የጤና ባለሞያዎች ጥያቄ ከሰብአዊ መብት አንፃር ሲዳሰስ

"የኢትዮጵያ ሃኪሞች #ጀግኖች ናቸው።" (አቶ ያሬድ ኃይለማርያም የሰባዕዊ መብት ተሟጋች ማዕከል መሥራች)
ሁለት የህግ ባለሙያወች የህክምና ባለሙያወችን ጥያቄ ከህግ አንፃር እንደምን ገመገሙት?
 
"የቤትህ ቅናት በላኝ።"
 
ኢትዮ ሰላም ዩቱብን ዝግጅት መጨረስ ያቃተኝን ይህን ጨዋ፤ የጨመተ፤ ሥልጡን፤ የህግ መሠረትን ያገናዘበ ሰውኛ እና ተፈጥሮኛውን የሃኪሞች ጥያቄ አስመልክቶ የተደረገውን ውይይት ደግሞ #ሁለት ጊዜ አዳምጨዋለሁኝ። የሚገርመው የአስተያዬት ሰጪወችም ተሳትፎ ዲስፕሊንድ የሆነ #የውስጥነት #ቀለም ያለው ነበር ማለት እችላለሁኝ።
 
ይህን ቃለ ምልልስ አደብ ገዝቶ ላዳመጠው የነጭ ለባሾች ቁጣ ታሪክንም በምልሰት የቃኜ፤ አሁን ያለውን የኢትዮጵያ ያሃኪሞች ጥያቄ ግሎባሊ ያለውን የተደማጭነት ልክ የገመገመ፤ የንቅናቄውን አነሳስ፤ አካሄድ እና አስተዳደሪዊ አቅሙንም ዕውቅና የሰጠ፤ ጥያቄውን #በቅንነት እና #በቀናነት የተመለከተ፤ በዝበት ለሚነገሩ አገላለፆችን ሙያዊ እርምት የሰጠ፤ ለአብይዝምም ጥንቁቅ የመፍትሄ ሃሳብ ያቀረበ ውይይት ነው። 
 
አወያዩ ልጅ ሞገስ ተሾመም፤ ተወያዩ አቶ ያሬድ ኃይለማርያም የህግ ባለሙያወች ስለሆኑ ቋንቋቸው ወጥ እና መምህር ነበር ማለት እሻለሁኝ። አጀንዳ በሳሰበት የኢትዮጵያ ፖለቲካ ይህን መሰል የሙያ ነፃ ትምህርት ቤት ሲገኝ ቁጭ ብሎ መማር ብቻ ሳይሆን ዝበት የሚያሰኛቸው ዕይታወችንም ማረቅ፤ ማስተካከል ይቻላል። 
 
ከሁሉ የውስጥን ችግር የእኔ ብሎ መቀበል፤ ዕውቅና መስጠት የማግሥትን የትውልዱን ተስፋ ያለመልማል። በምልሰት ህወሃት ሥልጣን በያዘበት ዘመን የመጀመሪያው ንቅናቄ የባንክ ሠራተኞች ነበር። ያንንም ለንጽጽር ያቀረቡበት አግባብ ተገቢ እና ወቅታዊ ነውም ማለት እሻለሁኝ። እንዲህ ዓይነት ሚዛን አስጠባቂ አቅምም ኢትዮጵያ ስላላት ህሊና ለዳኝነቱ ጥሩ ስንቅ ይኖረዋል ብዬ አስባለሁኝ። 
 
«የጤና ባለሞያዎች ጥያቄ ከሰብአዊ መብት አንፃር ሲዳሰስ»
 
እግዚአብሄር ይስጥልኝ። ደህና እደሩልኝ። አሜን።
ቸር አስበን፤ ቸር እንሁን። አሜን።
ቅን አስበን፤ ቀና እንሁን። አሜን።
ኑሩልኝ አሜን።
 
#Sergute©Selassie
20/05/2025

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

የእኔ እማ ልዕልቴ እንዴት ነሽ?