#ለምን? ቁራሽ እንጀራ ለጠዬቀ ካቴና??? ማህጸንን እንደ ዱባ ይቀረድዳል።
#ለምን? ቁራሽ እንጀራ ለጠዬቀ ካቴና??? ማህጸንን እንደ ዱባ ይቀረድዳል።
እስከ አሁን የተደከመበት፤ ሙሉ አቅም የፈሰሰበት፤ ብዙ ወገኖቻችን ያጣንበት የኢትዮጵያ ፖለቲካ #እርካታን ይለፍ ሊሰጠው አልቻለም። ለምን? ከሊቅ እስከ ደቂቅ ኢትዮጵያዊው ዜጋ በአደብ፤ በጥሞና ከራስ ፍላጎት፤ ጥቅም እና ድሎት አለፍ አድርጎ ሊያስብበት የሚገባ በኽረ ጉዳይ ይመስለኛል።
በፖለቲካ ምክንያት ትናንት #ስደት ላይ የነበሩት ፖለቲከኞች ዛሬ አገር ውስጥ ገብተው #መኖርን እያኖሩ ነው። ትናንት አገር ውስጥ ሆነው መኖርን ያኖሩ የነበሩ ፖለቲከኞች ዛሬ መኖርን #ለስደት ሰጥተዋል። ይህ ተመክሮ ለዛሬም፤ ለነገም የትውልድ #በረከት ወይንስ #እርግማን ይሆን ብሎ ማንሰላሰል ይጠይቃል። ወደ ራስ አቅርቦም አጀንዳዬ ማለት ይገባል።
በዚህ ውስጥ የእያንዳንዱን ዜጋ መብት እና ግዴታ #ሳይጫኑ ወይንም #ሳይጨፈልቁ በቅንነት የኢትዮጵያን የፖለቲካ ሂደት ቁመና መገምገምም ይገባል። እያንዳንዱ ዜጋ እውነቴ የሚለው የራሱ ሃቅ አለውና። ስለሆነም የችግሮችን #ሴል በማድመጥ እረገድ በወልም በጋራም ሊታሰብበት ይገባል።
ምክንያቱም ነገ የስርዓት ለውጥ ቢመጣ እንኳን፤ ይህ ጠቃሚ ያልሆነው የተመክሮ ሰርክል ወይንም አዟሪት ይደገማልና። ከሆነ ቦታ ላይ መቆም አለበት። የመጨረሻው የሊቃውንቱ የዕውቀት ደረጃ #ዶክተርነት ነው። በውነቱ በብዙ ትጋት እና ልፋት የሚገኝ የዕውቀት አስኳል ነው ዶክተርነት። ዶክተርነት የሊቃውንት #ቁንጮነት ነው።
ይህ አካል #የዳቦ ጥያቄ አለኝ ሲል፤ የደህንነት ዋስትና ይኑረኝ ሲል፤ መኖሬ በዜግነቴ ደረጃ በልፋቴም ልክ ይሁን ሲል፤ በሊቃውንት የምትመራ አገር #ተግ ብላ በጥሞና በመከፋት ሳይሆን ደስ ብሏት ማሰብ ይገባታል። ቀዳሚ፤ መርህ አጀንዳዋም ሊሆንም ይገባል። ለሊቃውንታት የታሰበበት ማንኛውም ጥያቄ የካድሬ ዳኝነት አያስፈልገውም። ወንዝ ወደ ታች እንጂ ወደ ላይ አይፈስም እና። ለጥያቄው በልኩ በሳል ዊዝደም ገብ መልስ ሊሰጠው ይገባል።
አሁንም ደግሜ ደጋግሜ በትህትና የማቀርበው ጥያቄ አስቸኳይ #የካቢኔ #ጉባኤ ተጠርቶ በእርጋታ፤ በስክነት ዘላቂ መፍትሄ የሚገኝበት #የፖሊሲ እርምጃ ሊደረግበት ይገባል ባይ ነኝ።
ጥያቄው ከላይ ስለተነሳ የመካከለኛው፤ የታችኛው አካልን በዚህ ስሌት ሲመዘን የኢትዮጵያን የፖለቲካ የሂሳብ ስሌት መዝገብ ያሳያል። ስለሆነም የማያዳግም ቁርጠኛ፤ ቅን፤ ለዘመኑ የሚመጥን ሰውኛ እና ተፈጥሮኛ መልስ ሊሰጠው ይገባል - ለጥያቄው። ውሽልሽል ከሆነ መንገዱ መዳን አይቻልም። በሃኪሞች ጥያቄ ውስጥ ቀጣይ ትውልድም እንደሚኖር ግንዛቤ ውስጥ ማስገባት ይገባ ይመስለኛል።
ብዙ ጊዜ ይመስለኛል አበዛለሁኝ። ምክንያቴ ጥናታዊ ስላልሆነ ነው። በመረጃ በዳታ ለማቅረብ ስላልቻልኩም ነው። እኔ እስከሚገባኝ ድረስ የዘመኑ ሃኪሞች ጥያቄ በኢትዮጵያ የፖለቲካ ታሪክም #መቅድም ይመስለኛል። "#ራህበን!"
ራህብ ----= ከካቴና፤ ከስጋት፤ ከማስጨነቅ፤ ከፍርሃት፤ ካልተገባ ፍረጃ ጋር ማጋባት ሰውኛ አይደለም። እርህርህና እኮ የሰው ልጅ የተፈጠረበት ሚስጢር ነው። ቁራሽ እንጀራ ለጠዬቀ #ካቴና??? ጥያቄው ሰውኛ ነው። በሰውኛ ጠረን ሊመለስ ይገባል። #ለታጋሽ #ትሁት ጥያቄ #ትህትናዊ መልስ ያስፈልገዋል።
ውዶቼ እንዴት አደራችሁልኝ።
ቸር አስበን፤ ቸር እንሁን። አሜን።
ቅን አስበን፤ ቀና እንሁን። አሜን።
ኑሩልኝ። አሜን።
እግዚአብሄር ይስጥልኝ።
ሥርጉተ©ሥላሴ
#Sergute©Selassie
19/05/2025
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።
ዕውነት #ጋራጅ አያስፈልገውም።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ