27.0.2022vኢትዮጵያ ከሊቅ እስከ ደቂቅ ከብዳናለች ትለለች ሥርጉትሻ።

እንኳን ወደ ከበቡሽ ብሎግ በሰላም መጡልኝ። 

ከሰሞኑ ፌስቡክ ላይ የሰራኋቸው ስብስብ። 27.07.2022

 

ኢትዮጵያ ከሊቅ እስከ ደቂቅ ከብዳናለች ትለለች ሥርጉትሻ።

የኢትዮጵያ ቅዱስ መንፈስ በገብያ ህግ አይተዳደርም።

መስቀል እልል አለ።

የኔታዊት በትፍህስት ራዕይ። መስቀላዊት በድል ጎዳና።

አራት ዕርዕሰ ጉዳይ አዋህጄ ላቅርብ።

"የቤትህ ቅናት በላኝ።"

አባ እንዴት አደሩልን? ደህና አደሩልኝ? ይፍቱኝ አባት ዓለም። አሜን።

ህሊና ይሞገት። በዬቦታው በጓዳ የተከዘነውን። በጦርነቱ ወቅት አባ ለአንድ ሠራዊት ሲያሳልሙ ፖስት አደረኩኝ።

እሳት ለብሳ እሳት ጎርሳ አንዲት አንስት ተነሳች። ምኑን ለጠፍሽ ብላ? ቀደም ባለው ጊዜ ላስረዳ እደክም ነበር። ዛሬ እንደዛ የለም።

ቅንነት ከተነነበት ጋር አቅም ማባከን ደግ አይደለም። መራራ ስንብት ይፈታዋል። ደጅ ላይ ቁመው የሚጠብቁኝ ቅኖች አሉ። እነሱ ቤተኛ ይሆናሉ። እራሱን ቆልፎ ለሚመጣም ቤቴ ህግ አለው።

የሆነ ሆኖ ያቺ ያልታደለች እህቴ ተዋህዶ እዮራዊ መሆኗን ስታ የብፁዑ ወቅዱስ አባቴን በረከት ከፔጅሽ አልይ ስትል በአክብሮት አሰነባትኳት።

ብዙ እንዲህ ዓይነት ሰብዕናወች አሉ። የመሸጉ የልዩነት አታሞወች ሌላም አዋሳ በግፍ የታረደችው እጩ ሊቅ ትግሬ አማራ በማለት ሃዘን ላይ የወደቁ ቤተሰቦችን ሲያቆስሉ ነበር። ያችን የመሰለች አበባ ወጣት አፈርነት አልነበረም ጉዳዩ።

የሚገርመው ሌላውን የሚያዝኑትን ሁሉ ረስተው የነበሩ ነበሩ። ታዝቤ ታዝቤ ሲበቃኝ መራራ ስንብት ሆነ። ሃዘን ካላስደነገጠ፣ የሞት ዓዋጅ ካልረበሽ እኛ ምንድን ነን?

#አሁን ደግሞ ……

የኦዳወገዳ ሥርዓት በእኛ ዘመን መርተን ለድል በአትሌቲክሱ መራን በቃን እያሉ ሰነበቱ። ሦስቱም አንስት ወርቅ ግኝት በብሄረሰብ ከሆነ ትግራዋይ ናቸው። ይህ አይካድም። ትውልድ እንዲህ ነው የሚታነፀው። የሠሩት ድል አሰበለ።

ኢትዮጵያ በደረጃ ሁለተኛ ናት። ትግራዋይ ባይኖሩ ብለው የጠዬቁም አሉ። ፈጣሪ ሌላ ያሰናዳል። ምክንያቱም #የኢትዮጵያ #መንፈስ #በገብያ ህግ ስለማይተዳደር።

ይህን ያደረገውም እዮራዊ ሚስጢር አለው። የተደሙ አባቶች ይፍቱት። ባለወርቆች ባለመስቀል ናቸው። ተዋህዶ ቀራኒዮ ላይ ናት ከእነ ሰንደቋ በአገረ ኢትዮጵያ። ከአርማዋ ላይ ለጠፋ። እሱም አልሆነም።

መንበረ ፀባዖትም በገዳ ወረራ፣ በገዳ አስምሌሽን፣ በገዳ ዲስክርምኔሽን የወደቀ ነው። አራት ዓመት ያዬነው ይህን ነው። መንበሩ ስንት ጊዜ ያልተገባቸው ጠቀጠቁት? በደል ይረሳል ወይንስ ይለመዳል?

የኔታዋ ግን በአገር ብትሰደድም በዓለም አደባባይ ልጆቿ ታምር ሠርተው ዕንቁነቷን አሳዩ። #መስቀል ከበረ። #መስቀል እልል አለ። #መስቀል ሐሴት አገኜ። ትፍስህትም ሆነ። ሆኖ የማያውቀው ዕውነት ሰበለ አሰበለ።

በዚኽው ሰሞን ኢትዮጵያ ስለከበደችን በዬጓዳው የሚርመጠመጥ ገመና ነበር። ያላወጣው ያልተነፈሰው። አሁን ፈነዳ። እግዚአብሔር ታምራቱን የሚሠራበት ጊዜ አለው።

ፀባዖታችን፣ ልዕልታችን፣ የኔታዊቲ፣ መስቀላዊት ገነነች። እናም መዳፈር ተከተለ። ማህበረ ማንዶልዶያ አንዶለዶሉት። ፍንክች ሳይል የመስቀል ልጅ #በአኃቲነት ፀና። እናም ከእሳት እንደገባ ፕላስቲክ ኩምትርትር፣ ኩፍትርትር ሆኑ።

መንፈስ ቅዱስ ታምራቱን ሠራ። ታላቅ ገድል በአሜሪካ አሳዬን። ተመሰጠረ። ሁለቱም ገድል አሜሪካን ላይ። በእትብታቸው የምከሰሱት፣ የምትዳፈሯቸው ሎቱ ስብኃት ስለ እናንተ ብፁዑ ወቅዱስ አባታችን ወርቅነት ይደምቃል። እኛ ልጆቻቸው የት ሄደን? አንሰበርም። ፊት ለፊት ወጥተን እንማገዳለን።

ቅን አባት ስለሰጠን አምላካችን እናመሰግናለን፣ እኔ ሁሉን ነገር ከውስጤ ስለምከታተል ፃድቁ አባታችን ብፁዑ ወቅዱስ ፓትርያርከ ዘኢትዮጵያ አገር ሲገቡ ያዬሁት ቅንነት እዮራዊ ነበር። ልዩ ነበር። በራሱ ማተቤ ነበር።

እኔም በዝምታ ውስጥ ስለነበርኩ ለመጀመሪያ ጊዜ ቦሌን ሲረግጡ የዩቱብ ቻናሌ ፕሮፋይል ብፁዑ ወቅዱስነታቸው ሆነ። ውስጤ የተቀበረበት መከፋት ይፍታህ አገኜ። ለዚህ ደግሞ የብፁዑ ወቅዱስ አባታችን የፓትርያርክ አባ ማትያስ ዕፁብ ድንቅ ቅንነት ነበር ለውስጤ ይፍታሽን ያጎናፀፈው።

የነበራቸው ሐሴት ልክ አልነበረውም። ያን ጊዜ ዲያቆን ዳንኤል ክብረት አድሎ ነበረበት። ሲያስተዋውቅ እኩል አልነበረም። ሰብሮት ነበር። ያደላው ነበረው። ዛሬ ደግሞ ሌላ ሰው ሆኗል።

ብቻ የሰውን ትቼ የአምላኬን ታላቅ ገድል ነበር የተደመምኩበት። እኔ ወስኜ ፕሮፋይሌ ለማድረግ የሚሞግቱኝ ጭብጦች አሉብኝ። ስጽፍም እንዲሁ። ቃለ ወንጌል ስከፍተው እማገኜው ምዕራፍ ላይ ነው እምጽፈው። ተረብ እንዳይመስላችሁ። የልቤን ነው።

"እግዚአብሔር በአንድም በሌላም ይናገራል

ሰው ግን አያስተውለውም" ይላል አካል የሌለው የአማኑኤል አገልጋይ ቃለ ወንጌል።

ትናንት ሲቧካ በነበረው ትርምስ ውስጥ ያለው ዕውነት አንድ ነው። ጽፌውማለሁኝ። መንበረ ፓትርያርኩ ለገዳ ይሸለም ነው። ሌላ ምንም ቀመር የለውም።

እንጂ ኢትዮጵያ በወርቅ ከበረች ሲል የሰነበተው ማንዶልዶያ ተገልብጦ በስሜን ኢትዮጵያ ሁለመናነት፣ በአሜናችን ላይ ይህን የመሰለ አተላዊ ጎርፍ አይለቅም ነበር። #እግዚብሄር ታምራቱ ድል ላይ ነው። ማተባችን አበራች። ቅድስታችን በአኃቲ ድምጽ አንድ ሆነች። #አንሰበርም

ኢትዮጵያ ላልከበደችው አንድ ዕውነት ነው ያለው። የዕውነት የክት እና የዘወትር የለውም። ማተባችን ዓለምን የመምራት የመንፈስ አቅም አለው። ተዋህዷችን አብሮነት ነው።

የወርቁ መዳያ ካስደሰተህ ፀባዖታችን ላይ እጅህን አንሳ።

አሜናችን ላይ እጅህን አንሳ።

ከጥንካሬያችን ላይ እጅህን አንሳ።

ማህበረ አቅመ ቢስ ብትክትክ።

ቅዱስ ሲኖዶስ አስቸኳይ ጉባኤ ተቀምጦ እንደተለመደው ለወረራ ነበር መሰናዶው። ከዛ በፊት ግን ታምር ተገለጠ። እንሆም ሆነ። #እኔ #የአባቴ #ነኝ ምን ይወስኑ ምን።

ተዋህዶ አንድ ናት። ተዋህዶ ህብር ናት። ተዋህዶ ብፅዕት ናት። ተዋህዶ ፀባዖት ናት። ማተቤ ብሄራዊ ናት። ማተቤ ዓለማቀፋዊት ናት። ማተቤ ዩንቨርስም ናት። መስቀሌ የሙሉ ዘመን ዩንቨርስቲ ናት። #አንሰበርም

ሦስት አንስት አናብስትን አድንቀህ ብጽዕናን ልታዋርድ አንተ ማን ነህ? ተጠዬቅ ማህበረ ጉድጓድ የጨለመብህ።

አባታችን ፍትኃታችን

አባታችን አሜናችን

አባታችን ሜሮናችን።

አባታችን ትርታችን

አባታችን የውስጣችን

መስቀላችን ጠሐያችን።

አባታችን አንድነታችን

አባታችን ቅንነታችን

አባታችን ቅኔያችን

ሰንደቃችን ጎዳናችን።

እግዚአብሔር ይስጥልኝ።

ሥርጉተ©ሥላሴ

Sergute©Selassie

27/07/2022

"አድርገህልኛል እና አመሰግንኃለሁኝ።"

"ወደ እግዚአብሔር ቤት እንሂድ ባሉኝ ጊዜ ደስ አለኝ።"

(ልብ አምላክ ዳዊት ምስባክ።)

 

የፖለቲካ አቋም ስጦ ያላደረገችው ልዕልት።

እንዴት ነን? ደህና አደራችሁ? አይዞን።

"የቤትህ ቅናት በላኝ።"

ከትንፋሽ ያገኜሁት ነው። የውስጤም ነው። እኔ ወሮ ቀለብ ታሥራ በነበረችበት ጊዜ ልዕልት ደራርቱን ተማፅኛት ነበር። ተስፋ አድርጌ። አሳር የበዛባት ፖለቲከኛ ስለሆነች።

እንዲያውም እኔ የልጆቿ ነገርን ከቦታው ሄዳ ብታይ ሁሉ ብዬ በትህትና አሳስቤያት ነበር። ጅል ነኝ የወጣልኝ። እና ልዕልቷ ከእስር ሲለቀቁ ለቲም ጃዋር የሰጠችውን አበባ ይዛ ባልደራስም ተገኜች።

ያንም ቢሆን አመስግኛለሁኝ። ጽፌበትማለሁኝ። እኔ እስሩ ላይ እንጂ ደስታ ላይ መገኜት ክፍሌ ስላልሆነ። ያን ሳይ ግን ስለ ክብሯ ጥፌያለሁኝ።

ልዕልት ደራርቱ ንፁህ ፖለቲከኛ ናት። ለእኔም። ግን ደልዳላ ወሮ ስለሆነች የፖለቲካ ውስጧ ስጦ ሆኖ አያውቅም። ይህ የልዕልት ደራርቱ ልዩ ፀጋዋ ነው።

ስለዚህ በደርግም ዘመን፣ በህወሃትም ዘመን በአብይዝም ዘመን ተከብራ፣ ተደንቃ፣ ተወዳ እዬኖረች ነው። መማገድን አስቦት ለማያውቅ ፖለቲካ እሳት ሳይሆን ወተት ነው። ሰብዕናው ሳይጨስ ይኖራል። ሙሉዑ ሰብዕና ለማን የትኛው ለሚለው ህሊና ይዳኜው። ዝምታ እና መማገድ ችሎት ይቅረቡ።

እስከ አሁን ካዬኋቸው ሴት ፖለቲከኞች ጥንቃቄዋ ፍጽምና ያለው እንደ ልዕልት አላዬሁም። አገር መሪ የመሆንም አቅም አላት። ምን አልባት የቀረው ነገር ጠቅላይ ሚር ወይንም ፕሬዚዳንት የአገር መሆን ነው።

እሱንም አዋን ዕድሜ ይስጣት እንጂ የሚነሳት የለም። በአብዛኛው ሰው ልብ አለች። እኔም አከብራታለሁኝ። አክብሮቴ ደርዝ አለው። ለሁሉ እኩል ትሆናለችን? ማን ቅርቧ ማን እሩቋ ከዚህ ዘመን በላይ ሁሉንም ሚዛን ያስቀመጠ ኤራ የለም። ጊዜ ቴርሞሜትር፣ ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።

የአሁኑ አትሌታዊ ዘመን 1500 እና 300 የአማራ ደም ዋዜማው ነበር። ከሁሉ ወላሂ ሁለተኛ አማራ አልሆንም የፈታተሸን ችሎት ነበር።

በአማራ እርድ ዙሪያ ዝምታ እና ወርቃችን በሚዛን ማስተናገድ ይቻል ነበር። ውስጥን ማጥቆር። መከፋትን አለሁህ ማለት። ግን ለጠንቃቃ ፖለቲከኞች መማገዱን ለእኛ ትተውታል።

ቲም ለማ ሲመጣም ልዕልቷ የተክለፈለፈ ነገር አላዬሁባትም። ከምከታተላቸው ሰብዕናወች አንዟ ስለሆነች። ጠንቃቃዋ ተሸለመች መኪና አይደንቀኝም። ብዙ አላት ብዙም መሆን ትችላለች።

ኢትዮጵያ ለክብር አብቅታለች። ኢትዮጵያ ማለት ሲያንስ ነው። ምንም ያልደረሰንም ኢትዮጵያ እያልን አይደለምን? የኃላፊነት ቦታውም በኢትዮጵያ የተገኜ ነው። ይህን አውቆ በልኩ መሆንም ብልህነት ነው። ፁሁፋን ወድጀዋለሁኝ። የአማራ ህዝብ ጥሞና ያስፈልገዋል።

ኢትዮጵያ ማለት፣ እሷን ማክበር የእኛን የአማራን ህሊና ሞተር የሚዘውር ብቻ ሊሆን አይገባም። የማንኛው ዜጋ ግዴታው ነው። ክብሩም፣ ልዕልናውም፣ ልቅናውም በእሷ የተገኜ ነው። ማንም ይሁን ማን? ሰሞኑን የተጋሩ ልጆች አንድ ሻንፒዮን፣ ሦስት ወርቅ አስገኙ።

ብዙ ነገር አይቻለሁኝ። የእነሱም እዚህ መድረስ መንፈሱ የኢትዮጵያ ፀጋ ነው። የችሮታ አይደለም። ሁለመናዋን በሰጠች አገር እንደ ገና ተወቃሽ ልትሆን ባልተገባ።

የሆነ ሆኖ አማራ ስንሞትም፣ ስንታሰርም፣ ስንሰደድም፣ ስንታረድም፣ ስንነድም፣ በዕንባ በደም ዶፍ ስንቀጠቀጥም ስንፈናቀለም ኢትዮጵያ አለች። ኢትዮጵያ ማለት እኛም ነን አማራወችም። ጋዜጠኛ ታዲዮስ ታንቱ ፀሎቴ ናቸው።

ኃላፊነቱ ካልተፈቀደልህ እንደምን ለክብር ትበቃለህ? በምንስ ትለካለህ? ፎቶው ከትንፋሽ ያገኜሁት ነው። መዝኑት ብላለች።

ሥርጉተ©ሥላሴ

Sergute©Selassie

27/07/2022

~~~~~~

"ከአቶ ዮናስ ሽብሽብ የተገኜ። የሳቸው ሃሳብ ማሳረጊያ ይሆናል። ትዝብቴን ግን በዝርዝር አቀርባለሁኝ። ትላለች ትንፋሿ

"ገና አገር ትሸለማለች። የአገር ፕሬዚዳንት ትሆናለች። ለሁሉም ከተመቸህ ሁሉም ይወድኃል። የእኔ የማትለው ቢኖር በግንባር ሥጋነት እራሷን አጋልጣ አይቼ አላውቅም። በዝምታ የሰከነ ነው። ይህ ሲሆን በውስጥ ዩለለውም ሁሉም የእኔ ይልኃል።

የለበሰችው ልብስ የአርሲ ባህላዊ ልብስ ነው።

አማራ ክልል የሚያዘጋጀው ልዩ ሴሪሞኒም ይኖራል። እኔ ሳስበው።

ሰሞኑን ከጎንደር ወደ ደብረታቦር መምህር ታዬ ቦጋለ እንደተዛወሩ አይቻለሁኝ። ፕሮፌሰር ፍቅሬ ቶለሳ ይከተሉ ይሆናል። ጎንደር ከተማ ስለባጁ። አዳርቃይ ግንባር ቲሙ ሌልኛ ነበር።

ይህ ልብስ ……

አሁን የመላ ኦሮሞ ልብስ ሆኗል። ሬቻ የቢሸፍቱ ወንዝ እና አካባቢ አሁን የሁሉም እንደሆነው። እኔ ሳውቀው የአርሲ ገጠር ሴቶች የሚለብሱት መደበኛ ልብሳቸው ነው።

እሷ የአርሲ ልጅ ናት። እንዲህ ለብሳ በዓለም አደባባይ አይቻት ባላውቅም፣ ሩጫ ከጀመረችበት ጊዜ አውቃታለሁኝ በአደባባይ። የዛሬው አለባበሷ ጥልቅ የፖለቲካ ዕድምታ አለው። ብልህ ስለሆነች ከብልህነቷ የተቀዳ ግሎባል ቅኔ አለው።

የዓለም የአደባባይም ዕንቁ ከሆነች ጀምሮ በዚህ ልክ የውስጧ ሰናይ ሲናኝ አይቼ አላውቅም። ሁለታችንም የአንድ ዘመን ሰወች ነን። ቤቷን ግቢውን በልጅነት አውቀዋለሁ። ቃሊቲ አዲሱ ገብርኤል ዝቅ ብሎ ነው። ሰርቢስ ነገር ነበር።

ቀለሙ የሚገርም ነበር። ለምን እንደ መረጠችው ሲገርመኝ ኖሯል። ዛሬ ገብቶኛል። ቀላል ሴት አይደለችም። ጥልቅ ናት። ቃለ ምልልሷን አዳምጡት። ቀላል ሰብዕና የላትም። እንደእነ ሞንጀሪኖ ዓይነት አይደለችም። በሩጫው አይደለም እኔ እምመዝናት።

ታላቅነቷን በጥበብ ስለያዘችው ሚዛን አስጠብቃ ስለክብሯ ያለች መሪ ናት። በክብሯ ውስጥ ሌላ የተደላደለ አመክንዮ አለ። አይለፈለፍም። ዶግማዋ ይመስለኛል። የእሷ ታሪክ የሩጬ ብቻ አይምሰላችሁ። በፀጥታ የሚራመድ ዓላማ እና ግቡን ጠንቅቆ የሚያውቅ ነው።

ብዙ መሪወች ለአገር የታጩ፣ ብዙ ተፅዕኖ ፈጣሪወች ድልድይ ይሆናሉ የተባሉ ተነስተው ወድቀዋል። ከስልት ንፍገት ብቻቸውን ዛሬ ባለው በዶር አብይ አህመድ አመራር ቁመዋል።

የእሷ ከዚህ የራቀ ነው። ቀረቤታዋ ይሁን ርቀቷ በጥበብ የሚመራ፣ ጥንቁቅ የሆነ ነው። አስፈላጊ ሲሆን ብቻ አደባባይ ላይ ይውላል።

አዲስ አበባ ለእሷ ፕሮጀክት ተብሎ የተለቀቀ ሰፊ ቦታ አለ። የእኔ ቢጢወች ተንገላተዋል። አስፓልት ላይ ከአለ አንድ ሊህ ባይ ወድቀዋል። ስትመለስ አግኝታ ታፅናናቸው ይሆን ብያለሁኝ። ጊዜ ስለሚኖራት። ዓላማዋን ስላሳካች። ስኬቱን በወርቅ ስላንቆጠቆጠችው።

ኮነሬል ደረርቱ ቱሉ ለእኔ ሩጭ አይደለችም። እራሷ አንድ ትልቅ ዩፖለቲካ ተቋም ናት። ለብዙ አመክንዮ ምርኩዝ ናት። የጀርባ አጥንት ናት። ድልድይ ናት። ተላምጣ እንዳትጣል በጥንቃቄ የምትጓዝ ጥበብ ናት ለውስጥ ፍላጎቷ።

ከእሷ ቤት ትርፍ ነገር በአደባባይ የለም። አንድ ጊዜ ኦሮምኛ ዘፈነች የሚል ዜና ነበር። የዘፈነችው አሪስኛ ነው። ባህሏ ነው። ሁሉም ወጣት እዛ ሲያድግ የሚፈፅመው ነው። ምንም አዲስ ነገር አልነበረውም። ባስፈለጋት የሚሊዮን ዕይታ ላይ ደፍራዋለች።

እኔም እችለዋለሁኝ። አርሲን ስለማውቀው። ልብሱንም እንዲሁ። ከምወደው ልብስ አንዱ ነው። የሆነ ሆኖ አስፈላጊ ሲሆን ባህሏን መዘዝ አድርጋ ታስተዋውቃለች። እኛ የዚህ ባለፀጋወች አይደለንም።

ብዙ በጣም ብዙ ዘመን በከንቱ ተጫውተንበት አባክነናል። ብዙ ዕድሎችን ሚስ አድርገናል። ኢትዮጵያ ስለምንል። ለኢትዮጵያ ነው። ስለዚህ የኢትዮጵያ የወል ተኮር ላይ ብዙ ዘመን ፈጀን።

እሷ ምርጫዋን ያስተካከለች ሰው ናት። ስትፈጠር። "ሙያ በልብ።" ሳስባት ጥልቅ የፖለቲካ ሰው ናት። መደበኛ ተፈጥሯዋ ፖለቲካ ነው። ሩጫ መግቢያ በርን ነው።

አሁን ከሚመሩት የአገር መሪወች ከመሪወችም በላይ ፍፁም በላይ ናት። ያን ሁሉ ሰቆቃ ለአፍታ ትተትን አብረን እንዴት እንደደለቅን እሰቡት።

እሷ ግን አትለፈልፍም። ትርፍ አትናገርም። በዝግታ ትራመዳለች። መስመሯን ታሳካለች። ለሁሉም በተመቸ ግን ምቾቱ ለማን እና እንዴትን በረቂቅ ያገናዘበ።

ሃሳቡን ያገኜሁበትን ለጥፌያለሁኝ።

"የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን ፕረስዳንት ኮለኔል ደራርቱ ቱሉ በአሜሪካን ሀገር እጅግ ዘመናዊ መኪና ተሸለመች!!"

ሚስጢር አይሞትም። ሚስጢር አይፈስም።

አባ እንኳን ነፍሰወት ተርፋ አሜሪካን ገቡ።

ወይ መራራቅ?

"የቤትህ ቅናት በላኝ።"

ሁልጊዜ ወጀብ፣ ሁልጊዜ ሰበር። እነ አያፍሬ ደግሞ ዝክንትላቸውን ያዝረከርኩታል።

ለእኔ የቅዱስ ወብፁዕ አባ በሰላም ካሰቡበት ቦታ መድረሳቸው ነው ጉዳዬ። ከዚህ ከፍም ዝቅም የለም። ብፁዓን ወቅዱሳን ሕይወታቸው #ሚስጢር ነው። ለእኔ ያልተገባኝን አልተገባኝምና በሐሴት እቀበለዋለሁኝ።

ለምን ብዬ አልጠይቅም። በህይወት ዘመኔ ከእኔ ጋር ግንኙነት የሚኖረው ሰው ከሚነግረኝ ውጪ ጠይቄ አላውቅም። በቃ። የሚገባኝን ይነግረኛል። ከዛ የተረፈው ምን ያደርግልኛል? ልንገርሽ ቢለኝም አልፈቅድም።

አባ በቁመታቸው ልቅ ሲቀቀሉ አራት ዓመት እኮ አለፈ። ቻይ በጣም ቻይ፣ ታጋሽ በጣም ታጋሽ፣ ቅን በጣም ቅን፣ ጠንካራ በጣም ጠንካራ ፃድቅ አባት ናቸው። ተንገርግበዋል።

ጉዟቸውም፣ ውሳኔያቸው የላይኛው ፈቃድ ነው። አቨው መሪያቸው መንፈስ ቅዱስ ነው። ሚስጥር አይፈስም። ሚስጢር አይሞትም። ሚስጢር ገብያ አይደለም።

አባ የፈቀደላቸውን ያደርጋሉ። መሪያቸው መንፈስ ቅዱስ ነው። በህልማቸውም ይነገራቸዋል። የራሳችን ሥራ እንሥራ። ቅድስታችን ፈተና ላይ ናት። ፈተናዋ ደግሞ በችሎት ነው የሚፈታው። ጽናት። ከብረት ቁርጥራጭ የተሠራ ጽናት።

ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ ጋር መስራት? ትልቅ የህይወት መሰናክል ነው። በህይወት መውጣታችው እራሱ ለእኔ ታምራቴ ነው። ገድል።

እነሱ ዛሬ አይደለም ገና የውጩ ቅዱስ ሲኖዶስ ወደ አገር ሲገባ በአይፒ ያስገቧቸው ብፁዑ አባት አሉ። ይህ ሁሉ በተዋህዶ ላይ ፈተናው እኮ የፓትርያርኩ መንበር ይለቀቅ ነው። ሌላ ምንም ነገር ዬለውም።

ምንስ ቢሆን ለምን ትደነቃላችሁ? 2011 የጥምቀት በዓል ማነው ቡራኬ የሰጠው? ሁለት ፓትርያርክ ተቀምጦ። ብሎጌ ላይ ጽፌበት ነበር።

በጎንደር የእስልምና ግርግር ሉዑክ መርተው ሄደው ብፁዑነታቸው። በዝም ብሎ የተከወነ አይምሰላችሁ። አደጋውም ታቅዶ፣ አረጋጊ አካሉም ሆነ ልዑኩ ሁሉ ታቅዶ የተከወነ ነው።

ጎንደር በሁሉም ነገር ይፈራል። አራት ዓመት ሙሉ የኦሮሞ ሊቃናት ጉልቻቸው ጎንደር ሆኗል። ለምን? ያውቃሉ።

ለእናንተ አቀባበል፣ አገባብ፣ አወጣጥ ይሆናል። ለእኔ ግን ህይወታቸው ይበልጥብኛል። የፈለገ ነገር ይወሰን መኖር የሚሰጠውን ምርቃት ማንም አይሰጥም። መኖራቸው ያስፈልገናል። ይኑሩልኝ አባቴ።

ትንሽ ረብ ሲል ከጨመታችሁ ስለማያስችላቸው ሲንፈራፈሩ ታገኟቸዋላችሁ። በቃ ሲንፈራፈሩ ከዛው ከወረራቸው፣ ከዛው ከመፈንቅላቸው ጋር ሲትበሰበሱ።

አሁን እኮ ቅዱስ ሲኖዶስ በአስቸኳይ እንዲሰበሰብ ነው ይህ ሁሉ አጀብ። የሠሩትን እነሱ ያውቃሉ። የነቀዘ ብል የሆነ ሴራ ነው አገር እዬመራ ያለው።

ብፁዑ ወቅዱስ አባታችን በራስ መተማመናቸው ከፀጋቸው ይመነጫል። እሳቸውን መጠበቅ አቅቶ መራወጥ ተቅማጥ እንደያዘው ሰው። መጥኔ።

አባ ዝምታ እንኳን ያሰቡት ተሳካ። ተመስገን።

"አድርገህልኛል እና አመሰግንኃለሁኝ።"

ሥርጉተ©ሥላሴ

Sergute©Selassie

26/07/2022

ቸር ዜናህን ስጠን።

ለፀሎት እንጠንክር።

ቅድስታችን ሕይወታችን።

መጥኔ ለእኛ? #ስንት ይሆን የሽግግር ዘመናችን?

#አጀንዳወችም ሽግግር ላይ ናቸው።

እንዴት ዋላችሁ?

ግን ሽግግር አይሰለችም? ሁልጊዜ? ከአቶ ፀጋ ወደ አቶ ገዱ አንዳርጌ፣ ከአቶ ገዱ ወደ አቶ የኋንስ ቧያለው፣ ከአቶ የኋንስ ቧያለው ወደ ዶር አጋምሳ፣ ከዶር አጋምሳ ወደ ዶር ሲሳይ መንግሥቴ፣ ከዶር ሲሳይ መንግሥቴ ደግሞ ወደ አቶ ታዬ ደንዳዓ? ከአቶ ታዬ ከንዳዓ ደግሞ ወደዬት ያሰኜን ይሆን? ወደ ፈረፈር ወይንስ ወደ አፋፍ? ለምን የአጀንዳ ሽግግር አትከአችሙትም።

አቅም ዋጮን ፊት መንሳት ነው። ፈልቶ፣ ተንፎቅፍቆ ረብ ሲል ቢና ጢናው ወጥቶ አድራሻው ይከስማል። የለትነት ይቁም እያልኩ ነው። ስንቱ ነገር በቃ ሊባል ይገባዋል?

እግዚአብሔር ይስጥልኝ።

ሥርጉተ©ሥላሴ

Sergute©Selassie

24/07/2022

ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው

ደስታን አታንጠራሩት። እባካችሁን?

"የቤትህ ቅናት በላኝ።"

ጦርነቱ አስፈላጊ አለመሆኑን ስገልጽ አኩራፊው ብዙ ነበር። ከዛ መቀሌ ድል ተብሎ ፈንጠዝያ ነበር። እኔ ከሁሉም አልነበርኩም። በግራ ቀኝ ጉዳቱን እዘግብ ነበር። ገዳ አጋጣሚውን እንደምን ሊጠቀምበት እንደሚተልም እጽፍ ነበር።

ስለ ደስታ ምድራዊ ደስታ ትንሽ ጣፍኩኝ። ደስታ አታብዙ ብዬ። አቶ ለምንን አናገርኩት።

1) ደስታህን በልኩ ካላገኜኽው ተስፋ ቆራጭ ትሆናለህ።

2) ተጨማሪ ደስታ ሲመጣ መደርደሪያ ታጣለህ።

3) የሰጠው በልክ ካልያዝከው ምርቃትህን ያነሳል። ርግማን ይከተላል ነበር የጣፍኩት።

የሆነው ሁሉ ነበር። አሁንም ደስታ በሚባለው ዙሪያ በልክ ያዙት። ወርቋን ኢትዮጵያን እያነደዳችሁ ሠው ሠራሽ ወርቅ የሐሴት ሁሉ ማህለቅ አታድርጉት።

ሁሉንም በልክ ሳያንጠራሩ መያዝ ይገባል። መከራችን አልተጀመረም። አይክፋችሁ በአገላለፄ።

እግዚአብሔር ይስጥልኝ።

ሥርጉተ©ሥላሴ

Sergute©Selassie

27/07/2022

ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።

 

#ዛሬ ሲፎርሽ የጉድጓድ ጉባኤ አፍ - በመደዳ።

አፍ ባለው መቃብር የተከዘነ ገመና።

ሁለት ርዕሰ ጉዳይ።

"የቤትህ ቅናት በላኝ።"

ፀረ አማራነት እስከ አጥንት የዘለቀ ስለመሆኑ ያዬሁበት ዘመን ነው። ሥርዓት፣ ህግ፣ ይትበኃል፣ ትውፊት፣ ትሩፋት የማይገዛው በመደዳ።

አንድ ጊዜ / ሙፍርያት፣ ወሮ ኬርያ አፈ ጉባኤ ሳሉ ለጋ እሸት በነበረበት ጊዜ ማለት ነው ገና ለጋ ገዳ 21ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ሳለ የሴት አፈ ጉባኤወች ጉባኤ ነበር።

ይገርም ነበር። ፕሬዚዲዬም። ኦድዬንስ የሚናገራው ቁምነገር ነበረው። ብሎጌ ላይ የፃፍኩት ይመስለኛል። መላመድ #ዛሬን #ፎርሾ #ሰጠን

መወራጨት የመሪነት አይደለም። የማበድ ሊሆን ይችላል። ነው አላልኩም። #ሊሆን ይችላል እንጂ።

ጭፍልቅልቅ አድርገው ጨፋፍቀው በጥድፊያ አቡክተው፣ ጠፍጥፈው፣ አንቦልቡለው ሁለመናው ገዳዊ ማድረግ ጋር ግብግብ ላይ ናቸው። ፍጥጫ እና እርግጫ ለግሎባል ህጉም ነው።

ኢትዮጵያ ህጓ

ኢትዮጵያ መንፈሷን አፍ ባለው መቃብር ለመከዘን ታጥቀው ተነሱ። እና ተነሰነሱ ………

እግዚአብሔር ይስጥልኝ።

ሥርጉተሥላሴ

SerguteSelassie

27/07/2022

ጊዜቴርሞ ሜትር!

 

ሐምሌ 19/ከግድፈት ያዳንኩበት ቤት።

ሰማዕትነት ፃድቅነትም።

በዋዜማው የጠቅላይ ሚኒስተሩ ባለቤት ጎንደር ነበሩ። ለማረጋጋት እንደላኳቸው ወዲያውኑ ብሎጌ ላይ ፃፍኩኝ። አሜሪካ ላለች ወዳጄ ገደሏቸው አልኳት። በስመ አብ በይ አለችኝ። ውዳሴ ማርያም አድርሻለሁ አልኳት። ገዳዩም ቁንጮው ናቸው ብዬ ነገርኳት።

ጠቅላይ ሚር አብይን እከታተላቸው የነበረው 2016 ጀምሮ ስለነበር ሲከሰቱ ውስጤ ደስታ ነበረው። ብዙም ሞግቻላቸው ነበር። ግንቦት 5 ቀን 2010 ላይ ግን ሙግት ፃፍኩኝ። ረጅም ነበር።

ሐምሌ 19/2010 ቀን ግን ቁርጤን አወቅኩኝ። ተስፋው መጠለፋን ተረዳሁኝ። እናም ቆርጬ ያስታገስኩትን ተጋድሎ ቀጠልኩኝ። በቃ።

ሰማዕቱ የተሰውት በአባይ ፕሮጀክት ላይ የገዳ ወረራን፣ የገዳን መስፋፋት፣ የገዳን አስሜሌሽን፣ የገዳን ልብ ለማድረስ ነበር። የቬንሻንጉል የአማራ ስቃይ ከአባይ ፕሮጀክት ጋር የተሳሰረ ነው። ሰሜን ጎንደር ለሱዳን የተሸለመውም እንዲሁ።

የሰማዕቱ ሰማዕትነት ሚስጢሩ 500 ዓመትን የወረራ ታሪክ ለመድገም ነው። እናም ፈፀሙት።

ሰማዕቱም ሰማዕትነትን ተቀበሉ።

እግዚአብሄር ይስጥልኝ።

ሥርጉተ©ሥላሴ

Sergute©Selassie

27/07/2022

#አንሰበርም!

 

ደስታን አታንጠራሩት። እባካችሁን?

"የቤትህ ቅናት በላኝ።"

ጦርነቱ አስፈላጊ አለመሆኑን ስገልጽ አኩራፊው ብዙ ነበር። ከዛ መቀሌ ድል ተብሎ ፈንጠዝያ ነበር። እኔ ከሁሉም አልነበርኩም። በግራ ቀኝ ጉዳቱን እዘግብ ነበር። ገዳ አጋጣሚውን እንደምን ሊጠቀምበት እንደሚተልም እጽፍ ነበር።

ስለ ደስታ ምድራዊ ደስታ ትንሽ ጣፍኩኝ። ደስታ አታብዙ ብዬ። አቶ ለምንን አናገርኩት።

1) ደስታህን በልኩ ካላገኜኽው ተስፋ ቆራጭ ትሆናለህ።

2) ተጨማሪ ደስታ ሲመጣ መደርደሪያ ታጣለህ።

3) የሰጠው በልክ ካልያዝከው ምርቃትህን ያነሳል። ርግማን ይከተላል ነበር የጣፍኩት።

የሆነው ሁሉ ነበር። አሁንም ደስታ በሚባለው ዙሪያ በልክ ያዙት። ወርቋን ኢትዮጵያን እያነደዳችሁ ሠው ሠራሽ ወርቅ የሐሴት ሁሉ ማህለቅ አታድርጉት።

ሁሉንም በልክ ሳያንጠራሩ መያዝ ይገባል። መከራችን አልተጀመረም። አይክፋችሁ በአገላለፄ።

እግዚአብሔር ይስጥልኝ።

ሥርጉተ©ሥላሴ

Sergute©Selassie

27/07/2022

ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።

 

#ዛሬ ሲፎርሽ የጉድጓድ ጉባኤ አፍ - በመደዳ።

አፍ ባለው መቃብር የተከዘነ ገመና።

ሁለት ርዕሰ ጉዳይ።

"የቤትህ ቅናት በላኝ።"

ፀረ አማራነት እስከ አጥንት የዘለቀ ስለመሆኑ ያዬሁበት ዘመን ነው። ሥርዓት፣ ህግ፣ ይትበኃል፣ ትውፊት፣ ትሩፋት የማይገዛው በመደዳ።

አንድ ጊዜ / ሙፍርያት፣ ወሮ ኬርያ አፈ ጉባኤ ሳሉ ለጋ እሸት በነበረበት ጊዜ ማለት ነው ገና ለጋ ገዳ 21ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ሳለ የሴት አፈ ጉባኤወች ጉባኤ ነበር።

ይገርም ነበር። ፕሬዚዲዬም። ኦድዬንስ የሚናገራው ቁምነገር ነበረው። ብሎጌ ላይ የፃፍኩት ይመስለኛል። መላመድ #ዛሬን #ፎርሾ #ሰጠን

መወራጨት የመሪነት አይደለም። የማበድ ሊሆን ይችላል። ነው አላልኩም። #ሊሆን ይችላል እንጂ።

ጭፍልቅልቅ አድርገው ጨፋፍቀው በጥድፊያ አቡክተው፣ ጠፍጥፈው፣ አንቦልቡለው ሁለመናው ገዳዊ ማድረግ ጋር ግብግብ ላይ ናቸው። ፍጥጫ እና እርግጫ ለግሎባል ህጉም ነው።

ኢትዮጵያ ህጓ

ኢትዮጵያ መንፈሷን አፍ ባለው መቃብር ለመከዘን ታጥቀው ተነሱ። እና ተነሰነሱ ………

እግዚአብሔር ይስጥልኝ።

ሥርጉተሥላሴ

SerguteSelassie

27/07/2022

ጊዜቴርሞ ሜትር!

 

ሐምሌ 19/ከግድፈት ያዳንኩበት ቤት።

ሰማዕትነት ፃድቅነትም።

በዋዜማው የጠቅላይ ሚኒስተሩ ባለቤት ጎንደር ነበሩ። ለማረጋጋት እንደላኳቸው ወዲያውኑ ብሎጌ ላይ ፃፍኩኝ። አሜሪካ ላለች ወዳጄ ገደሏቸው አልኳት። በስመ አብ በይ አለችኝ። ውዳሴ ማርያም አድርሻለሁ አልኳት። ገዳዩም ቁንጮው ናቸው ብዬ ነገርኳት።

ጠቅላይ ሚር አብይን እከታተላቸው የነበረው 2016 ጀምሮ ስለነበር ሲከሰቱ ውስጤ ደስታ ነበረው። ብዙም ሞግቻላቸው ነበር። ግንቦት 5 ቀን 2010 ላይ ግን ሙግት ፃፍኩኝ። ረጅም ነበር።

ሐምሌ 19/2010 ቀን ግን ቁርጤን አወቅኩኝ። ተስፋው መጠለፋን ተረዳሁኝ። እናም ቆርጬ ያስታገስኩትን ተጋድሎ ቀጠልኩኝ። በቃ።

ሰማዕቱ የተሰውት በአባይ ፕሮጀክት ላይ የገዳ ወረራን፣ የገዳን መስፋፋት፣ የገዳን አስሜሌሽን፣ የገዳን ልብ ለማድረስ ነበር። የቬንሻንጉል የአማራ ስቃይ ከአባይ ፕሮጀክት ጋር የተሳሰረ ነው። ሰሜን ጎንደር ለሱዳን የተሸለመውም እንዲሁ።

የሰማዕቱ ሰማዕትነት ሚስጢሩ 500 ዓመትን የወረራ ታሪክ ለመድገም ነው። እናም ፈፀሙት።

ሰማዕቱም ሰማዕትነትን ተቀበሉ።

እግዚአብሄር ይስጥልኝ።

ሥርጉተ©ሥላሴ

Sergute©Selassie

27/07/2022

#አንሰበርም!

 

 

 

 

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።