ልጥፎች

የፕሬዚዳንት ለማ መገርሳ ትምህክት ተረገጥ! /ክፍል አራት/

ምስል
 እንኳን ደህና መጣችሁልኝ  ምርመራ። ክፍል አራት። „እግዚአብሄር ፍርድን በማድረግ የታወቀ ነው።“ መዝሙር ፱ ቁጥር፲፮ ከሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 02.04.2019 ከእመ ዝምታ ሲዊዘርላንድ። እንዴት ናችሁ ከንጹሁ ልቤ የማከብራችሁ ደህና ናችሁ ወይ? ዛሬም በባጀው በፕሬዚዳንት ለማ መገርሳ ንግግር ላይ ቆይታ ማድረግን ፈለግሁኝ። አብዛኞቻችን አንዱን ይዘን ሌላውን እዬጣልን ከጎረፈው ጋር ጎርፈን፤ ከወጀበው ጋር ወጅበን፤ ከነፈሰው ጋር ነፍስን አቅማችን አባክነናልን፤ ይቅርታውም ምኑም አሁን ላይ ሳዬው በውስጥነት የሰከነበት ተፈጥሮ እንደሌለ ነው እኔ የሚገባኝ። የልብን እያደረሱ ይቅርታ ማባጨል ይለዋል ጎንደሬው ... ባተደሞው የዕድምታ ባለሟል።  ስለሆነም አላምጠን እንውጥ ዘንድ እያንዳንዱን ሂደት ሰብን በማመን ብቻ መተው ተፈላጊ አለመሆኑ ልብ ልንለው ይገባል። የሰሞናቱ የዛ መከረኛ የጋዜጠኛ አስክድር ከመጋቢት ልደታ ጀምሮ ያለው ጫና እና ወጀብ ሁሉ ሳስበው፤ ሳስተውለው በዝግታ እንራመድ ዘንድ መልክት ልኮልኛል። መፎካከር በማይገባው ጊዜና ሁኔታ ሲሆን እጅግ ይከረፋል። የሚሊዮን ግርማ ሞገስ ተሸከመህ ይህን ያህል ከብዕር ገበሬ ጋር እሰጣ እገባ ሁለመናውን ለመዝጋት መታታተር ስልጣን አለኝ ብለህ በፍጹም በምንም መስፈርት ከዚህ ተፈረጅ የሚባል አይደለም።  ሁሉ ነገር አይጠቅምም ሁሉነገር አይጎዳም። ጎጂና ጠቃሚውን ለመለዬት ደግሞ ከሥር እዬጀመሩ ጉዳዮችን በምልሰት አጥሞ ማጥናት ይጠይቃል ። ቀጣዩ ትውልድ ፍዳን ተሸካሚ እንዳይሆን የመንፈስ ውላችን እውነትን ወግኖ ከመቆም ጋር መሆን እንዳለበት በጽኑ አምናለሁኝ።  ዘመን ተቀበልን ዘመንን ስንሸኝ እንደ ጥንቸል መንፈሳችን፤...