የፍቅር ትርፉ።
የፍቅር ትርፉ ፍቅርን ለፈቀዱ ብቻ ይገለጥላቸዋል!
ከሥርጉተ ሥላሴ 19.06.2018 (ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ)
"እግዚአብሄር እርሱን መርጦታል እና። ለባለ መድኃኒት
ሥራውን
ሥራለት እሱን ትሸዋለህና ካንተ አታርቀው"
(መጽሐፈ ሲራክ ምዕራፍ ፴፰ ቁጥር ፲፪)
የፍቅር ተፈጥሮ መርህ ትርፍ ኪሳራ የለሌበት ብቻ አይደለም። በኪሳራ ውስጥም ትርፍ አለ። ለምሳሌ አንድ ሰው ለሌላው ሰው በሚሰጠው ፍቅር ውስጥ እሱ ይቅርብኝ የሚለው ነገር ይኖራል።
ፍቅር በመስጠትና በመቀበል ውስጥ የተፈጠረ ሲሆን በመስጠት ውስጥ ሰጪው የሚያጣው ወይንም የሚጎድልበት ነገር ሊኖር ይቻላል።
የሚጎድለው ነገር ምንአልባትም የኑሮው አንኳር ጉዳይ ሊሆን ይችላል። ነገር ግን ፍቅርን ፈላጊ ከሆነ ያን አንኳር የህይወቱን ጉዳይ ቅርብኝ ብሎ ፈቅዶ የፍቅሮን ስጦታ በተግባር ሊያከብረው ይችላል።
ፍቅሩ የከበረ ሊሆን የሚችለው ግን ፍቅርን ተቀባዩ የተወዎ አንኳር ጉዳይ ቢኖር እንኳን ሊጸጸተው ወይንም በምልሰት ሊያውከው እንዳይችል አድርጎ ከወሰነበት ብቻ ነው።
እርግጥ ፍቅር ከተተወው ጉዳይ በላይ እንዲያውም በላቀ መልኩ ረቂቅም ሊሆን ይቻለል። መንፈሳዊ ትርፉ አጥጋቢ ነው። ሰው ለሚወደው ነገር እራሱን ሲገብር ለወደደው ነገር ፍቅር ስለሰጠ ነው።
ያ የወደደው ነገር ላይመቸውም ይችላል ግን በወደደው ነገር ውስጥ መኖርን መፍቀድ በራሱ ፍቅርን በመስጠት ብቻ ምላሽ ሳይገኝ ደስታን ማግኘት ይቻላል። ረቅቅ ነው ደስታ።
- · የፎቶ ምንጭ ከሳተናው ድህረ ገጽ ከአቶ ኃይሉ አባይ ተገኘ የተወሰደ።
- · የፍቅራዊነትን ዩቱብ ይጎብኙልኝ … Seregute Selassie
ደግነት አይበርድም!
የኔዎቹ ኑሩልኝ።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ