Adaptable ተስማሚ፤ Visibility ተጎብኝነት።

ስለምን ይሆን ዶር አብይ አህመድ 
መከላከያውን የተፎካካሪ ፓርቲ አካላት
እንዲጎበኙት ይደረጋል ያሉት?
ከሥርጉተ ሥላሴ 19.06.2018 ከገዳማዊቷ ሲዊዘርላንድ


               „መባህን አግባ አስበህ፤ ስንዴህን አግባ የተቻለህን ያህል መሥዋዕትህን አብዝተህ አቅርብ።"
                                          (መጽሐፈ ሲራክ ምዕራፍ ፴፰ ቁጥር ፲፩)

  • ·        የመነሻ ሃሳብ።


በትናንትናው ውሎ የፓርላማ ጉባኤ ውሎ የክቡር ጠ/ ሚር አብይ አህመድ መከላከያን በሚመለከት ለተፎካካሪ ፓርቲዎች ክፍት ይሆናል ያሉበት መሰረታዊ ምክንያት በግርግር የፖለቲካ ትርምስ እንዲታይ ስለማልሻ እራሱን አስችዬ መግለጽ ፈለግኩኝ።

  • ·        ውኛው መሪ!


የዶር አብይ አህመድ ሰብዕና ሰውኛ ነው። ሰውኛ መሆን ደግሞ ከሰውኛ መንፈስ ጋር የተዋህደ ነው። ከሰውኛ ፍላጎት ጋር የተስተገባረ ነው። ከሰውኛ ጠርን ጋር ደማዊ፤ ደማማዊም ነው። ጥምረት አይደለም ውህደት ነው። ውህደቱ የፖለቲካ ሊሂቃን የቀደሙት እንደሚሉን በማስመስል የሚለበጥ አይደለም። ሰው ለመሆን የፈቀደ ሰው ሰው ነው። ለሰው ልጅ ትልቅ አክብሮት ያለው። ለሰው ልጅ አለው አክብሮት የሚመነጨው ደግሞ "ቃል" ሰው ስለመሆኑ ስለሚያምንበት ነው። "ቃል" ስለፍቅር የቀደመ ነው። "ቃል" ነው መዳህኒታችን እዬሱስ ክርስቶስን ወደ መሬት አውርዶ እንደ ሰው ሰውን መከራ እንዲቀበል ያደረገው። "ቃል" ነው ፍቅርን የሰጠን። አብይንም የሰጠን "ቃል" ነው።፡ስለሆነም የአብይ መንፈስ የቃል ሐዋርያት ከፈጣሪያቸው ህግጋት ጋር በውል የተዋህደ ስለሆነ መፈጠሩ በአምሳሉ ስለሆነ ውስጡ የእሱ ማዳሪያ እንዲሆን የፈቀደ ነው። ስለዚህም ሰዎች ስለሚያስቧቸው፤ ሰዎች ስለሚያልሟቸው፤ ሰዎች ስለሚያመኟቸው፤ ሰዎች ሰለሚታትሩባቸው፤ ሰዎች ሰለሚያምኗቸው፤ ሰዎች ስለሚተገብሯቸው፤ ሰዎች ስለሚፈጥሯቸው ወዘተ ነገሮች ሁሉ ቤተኛ ናቸው በዚህ ቅን፤ ደግ ንጹህ መንፈስ ውስጥ። የእኔ የራሴ ወዜ ደሜ ብለው ነው የሚያደምጡት።
  • Adaptable ተስማሚ፤

በዚህ ስሌት ስንሄድ ባለፈው ጊዜ የመከላከያ ከፍተኛ መኮነንኖችን ባለቅኔው ጠ/ ሚር ሲያነጋግሩ ቋሚ መንፈስን፤ ዘላቂ መንፈስን ማቋዬትን አበክረው ገልጸዋል። እያንዳንዱ እራሱን ለማስቀጠል በህዝብ ውስጥ ራሱን ለማኖር መፍቀድን በጥሞና ገልጸዋል። ይህ ምን ማለት ነው? የቀደምቱ የንግሥና ሹም ሽር ሰራዊቱን እያሸጋገረ መጥቶ ወያኔ ሃርነት ትግራይ ግን አልተጠቀመበትም። ትወልድ ሊተካቸው የማችሉ ዕሴቶችን አወደመ። ይህም ብቻ አይደለም ደርግም ቢሆን ዘመን ሊተካቸው የማይችሉትን ከፍተኛ መኮነንኖች እነ በዬዘመኑ አመከነ። ትውልድ ቀርቶ አፍሪካ ልታገኛቸው የማትችለውን ከፍተኛ ሊሂቃንን ዕሴት አልባ ታሪክ ጠቆረ። እነዚህ ሃብቶች የአገር ትሩፋቶች ናቸው። ትክ የሌላቸው። ደርግ የኢትዮጵያ ሠራዊት እንዲቀጥል ቢያደርግም ባለውለታዎችን ቀዝፏል። ይህ እንግዲህ እንደ ውርስ ተይዞ ጭራሽ ወያኔ ሃርነት ትግራይ ስልጣን ሲይዝ ጠቅላላ ባህር ሃይል፤ አዬር ሃይል፤ ምድር ጦር፤ ፖሊስ ሠራዊት ሁሉም ተበተነ ለማኝ ሆነ። ያን ጊዜ በሠራዊቱ ውስጥም የለዬለት ሸር ስለነበረ ይፍርሳል የተባለው ፓርቲው ኢሠፓ ብቻ ነበር። ግን ሁሉም ደረሰው። በዚህ ውስጥ የተቀጣለውን የህዝብ ዕውቅት እና የባከነው የትውልድ አንጡራ ሃብት፤ የነደደው ተመክሮ፤ የጋዬው ሳይንስ፤ መላ አልቦሽ እርሾ አልቦሽ የቀረው ትውልድ በርቀት አዳመጡት ወገኖቼ።

ለመሆኑ ኢትዮጵያ ኋላቀር ያልሆነች ማን ይሁን? ይህን በግልጽ ቋንቋ ለዘመኑ መኮንኖቹ ጠ/ ሚር አብይ አህመድ በግልጽ በአደባባይ ተናገሩ። ራሳቸውን አፍረሰው ማዕረጋቸውን ማስቀጠል እንደማይችሉ እንቅጩን ነገሯቸው። "ከፈረሰ አገር ጄኒራል ያልፈረሰ አገር አስር አለቃ ይበልጣል ይከበራል" ብለው።

ይህም ብቻ አይደለም ሠራዊቱ ጎሳ ሊኖረው እንደማይገባ ገልጠዋል። ሲሞቱ እኮ አብረው ነው የሚቀበሩት። ግን ሲኖሩ በጎሳ ተከዝነው ነው። ሲሾሙም እንዲሁ። መቼስ የእክሌ ጎሳ ከሞት አይቀርም። ሠራዊት የህዝብ ተስፋ እንጂ የባልሥልጣን ተስፋ መሆን አይገባውም ነው ፍሬ ነገሩ። የተኖረበት 27 ዓመት ግን ሠራዊቱ የወያኔ ሃርነት ትግራይ ሥልጣን ማስጠበቂያ፤ የአንድ ጎሳ ፈቃድ ማስቀጠያ ሆኖ ከህዝብ አፍቅሮተ አዱኛ ጋር ግን ከባህር የወጣ አሳ ሆኖ ነው የተኖረው።

የደርጉስ ለማኝ ሲሆን እያዘነ ቁራሽ ሰጠው ደጉ የኢትዮጵያ ህዝብ የእኔም ይለዋል። ለወያኔ ሃርነቱ ሠራዊት ግን ለማኝም ቢሆን ቁራሽ አያገኝም። በፍጹም። ከህዝብ ጋር ተለይቷል። ጎሳ አምላኪ ስለሆነ። ኤትክሱም ሙጥጥ ብሎ ጠፍቷል። ይሄነን ኤቲክስ አምጦ መውለድ ግድ ይል ሰለነበር በተለዬ ሁኔታ ለመረዳት እጅግ ከባድ ነበር ማብራሪያው። ለተወሰነ ሰዓት የሚባልም አይደለም። ለወራት ቢዘለቅም ያን የመሰለ የጭብጥ አስኳል አፍልቆ መስመር ለማስያዝ ከባድ ነው። እኔ አራሴ ሳዳምጠው ከብዶኛል። ወንድሜ ከካናዳ ደውሎልኝ ሲነግረኝ ሙሉ ለሙሉ ገብቶኛል አለኝ። እኔ ደግሞ 6 ጊዜ አዳምጬዋለሁኝ አሁንም እንደ ከበደኝ ነው። እርግጥ ነው ዶር አብይ አህመድ በመከላከያው ውስጥ ስለነበሩ አጠቃላይ ዕውቀት እንዳለቸው ባምንም ግን ካሰብኩት በላይ ጥልቅ ነው የሆነብኝ የግንዛቤያቸው አድማስ። በዛ ላይ የደህንነቱ ሙያ ሲታከልበት የማይደፈር ነው የሆነው። የሆነ ሆኖ የሰራዊቱ መኮንኖች ገለጻ ዋናው እንብርት ፓርቲዎች ተወዳድረው ሲያሸንፉ፤ ለዛም ተልዕኮ የህሊና መሰናዶ የማዘጋጀት ነው። የመሰናዶ ት/ ቤት ነበር። ዋናው ተልዕኮ ኢትዮጵያዊ የሆነ መንፈስን መስረጽ ነው። የነበረውን  የኢትዮጵያ የመከላከያ ሠራዊት ተክለ ቁመነውን ሙሉ ለሙሉ በመቀዬር ኢትዮጵያዊ አድርጎ የማብቀል።  

  • Visibility ተጎብኝነት


በሌላ በኩል ወገናዊነቱ ለህዝብ እንዲሆን በማያወላዳ ሁኔታ ነበር የገለጹት። ይህን ነው ትናንት ባደረጉት ገለጻ መከላከያውን አንዳንድ ነገሮችን ካስተካከልን በኋዋላ ተፎካካሪ ፓርቲዎች ይጎብኙታል ሲሉ፤ ከሠራዊታቸው ጋር ትውውቅ ያደርጋሉ ማለት ነው። በዛ ጉባኤለ ላይ ለኢትዮጵያዊ ተፈከካሪ ፓርቲዎች ተስማሚ Adaptable ሁኑ ብለዋቸዋል ። ይህ አዲስ ጥርጊያ መንገድ የማለማማድ ሥራ ለመሥራት ነው። ፓርቲዎች ይወዳደራሉ ሲወዳደሩ ሠራዊቱ ማንም ቢያሸንፍ አይደነግጥም፤ ያሸነፈንው ፓርቲ ለመቀበልም አይቸገርም። በሌላ በኩልም ገዢውን ፓርቲ ደግፎ ሌሎችን የሚቀጠቅጥበት ምክንያት አዲሱ ፓርቲ ሥልጣን ሲይዝ ከኑሮዬ ያፈናቅነኛልም በማለት ለራሱም ከመስጋት ጭምር ነው። በ አካልም በ  አ ዕምሮም እንደ ጠላት ከመተያዬት ያወጣል። ማየት መልካም ነገር ነው። አንዲት እህቴ አዋሳ ላይ "ተፎካካሪ" ሲሉ እኔ አስበው የነበረው "እንደ ጠላት" ስለነበር አሁን ተረዳሁኝ እነሱም ወገኖቼ እነሱም የ እኔ ስለመሆናቸው ነበር ያሉት ዕድምታው። "ቃል" ይህን ያህል የመንፈስ ለውጥ ያመጣል። "አትናገር ወደ ሥራ ግባ ቃል ምን ሲያመጣ" ወዘተ ለሚሉት ታላቅ መልእክት ነበር እኒያ ክብርት እህቴ ያስተላለፉት። አሁን ተወዳዳሪ ፓርቲዎች የአገር አካል ብቻ ሳይሆኑ የነፍስም የደምም የሥጋም አካል መሆናቸው ነው የታወጀው። ይሄ ሰውኛ ነው። ይህን ሰውኛ መንፈስ ባልባሩዱ ደግሞ ደግኖ፤ አጥምዶ ገዢ መሬቱ ላይ ጎድቦ ሳይሆን እንግዶቼ የእኔዎቹ ብሎ እንዲቀበል ፍቅር ሰጥቶ ፍቅር እንዲቀበል ነው ኮረኮንቹ እዬተጠረገ ያለው ...  

በሌላ በኩል ለቀጣይ ህይወቱም ሠራዊቱ እርግጠኛ ሆነ ግን ገለልተኛ በመሆነ ሁኔታ ሁሎችም የ እኔ ናቸው በማለት ለኢትዮጵያ የሚጠቅም ህዝብ የፈቀደው፤ ህዝብ ይሁንታ የሰጠው ማንኛውም ፓርቲ ከመጣ ሠራዊቱ ደግሞ ህዝብ እንዲወደው፤ ህዝብ የእኔ እንዲለው ሥር ነቀል ለውጥ ካመጣ ለወል ተልዕኮ የወል አቅም ለተሻለ ብልጽግና ብቻ ሳይሆን የተሻለ ትወልድ ለመተካት መሠረት ይጥላል ማለት ነው። እራሱ ሠራዊቱ ትውፊት ይሆናል ማለት ነው። ተተኪዎችንም በዚህ ሞራል ይገነባል። ይህን የጤንነት ሃዲድ ነው የዘረጉት። እያንዳንዱ የፖለቲካ ሰው፤ እያንዳንዱ የፖለቲካ ሊሂቅ፤ እያንዳንዱ ጸሐፊ፤ እያንዳንዱ ተንተኝ ቁጭ ብሎ መማር አለበት። አቃቂር እያወጣ በማያውቀው፤ ባልነበረበት በሳል አመክንዮ ከሚሰላቅ ይልቅ። የአብይን እና የለማ መንፈስ መጥናት አለበት የምለውም ለዚህ ነው። የአብይም ሆነ የለማም ሆነ የገዱ መንፈስ የኢትጵያዊነት አዲስ የትምህርት ክፍለ ጊዜ ነው።
  
አንዱ ሦስት ወር ይበቃዋል ሲለን፤ ሌለው ስድስት ወር ሲለን ፤ ሌላው ሽገግሩን ከፈጸመ ዓይኑን ማዬት አያሻንም ሲል፤ ሌለው ደግሞ ለዛውም ዘመን ጠገብ አንጋፋ ጋዜጠኛ ተለጠጠ ሲለን፤ ሲብተከተክ የከረመው ሁሉ አደብ ገዝቶ የኢትዮጵያን የተስፋ አዲስ ብሩህ ጥበባዊ ምስባካዊ መንገድ ሊያጠናው ግድ ይላል። ኢትዮጵያ አዲስ ዘመን ላይ ናት … ለዚህ ነው ሥርጉተ ሥላሴ የሽገግር መንግሥት፤ የአደራ መንግሥት አስፈላጊ አይደለም የምትለው … ኢትዮጵያ በህልሟም አላሰበችውም ነበር ይህን የመሰለ ሙሴ አገኛለሁ ብላ። ኢትዮጲሻ ቀኑ ፏ ብሎላታል። ጉሙሙ ተገፏል። የፈጣሪ ሥራ የእጅ የዳንቴል ሥራ አይደለም። ግርግር ተፈጥሮ እኮ ይህ አቅም ከስሞ እንዲቀር የተደራጀ ዘመቻ ነበር። ግን አማኑኤል ታምሩን ሠራ በጥበቡ።
  • አብይ ምን አለው?

በዚህ ሰው ጭንቅላት ውስጥ ሰው ብቻ ነው ያለው እንጂ ማንፌስቶ አይደለም። በዚህ ሰው ህሊና ውስጥ ፍትህ ብቻ ነው ያለው እንጂ ኢጎ አይደለም። በዚህ ሰው ነፍስ ውስጥ ክብር አይደለም ያለው ማግስት ብቻ ነው። በዚህ ሰው ጭንቅላት ውስጥ የተቃጠለ ካርቦናዊ አይደሊዮሎጂ ሳይሆን የርትህ ሰናይ ነው። በዚህ ሰው ኩላሊት ውስጥ አፍሪካዊነት ብቻ እንጂ ምቀኝነት አይደለም ያለው። በዚህ ሰው አዕምሮ ውስጥ መልካምነት ብቻ እንጂ ሴራ አይደለም። ሰው ማዳን፤ ስለሰው ልጆች መኖር እራስን በመገበር። ሌት ተቀን ካለ እንቅልፍ መባተል ብቻ እና ብቻ። ንጹህ ውሃ ተጠጥቶ የማይጠገብ። እንደ አንጀራ የማይሰለች። ይህን ተጻሮ መቆም ዲያቢሎስነት ነው። አርዮስነትም ነው።

እኔ ከፖለቲካ መሪዎች አንድ ሰው ብቻ ነው በግልጽነት ቁልጭ ያለ ፖለቲካዊ አቋም ያደመጥኩኝ የመኢሶን መሪ ዶር ነገደ ጎበዜ። የምርጫ ሥርዓት ቢኖር „እኔ እምመርጠው ዶር አብይ አህመድ ብቻ ነው“ ነበር ያሉት ዶሩ። ምን መልዕክት አለዎት ሲባሉም „ቀጥል ©አብይ“ ነው ያሉት። ከሲቢክስ ድርጅት መሪዎችም ሙሽራዬ ዶር ኦባንግ ኢትዮጵያ ሜቶ „ጀግናዬ ጠ/ ሚኒስተሬ፤ መሪዬ ነው“ ያለው። ሌላው አገር ቤት ያሉትን ሁሉንም የሰማችሁት ነው። ዘጋቢ ሆነው ነው ያረፉት። ይሄንን አቅም ተወዳድሮ ለማሸነፍ ሌት እና ቀን ተሠርቶም እሚደፈር አይደለም። የሁሉንም አቅም አብረን ኖረን ስላዬነው። አንዲት አጀንዳ ለማጽደቅ ምን ያህል ጣር እንደ ነበረ የኢተፖድህ ሁለተኛ ጉባኤ ሰብሳቢ የነበሩት ዶር. ነገዴ ጎበዜ ምስክር ናቸው። አጀንዳ ለማጽደቅ ብቻ ተውሎ ታድሮ ተውሎ … ባዶ እጅ ነበር ከህዝብ ጉባኤ ጋር ገጥ ለገጥ የተገጠመው።

  • ሚስጥሩ። 


የሆነ ሆኖ ሚስጥሩ ኢህአዴግ ቢሸነፍ ሠራዊቱ ማንም ይምረጥ፤ ማንም፤ ህሊናው ስንዱ ሆኖ መጠበቅ ማስቻል ትልቁ ግባቸው ነው። ይሄ ሲባክን ለነበረው የኢትዮጵያ አንጡራ ሃብትም፤ የሰለጠነው አቅም ደግሞ የሰው ሰው ነው፤ የሚበተነው ቤተሰብም፤ የልጆች ጉዳይም፤ የእናቶች ጉዳይም ትወልዱም ጉዳይ ቀጣይነትን፤ በእርሾ ላይ መብቀልን፤ በበቀለው ላይ ማስቀጠልን፤ መሰልጠንን ዘመናይነትን የቀዬሰ አዲስ የአብይ ዶግማ ነው። በጣም ብዙ ትርፍ አለው። የቁስ ብቻ አይደለም የሥነ - ልቦና፤ የመንፈስ፤ የህሊና፤ የቤተሰብ ዕሴት፤ የማህበራዊ ዕሴት፤ የአህጉራዊ ዕሴት፤ የሉላዊነት ዕሴት። ኢትዮጵያዊነት የላቀ ነው ሲባል ናሙናነቱ በቁንጽል ተዘንጥሎ መሆን የለበትም፤ ተወራራሽ እና ተያያዥ አድርጎ ማግስትን በዛሬ ውስጥ በሁለገብ አቅም እና ብልህነት ማደረጀት የድንቅነህ ተልዕኮ ነው። ይሄን መደገፍ፤ ይሄን መርዳት፤ ይሄን ማገዝ ይገባል። 

ለሚያብጠለጥሉት የፖለቲካ ድርጅት ተፎካካሪ መሪዎችም ቦታውን እዬደለደለላቸው ነው፤ አቅሙ ከኖራቸው። ቤቱን እዬሠራለቸው ነው ላዛውም በቅንነት … ሙሴ እረኛ መሪ የሚባለው እንዲህ ዓይነቱ የመርህ የፍትህ ቅን ንዑድ ሰው ብቻ እና ብቻ ነው። ስስታም አይደለም ይህ መንፈስ። ቂመኛም አይደለም ይህ መንፈስ። ስግብግብም አይደለም ይህ ሩህሩህ መንፈስ።

  • የድብብቆሽ እንካ ስላንትያ ተቀበረ …. እልል ብለናል …


ሌላው ግልጽነት ነው። በድብቆሽ ለኖረው ለልግመኛው የኢትዮጵያ ፖለቲካ መርዶ ነው። ቁልጭ ያለ መርዶ። ውስጥ ለውስጥ፤ ተመስጥሮ ነው የተኖረው። በአደባባይ ወጥተህ ፖሊሲ አለኝ ብለህ መንገድህን አትናገርም። ግን ጽፈህ ይዘሃዋል። አደባባይ ላይ ፖሊሲ የለኝም ትላለህ፤ ፖሊሲ እንዳላቸው ደግሞ የሽግግር ሰነድ አዘጋጀሁ ትላለህ፤ አማራርህ አይታወቅም፤ ማን ምን ሃላፊነትም እንዳለው አይታውቅም፤ ጉባኤህ ክፍት አይደለም፤ ስብበሰብህ ዝግ ነው፤ ለሚዲያ ደግሞ ለነጻነት አዬተጋገልኩኝ ነው ትላለህ ትፎክራለህ - ታቀራራለህ፤ ለፍትህ ቁሜያለሁ እኔ ትንሳኤ እና ህይወት ነኝም ትላለህ። ጉራማይሌ። ፖሊሲ ያለውም አታብቂኝ ሲመጣ ደብቆ ያቆአትን ብቅ ያደርጋታል፤ ዛሬ የአበጠው ፈነዳ ከእንግዲህ አንድ ስንዝር መራመድ አይቻልም። በድብቅ ፖለሲ አገር የሚታመስመትብ ጎንደርም አማራ የሚማገድበት መንገድ የለም። ገጥ ለገጥ ፖሊሲህን ታቀርባለህ፤ ከላይ እስከታች የደረደርካቸውን ቤተኞችህን ታሳውቃለህ ህዝብ ፊት ቀርበው ይገመገማሉ - ይተቻሉ ውስጥ ለውስጥ እዬተሄደ እክሌን አሳርፉልን፤ ማዕቀብ ጣሉልኝ፤ የለመ ወይንም አቅም የት ላይ ነው እያልክ ማደን የለም፤ በልክህ - በቁማናህ - በወርድህ እና በስፋትህ ልክ በአደባባይ ተፈትሸህ ታልፋለህ ወይ ትወድቃለህ በቃ  … ይሄ ሁሉ ነው መልክ ነውያዘው። 

ሰሞኑን ከአረብ ኢሚሪት አልጋወራሽ ጋር የተደረገው ስምምነት በግልጽ ነበር የቀረበው። አንድ ሁለት ተብሎ። አንተ ግን ተደብቀህ ማታ ለማታ ጎደብህ ምን እንዳሰብክ ሳይታወቅ፤ ስምምነትህ ስለምን መሆኑን ሳትነግረን፤ ሰው ታሰማገዳለህ አዬር ላይ ተነሳፈህ ለዛውም። አንድ አባልህ ስለደንብህ ቆሞ መከራካር፣ መሞገት በማይችልብት ሁኔታ።  … ምን አለ የጎንደር እናት መቼ ደክማ 43 ዓመት ሙሉ ሥንቅ ታቅርብ ለዛውም የሰው። ለዚህም ነው እኔ አንድ ቋሚ አቋም ላይ የጎንደር ህዝብ በሙሉ መድረስ አለበት ብዬ እማስበው። የፈለገ ከፋኝ ያለ በዬጫካው እንጂ ጎንደር የግራ ቀኝ የደም መሬት ከእንግዲህ መሆን አይገባትም የምለው።
 
ባለቅኔው ጠ/ ሚር የሚናገሩት የወያኔ ሃርነት ትግራይን ነው የሚሉ ሊኖሩ ይችላሉ እእ … የሚቀራቸው የለም ዛላውን፤ ዘነዘናውን፤ ገመናው አጥነተዋታል የሁሉንም የተፎካካሪውን፤ የተንታኙን፤ የሚዲያውን፤ የጋዜጠኛውን ሁሉንም ስለዚህም ቀስ እያሉ እዬዘረሩት ነው … እያንዳንዷን ቅንጣት ነገር መብት ስጠትዬቅ ግዴታም አብሮ መታዬት እንዳለበት እያስገዘቡ ነው። ያልተዝረከረከ የፖለቲካ ድርጅት የለም። ሁሉም መያዣ መጨበጫ ብቻ ሳይሆን ማያያዣ ስምኒቶም አላገኘም … ሲቀለድ ነው የኖረው የኢትዮጵያ እናቶች የ43 ዓመት ሙሉ ለሥመኞች የሰው ብርዶ ሲያቀርቡ … በእነሱ የሥልጣን ልዩነት ህዝብ ሲታረድ ኖረ፤ መዋለ ሃብት ሲባክን ኖረ፤ ወጣትነት ሲባክን ተኖረ … ከእንግዲህ ቀልድ የለም። አጀንዳም የለም። ወይ ሞጥረህ ታግለህ ታሸንፋለህ ወይ ደግሞ ትለቃለህ። ምርጫው የአንተ ነው … 

ዬዬክልሉ ስብሰባ እራሱ እጅግ አስፈሪ ነው … መናጆ፤ ማገዶ፤ አንጋች ድልድይ ሰሪ ሆኖ የኖረው አማራም ቆርጧል። አምሯል። ከ እንግዲህ ለ እነ እናቶኔ ሥም እና ዝና ተማግዶ የሌላ እንጀራ ጋጋሪነት ወጥ በዓይነት አቅራቢነት አክትሟል።

ተመሰገን ብለናል! የራበንን የጠማን የሰማይ ገነት ምድሪቷ ላይ የኤዶም ውሃ ነፋሻማ ፏፏቴ ነፍሳችን እያረሰረሰው ነው። የኔ አብይ ለዘለዓለም ብለና … አብይ የእኔ የአንተ የአንቺም ነው ግን ለቅኖች። እኔ የምጽፈው ለቅኖች ብቻ ብቻ ነው።

  • የእንጸልይለት የኬኒያ ሙሁራን ሊሂቃን ጥሪ!


PM Abiy Ahmed faces an uphill task in uniting and reforming Ethiopia


ቅንነት ያሸንፋል!
ድሉ ለቅኖች ብቻ ነው!
ቅነንት ይመራል!

የእኔዎቹ አዱኛዎቼ ምን ልሸልማችሁ ይሆን? ኑሩልኝ ብቻ ሳይሆን ጤናችሁን አባቴ አዶናይ ይስጥልኝ።
አክባሪያችሁ።

መሸቢያ ጊዜ። 

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።