በፍፁም እንዲህ አልጠበኩም ነበር! ዶክተር ብቻ አይደለም! በአሜሪካ የዶክተር ህይወት እንዴት ነው? #usa#ame..."ቅኔው፤ ድጓው፤ ተደሟዊው ዶር. ይሳህቅ መሃመድ አደም የግዕዝን ቁጥር በሉላዊ ደረጃ ብራንድ ያደረጉ ምጥቅ የማስተዋል ጀግናዬ።
ቅኔው፤ ድጓው፤ ተደሟዊው ዶር. ይሳህቅ መሃመድ አደም የግዕዝን ቁጥር በሉላዊ ደረጃ ብራንድ ያደረጉ ምጥቅ የማስተዋል ጀግናዬ። ካሰብኩት ሼር ለማድረግ ቆዬው። የባተሌ ነገር በዛብኝ እና ሳልችል ሰነበትኩኝ። ግን የእኔ ክብሮች እንዴት ሰነበታችሁልኝ? ከመጋቢት 10/ 2010 እስከ ዛሬዋ ዕለተ ሰንበት 2016 ዓም ድረስ ፲፩ ምዕራፎችን አዬን። ፲፪ኛውም ተጀምሯል። የኛ ቤት ታዳሚው በደራሽ ዜናወች ስለባተለ ተግ አደረኩት አዲሱን ምዕራፌ። አጤ ቲክቶክም መፈንቅለ በአጤ ፌቡ እያካሄደ ነው። የጤና ያድርግለት ብቻ አጤ ቲክቶክ። እዬገሰገሰ ነው። ለነገሩ ወጣቶቹ ለአወንታዊ የተሰለፋት ይስባሉ። ሁሉም ቦታ ለመሳተፍ ጊዜውም ድካሙም ሆነ እና ብዙም አላተኩርም ቲክቶክ ላይ ሰሞኑን በአርቲስት ዳኜ ምክንያት እኔም ትንሽ ሰሞኑን ሼር አድርጌያለሁ። ደስ የሚሉ ወጣቶች ናቸው። ወኔ!!!!! #ጉዳዬ ። "አድርገህልኛል እና አመሰግንኃለሁ።" የዶር ይሳህቅ ሥም የእስልምና ነው። ተግባራቸው ደግሞ ቀደምቷን የኢትዮጵያ ክብር ምራኝ ያለ አንቱ ነው። ለብዙ የእስልምና እምነት አዋቂወች ግዕዝን አጥኑት ሚስጢር ይገለጥላችሁ ዘንድ ስል ኑሬያለሁ በመድረክ ዙሪያ ላሉት። እግዚአብሄር በአንድም በሌላም ይናገራል ሰው ግን አያስተውለውም የሚለው ቃለ ወንጌል ተስተውሎ አገኜሁት። እኒህ ታላቅ ሰው የኢትዮጵያን ቀደምት ጥሪት ብቻ ሳይሆን የፐርስሽንም የሌሎችንም የሰዓት ብራንዳቸው ለማድረግ ቆርጠዋል። ለእኔ አናባቢም ተነባቢም ሆነው አግኝቻቸዋለሁኝ። እናታችን ቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ለእኒህ አራት ዓይናማ ትጉህ ዕውቅና ሰጥታ እንድታከብራቸው፤ እንድትሸልምቸው ስል በትህትና አሳስባለሁኝ። በሀገረ አሜሪካ የምትገኙ የተዋህዶ ልጆች፤ ኢትዮጵያን ውስጣችሁ ያደረጋችሁ ልዩወቼም ለእኒህ ፍፁም ቅን የ...