኝ ብላ ራሺያ ከተመች። አቤት እንደ እሷ ፍቅርን በመደለቅ የሚያሽሞነሙን እኮ የለም። ውበቴ ነው ድለቃ ትለላች። ድለቃው ላብ በላይ ሲያደርገኝ አራጋቢዎቼ አሉልኝ። እልልታው ሲያመረኝ ደግሞ ሌጋባው ፊሻካ የት ሄዶ ትለናለች።
ብቻ የዘንድሮ የዓለም ዋንጫ ርስት ተደረገ፤ ዕድሜ ለመደመር ፖለቲካ … በሉ ዛሬ አንድ ጨዋታ አዬሁኝ። ሙሉውን።
ስችል ቀን ስመለከት አልጨርሰውም አገራዊ ጉዳይ አዳዲስ ክስተቶች ስላሉ ሙሉውን አልከታተለውም። የሆነ ሆኖ ካዬሁት ብዙም ድንቅ ጨዋታ አልገጠመኝም። አንዳንድ ጊዜ ታጣፊ አልጋ የገዙ እስኪመሰል ድርስ አሰልቺም ነው። ዛሬ በሲዊዙ ሰዓት አቆጣጠር 17.00 ሰዓት ላይ የተጀመረው ጨዋታ ሁለት ለአንድ በሆነ ውጤት ተጠናቀቀ።
ጨዋታው አፍሪካዊዉ የሴኔጋል ቡድን ከአውሮፓዊው ከፖላንዱ ጋር ነበር። እውነት ለመናገር እስከ አሁን ከዬኋዋቸው ጨዋታዎች በጣም በተሻለ ሁኔታ ነበር። በተለይ በመጀመሪያው የጨዋታ ክ/ ጊዜ የሴኔጋል ቡድን ጥበባዊ ጨዋታ ማራኪ ነበር። አንድ ጎል አስቆትሮ ነው ለ እረፍት የወጣው። በጠቅላላ በጨዋታው ይዘትም ፖላንድ በመከላከል ሴኔጋል በማጥቃት ሲጫወቱ ከቆዩ በኋዋላ በመጨረሻ ደቂቃ ላይ ፖላንዶች ድንቅ የሆነች ግብ አስቆጠሩ እና እና አንድ ለሁለት ሆኖ።
በቀሩት ባለቁ ጥቂት ቅርጥምጣሚ ደቂቃዎች ፖላንዶች ከተከላካይነት ወደ አጥቂነት የመሸጋገር እድገት ቢያሳዩም ጠይም ዕንቁ አብሶ ዘንድሮ መቼም ዘመኑ የአረንጓዴ ቢጫ ቀይ ሆኖ ሴኒጋል ሁለት ፖላንንድ አንድ በሆነ ውጤት ጨዋታውን በድል ተፈጽሟል።
ሴኒጋሎች ወጣቶች እና ፈጣኖች ሲሆኑ ፓላንዶች ደግሞ ፈዘዝ ብለው ታይተዋል። ሁለተኛዋን ጎል ሴኒጋል ያስቆጠረው የፖላንድ ጎል ጠባቂ ቡና አምሮት ቡናዋን ፉት ሊል ማህል ሜዳ ላይ ካለው ካፌ ቤት ጎራ ሲል፤ እግረ መንገዱንም ኢንተርኔት ቢጤ ሲጎራጉር ፈጣኑ የሴኒጋል ቡድን ዕድሉን ከመረብ ጋር ሞሸረው እና አሸናፊነቱን አረገጋጠለት።
እርግጥ ነው ሴኒጋል ትንሽ መጋፋት በዛ አድርጎ ሁለት ቢጫውንም በተቀማጭ ከሁለት ነጥቡ ጋር አዳምሮ ነው ያሸነፈው። ለዛውም የጀርመኑ ባዬር ሙንሽን ኮከብ ተጫዋች ሊቦንድስኪ ጋር ነው በዚህ የልዩነት ጨዋታ የተላያዩት። ይህን ሳይ ማን ትዝ እንደለኝ ታውቃለችሁ ያ ጀግና ኮ/ አብዲሳ አጋ።
ስፖርት እና ፍቅር ይኑሩ!
መሸቢያ ጊዜ።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ