መኖር እንዲያምርበት።
መኖር እንዲያምርበት …
ከሥርጉተ ሥላሴ …. 09.02.204 (ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ)
"ጥበብ በቀደሙ ሰዎች ሁሉ ዘንድ ተመረመረች።" (መጽሐፈ ሲራክ ምዕራፍ ፴፱
ቁጥር ፩)
- አዳም እንደተቆለፈ ነውን? ….
ከአህዱ በፊት በዚህ ጉዳይ ዙሪያ እንድል ፈቀደ አባቴ ….. እሱ እራሱ ለሰጠው ሥጦታ ጊዜን ተመኙ ባለሙሉ ባለሥልጣኑ ክርስቶስ ነውና። ጥበብ እራሱን ፈልጎ ያገኛል። በጮሪት ወይ ቀን- እኩል ላይ ወይንም ከብት ግባት ወይ በግርማ ሞገስ ታጅቦ ድንግዝግዝን ተገን አድርጎ እረፍት በሚሰጠው …..
በተጨማሪነት ወይንም በማሟያነት አልነበረም፤ በክፍት ቦታ ሸፋኝነትም አልነበረም፤ እንዲያምርብን - እንድንዋብ - ሰውነታችን ኃይል ኖሮት የኑሮን ዝክንትል ሳይቀር ደስ ብሎን እንሸከም ዘንድ፤ የተቆጣጠሩ ችግሮችንም ለመዳኘት ነው የተፈጠረቸው - ሴት።
ስለ ድርጅት መፈጠር ስናስብ እስትንፋሳዊ የድርጅት ሰቅ አድርጎ የፈጠራት ሴትን ነው አባታችን። የመጀመሪያው የህይወት ባለሙሉ ሥልጣን የመፈቃቀድ ድርጅተ ጥንስስ ሚስጢር ናት ሴት። ህይዋን ባትፈጠር ዓለም ወላቃ ትሆን ነበር። ዓለም ያዳልጣት ነበር። ትውልደ - አዳም ላይ ያቆም ነበር። ፋዳሳዋ አላም በአንድ እግሯ እንደቆመች ቆሞ ቀር በሆነች ነበር። ወጣ ገቧ ዓለም ቀን ተሌት የማይለይባት ገድል በሆነችም ነበር - አጥንት ነገር።
የጡት - እትብትነቱ መገለጫውም ሴት የእናቷን መክሊት ፈጻሚ አድርጎ ትውልድን ልጅ ሆና ብቻ ሳትቀር እንት ሆና እንድታዬው ማደረጉስ ይህ ሰማይና ምድርን በሥልጣነ ክህሎቱ፤ በእስትንፋሱ የፈጠረው አምላክ የጥበቡን ዲካ ለተሰጣቸው ብቻ እንዲለኩት ፈቀደ። ፍሬ ዘሩ የማይነጥፍ ሰው ሰራሽ መገጣጠሚያ ሳያስፈልገው ቀጥ ብሎ በጥበቡ ይጓዛል ….
በኃያል በጥበቡም አሳምሮና አስመችቶ ገነባ …
ይህ ልዑቅ የመኖር ሰማያዊ ኪነ ጥበብ መኖር እንዲያምርበት ብቻ ሳይሆን መኖርም እንዲኖር እራሱን መኖር የፈጠረበት ታላቅ ሚስጢር ነው። በዚህ አንጻር ገባ ብሎ እልፍኙ ሲፈተሽ የመኖር ማለቴ ነው፤ የደም ጋኑ ሥር ያለው ከሴት ስለመሆኑ ያለምንም አስተርጓሚ ማግኘት ይቻላል።
ለ ኦርቶዶክ ተዋህዶ አማንያን„እመ ብዙኃን፤ እመ ብርኃን፤ የመዳህኒት እናት፤ የሰላም መገኛ፤
የብሥራት ምንጭ“ እነዚህ ንዑዳዊ ኃይለ ቃሎች ሁሉ ውክልናቸው ለሴት ነው። „እመ ብርኃን“
የብርኃን ውድ እናት ጨላማ የተገፈፈበት፣ ጨለማ የተሸነፈበት፣ ጨለማ የተገረሰሰብት፣ ሰው እንደ ሰው ህሊናው በርቶ ፍጥረተ ነገሩን ይመረምር ዘንድ ብልኃት የተቀዳጀበት፤ ቀንና ሌሊት - ጽድቅና ኩነኔ፤ እሳትና ውሃ፤ መደመርና መቀነሱ፤ ክፉና ደጉ፤ ሀዘን ተፍሰኃው
የተለዩበት ላቅ ያለ ሥነ -ትርጉምን ይሰጣል። የዚህ ሃዲድ ጭብጥ ማክል ደግሞ ሴት ናት - ጉልላት።
„እመ ብዙኃን“ የብዙሃን ማህጸን፤ የአዲስ ጥንስስ አብሳይ ፍሬ አደራ ተረካቢ፤ ለፍጥረት ሙሉዑነት ያታመነች ፍጡር እንደ ማለት። ለዝክንትለኛዋን ዓለም ፈውስ ትሆን ዘንድ የተመረቀች - የተመረጠች - መዳህኒተ - ፍጡር እንደ ማለት ….. ለብዙኃኑ ድህነተ - ሥጋና ነፍስ በወጥነት እንድትከሽን የተሰጠች የተፈጥሮ ፍጽምና ያላት ሥጦታ …. እንደ ማለት፤
„መዳህኒት“ ከበሽታ - ከድውይነት - ከጭንቀት - ከችግርም - ልትታደግ የምትችልበት ቁልፍ የተሰጣት …. እንደ ማለት … ግን ስንቶቻችን ፈትሽነው፤ ስንቶቻችን ሰማይ ላይ ከማፍጠጥ ችግሮቻችን - መከራዎቻችን - ፈተናዎቻችን - ስንጥቆቻችን ለመፍትሄነት በሥጦታችን ተጠቀምንበት?! ….. ለመሆኑስ በዚህ አምላካዊ አምክኖያዊ ሥጦታ ሰማያዊ ቋንቋ ስምምነቱስ አለን?! መግባባት እንችላለን?! ለማድረግ ቀርቶ ለማድምጥ ፈቃዱ አለን?! ለአዳም ልጆች ጥያቄውን በጥያቄ ሳይሆን መልሱን እራስን ውቅሱ ድርጊት ማሳ ላይ እንዲሆን ትጠበቃላችሁ ….
ግን ዕንባ ምንድን ነው - የጥያቄ ምልክት። ዕንባስ ከዬት ይመጣል - የጥያቄ ምልክት። የዕንባ ተፈጥሮስ ምንድ ነው -የጥያቄ ምልክት። የእንባ ክፈለ አካላት አወቃቀሩ - አደረጃጃቱ - ስምሪቱ እንዴት ይሆን - የጥያቄ ምልክት። ዕንባ ገባር ወይንስ ውቅያኖስ ወይንስ ሃይቅ - ወይንስ ምንጭ ወይንስ ማህጸን ምንድን ነው - የጥያቄ ምልክት። ዕንባና ስኬቱ፣ እንባና ፍቅሩ፤ ዕንባና ሰርጉ፣ ዕንባና ድግሱ፣ ዕንባና ድንግልናው፣ ዕንባና ጫጉላው፣ ዕንባና ተስፋው፣ ዕንባና ልምናው ምንና ምን ናቸው - የጥያቄ ምልክት። ይህም ጥያቄ የአዳም ልጆች እንዲመለሱት ዓሻቅዬ ሽው ልል ወደደድኩ …..
ግን ዕንባ አድማጭ - ተናጋሪ - ተዋናይ - የጭብጥ አናት፣ ተራኪ፣ ትራጀዲ፣ ኮሞዲ፣ ስሜት፣ ሃሳብ፤ አይዲያ፣ ዓላማ፣ ውስጥ፣ ውጭ፣ ገር፣ ቁጡ ወይንስ የበቃ ባህታዊ … ወይንስ ሐዋርያ … ቀንዱ ማን? ለምን ተልዕኮ? ምን ለማሳካት ትልሙ ምን ለማምረት? የምርምር ማዕሉስ ምን? ግን ዕንባ ዐይን አለውን …. ከዓይን ብቻ ነውን ተፋሰሱ - የላቀ የመጠቀ ትውልድን የመገንባት ስበት አለውን? …. ለአዳም ልጆች ፈተና ይሰጥ …. መኮረጅ አይፈቀደም። ቾኩም ሰላዴውም አፋጧል ተፋጠጡ።
ራስን ችሎ መመለስ …. ወኔን ይጠይቃል ….
ዕንባ መፍትሄ - ጸሎት - ጥያቄ ወይንስ ሳቅ። ግን እኮ ዕንባ ስለምን ነው ሙቅ የሆነው ፍቹን ታውቁታላችሁ? ዕንባ ግን በማን ያምራል? ግን ያምራል? ውበት አለው ዕንባ? ሃይልና ግፊቱ ምን ያህል ዋት ነው? … መስፈር ይቻላል … ስፋቱ በጋሻ ወይንስ የበሬ ግንባር ታክል …. ግን ጠብታ ህይውት ሰጪ …. ይባል ምን ይባል?
ተከታይ ናት መስራች፣ ተለጣፊ ናት ወይንስ ደም፣ ጥገኛ ናት ወይንስ እራስ አስቻይ
ሴት፣ ስለምን ተፈጠረች፣ ስለምን መጣች፣ ስለምን ታዬች፣ ስለምን በቀለች፣ ለላንቲካ፣ ለፎቶ፣ ለምስል …. የጥያቄ ምልክት። ለአዳም ልጆች …. ምንድ ናት ለመሆኑ ሴት ዕቃ ---- ክክክክክክ ~___~ መንፈሰ - ህሊ፣ና
የመንፈስ ልብ፣ የመንፈስ ክናድ፣ የመንፈስ ጥርኝ፣ የመንፈስ ማዕዛ፣ የመንፈስ ወዝ፤ የመንፈስ ግድግዳ እኮ ምን ትሆን ይህቺ ብልኃት …. ማስተዋልን ጠይቁት የአዳም ልጆች።
በጥያቄ ሳጣድፋችሁ … ይቅርታ ግን አዳም እንደ ተቆለፈ ነውን? ስለሆነም የአዳም መፍቻ ቁልፍ ጠፍቶበት አብሬ ስባትል ሳፈላልግ፤ ጥሎብኝ እኔም በማረፊያዬ ጊዜ አብሬ ስማስን ደከመኝ፤ እናንተንም አደከምኩኝ። አይዞን ቁልፉ ተገኜና በድንቀንሽ ዕንባ አብረን አረፍን። ናፍቆቴን ሰንቄን አምቄ ግን እጅ ነስቼ በክብር ምስጋናዬን በሐሤት ላኩላችሁ … እኔ ካለናንት ምንም ነኝና … ክብሮቼ።
ጠብታ የፍጥረት ቅምረት
ሙቀት ~~~__~~~ ለፍውስት
እርቀት--------------------------------------------------------------~
ስንቅ በቅነንት
ቀደምት
ስኬት - በብልሃት
ሴት
ናት
ኣናት
የድንቅነሽ ው - ስ - ጠ - ት
እርገት በጥበባት!
- ክወና።
የመኖር ፍጠረቱ ሴት!
የመኖር ውበቱ ሴት!
የመኖር ምቾቱ ሴት!
እግዚአብሄር ይስጥልኝ። መሸቢያ ጊዜ።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ