ሻለቃ አድማሴ ዘለቀ ከሞት ተነሱ!
እንኳን ደህና
መጡልኝ
የጠ/ሚር
አብይ አህመድ
ሦስተኛው … ው
መዶሻ በአቶ ዮናስ ደስታ።
„ሳቅን እብድ ነህ፤ ደስታንም፤
--- ምን ታደርጋለህ? አልኩት።“
መጽሐፈ መክብብ ፪ ቁጥር ፪
ከሥርጉተ©ሥላሴ።
Seregute©Selassie
22.04.2019
ከእመ ብዙኃን ሲዊዚሻ።
ጀግናን ጊዜ ይሰጣል! ሻለቃ አድማሴ እንደገና ተወልደዋል!
·
ክፍል ሁለት።
ክብሮቼ እንዴት አላችሁልኝ ... ዛሬ ቀኑም ፏ፤ ሥርጉትሻም ፏ ብላለች።
ቅኖቹ ቅኔዎቹ ... ክፍል አንድን በዚህ ነበር ያጠናቀቅኩት።
ሌላ አዲስ ተሿሚዎችን በሚመለከት ምክትል አድርገው
የሾሟቸው ፕ/ አበባው አያሌውን በሚመለከት ብዙ ጹሑፎችን በአንድም በሌላም በአዎንታዊነት ገልጫለሁኝ። ሚዛናዊ የሆነ እሳቤ ያላቸው
ናቸው፤ ትርፍ ነገር ለመናገርም የማይደፍሩ ዲፕሎማት
የሆነ ሰብዕና አይቸባቸዋለሁኝ።
የታሪክ ተመራማሪ እንደመሆናቸው በታሪክ ቀናይነታቸውም
እሳቸውም ከከአቶ ዮናስ
ጋር በተመሳሳይ አቋም የሚገኙ መሆኑን ነው እኔ የማስበው ስለምን ምክትል እንዲሆኑ እንደተፈለገ ግን ግልጽ
አልሆነልኝም። የተፈራ ነገር ስላለ ይመስለኛል። ያ ጠ/ሚር
አብይ አህመድ እንደ ጦር የሚፈሩት „አይ“ ቀጣይነቱም ስለ አለ ይሆናል፤
ከላይ ሌላ ጫኝ መንፈስ እንዲኖር የተደረገው …
ብቻ ያው ባለተራ እንደሚሆኑም አስባለሁኝ። ምክንያቱን
የጠ/ሚር አብይ አህመድ የሹም ዶሮ ነኝ መንገድ ብዙም ለዚህ ትውልድ መንፈስ አይመጥንም። ሥልጡን
አይደለም ዱካክም ነው …
ቅኔቹ … እንሆ ክፍል ሁለት …
የቀን ሰው፤ የእኩለሌሊት ሰው የድቅድቅ ሰው የንጋት ሰው የማለዳ ሰው የረፋድ ሰው የቀትር ሰው የማምሻ ሰው የምሽት ሰው እንዲህ እያለ ቡፌው ይዘረዘራል። ኢትዮጵያ መንግሥት አመራር የ አብይ መንፈስ በዚህ ልክ የተዥቆረጎረ፤ የተቀያዬጠ፤
የተሰባጠረ
ነው …
በቀንም በሌሊተም ሲሰራ ውሎ፤ ሲሳራ አምሽቶ፤ ሲፍርስ ውሎ ሲያፈርስ የሚያድር፡፤ የኔዎቹ እባካችሁን ሞገድን መጸሐፍ
አንብቡት። ብዙ ነገር ከዚህ አመራር ጋር ሹክ ይላችሁዋል። ሞገዱን አበጅቶ ሚዲያን እንዴት እንደሞነግድበት
… በዛ ላይ ከነጓዙ ወደ አገር የገባው ሁሉ ከግል ሰብዕናው
ጀምሮ የትውልዱን
መንፈሱን፤ የትውልዱን አቅሉን በምን መልክ ቤተ ሙከራ እንደሚያደርግ
እከሉበት እና ነፍስ በኢትዮጵያ ምን ያህል
ውጥንቅጥ እንደሆነ በአስተውሎት
መዝኑት …
ያም እንሱ የኦነጋውያኑን መንፈስ እስኪተገብሩ ፋታ ለማግኘት ነው ሲያሸበሽቡ
የባጁት … በጭብጨባ በጃኖ በተክሊል በሙገሳ
በውዳሴ ከንቱ … ያው በርድን
ተሸካሚው ሎሌው ብአዴን ሰርግ እና መልስ የነበረው … ብአዴን ሁለት ተልዕኮ
ተሰጥቶት ነበር ወጣቶችን
እዬሰበሰበ ብሄርተኝነትን እንዲተዉ ማባበል፤ በሌላ
በኩል በጥንድ ድርብ የታጠቀው የለማ መንፈስ የዲሞግራፊ ፍልስፍናውን
ካለምንም
ከልካይ የከውን ዘንድ የውስጥ ሰላሙን ማስጠበቅ …
ግን ግን ግንቦት 7 ወደ ዴያስፓራ ከነኪሳራው መቼ
ይሆን የሚመለሰው የናፈቀኝ
እሱ ነው … ሃሞት ቢሆንም … ስንት መንፈስ አድቅቆ፤ ትጥቅ እስፈታ? ይህ
መራጃ የሌላ ፕላኔቴ የመረጃ
ባለሙያ ያስፈልገዋል … ይመስለኛል፤
·
እንዴት ግን ?
እኔ ጠ/ሚር አብይ አህመድን የማውቃቸው በመንፈስ
ለፍቅራዊነት እንቡጢጣ ፕሮጀክቴ
በዬአህጉሩ ንጹሃን መንፈስን ሳፈላልግ ነበር ያገኘሁዋቸው የዛሬ ሦስት ዓመት። ከዛ መንፈሳቸውን
ስለተመቸኝ መከታተል ጀመርኩኝ።
በሳቸው ጉዳይ ጎርባጣ የሆኑ ነገሮች አሉ ሲባል
ወደ ፖለቲካው መድረክ ሲመጡ ማለት ነው
በዓይኔ መጣችሁ ብዬ በቀደመው
የመንፈስ ቤተኝነቴ በጣም በሰፋ ሁኔታ ተሟግቸላቸው
አለሁኝ።
ያው እሳቸው ፌስ ቡክ መደበኛ ሥራቸው ስለሆነ፤
በዛ ላይ ማንበብ ይወዳሉና አንብበውታል
ብዬ አስባለሁኝ። ጹሑፎችን ብዙ ሰዎች ሸር ያደርጉት ስለነበር ከደጉ ሳተናው ብራና ላይ
ማለት ነው። የነበረኝ እርግጠኛ የሆነ ጤናማ መንፈስ ነበር የዛሬን አያድርገውና። ዛሬ እሳቸው
ከላይ የዘርዝርኳቸው የጊዜ ሂደት ዝንቅ ፍላጎት ቤተኛ ናቸው።
ሰብእናቸው እዬተቀረፈፈ
ቀደም ያለው አወንታዊ ጥሪቱ አውሬዎ ያልሆነ ሰዋዊ፤
ተፈጥሯዊ መንፈስን የተላበሰ ሰብዕና
ያላቸው ሙሉሰው፤ ምራቁን የወጣ የተረጋጋ መንፈስ ባለቤት የሆኑ፤ ደልለዳ እና በወጀብ
የማይናወጽ
ሃሳብ ማፍለቅ የማይገደው ሰብዕና፤ ሩቅ ያለመ ተፈጥሮ፤ በሃሳቡ በቃሉ የሚጸና
አድርጌ ነበር ከውስጤ የተቀበልኳቸው።
እንዲያውም ወንድሜ በሆኑልኝ ሁሉ ብዬም ነበር።
የሚያሳስበኝ መልካም ሰውነታቸው ጎልቶ
ይታዬኝ ስለነበር ህይወታቸው ላይ ጥንቃቄ ያደርጉ ዘንድ አሳስብና አብዝቼም እጸልይ ነበር።
እንዲህ ዓይነት ተዛነፍ የሆነ ሰብዕና ፈጽሞ አላስበውም
ነበር። እምነቴ ሙሉ እና
ደልዳለ ነበር።
ያ አቅም አገር ላይ ሃላፊነት ተረክቦ የማይበት
ዘመን ነበር ያጓጓኝ የነበረው። ተስፋ ሲለመልም፤ ስንባረክ፤ ስንመረቅ፤ አበረን ስንደሰት፤ አብረን ፈተናውን ሁሉ ተረዳድተን ስንገረስስ፤
ስንደጋገፍ፤ ስንጽናና እንጂ መልሰን ከዛ ከነበርንበት ተዘፍቀን ስንረጋገም፤ ስንናናቅ፤ ስንበቃቀል፤ ሴራ ስንተክልና ስንኮተኩት
መሽቶ ይነጋልናል ብዬ አላስብኩትም ነበር።
ከሁሉ በላይ ቤተሰባዊ አቀራረባቸው የሁሉም ሃብት
ሆነው አያቸው ዘንድ ብዙ አድክሞኛል።
ዛሬ ደግሞ ሌላ ዝንቅ ቅይጥ ሰብዕና ላይ ናቸው። አዝናለሁኝ። እኔ እውነት ተነጋሪ ብባል ፋሲል
ግንብ
የተደረመሰ ያህል ነው የተሰማኝ የአቶ ዮናስ ደስታን ስንብት ሳዳምጥ። መትከል ሳትችል የተተከለን ስትነቅል ትንሽ ድፈረቱ ልክ አጣ …
የሰው ልጅ መላዕክ አይደለም። ስህተትን ማድመጥ፤
ስህተትን መቀበል ካልተቻለ መሪነት ከወንዝ
ላይ የተንሳፈፈ ኩበት ነው የሚሆነው። ወይንም ውሃ ሲሄድበት የባጀ አለት …
ስለምን ድርጅታችን ሳያውቅ ይህ ተከወነ ብሎ መጠዬቅ እርግጥ ከሆነ ምን እንደሚጠብቀው ትውልዱን አሳሳቢ አደጋ ላይ ያለ መሆኑን
ያመላክታል።
ቅርሳችን ውርሳችን ትውፊታችንም አደጋ ላይ ነው።
ስለምን ብትሉ የአማራን አገር አባጅነት
ማድመጥ አይፈለጉም በተደጋጋሚ ሲያወጉዙት አዳምጣለሁኝ፤ አማራ በዚህ ደግሞ በዳይ ተደርጎ
ስለደረሰበት የጸር ማጽዳት ፖሊሲያዊ መከራም ይክዳሉ፤ ወደፊትም አገር መምራት አትችሉትም ብለው በልበ ሙሉን ይነገራሉ በአደባባይ
… በዚህ ውስጥ ሆኖ እሳቸውን ለሚይ ቁሮሾ አላባቸው የሚሰለስላቸው፤ ውስጣቸውን የሚቆረጣጥመው …
አዲስ ኦሮማማ የሆነ መንፈስ ለመገንባት ጥድፊያቸውም ያ ዘመናትን የተሻገር
ስልጣኔ ቅድድ
አድርገው ማግደው ቢሞቁት ይሻሉ … ለዚህም የቆረጡ ስለመሆኑ ምንም ማስተባባያ ማቅረብ አይቻልም … ለዚህ ነው አዲስ
አባባ ላይ አዲስ የዴሞግራፊ ለውጥ እንደ ፍልስፍና የተያዘው።
ለዚህም ነው ቀዳሚ የጥቃቱ ሰለባ አቶ ዮናስ ደስታ
የሆኑት። እሳቸውን መንቀል የጀመጀሪያ
ተልዕኳቸው የሆነው። በዚህ እርምጃ እኔ እኒያ ብቻቸውን ተነጥለው ሲሞግቱ የነበሩት የጀግኖች
አውራ ሻለቃ አድማሴ ዘለቀ እንደገና እንደተፈጠሩ ነው የሚሰማኝ። ትንሳኤያቸው ነው ይህ ቀን
አቶ ዮናስ ደስታ ታሪካዊ እርምጃ የታወጀበት
ቀን።
ዛሬ ማንም አይታዬውም ከ10 ዓመት በኋዋላ ሁሉ
ነገር ወላልቆ ከተገጣጠመ በኋዋላ ሁሉም
ጸጸቱን ተሸክሞ ያገኛዋል። ትውልድ የማይተካቸውን ፕሮፌስር አስራት
ወልደዬስን ተከተልን
ቢሆን ኖሮ ይህ ሁሉ መከራን የመሸከም ታሪካዊ ግዴታ ይህ ትውልድ አይኖርበትም ነበር።
·
መሪነትን
ስጠብቀው ወይንም ሳስበው በጥቂቱ …
የመሪነት ቃና መጀመሪያው ማድመጥ ነው። ማድመጥ ከሌለ
መሪነት ባይፈጠር ይሻለዋል።
መሪነት ህግ እና ሥርዓት አክባሪነት ነው። ህግ እና ሥርዓት ተራጋጭነት ከመጣ
መሪነት ተኗል።
መሪነት ምክር ተቀባይነት ነው፤ እኔ አውቃለሁ
በሁሉም ዘርፍ ከመጣ እንደመሸበት
ይኖራል
መሪነቱ። መመራት ይቻላል ግን የህዝብን ህሊና አይደለም አይሆንምም የሚመራው የሸፈተ
ልብ ብቻ ይሆናል። ህሊና
ላይ መምራት አይደለም መንፈሱን ለማቀራረብም ይቸግራል።
እኔ አውነቱን ብናገር በዬእለቱ በሚፈጥሩ የጠ/ሚር
አብይ አህመድ አደናግሬ ትውና
ከጋዜጣዊ መግለጫዋ ወዲህ ያደረጉትን ንግግር አቅም ስላጣሁኝ አላዳመጥኩትም። ቀደም
ሲል ተስፋ ለመሰነቅ፤
ህሊናዬን ጤና ለመስጠት እስከ 6 ጊዜ የማዳምጠው ንግግር ነበር ዛሬ ለመታመመ፤ ለመቁሰል፤ ለመምገል፤ ተስፋ ለማጣት ለምኑ ብዬ
ላድመጠው … ዴሞግራፊው
እንደ ዶር አንባቸው መንፈስ ለማስበወዝ … እእ። ለ እብሪት የሚሆን የህሊና ስጋጃ የለኝም።
መቼ ነግቶ አዲስ መንፈስ ፈዋሽ ቃለ ምህዳን ሰምተን የምልበት ቀን
እኮ እዬራቀን ነው …
ለዛውም ስለሳቸው በግንባር ቀደምትነት የተጋሁ፤
ማህበራዊ ኑሮዬን ያቀወስኩት እኔ ሥርጉተ
ሥላሴ። አሁን ይገርመኛል አሁን ከሆነ አንዳንድ የኦሮሞ
አክቲቢስቶች የቀደመውን ንግግራቸውን ሲለጣጠፉ፤ ሲጽፉ ወዘተ … ያን ጊዜ የት ነበሩ ለመሆኑ?
ሰሞኑን ደግሞ አዲስ ወግ ተይዟል እንሱ ትወናቸው
አያልቅም፤ ይሉኝታም የላቸውም። ባቢሎን
ግንቡን የገንቡትን፤ ዘፍጥረትን በድፍረት የደረመሱትን አውሪያዊ መንፈስ ማንፌስቶ ጸሐፊን
አቶ በቀለ ገርባ በሚዲያ ሲያሽሞነሙኑ፤ ግራጫማ ጃዋር መሃመድን ሰብዕና የሚሞግቱ
የራሳቸውን ሰዎች በመሳለፍ፤ እንደ ከብት የሚዩትን
ለብአዴን አሞሌ የሥም ብቻ የውጭ
ጉዳይ ቦታን በመስጠት፤
በግንባር ቀደምትነት አማራን ለሎሌነት፤ ለስንኛው እግር ብረት እንደሆን
አይታውቅም የጃዋርዊው
አቶ ንጉሡ ጥላሁን ስሌት ተሳክቶ አንቦ ላይ ስለሆነው አዲስ የሰብዕና ግንባታ ልክ የጣና ኬኛ
መከራ ተደግሞ
ስለገዳላችሁን፤ ስላፈናቀላችሁን፤ ስላቃጣላችሁን፤ ዳር አውጥታችሁ
ስላንገዋላላችሁን እንማስግናለን የሚል ግዑዝ መንፈስ ጋር „እያሪኮ
ቡርቃ“ የሚል
አዲስ ስንጥቅ ስንጥር ወልጋዳ ዜማ ደግሞ ተይዞ አዲስ የሰብዕና ግንባታ ላይ ሰው ተጥዶ
እያዬሁ ነው። አውነት እብኖች
ነን። አይበቃም ወይ ጅልነቱም ሞኝነቱም።
እንዲያውም እኔ ይህን ሳይ ሰው እና እንሰሳ መለዬት
ነው የቸገረኝ። ሳተናውን
እንደ ህሊናዬ ነው እማከበረው፤ ሰላም መሆኑን ለማረጋገጥ ሳላዬው አንድም ተግባር አልጀመርም ትናንትም ዛሬ ስከፍተው በሩን ይኸው
ነው ከእርእሱ በስተቀር ከፍቼ ለማንበብ ፈቅዳ አጣሁኝ። የማንን ሰብዕና
ነው እምንገነባው … ኢትዮጵያ በፀርነት ተይዛ ርዕሰ መዲና
አልባ በስጋት ተወጥራ ስለነሱ ደግሞ
አሁን ሰው መድከም አለበትን? ግን ምኖች ነን? ጊዜም ሁኔታም የማይሰተምረን?
ታስታውሱ እንደሆን ጠ/ሚር አብይ አህመድ የመጀመሪያ
የባህርዳር ጉዟቸው ስለ አኖሌ ሲነሳ
እንዴት ደማቸው እንደተንተከተከ አሁን ሁሉም አለቀ ዓመት ሙሉ የአማራን ነፍስ ባሻቸው ያህል
ሲጎረጎሩ ግማሽ ሚሊዮን ነፍስ ብወዛ ሲያካሄዱ ባጅተው ለሌላው ትልም ደግሞ ትንፋሽ ለመሰብሰብ አዲስ ትወና ላይ ይገኛሉ እና ይህ
ምኑ ይነበባል? እኔ አኖሌን እንደ ቅደመ መደራደሪያ የሚአደርጉት ሰዎች ይገርሙኛል። አጀንዳዬ ሆኖ አያውቅም።
በይፋ በአደባባይ ዲሞግራፊ እርስ መዲናህ ላይ
እዬተካሄደ፤ የጎረምሳ ማህበር በመንግሥት አገር
ስብሰባ እያገደ፤ ጋዜጣዊ መግለጫ እያሳገደ፤ አራስ በገርዲር እያታረሰች፤ አኖሌ
ፈረሰ አልፈረሰ
ስለ አኖሌ ተቀሰቀሰ አልተቀሰቃሰ ምኑ ይሆን ትርፉ?
አሶሳ፤ ወተር፤ አርባጉጉ፤ በደኖ፤ ላይ እኮ ድርጊቱን
የፈጸሙት እኮ ናቸው ዛሬ አማካሪዎች እነ
አቶ ሌንጮ ለታ … ኬምሴ፤
አሳዬ ማጀቴ አዲስ አባባ ላይ ህዝብ እንደጉድ መንፈሱም አካሉም እዬተረሸነ ምን አኖሌ ምንስ አቶ ተስፋዬ ገብረ አብ ያስኬዳል ከወይዘሮ
ጠይባ ሃሰን ጋራ አብረህ
እጅ ለእጅ ለመያያዝ … ከ/ወሮ ሃቢባ ሲራጅ ጋር አብረህ ማዕደኛ ለመሆን ምኑ ይሆን የሚያጓጓህ? እብንነት
… ም አለው አይነት …
የማዬው ገለባነት ግርም ይለኛል … ጣና ኬኛስ
ያን የሶቃቃ ዘመን ረስተን ልባችን ከፍተን በበዛ
ቅንነት እና ልበ ሰፊነት ተቀበልን፤ ለዛም ተጋን፤ በተጋነው ልክ ታማኝነት እና
ካህዲነትን እነሱን
አሳምረን አዬን … ከቶ 4 ሚሊዮን ብር ትራፊ የ ኦነጉ ባንክ አስተዳደር ስላክልህ ይህ ክብርህ ሆኖ ይሆን
… ለዚህም ነበር እኮ እንደ ከብት አሞሌ ስጡት ተብሎ የአዲስ አባባ ከንቲባ ቢሮ 10 ሚሊዮን እርዳታ ሰሞኑን ያዳመጥን … ከከብትም
ማነሳችን ይኸው ነው …
ሰው ራሱን እያስገደለ፤ መንፈሱን እያስጣሰ፤ ክብሩን
እያስረከበ፤ ትውፊቱን እያስደረመሰ፤ የራሱ
ልጆች በዬምክንያቱ እያስመነጠረ፤ ቅርስ እያቃጣለ እንዴት ደግሞ ለአዲስ የሰብ ግንባታ
ይሰለፋል?
እነሱ ከጠ/ሚሩ ጀምሮ ስለ አድንድ አማራ ሊሂቅ፤
ስለ አንድ አማራ ድርጅት፤ ስለ አንድ አማራ ጋዜጠኛ፤ ስለ አንድ
አማራ ጸሐፊ፤ ስለ አንድ አማራ አክቲቢስት፤ ስለ አንድ አማራ መከራ፤ የጻፉት አይደለም፤ በመጻፉ አይታሙም የተናገሩት ….አለን።
እስኪ ስለ አማራ ሊሂቃን ሥም በጠ/ሚሩ አንደበት ተጠርቶ ሰምታችሁ ታውቃላችሁን?
ሲዳማ ላይ ምን እንደሚሰሩ፤ ጉሙዝ ላይ ምን እንደሚሰሩ
ፈጣሪ ብቻ ነው የሚያወቀው አንድ
ቀን ላለደረ የክልል መስተዳድር ሹም ጋር ድርድር? ምስክርነት ከቶ እኔ ሰው ሁሉ እንዴት ያለ
ፍጥረት ይሆን ያለው።
ቢያንስ በአንድ ቀን ውስጥ የቀደመ መሪ ሽኝታ፤
የተከታይ መሪ ሹመት፤ የ አማራ እና የኦሮሞ
ውይይት ጥድፊያው ለምን
ስልምን? የቀደሙት ሊሂቃን ለ አማራ ከቶ ይህን ነው ያወረሱትን?
ዶር አንባቸው መኮነን በእጅጉ አነሱብኝ። ሌላው ዝብርቅ እና ብርቅርቅ
ትቼ ማለት ነው …
ሎሌነት እንዲህ ይጥማልን? ትናንት ለተጋሩ ዛሬ
ደግሞ ለ ኦሮማማ … ኦሮሙማ መሆኑን
አውቃለሁ ቲም ለማ ኦሮሞ ነው ማማው … ለዚህ ነው እኔ ኦሮማማ የምለው …
በውነት ቋቋ ነው ያለኝ… ከፍቼ ማዳመጥ፤ ከፍቼ ማንበብ ስለምን ብዬ? በዚህ
ኦነገን
እስካፍንጫው አስታጠቀው፤ በተሟላ ሌጅስቲክ ህዝብን ያሳርዳሉ፤ ህዝብን ያሰቅላሉ፤
ህዝብን ያሰቅቃሉ፤ ቤተ መንግሥት ያቃጥላሉ፤
በዚህ ስብሰባ ላይ ለአንድ ሰፍር ተብሎ
ህገመንግሥት አይቀዬርም እያሉ መንፈስ ያላሽቃሉ፤ በዚህ ጎረምሶቻቸውን አሰናድተው
ጀግና
ያሳድዳሉ፤ በዚህ ካንሰር ተክለው ስጋት ሽብር በህዝብ ላይ ይለቃሉ ዓመት ሙሉ
ይህ ክብር ይህ ልዕልና ሆኖ ደግሞ ስለነሱ ሰው ተሰልፎ
ሲያንቆለባብስ ይገኛል … ሰብዕና
ሲገነባ ውሎ ያድራል፤ ያመሻል፤ ያነጋል።
በውነቱ ዶር አንባቸው መኮነን በግንባራቸው ሳይሆን የጀርባውን
ባሩድ መቀበላቸውን በጥልቀት አስተውዬበታለሁኝ። ሽንፈት ነው! የግንቦት 7 ሊቀመንበርን ፕ/ ብርሃኑ ነጋ ሰብዕናን OBN
እንዴት
ጢባ ጢቦ እንደተጫተባቸው ተመልክተናል። አሁን ደግሞ በሉላዊው መድረክ ዶር
አንባቸው መኮነን ውልቅልቃቸውን ነው ያወጣው ገና በጥዋቱ።
መልሶ ለመነሳት አይቻልም።
ፈጽሞ። እኔ እንዲያውም የቀደመ የሚያስፈራ ምን ገመና ኖሯባቸው ነው እንዲህ ለጥይበሉ
የሆኑት ሁሉ ብያለሁ
ለዛውም ታች ጋይንት እና ገብርዬን ሳስበው …
ለዚህም ነው የውጭ ጉዳይ ሚ/ር ቢሆኑ ዶር አንባቸው
መኮነን ስኬቱን በማጨናጎል የቀደመ
ትወና የተከናወነው። ለ ዓለም የ ኢኮኖሚ ፎረም ስብሰባ እንኳን አላበቋቸውም የአሜሪካ
አንባሳደር
ሆነው ከተሾሙ በሆዋላ ወደ ዛ የወሰዷቸው አቶ ፍጹም አረጋ ነበር። እነሱ በንድፋቸው
ልክ ነው የሚንቀሳቀሱት፤ ለራሱ ለውጭ ገዳይ
ሚ/ር ገዱ አንዳርጋቸው ሌላው ግማድ ደግሞ ነገ የሚታይ ይሆናል … የለወጥ ሐዋርያነት በዚህ እና በዚህ ይመነዘራል … በመውደቅ
እና ማህበራዊ መሰረትን አሳምሮ በመመንጠር …
ለዚህም ነው አዲስ ሰው ይዘው ብቅ ብለው አጉልተው፤
አስደምቀው፤ ሰብዕናውን ለመገንባት
አቶ ሽመልስ አብዲሳን ላይ ልዩ ትትርናው ጎልቶ የሚገኘው፤ አንዱን ከፎቅ አውረድህ ስትፈጠፍጥ
ሌላውን ደግሞ እጬጌ ማድረግ፤ ልብ ከዬት ይገዛ …
ስፔን እግርኳስ 2010 ላይ ከጀርመን ጋር በነበራቸው
ጨዋታ ጢባ ጢቦሽ ነበር የተጫወቱባቸው ለዛውም የጀርመን ቡድን 6 ለባዶ ሁሉ የሸኛቸው ቡድኖች ብቻ ሳይሆን እነ ሙለር የወርቅ ጫማ
የተሸሉበትን አቅም ነበር ያን ያህል … እንደዛ ያደረጉት …
አሁንም ያዬሁት ይኽንኑ ነው … የየህወሃቱ ኦህዴድ/
የኦነጉ ኦዴፓ አማራን ሰፋሪ፤ ስደተኝ፤
የጎንደር ሰው ድሮም ሽፍታ ነበር፤ ከጎንደር እና ከወሎ የመጡ ሌቦች፤ ዘራፊዎች፤ ጫተኞች፤
ወንበዴዎች፤ የደረቅ ወንጀል ባለሟሎች ስትባል ባጅተህ አሁን ደግሞ ለዋንጫችን ያቅለሸልሻል
… ምን ያህል አማራ ሰው አልባ እንደሆነ ጥቃትን ትጥቁ እንዳደረገ አስተውዬበታለሁኝ።
ከውድቀቱ የማይማር ግርባ
ድርጅት ነው የህወሃቱ ብአዴን/ የኦነጉ አዴፓ ማለት።
ዛሬ በሚኒሊክ ቤተመንግሥት እደሳት ባለሙሉ ሥልጣን
ዳይሬክተር ሳይጠዬቅ፤ ሳይማከር
ስለሆነው ነገር በአንድ ደብዳቤ ሲባረር ይህ የምሥራች ሆኖ መርዶውን ተሸክሞ ከረባት እና
ገበርዲንን
አሳምሮ እንዲህ መሆን የሽንፈቶች ሁሉ ቁንጮ ነው ለእኔ። ብአዴን በዚህ ጉዞ
ተዋርዷል ማቅ ለብሶ ነው የሚመለሰው።።
አቶ ያሬድ አስራት በቲተር ገፃቸው እንዲህ ሲሉ
ነው የገለጹት። የ እኒያን የዘመን አርበኛ፤ ደፋር፤ ጀግና የ ኢትዮጵያ ባለውለታ …
„አቶ ዮናስ ደስታ፤ የቅርስ ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር፤ "የሚኒሊክ ቤተ-መንግስት ታሪካዊ ቅርስነቱን ባልጠበቀ መልኩ መታደሱ ስህተት ነው" ብሎ አስተያየት በመስጠቱ በጠ/ሚ አብይ ደብዳቤ ዛሬ ከስልጣን መነሳቱ ታውቋል። „#StopDestroyingOurHeritage“
ይህ
የሁሉም ድምጽ መሆን ሲገባ፤ አብሶ „ለሚኒሊክ ሰፋሪዎች“ ለአዲሱ ሽብሸባ ደግሞ አዲስ የሞት ዋዜማ ላይ እንገኛለን ….
·
መሪነት እና ላንቁሶነት።
ወደ ቀደመው ምልሰት ሳደርግ መሪነት ለሁሉም ሙያ
ባለሙያ ስላለው የባለሙያን
ነፃነት የመጠበቅ ብቻ ሳይሆን
አክብሮ የመቀበል፤ ዝቅ ብሎ ምክር የማግኘት ነው።
እጅግ ደግ መሪ ስለበሩ እራሱ በካራ እና በቅባት መሃል ተፈጥሮ የነበረውን የመቋሚያ
መቀጣቀጥ በዲሞክራሲአዊ መንገድ ሁለቱን ወገኖች ቁጭ አድርጎ የሊቀ ሊቃውንት
ጉባኤ ተሰይሞ በሃይማኖታዊ ዶግማ ሙግት ነው ፍትህ
እያዲያገኝ ያደረጉት ይላል ስለሳቸው የተጻፈው ታሪክ።
የንጉሦስ
ንጉሥ አጤ ሚኒሊከልም ቢሆኑ የ አንቀጽ 17 የሸፍጥ ውል እንደረመስ ያደረገው ባለቤታቸውን የማድመጥ አቅማቸው ነው፤ የንጉሶች ንጉስ
አጤ
ቴወድሮስም ብስጩ የሆኑት ባለቤታቸው እቴጌ ተዋቡ በሥጋ ሲለዮዋች ነበር አሉ።
ይህ የሚያሳዬው አድመጭነት ሲጠፋ አድማጭነት
ሲኖር ያለው ርጋ መንግሥት ልዩነት አለው። እንኳንስ ዛሬ በዚህ ባልጸናው ኢትዮጵያዊው አልጋው። ብዙም ጠላት
ማብዛትም መልካም አይደለም።
መሪዎች ማድመጠን የተው ዕለትንለመሪነት እዮር የፈቀደው ምርቃት ይበረግግና
ይሸሻል። ምክንያቱም መሪነት ለአሉታዊውም ሆነ ለአዎንታዊነት እዮራዊ ቅብዕ ነው።
ሰው ስለፈለገ መሪ መሆን አይችልም። ስላልፈለገም
መሪ ሳይሆን አይቀርም። መሪነት አብሶ የአገር መሪነት እና ሃይማኖታዊ ሥልጣን የፈጣሪ ቅብዕ ነው። ዕድሜልካቸውን
የ አገር መሪ
ለመሆን እንዳለሙ የሚያልፉ ብዙ ሰዎችን ዓለማችንም አገራችንም አስተናግዳለች። ይህ የሚሆንበት ምክንያት መሪነት ቅብዕ ስለሆነ ነው።
አንድ ሰው መሪነትን ጸጋ ሲያገኝ ዕድሉን ዘመኑን
በምርቃት ለማሳለፍ ራሱን ዝቅ
ማድረግ ይኖርበታል፤ በስተቀር ይወድቃል። መንጠራራት፤ ማበጥ፤ አይደለም ለመሪነት ለተመሪነትም አይሆንም።
ቢያንስ ከእኔ በላይ አንድ ፈጣሪ አለኝ የፈጠረኝ ብሎ ማሰብ ይገባል።
አንድ መሪ የበዛ ታጋሽ መሆን ይኖርበታል። አይቶ
እንዳለዬ፤ ሰምቶ እንዳልሰማም፤ እንኳንስ ራሱ ለፈጠረው ችግር ሌላው በፈጠረው ችግር ሳቢያ አጥፊ ነህ ቢባል
እንኳን ስቆ ደስ ብሎት
በአክብሮት ማሰረዳት ይገባዋል እንጂ እኔ ቃለ ወንጌል
ወይንም ቁራአን ነኝ ማለት አይገባውም። መታበይ መጨረሻው መሰበር ስለሆነ።
እውነት ለመናገር ጥያቄው እኮ እውነት ነው። ወይንም
የቅርስ ጥናትና ጥበቃ
ባለስልጣን ቢሮውን
መዝጋት ወይንም እሳቸው ደርበው መስራት ወይንም
ባለሙያዎችን ማማከር ግድ ይላል። አሳቸው እኮ ብዙ ነው የሆኑት። ሌላ
ሰው አገር
አልፈጠረች ይመስል። ኧረ በህግ …
ስንት ጉድ ነው የራስ ገመናቸው ከሰብዕና በታች
ድቅቅ አድርገው እንደ ሰው አልተፈጠርክም ያሉት፤ እነሱ እንኳን ክብር አግኝተው ጠባቂ ተመድቧላቸው
ስንት ጉድ አይተናል። እስኪ
የሄ በ በአደብ ይደመጥ። ከዚህ መንፈስ ጋር
ትቅቅፉን ብቻ ሳይሆን የሚሊዬንም አዳራሽ አቀባበል ራሱ ምስከር ነው። ከዛም በዬሚዲያው
የመደረገው ቃለ ምልልስ „አቅም የለም፤ መሪው እኔ ነኝ ነው“
„ሕወሓት ለማ መገርሳን ለጠቅላይ ሚኒስተርነት ለምን አልፈለገችውም – ጀዋር መሐመድ ያብራራል | ከሳዲቅ አህመድ ጋር ተወያይቷል“
ለነገሩ ዬዬትኛውም የፖለቲካ ድርጅት ሊቀመናብርት
ችግር ይህ ነው። ዬትኛውም
ተጽዕኖ ፈጣሪ ነፍስ መከራም ይኸው ነው። እነሱ ካሉት ውጭ አይቀበሉም። ባለው
ላይ አቅምን አሰባስቦ
ማጠናከር ሲገባ እነሱ ጎልተው፤ ጎምርተው መውጣት
ካልቻሉበት አዳዲስ ውጥኖች መክነው እንዲቀሩ መትጋት፤ የራሳቸውን ያፈነገጠ
ነገር
መፍጠር መጨረሻ ላይ እንሱም ሳይበረክቱ መንፈስን ነፍስን መበተን ነው።
ትውልድን ማባከን።
አሁን በ ዶር አብይ ደጋፊና ተቃዋሚ መሃከል ያለው
ጉግስ ይገርመኛል። እኔ ፅኑ ዳጋፊያቸው ነው የነበርኩ ዛሬ ሁሉም የ እኔ ሳይላቸው ግን ያን ጊዜ የደገፍኩበት
ሰብዕና ካጣሁኝ መቃወም
ደግሞ መብቴ ነው። የድል አጥቢያ አርብኛው ሁሉ
ነው አሁን ልማታዊ ካድሬ ሆኖ አገር እያመሰ የላው።
·
መውጫ በር
ለለት።
እውነት መወገን። እውነት ስትጠቀጠቅ አይ ማለት ይገባል። አሁን
በሚታዩ የነጠሩ ሃቆች ላይ ጎሽ አበጀህ፤ ቀጥል ከሆነ ከዚህ በባሰ ነገ አውሬ ሆነው ይመጣሉ፤ አንድ ቀንጣ የተለዬ ሃሳብ የማስተናገድ
አቅም ፈጽሞ የላቸውም ጠ/ሚር አብይ አህመድ።
እኔ ያ የርግጫ እና የፍጥጫ ምርጫ መጥቶ አይቸው
ብያለሁኝ። መኖሩ ከተገኜ። በርደኑን የሚችሉት አይመስለኝም፤ ከአሁኑ ነፍሳቸው ደንጋጣ- ርብትብት - ፈሪ- ትጥቅ ፈቺ ሆኖ ነው
የማዬው። የገቡት ቃል፤ የፈረሙበት ውል ያለ ነው የሚመስሉት … ለ ኦነጋቸው ሆነ ኢትዮጵያን በልጽጋ ራሷን ችላ ማዬት ለማይሹት
ቀደምት ጠላቶቿ ሁሉ …
ውዶቼ ይቀጥላል …
(ከአቶ
ያሬድ አስራት ቲተር ገጽ ላይ የተወሰደ።)
ትእግስት ሲያልቅ ፍቅር ይሰደዳል!
የኔዎቹ
ኑሩልኝ
መሸቢያ
ጊዜ።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ