ልጥፎች

ዘመናቸውን #ያላባከኑ ታላቅ ሰው።

ምስል
  ዘመናቸውን #ያላባከኑ ታላቅ ሰው።    እኒህ የእናት ኢትዮጵያ ድንቅም በሰሞናቱ ነው በሥጋ የተለዩን። ለክቡርነታቸው ሰላም እና አጸደ ገነትን፤ ለኢትዮጵያ እና ለቤተሰቦቻቸውም መጽናናትን እመኛለሁኝ። አሜን። ሥርጉትሻ 2025/11/10

ቸር ዜና። "ዐዲስ ቸኮል ቀዶ ሕክምናውን አጠናቆ በጥሩ ጤንነት ላይ ይገኛል! Tsion Girma Tadesse"

ምስል
  ዐዲስ ቸኮል ቀዶ ሕክምናውን አጠናቆ በጥሩ ጤንነት ላይ ይገኛል!  Tsion Girma Tadesse   "የአሜሪካ ድምጽ፣ የድሬዳዋ ዘጋቢ ዐዲስ ቸኮል፣ የተደረገለት ቀዶ ሕክምና ተሳክቶ በጥሩ ኹኔታ ላይ ይገኛል። ዐዲስ ቸኮል፣ ከቀዶ ሕክምናው በኋላ የንግግር እክል ሊያጋጥመው ይችላል በሚል የነበረው ፍርሃት ሙሉ ለሙሉ ተወግዷል። ከቀዶ ሕክምናው በኋላ በተደረገለት ክትትል የንግግር ብቃቱ፣ ቀድሞ ወደ ነበረው ጤናው መመለሱን አረጋገጠዋል። ሰባት ሰዓት አካባቢ በፈጀ ቀዶ ሕክምናም፣ ዕጢው ሙሉ ለሙሉ ወጥቶለታል። በአኹኑ ሰዓት በሆስፒታሉ ውስጥ በማገገም ላይ ይገኛል። “እግዚያብሔር ይመስገን ለዚኽ በቅቻለኹ” ያለው ዐዲስ፣ “ እኔን እዚኽ ለማድረስ የተረባረባችኹ በሙሉ እግዚያብሔር ብድራችኹን ይክፈላችኹ። ለእኔ እንደደረሳችኹልኝ። እግዚያብሔር ለእናንተም ይድረስላችኹ” ብሏል። ዐዲስን ለማሳከም፣ የተረባረበው ሰው በቁጥርና በስም ተለይቶ የሚቀመጥ አይደለም። በኹሉም ነገር ከላይ እስከ ታች የተሳተፈው በሙሉ ድጋፉ ፍሬ አፍርቷልና፣ ኹላችሁንም እግዚያብሔር ይባርካችኹ። በደግ ይመልስላችኹ። ጓደኞቹ እና የሞያ አጋሮቹ!"

#ጦርነት #ቤርሙዳ #ትርያንግል ነው።

ምስል
  #ጦርነት #ቤርሙዳ #ትርያንግል ነው። #ጦርነት #ነጣቂ ነው። ጦርነት #በቃኝ #ብሎም #አያውቅም ።     አባት አርበኛ ሻለቃ መሳፍንት እግዚአብሄር ያጽናወት። አሜን። እግዚአብሄር መጽናናቱን ይስጠወት። አሜን። በስተእርጅና #ጧሪ ፤ #ጠዋሪ ፤ #አይዞህ #ባይ #ማጣትን የመሰለ መከራ የለም። አጤው #ጦርነት እንዲህ የሚሳሱለትን የዓይን አበባን፤ ተስፋን #ንጥቅ ያደርጋል። ባለፈውም አንድ ልጃቸው ተሰውቷል።    "አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ።" አሜን።    ለመላ ቤተሰብ እና ስለ ሰው ልጅ ግድ ለሚለው ሁሉ መጽናናትን እመኛለሁኝ። #ሁሉም #እናት #አለው ። እናት በዕንባ ስትዋጥ፤ እናት ጭብጥ ኩርምት ስትል በመራር የልጅ ሃዘን እና በመርዶ ያሰቃያል። መቼ ይሆን እናትነት #እፎይ የሚለው???? ሥርጉትሻ 2025/11/11

#ፋታ #ለማይሰጥ #ድንገተኛ #ወረርሽኝ #ብሄራዊ ዝግጅት #በአፋጣኝ ሊደረግ ይገባል።

ምስል
  #ፋታ #ለማይሰጥ #ድንገተኛ #ወረርሽኝ #ብሄራዊ ዝግጅት #በአፋጣኝ ሊደረግ ይገባል።     ማንነቱ ያልታወቀ #ሥምአልቦሽ በሽታ ሲመጣ #ለእስረኞች እጅግ አሳሳቢ ነው። የብልጽግና መንግሥትም ልዩ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል። ጉዳዩ ከከፋ ደረጃ ከመድረሱ በፊት የደንበር ዝውውሮችን ሊቆጣጠር፤ እስከ #የአስቸኳይ ጊዜ ዓዋጅ ሊያደርስ የሚችል እርምጃወችን በአፋጣኝ መውሰድ ይኖርበታል። አቤቶ ብልጽግና #ብሄራዊ ኮሜቴ ማቋቋም የአለበት ይመስለኛል።    "አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ።" አሜን።   ይህን ዘገባ ካለወትሮው BBC ዘግይቶ ነው የዘገበው። የሆነ ሆኖ በጣም #የሚያስጨንቅ ነው። በሽታው ወዲያው የሚያጠቃው #ኩላሊትን ስለመሆኑ ዘገባው ይጠቅሳል። እስር ቤት ውስጥ ያሉ ወገኖች እጅግ ያሳስባሉ። በዩንቨርስቲ፤ በሆስፒታል፤ በመጓጓዣ የተሰማሩትም እንዲሁ።    ለሰመዓታቱ ቤተሰቦች ሁሉ መጽናናትን እመኛለሁኝ።    እግዚአብሄር ሆይ! እንደ ቸርነትህ ይሁንልን። አሜን። በደላችን በዝቷል እና ይቅር በለን። አሜን። ሥርጉትሻ 2025/11/13   ምህረትህ ይናፍቀኛል ጌታ ሆይ! እባክህ እርዳን! አሜን።    https://www.bbc.com/amharic/articles/ce3x459q5k1o "በጂንካ ከተማ የተከሰተውን በሽታ "ሲያክሙ የነበሩ" ሁለት የጤና ባለሙያዎችን ጨምሮ ስድስት ሰዎች ሞቱ" ከ 12 ደቂቃዎች በፊት   "በደቡብ ኢትዮጵያ ክል፣ ጅንካ ከተማ በተከሰተው በውል ያልታወቀ በሽታ ለተያዙ ሰዎች "ሕምክና ሲሰጡ የነበሩ" ሁለት የጤና ባለሙያዎችን ጨምሮ ስድስት ሰዎች መሞታቸውን የጂንካ አጠቃላይ ሆስፒታል ለቢቢሲ ገለጸ። የበሽታውን ምልክታ ባሳዩ ታካሚ...

አዲስ #ወረርሽኝ በኢትዮጵያ መከሰቱ ተደመጠ። የህክምና ባለሙያወችም በጅንካ ከተማ ሰማዕትነትን ተቀበሉ።

ምስል
  አዲስ #ወረርሽኝ በኢትዮጵያ መከሰቱ ተደመጠ። የህክምና ባለሙያወችም በጅንካ ከተማ ሰማዕትነትን ተቀበሉ።       አፋጣኝ እርምጃም፤ አፋጣኝ ጥንቃቄም ማድረግ የሚገባ ይመስለኛል። በተለይ በአዋሳኝ ባሉ ከተሞች እና በመሃል አዲስ አበባም በሽታው የመዛመት ዕድል ሊኖረው ስለሚችል መረጃውን ሼር በማድረግ መተባበር ይገባል። የኢትዮጵያ ጤና ሚኒስተር የሰጠው መግለጫ አያይዤዋለሁኝ። ይህን የጤና መስሪያ ቤት ያወጣው ቅድመ መከላከል አስመልክቶ የተሰጡትን መመሪያወች በድርጊት ላይ ማዋል አገር ቤት የሚገኙ ወገኖቻችን እንደ ህይወት #መርኃቸው ሊወስዱት ይገባል።     ከዚህ በተጨማሪም ጉዞወችን #መከርከም እና፤ በወል በሚሠሩ አስገዳች የሥራ ባህሪያት ላይ ጥንቃቄ ማድረግ፤ የጋራ ጉዞ እና የተለያዩ የማህበራዊ ኑሮ መስተጋብሮችን ክስተቱ መልክ እስኪይዝ፤ ወይንም በቁጥጥር ሥር እስኪውል ድረስ ከፈጣሪ በታች የተቻለውን ሁሉ ማድረግ ያስፈልጋል። #ማስክ መጠቀም እጅግ አስፈላጊ ጉዳይ ይመስለኝ።   በተረፈ ምንጊዜም ለሰብዓዊነት ግንባራቸውን አጥፈው ለማያውቁት የህክምና ባለሙያወች፤ እራሳቸውን ለሚማግዱት ለኢትዮጵያ የጤና ባለሙያወች፤ የጤና አገልግሎት ሠራተኞች ሁሉ ክብር መስጠት ይገባል። እራሳቸውን አስቀድመው ሌላውን ለማትረፍ #ሰማዕትነት ለተቀበሉት የጤና ባለሙያወች፤ እንዲሁም በበሽታው ለተቀዘፋ ወገኖቻችን ነፍሳቸውን ፈጣሪ በገነት ያኑር አሜን። ለቤተሰብም መጽናናት ይስጥልን አምላካችን አሜን።    ፈጣሪን የምናስከፋበት መንገድ በረከተ። ልብ ይስጠን አሜን።   "አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ።" አሜን።   እግዚአብሄር ይስጥልኝ። አሜን።    ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Sela...

ድንቄ ጋሼ ማስቲካ

ምስል
        https://www.facebook.com/reel/26018093327778130   እንዴት ናችሁ? እኔ እና ክረምት ቅርርብ የለንም። የሆነ ሆኖ ጋሼ ማስቲካን በአካል አውቀዋለሁኝ። ለለገዳዲ የራዲዮ ፕሮግራም ጹሁፍ እንዳቀርብ የፈቀደልኝ ድንቄ ነው። እጅግ ቅን ሰው ነው። የመጀመሪያ ጹሁፌ " ግንጥል ጌጥ" የሚል ነበር። ሥርጉተ እርቅይሁን በሚል የብዕር ሥም ነበር ያን ጊዜ በአፍሪካ ቀንድ፤ በሙዳይ መጽሄት እንዲሁም በአዕምሮ ጋዜጣ እሳተፍ የነበረው። ሁሎችንም አመሰግናለሁኝ። ለመክሊቴ ለከፈቱልኝ #ፏም #ቧ ም ላለው ፍጹም #ቅናዊ እገዛቸው አመሰግናቸዋለሁኝ። የሆነ ሆኖ ያን ትንታግ ጋሼ ማስቲካን እሱን ላሚያስታውሱ ድንቆቼ ልዩ ክብር አለኝ። በውስጤ ትንሽ ሙዳይ አለች። ለድንቆቼ ቦታቸው ያ ነው። እግዚአብሄር ይስጥልኝ። አሜን። ኑርልን ዓራት ዓይናማው ሊቀ - ትጉኃን ጋሼ ማስቲካ።

#ወዳጃችን ጋሼ ብስጭት እና ጉዟችን።

ምስል
  #ወዳጃችን ጋሼ ብስጭት እና ጉዟችን።   "አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ።" አሜን።    #ምዕራፍ ፲፯    ማህበረ ቅንነት እንዴት ናችሁ? እኔ አምላኬ ክብሩ ይስፋ ደህና ነኝ። ትንሽ ነገር ስለ ጋሼ ብስጭት።   ተበሳጭተህ ምግብ ከበላህ ምግቡን ሳይሆን #ብስጭቱን ነው የምትበላው። አኩርፈህ ምግብ ከተመገብክ ከኩርፊያህ ጋር ነው ምግቡን #የምትውጠው ። ተበሳጭተህ የምትጠጣው ማናቸውም ፈሳሽ ወደ ጉሮሮህ ሲንቆረቆረ ብስጭት #እየገረፈው ይሆናል።   ተበሳጭተህ ከተኛህ እንቅልፋ በብስጭት ተዥጎርጉሮ የተኛህበት የለመድከው ምቹ አልጋ ሲጎረብጥህ፤ የለመድከው አተኛኝ ሲሰለችህ ሰላምህን አጥተህ እንዲሁ ከብስጭትህ ጋር ግብ ግብ እንደገጠምክ የወፎች ዝማሬ ዓዋጅ ይደመጣል። እነሱ ምን አለባቸው፤ የሰው ልጅ ነው የሚያሳድዳቸው እንጂ ሰናይ ናቸው። አቤት ዜማቸው፤ አቤት እንጉርጉሯቸው።   የሆነ ሆኖ ሲነጋ የሰራ አከላት ተቆራርጦ፤ በስትራፖ #እግዚኦ እያለ፤ ቀኑ ደብዝዞ ይቀበልሃል። ይህን ተሸክመህ ወደ ፀሎት አትሰበው፤ ይህን ተሸክመህ ወደ ማህበራዊ ሚዲያም አትወጥነው፤ ይህንኑ እንዳዘልክ ወደ ቁርስ ብታተኩር ሁለመናህን ያጋየዋል። ስለዚህ ከውጥኑ የሚያበሳጭ ነገር ቢገጥምህ እንኳን ሲሆን ሲሆን እንዳላየህ እለፈው። በስተቀር ብስጭትህን ከውስጥህ የሚያወጣ ሆቢ ብትለምድ ምን ይመስልኃል ውዴ እና ክብሬ የአገሬ ልጅ፤ ብትለምጂ ምን ይመስልሻል ተክሊሌ እና ዘውዴ የአገሬ ልጅ እታለም።    #እስቲ ።    ጋሼ ብስጭት ፊት ከተሰጠው ካለምንም ቅድመ ሁኔታ ጦርነቱን በራሱ ጊዜ ይከፍት እና ያጣድፋል። ስለዚህ ፊትነሺነት መልካም ይመስለኛል። ይህ ባይቻል ቤትህን ለቀቅ አድርገህ ወጣ በል...