LIVE: Austria's Eurovision Winner JJ Meets Chancellor Stocker | DWS News... ጥበብ የሆነ #የሊቃውንት #ጉባኤ በኦስትራሽ።
ጥበብ የሆነ #የሊቃውንት #ጉባኤ በኦስትራሽ። የአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስተር ከከፍተኛ የካቢኔ አባሎቻቸው ጋር አሸናፊውን አርቲስት ጄጄን (አርቲስት የኋንስን)እንዴት አክብረው አቀባበል እንዳደረጉለት። ዕውቅና በምን ልክ እንደሰጡት ተመልከቱ። አገር እና ህዝብ፤ ጥበብ እና መሪ፤ መሪ እና ትውልዱ #ዕውነት የሆኑበት ልዩ #ክስተት። ልዩ መታደል። ልዩ የምድር ገነት።
ለዚህም ነው እኔ ኢሮ ቪዥን ሶንግ ኮንቴስት በዬአመቱ ORF 1 እምከታተለው። ልዩ ጣዕም ልዩ ቃና አለው። የአርቲስት ጄጄ እናቱ ከፊሊፒን አባቱ ከኦስትርያ ዱባይ ለስራ ሄደው ነው የተገናኙት። እና ይህ ሙሉ አቅም ያለው ወጣት ከውህድ ማንነት የተገኜ ነው። ኢንቴግሬሽን ክብር ሲሰጠው፤ ውህድ ማንነት እንዲህ የላቀ ክብር ሲሰጠው ዓለማችን ያምርባታል። #እንማርበት።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
2025/05/19
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ