ልጥፎች

የጤና ባለሞያዎች ጥያቄ ከሰብአዊ መብት አንፃር ሲዳሰስ

ምስል
"የኢትዮጵያ ሃኪሞች #ጀግኖች ናቸው።" (አቶ ያሬድ ኃይለማርያም የሰባዕዊ መብት ተሟጋች ማዕከል መሥራች) ሁለት የህግ ባለሙያወች የህክምና ባለሙያወችን ጥያቄ ከህግ አንፃር እንደምን ገመገሙት?   "የቤትህ ቅናት በላኝ።"   ኢትዮ ሰላም ዩቱብን ዝግጅት መጨረስ ያቃተኝን ይህን ጨዋ፤ የጨመተ፤ ሥልጡን፤ የህግ መሠረትን ያገናዘበ ሰውኛ እና ተፈጥሮኛውን የሃኪሞች ጥያቄ አስመልክቶ የተደረገውን ውይይት ደግሞ #ሁለት ጊዜ አዳምጨዋለሁኝ። የሚገርመው የአስተያዬት ሰጪወችም ተሳትፎ ዲስፕሊንድ የሆነ #የውስጥነት #ቀለም ያለው ነበር ማለት እችላለሁኝ።   ይህን ቃለ ምልልስ አደብ ገዝቶ ላዳመጠው የነጭ ለባሾች ቁጣ ታሪክንም በምልሰት የቃኜ፤ አሁን ያለውን የኢትዮጵያ ያሃኪሞች ጥያቄ ግሎባሊ ያለውን የተደማጭነት ልክ የገመገመ፤ የንቅናቄውን አነሳስ፤ አካሄድ እና አስተዳደሪዊ አቅሙንም ዕውቅና የሰጠ፤ ጥያቄውን #በቅንነት እና #በቀናነት የተመለከተ፤ በዝበት ለሚነገሩ አገላለፆችን ሙያዊ እርምት የሰጠ፤ ለአብይዝምም ጥንቁቅ የመፍትሄ ሃሳብ ያቀረበ ውይይት ነው።    አወያዩ ልጅ ሞገስ ተሾመም፤ ተወያዩ አቶ ያሬድ ኃይለማርያም የህግ ባለሙያወች ስለሆኑ ቋንቋቸው ወጥ እና መምህር ነበር ማለት እሻለሁኝ። አጀንዳ በሳሰበት የኢትዮጵያ ፖለቲካ ይህን መሰል የሙያ ነፃ ትምህርት ቤት ሲገኝ ቁጭ ብሎ መማር ብቻ ሳይሆን ዝበት የሚያሰኛቸው ዕይታወችንም ማረቅ፤ ማስተካከል ይቻላል።    ከሁሉ የውስጥን ችግር የእኔ ብሎ መቀበል፤ ዕውቅና መስጠት የማግሥትን የትውልዱን ተስፋ ያለመልማል። በምልሰት ህወሃት ሥልጣን በያዘበት ዘመን የመጀመሪያው ንቅናቄ የባንክ ሠራተኞች ነበር። ያንንም ለንጽጽር ያቀረቡበት አግባብ ተገቢ እና ወቅታዊ ነውም ...

#ራህብን ለመግለጽ ሌላ "#ራበኝ" ከማለት ሌላ ቋንቋ ይኖረው ይሆን?

ምስል
  #ራህብን ለመግለጽ ሌላ " #ራበኝ " ከማለት ሌላ ቋንቋ ይኖረው ይሆን?   "የቤትህ ቅናት በላኝ።"       እንዴት አደራችሁ ማህበረ ቅንነት? ደህና ናችሁ ወይ? https://www.youtube.com/watch?v=bR2GqRI2ZaU «ስራ ማቆም ትግል ሳይሆን ደሀ ላይ መፍረድ ነው»    # የአብይዝም መንግሥትስ?   የኢትዮ ሰላም ሚዲያ ባለቤት ልጅ ቴወድሮስ አስፋው ከሚያነሳቸው በርካታ ጉዳዮች ላይ #ሦስት ጉዳዮች እኔንም ሞገቱኝ እና ሃሳቤን ላጋራ ወደድኩኝ። ለመነሻነት ይህ ይሁን እንጂ ተያያዥ ጉዳዮችም ሊነሱ ይችላሉ።    የሆነ ሆኖ በአመዛኙ ከሁለት ዓመት ወዲህ #ቅይጥይጥ ክስተቶች ከመበራከታቸው የተነሳ በብዙ ክስተቶች ላይ ጥንቃቄያዊ ጉዞ ላይ ነው የባጀሁት። የኃይል አሰላለፋም ተለዋዋጭ ባህሬ መኖሩም። ስለሆነም የአቅም መግቦቱ እና ስኬቱ ለማን? የሚለውን በጥልቀት ማየት ያስፈልግ ስለነበር ተግታን መርሄ አደረኩኝ። ያ ጥንቃቄ ለእራሴ የውስጥ መንፈስ ቅዱስ መዳህኒት ሆኖልኛል።    ሰማይ ዝቅ ምድር ከፍ ቢል ቅንጣት አቅም የህወሃትን ተስፋ እንደገና በሚያለምልም አዟሪት ውስጥ መግባት በቁም ሬሳ የመሆን ያህል ይሰማኛል። ከመሼ እየታየ ያለው ሂደት ይህን እንደሚያመሳጥርም እዬታዘብኩ ነው። አቤቱ ህወሃት ለሚናፍቃቸው ወገኖቼ አቅም ብጣቂ አላዋጣም። ፈጽሞ። አቤቱ የሴራ ካፒቴኑ ህወሃት እና #አኞ ፖለቲከኛው ናፍቆኝ አያውቅም። ወደፊትም አይናፍቀኝም። ግድፈት፤ ሂደት፤ ወቅትና ዘመን ሊያስተምረው የሚችል ድርጅት አይደለም እና።    በሌላ በኩል የበዛው ቅንነቴ ስለ ወገኔ የምሰጠው ምስክርነት ሆነ ማገዶነት ጊዜ ራዲዮሎጂ ነውና የግለሰብ ሰብዕና ግንባታ...

#ለምን? ቁራሽ እንጀራ ለጠዬቀ ካቴና??? ማህጸንን እንደ ዱባ ይቀረድዳል።

ምስል
  #ለምን ? ቁራሽ እንጀራ ለጠዬቀ ካቴና??? ማህጸንን እንደ ዱባ ይቀረድዳል።   "የቤትህ ቅናት በላኝ።"     እስከ አሁን የተደከመበት፤ ሙሉ አቅም የፈሰሰበት፤ ብዙ ወገኖቻችን ያጣንበት የኢትዮጵያ ፖለቲካ #እርካታን ይለፍ ሊሰጠው አልቻለም። ለምን? ከሊቅ እስከ ደቂቅ ኢትዮጵያዊው ዜጋ በአደብ፤ በጥሞና ከራስ ፍላጎት፤ ጥቅም እና ድሎት አለፍ አድርጎ ሊያስብበት የሚገባ በኽረ ጉዳይ ይመስለኛል።    በፖለቲካ ምክንያት ትናንት #ስደት ላይ የነበሩት ፖለቲከኞች ዛሬ አገር ውስጥ ገብተው #መኖርን እያኖሩ ነው። ትናንት አገር ውስጥ ሆነው መኖርን ያኖሩ የነበሩ ፖለቲከኞች ዛሬ መኖርን #ለስደት ሰጥተዋል። ይህ ተመክሮ ለዛሬም፤ ለነገም የትውልድ #በረከት ወይንስ #እርግማን ይሆን ብሎ ማንሰላሰል ይጠይቃል። ወደ ራስ አቅርቦም አጀንዳዬ ማለት ይገባል።   በዚህ ውስጥ የእያንዳንዱን ዜጋ መብት እና ግዴታ #ሳይጫኑ ወይንም #ሳይጨፈልቁ በቅንነት የኢትዮጵያን የፖለቲካ ሂደት ቁመና መገምገምም ይገባል። እያንዳንዱ ዜጋ እውነቴ የሚለው የራሱ ሃቅ አለውና። ስለሆነም የችግሮችን #ሴል በማድመጥ እረገድ በወልም በጋራም ሊታሰብበት ይገባል።    ምክንያቱም ነገ የስርዓት ለውጥ ቢመጣ እንኳን፤ ይህ ጠቃሚ ያልሆነው የተመክሮ ሰርክል ወይንም አዟሪት ይደገማልና። ከሆነ ቦታ ላይ መቆም አለበት። የመጨረሻው የሊቃውንቱ የዕውቀት ደረጃ #ዶክተርነት ነው። በውነቱ በብዙ ትጋት እና ልፋት የሚገኝ የዕውቀት አስኳል ነው ዶክተርነት። ዶክተርነት የሊቃውንት #ቁንጮነት ነው።   ይህ አካል #የዳቦ ጥያቄ አለኝ ሲል፤ የደህንነት ዋስትና ይኑረኝ ሲል፤ መኖሬ በዜግነቴ ደረጃ በልፋቴም ልክ ይሁን ሲል፤ በሊቃ...

LIVE: Austria's Eurovision Winner JJ Meets Chancellor Stocker | DWS News... ጥበብ የሆነ #የሊቃውንት #ጉባኤ በኦስትራሽ።

ምስል
ጥበብ የሆነ #የሊቃውንት #ጉባኤ በኦስትራሽ። የአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስተር ከከፍተኛ የካቢኔ አባሎቻቸው ጋር አሸናፊውን አርቲስት ጄጄን (አርቲስት የኋንስን)እንዴት አክብረው አቀባበል እንዳደረጉለት። ዕውቅና በምን ልክ እንደሰጡት ተመልከቱ። አገር እና ህዝብ፤ ጥበብ እና መሪ፤ መሪ እና ትውልዱ #ዕውነት የሆኑበት ልዩ #ክስተት ። ልዩ መታደል። ልዩ የምድር ገነት።    ለዚህም ነው እኔ ኢሮ ቪዥን ሶንግ ኮንቴስት በዬአመቱ ORF 1 እምከታተለው። ልዩ ጣዕም ልዩ ቃና አለው። የአርቲስት ጄጄ እናቱ ከፊሊፒን አባቱ ከኦስትርያ ዱባይ ለስራ ሄደው ነው የተገናኙት። እና ይህ ሙሉ አቅም ያለው ወጣት ከውህድ ማንነት የተገኜ ነው። ኢንቴግሬሽን ክብር ሲሰጠው፤ ውህድ ማንነት እንዲህ የላቀ ክብር ሲሰጠው ዓለማችን ያምርባታል። #እንማርበት ።    ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 2025/05/19

«#UnitedByMusic” ይህ የእምዬ ሲዊዘርላንድ ለዓለም የላከችው የመንፈስ ስጦታ ነው። #Stolz!

ምስል
  • « #UnitedByMusic ” ይህ የእምዬ ሲዊዘርላንድ ለዓለም የላከችው የመንፈስ ስጦታ ነው። #Stolz ! "ጥበብ ቤቷን ሠራች፤ ሰባት ምሰሶም አቆመች።"   79ኛው የዓውሮፓ የሙዚቃ ውድድር ትናንት በባዝል ከተማ በእምዬ ሲዊዘርላንድ #ኦስትሪያ ያሸነፈበት መሰናዶ በስኬት ተጠናቋል። በ2024 እምዬ ሲዊዘርላንድ አሸናፊ ስለነበረች የ2025 አዘጋጅ ቅድስቷ ነበረች። አንድ ሳምንት ቀድሞ መስተንግዶ የነበረ ሲሆን ተሳታፊወች በተመረጡ ከተሞች በነፍስ ወከፍ ግብዣ ነበራቸው። ህሊናቸው #ቤተሰባዊነትን ይዋህድ ዘንድ የነበረው ቅድመ መሰናዶ እጅግ ሳቢ ነበር ለእኔ።   ዘመናችን የዲጅታል ሆነ እና ሰውኛ ጸጋችን እዬተጫነው ስለሆነ የእኔ ማሽን ጄኔሬሽን አስመልክቶ ስጋቴ እጅግ የላቀ ነው። ለዚህም ነው ዓለማችን የፍቅር ተፈጥሮን በትምህርት ደረጃ #ካሪክለም ነድፋ ልትሰጥ ይገባል በማለት የዛሬ 15 ዓመት #ለተመድ እና #ለአውሮፓ ህብረት መሻቴን በክብር የላኩት። እነሱም የተከበሩ ስለሆኑ ለእኔ አንዲት ባተሌ ብላቴና አክብረው መልስ ሰጡኝ።   ይህን ያነሳሁት የነገ ጉዳይ ውስጤ ስለሆነ የኦስትርያ፤ የሲዊዝ የጀርመን እና የኢትዮጵያን የትውልድ ቀረፃ መሰናዶወችን ከውስጤ ሆኜ ነው እምከታተለው። ጭንቅላቴን የሚመራውም ይህ ትጉህ ሰውኛ የተስፋ ብርኃናማ መንፈስ ነው። ሰዋኛ! ሰውኛነት! ተፈጥሮ! ተፈጥሮኛነት! ቢፈቀድላቸው በዓለማችን ያለው የስጋት ዳመና ተወግዶ #ቤተሰባዊነት ይነግሥ ነበር።   የሆነ ሆኖ ዊዝደም ያበቀለው የአውሮፓ የየዓመቱ የሙዚቃ ድግሥ የዬዓመቱን ቴክኖሎጂ፤ የየዓመቱን የሳይንስ፤ የዓመቱን የሞድ፤ የየዓመቱን የሙዚቃ ምርት ዕድገት፤ የያዓመቱን የሚዲያ ክህሎት፤ የየዓመቱን የኮስሞቲክ ሥልጣኔ ብቻ ሳይሆን የየዓመቱን...