ፕሮፌሰር ዶር. በየነ ጴጥሮስ ከዚህ ዓለም ድካም ማረፋቸውን ሰማሁኝ።

 

 
 
ፕሮፌሰር ዶር. በየነ ጴጥሮስ ከዚህ ዓለም ድካም ማረፋቸውን ሰማሁኝ። መታመማቸውን ሳንሰማ በድንገት የማረፋቸውን ዜና ማድመጥ ያስደነግጣል። 
 
በአካልም አውቃቸዋለሁኝ። እሞግታቸውምዉ ነበር። ተተኪ በማፍራት ዙሪያ፦ ሴቶችን በማብቃት እረገድም። ህይወታቸው በፖለቲካ ዙሪያ በቋሚነት የዘለቀ ነበር። 
 
ለረዥም ጊዜም በመሠረቱት የፖለቲካ ድርጅት በመሪነት አገልግለዋል። ህብረት፥ መድረክ በሚባሉ የወል ፖለቲካ ስብስብም መሪነትንም ተጋርተዋል። የማያቆም የትግል ፍላጎተኛም እንደነበሩ አስባለሁኝ።
 
በዘመነ ህወሃትም የፓርላማ አባል ነበሩ። በብልጽግና ዘመንም በኃላፊነት ተሹመው አገልግለዋል። አንጋፋ መምህር፤ አንጋፋ ፖለቲከኛ ነበሩ። ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ሁለት የጥበብቤተኛ፤ሦስት የዩንበርስቲ ሊቃናት በሥጋ መለየት። 
 
ለቤተሰቦቻቸው፤ ለሥራ ባልደረቦቻቸው፤ ለአድናቂወቻቸው መጽናናትን እመኛለሁ። ለሳቸውም ነፍሳቸውን ይማር ፈጣሪ። አሜን።
 
እግዚአብሄር ይስጥልኝ።
ቸር አስበን ቸር እንሁን። ቅን አስበን ቀና እንሁን። ኑሩልኝ።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
17.09.2024

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።